TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
NiSiR International Broadcasting Co.

24 Jan, 08:40

Open in Telegram Share Report

የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ በቤተክርስቲያን ላይ ክህደት የፈጸሙ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ሰኞ ጥር 15 ቀን 2015 ትዕዛዝ መስጠቱ ተሰማ

ንሥር ብርድካስት
ጥር 16/2015

ሰኞ ጥር 15 ቀን 2015 የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ በቤተክርስቲያን ላይ ክህደት የፈጸሙ አካላት ወይም የሿሚና ተሿሚ ነን ባዮች ደመወዝ እንዲታገድና የሚገለገሉባቸው ቢሮዎችና ማረፊያ ቤቶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ጥር 15 ቀን 2015 በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት ባካሔደው አስቸኳይ ጉባኤ፤ ሃይማኖታዊ ክህደት፣ ቀኖናዊ ጥሰት እና አስተዳደራዊ ግድፈት የታየበትን የወሊሶውን "ሹመት" አወገዞ ቅዱስ ሲኖዶስ ተገቢውን ውሳኔ እስኪሰጥ ምዕመናን በጸሎት እንዲቆዩ አሳስቧል።

ጉባኤው በቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመው ሁሉን አቀፍ ክህደት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ ክህደቱን የፈጸሙት አካላት ሥልጣን የሰጣቸውን መዋቅር (ተቋም) በመካድ የፈጸሙት ድርጊት እጅጉን አሳዛኝ ነው ብሏል።

የተፈጸመው ጉዳይም ህገ ወጥና ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ወንጀል ነው ያለው አስተዳደር ጉባኤው፤ በምንም መመዘኛ ይህን ከፈጸሙ አካላት ጋር መደራደር በተዘዋዋሪ የቤተክርስቲያናችንን ሕግና ሥራዓትን ማፍረስ ነው ሲል አስታውቋል።

ጎሰኝነት ኑፋቄ መሆኑን የገለጸው አስተዳደር ጉባኤው፤ ይህን በመሰለ ተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ ክህደቶች በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ተነቅፏል ካለ በኃላ በቋንቋ መማርና ማስተማር ችግር እንዳልሆነ በመረዳት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያስተምሩ አባቶችን በመሾም አገልግሎት እንዲሰጡ ስታደርግ መቆየቷን ሕገ ወጥ ድርጊቱን ከፈጸሙ አካላት በላይ ማስረጃ አይኖርም ብሏል።

ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ አካል ሊሆኑ የሚችሉ የውሳኔ ሀሳቦችን ከቀኖና ቤተክርስቲያን እና ከሕግ አንጻር በመነሳት የጠቆመ ሲሆን፤ የተፈጸመው ክህደት ከቀኖና ቤተክርስቲያንና ከሕግ አንጻር እንዴት እንደሚገለጽ የሚያመለክት ሰፊ የሚዲያ ሥራ እንዲሰራ በመወሰንና በቂ ማብራሪያ የሚሰጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን በመመደብ በሁሉም ቋንቋዎች ማብራሪያ እንዲሰጥ ወስኗል።

በተጨማሪም ሁሉም የቤተክርስቲያናችን መዋቅር ተቋማቱን በንቃት መጠበቅና ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚተላለፍ መመሪያን በትጋት መጠበቅ እንደሚገባና አስፈላጊው መመሪያ በአስቸኳይ እንዲተላለፍ የወሰነው አስተዳደር ጉባኤው በቤተክርስቲያን ላይ ክህደት የፈጸሙ አካላት ወይም የሿሚና ተሿሚ ነን ባዮች ደመወዝ እንዲታገድና የሚገለገሉባቸው ቢሮዎችና ማረፊያ ቤቶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ መንግሥትም እያደረገ ያለውን የቤተክርስቲያናትን ጥበቃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጉባኤው ጠይቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናንና ምዕመናት ከጸሎት በተጨማሪ መዋቅራዊ መመሪያዎችን በትዕግስት እንዲጠብቁ አደራ በማለት የዕለቱን ስብሰባ በጸሎት ማጠናቀቁን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘውን መረጃ አመላክቶ አዲስ ማለዳ በዘገባው አስነብቧል።

=====================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https:  https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
Nisir International Broadcasting Corporation
Nisir International Broadcasting Corporation, Washington D. C. 90,055 likes · 10,855 talking about this · 3 were here. ልክ እንደ ንሥር ከአድማስ ከፍ ብለን የናንተው የመረጃ ምንጭ ለመሆን ከናንተው አብራክ በዎጡ ልጆች የተቋቋመ ለእውነት ብቻ...

3.8k 0 7 9
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot