በዚህ የከፉ ዘመን ዝም ማለትና ለህዝብ አለመጮህ የአማራውን ህዝብ እንደመካድ ይቆጠራል።
===================ከሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ===========
#ሂትለር በአይሁድ ህዝብ ላይ ጦርነት እንዳዎጀ ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስትም ግራኝ መሃመድ ከፈፀመው ግፍና በደል ጭፍጨፋ የበለጠ መከራ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ይገኛል። ዓለም በሰለጠነበት በዚህ በሃያ አንደኛው ክህፍለ ዘመን ሀገር መምራት ሲያቅት በሀገር እና በህዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ ሂትለራዊነት ነው።
የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያ ተወረረች ሲባል ሀብቱን ንብረቱን ሚስቱን ጥሎ ለእናት ሀገሩ ራሱን ሲገብር የኖረ፤ ኢትዮጵያ እንዳትደፈር ያደረገ ሀገር ያስከበረ የሀገር ባለውለታ ኩሩ ህዝብ ነበር።
ላለፉ ሶስት አስርት አመታት በሀገር በቀል ጥላቻ እየተጨፈጨፈ ከኖረበት ሀገሩ ሀገርህ አይደለም ውጣ እየተባለ፤ ጥሮ ግሮ ያፈራውን ንብረት እየተነጠቀ በምድር ላይ የመኖር መብት ተነፍጎት፤ ምድር ገሃነም ሁናበት የራሱን ሀገር እየረገመ፤ በእየጎዳናው ወድቆ እጆቹን ወደ ፈጣሪ ዘርግቶ፤ በምድር ላይ ያለችው የፍትህ ደጅ ስለተዘጋችበት፤ፍትህን ከፈጣሪው ጠይቆ፤ ይግባኙን ከክርስቶስ ዘንድ እየጠበቀ ይገኛል።
#አማራ የዮዲት ጉድትን የአርባ አመት፤ የግራኝ አህመድን አስራ አምስት አመት፤ የጣልያንን
አምስት አመት ወረራ ተቋቁሞ ሲታገል የነበረና ኢትዮጵያን ከጥላት የጠበቀ ህዝብ ሁኖ እያለ ከግራኝም ከጉድትም ከጣልያንም በበለጠ በአማራ ህዝብ ላይ ሀገር በቀል ጠላት ጭፋጨፋና ወረራ ፈፅሟል። በዘመነ ወያኔ ተላላኪ ሁኖ የቆየው በሀገር መከላክያ ሰራዊት የታገዘ ጥቃት በንፁሃን ላይ ፈፅሟል። በብአዴን አስተባባሪነት ለሰላሳ አመት ያህል አማራ ሃገር አልባ ሁኖ የተናቀ ትቢያ ሁኖ ለሀገር የከፈለው ውለታ እንደመርገም ጨርቅ ተቆጥሮ እየተሳደደ ሲገደል ኖሯል።
በመንግስት ወታደር የታገዘ ጭፍጨፋ ከጎርጎራ እስከ ወገራ ከባህርዳር እስከ ወልድያ፤ ራያ መርሳና በተለያዩ በጎንደርና በጎጃም በወሎና በሸዋ ተፈፅሟል። አማራ ከፋኝ ብሎ ዱር ገብቶ ሲዋጋ ኖሯል። ለዚህም በረሃ የቀሩት እነጎቤ መልኬ የነፃነት ታጋይ ስለ ፍትህ የሞቱ አርበኞች ህያው ምስክር ናቸው። ጀግኖች ታግለው መስዋትነት የከፈሉበትን ለውጥ ወስዶ ራሱን የለውጥ አካል አድርጎ በወንድሞቻችን ደም ላይ ተረማምዶ ዛሬም ከስልጣን ላይ ያለው ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚለው ብአዴን የምኒልክን ሂሳብ እናወራርዳለን ብለው በተነሱ የሀገርና የህዝብ ጠላት በሆኑ ሃገር ጠል በለስልጣናት ትዛዝ ብአዴን ህዝባችን እየጨፈጨፈ እያረደ ይገኛል። ይህ በቃህ ካልተባለ የአማራ ህዝብ ሰቆቃ እስከ አሁን ከነበረው የከፋ ይሆናል። የአማራ ህዝብ እየሞተ መኖሩን አቁሞ ሁሉም ለትግል መዘጋጀት ይኖርበታል ጠላት ከወያኔ ጋር አብሮ ኤርትራ እንድትገነጠል ያደረገ፤ ኢትዮጵያ ባህር አልባ እንድትሆን የፈረመ፤ ከመጣው ሁሉ ጋር የሚያጨበጭብ የኢትዮጵያ ጠላት፡ ሃገር አፍራሽ የማይጠቅም በደም የተነከረ የአማራን። ልጆች ቢበላይ የማይይጠግብ ነው። ትናት ከራያ እስከ ጉና፤ ከሰቆጣ እስከ ሞላሌ፤ ከማይፀብሪ እስከ ዳባትና ደባርቅ ድረስ አማራን ያስወረረ እናቶቻችንን እህቶቻችን ያስደፈረ፤ ጠላት ሀገር ሲወር ሀብት ሲከፋፈል የነበረ፤ ህዝብን አስደፍሮ ሲፈረጥጥ የነበረ፡ ድርጅት ዛሬ ህግ አስከባሪ ሁኖ ለሀገር ለህዝብ በጨበጣ ሲዋጋ የነበረውን ፋኖን እያሳደደ ይገኛል። ስልታዊ ባህሪ ያለው በየደቂቃው የሚቀያየር፤ እንደ መቃብር ድንጋይ በህዝባችን ላይ የተጫነ ድርጅትና የወሮበሎች ስብስብ ልንታገለውና ሁላችንም ከፋኖ ጎን ልንቆም ይገባል። ያ ካልሆነ አማራ የብልፅግና ባርያ ሁኖ ተንቆ እንደትቢያ እየተረገጠ ይኖራል። ከብአዴን ኮፈን የምንወጣበት መንገድ በትግላችን ማምጣት አለብን። ከባርነት ነፃነት ይሻለናል ልንል ይገባል። ኢትዮጵያ ስንኖር በፍቅር የምንኖርባት ሀገር እንጅ በቁማችን ፍትህን ነፍጋን ስንሞት መቃብር ከልክላን የምንኖርባት ምድር የግዞት ሀገራችን አይደለችም።
አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ለአማራ ህዝብ ገሃነም ሁና አማሮችን በመከራ በሲኦል ባህር ውስጥ ልታሰጥመው እየጣረች ትገኛለች። አማራ ንቃ1 አማራ ንቃ! አማራ ንቃ! ፍትህ ለወገኖቻችን፤ ፍትህ በሌለበት ዓለም ውስጥ አንዱ መሪ ሌላው ተመሪ ሁነን አንቀጥልም።
ህይዎቴን እስከ መስጠት ድረስ ከፋኖ ጎን እሰለፋለሁ! ፋኖ የኢትዮጵያ የነፃነት አርማና ምልክት ነው።
ከሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ለንሥር ብሮድካስት የተላከ
ንሥር ብሮድካስት
ሰ. አሜሪካ
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት ፡
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
Tiktok https://vm.tiktok.com/ZTds2F1e9
www.nisirbroadcasting.com
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።