ኖኅ Book Delivery


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Telegram


The first online bookstore in Ethiopia delivers books locally and internationally. We offer fair prices and fast delivery. You can order books by texting @Noahbook7
or calling 0939115238
📚Free Delivery (A.A)

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Telegram
Statistics
Posts filter


Fifty Shade by E L James

1. Fifty Shade of Grey I

2. Fifty Shade Darker II

3. Fifty Shade Freed III

📚Used

Total price 1850 birr

ማሳሰቢያ ፦ ውስጡ ላይ ምንም አይነት የገፅ መጉደል ወይ መቀዳድ የለውም ። አያጋጥሞትም ካጋጠሞዎት እንኳን ኖኀ Book Delivery ሀላፊነቱን ይወስዳል።🙏😊
⛵️⛵️⛵️
ለማዘዝ
📚የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።

Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ማንም የማይቀርበት Event 📚☕️

Book and Brew

Event is on March 8/ የካቲት 29

At the wild coffee tasting house #2

ከ10 ሰአት እስከ ማታ 4 ሰአት

Early bird ticket is  almost sold out and it’s 500 birr regular  is 1000birr

they can get their tickets from
0929291604 or at bole istore by Sofi shop should be in the caption💕

At the event early attendees get cocktails by double Dutch vodka, all attendees get a free book and coffee.

7 vendors where they can shop for books, bags, jewelry, accessories and stationery

Kine Fews band performance

Then sound by Dj Abel
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ነፃነት ስንት አውሮፕላን ያወጣል?

"የሚመጣው ዓመት ፒኤችዲዬን ስለምሠራ ትንሽ ንባብ በዝቶብኛል፡፡

ማርኬ እየተሻሻለ ስለመጣ እነ ሚሎስ 'ታዲያስ ጂኒየስ!' ይሉኛል፡፡

ምንም 'ሶሻሊስት ነን' ቢሉ፤ በጎን በስልት የሚሄድ፣ አምልጧቸው ይሁን ሳያመልጣቸው ቅር የሚያሰኝ ዘረኛነት ብቅ ይላል፡፡

'ጂኒየስ' ሲሉኝ ቅላፄው ውስጥ የማሳቅ ብቻ ሳይሆን የመናቅ ድምፅ አለ፡፡

ልክም ናቸው፡፡

'ጎበዝ አገር የተወለድኩ ነኝ' ለማለት ምን ላሳያቸው?

የአድዋ ጦርነት?

ግን ሉዓላዊነት ማሺንና ገንዘብ አይደለም፡፡
በገንዘብም አይሰላም፡፡

ነፃነት ስንት አውሮፕላን ያወጣል?"

***
መረቅ
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


🛡⚔አድዋ⚔🛡

እንኳን ለታላቁ የጥቁር ህዝብ የነፃነት ብርሀን ለሆነው በኢትዮጵያውያን የአፍሪቃ ልጆች አያቶቻችን የድል ስራ እስከወዲያኛው ላይሻር ለተፃፈው 129ኛው አመት የአድዋ በዓል አደረሰን::
🙏🥰🙏
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ኖኀ የምድሩን መጽሐፎች ጨርሶ ። ከሰማይ ያለውን እያመጣ ይገኛል ። 😂 በቀጣይ ከየትኛው planet መጽመፎችን እንድናመጣላቹሁ ትፈልጋላቹ ?😁

ኖኀ የግስላው ደቀ መዝሙር😂
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ባሻዬ! ዛሬ ለካ የፍቅረኞች ቀን ነው። አንዷ የጨርቆስ ልጅ "የፍቅረኞች ቀን Valentine's Day የሚባለውን አልወደውም" አለችኝ።

እኔም "ለምን?" ብዬ ስጠይቃት ዝርዝሩን አጫወተችኝ፣

አንድ ቀን የፍቅረኞች ቀን ዕለት ዝንጥ ብላ ስትሄድ አንድ በዕድሜው ጠና ያለ ሰው መኪናውን አቆመና ልሸኝሽ አላት። እሺ ብላ መኪናው ውስጥ ገብታ በዚያው ቀረች።

አብረው መኖር ከጀመሩ በኋላ ዕድሜ ጠገቡ ሰውዬ እየቆየ ክፉ ባህሪውን ማሳየት ጀመረ። የቤቱን የምግብ ፍጆታ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች ብሎ ስለሚያስብ እሷ ከቤት ስትወጣ እሱ ደሞ መሶብ ከፍቶ የመሶቡን ክዳን ጭንቅላቱ ላይ ደፍቶ እንጀራ ይቆጥራል።

ሰውዬው ምንም ስህተት ሲያጣባት ምናልባት ከእንጀራው ይልቅ በሊጥ መልክ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች ብሎ ስለሚያስብ እንደ መኪና ዘይት ሊጡን በረጅም እንጨት deep stick  ሊቤሎ ለክቶ ወደ ሥራው ይሄዳል።

ሰውዬው ስለሚቀና አንዳንዴ ከሥራ ሲመለስ ጫማዎቿን እያገላበጠ ያይና አቧራ ካገኘ የት ሄደሽ ነበር እያለ እንደ ምርጥ ተጫዎች እየተወረወረ በቴስታ ይመታታል። በዚህ ተማርራ ቤቱን ጥላለት ወጣች።

ባሻዬ! ልጅቷ ባትነግረኝም ሰውዬው የቤቱን ቅቤ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች ብሎ ስለሚያስብ የቅቤ መያዣውን ከፍቶ የረጋው ቅቤ ላይ በጣቱ ለምልክት ፈርሞበት እንደሚወጣ ልቤ ጠርጥሯል።

ይቺ ልጅ የፍቅረኞች ቀን በመጣ ቁጥር ያንን የመጋዘን ተቆጣጣሪና የካዝና ቁልፍ የሆነው ባሏን ታስታውሰዋለች።

ሴቶቻችን ዛሬ በፍቅረኞች ቀን ደስታ ተሰምቷችሁ ከተዘናጋችሁና ነገ ጠዋት ፋርማሲ ከተዘጋባችሁ ከወዲሁ መልካም የእናቶች ቀን እመኛለሁ።

ተስፋዬ ሀይለማርያም ✍
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


አና እና ዶስቶቭስኪ ሲጋቡ እሷ የ21 አመት ወጣት፣ እሱ ደግሞ የ47 አመት ጎልማሳ ነበሩ። ለ14 አመት ፍቅራቸው የሚያስቀና፣ ደስታቸው ሙሉ ሆኖ ከኖሩ በኋላ ዶስቶቭስኪ በ61 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

አና ከዶስቶቭስኪ ሞት በኋላ ብዙ የእናግባሽ ጥያቄዎች መጥተውላት ነበር። ገና 35 አመቷ ነው። አሁንም ውብ ናት። አሁንም በህይወት እንደተሞላች ነው። ብሩህ ጭንቅላት አላት። አና ግን ሁሉንም ጥያቄዎች በእንቢታ መለሰች። ምክንያቱ ምን ይሆን?

ከረዥም አመታት በኋላ አንድ ጋዜጠኛ ይህንኑ ጥያቄ ጠየቃት፦

"አና ቆንጆ ነሽ። ወጣት ነሽ። ብልህ ነሽ። ለምን ዳግመኛ አላገባሽም?"

አናም መለሰች፦

"ከዶስቶቭስኪ በኋላ ማንን ላግባ? ቶልስቶይ እንደሆነ አግብቶ ወልዷል!"

የአና መልስ አንጀት አርስ ነው። ዶስቶቭስኪን የሚያክል ስብእና ጋር የኖረች ሴት ተገዳዳሪ ስብእና ያለው አቻ ለማግኘት ብትቸገር አይገርምም።
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ለ ፈ ገ ግ ታ
😁 😁 😁

ዶሮዋ . . .

ጥያቄ፦ ዶሮዋ መንገዱን አቋረጠች፤ ለምን?

ይህ ጥያቄ ለሀገራችን መሪዎች ቢቀርብላቸው ምን መልስ ሊሰጡ ይችላሉ?

አፄ ቴዎድሮስ
ይህቺ እብድ ዶሮ መሄድ የለመደች
ባታውቀው ነው እንጂ ንብረቴ ነበረች
ነይ ተመለሽ በሏት ርቃ ሳትሄድ
እቴጌዋ ዶሮ ምሳ ነች ራት


አፄ ዮሐንስ
ማቋረጡንስ ታቋርጥ፤ ግን ይህቺ ዶሮ ተጠምቃለች? ማኅተቡንስ እንዳሰረች ነበር?

አፄ ምኒልክ
ስማኝ ያገሬ ሰው! እስከዛሬ ድረስ አላስቀየምከኝም፤ እኔም ያስቀየምኩህ አይመስለኝም፤ ዶሮዋን መልሳት ... ይህንን ሳታደርግ ባገኝህ ግን ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ትሁን፤ አልምርህም፤ ማርያምን!

አፄ ኃይለ ሥላሴ
የምንወድህና የምትወደን የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ... ዶሮዋ መንገዱን ስታቋርጥ በቸልታ መመልከት የለብህም። በአንዲት ዶሮ መንገዱን ማቋረጥ ምክንያት ሀገርህን፣ ንጉሥህን፣ ዘርህን ማሰደብና ታሪክህን ማበላሸት የለብህም!

ኮሎኔል መንግሥቱ
ጓዶች! ተደፍረናል! ተዋርደናል! ዶሮዋ መንገዱን አቋርጣለች፤ ይህ ደግሞ አድሃሪያን አብዮቱን ለመሸርሸርና አብዮታዊ ትግላችንን ለማደናቀፍ የሸረቡት ሴራ ነው። ዶሮዋን ለማስመለስ አንድ ሰውና አንድ ጠመንጃ እስኪቀረን ድረስ እንዋጋለን።

አቶ መለስ
በመሠረቱ ዶሮዋ መንገዱን ማቋረጧ በልማት እንቅስቃሴያችን ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ አለ ወይ? ነው ጥያቄው መሆን ያለበት፤ የለም! ስለዚህ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላት፤ አራት ነጥብ።
.....
😂 😂 😂
━━━━━━━━
ምንጭ ➢ ኢንፎቴይመንት
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


💬
❝ብዙ ጊዜ ላለመሥራት የምትተዋቸው ሥራዎች በውስጣቸው ብዙ ዕድልን የያዙ ናቸው።❞
          ሮቢን ሻርማ

💬
❝ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሠራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሠራተኛ ይበለጣል።❞
          ቲም ኖትኪ

💬
❝በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ ሰርተኸው የማታውቀውን አዲስ ሥራ ለመሥራት መፍቀድ ይኖርብሀል።❞
          ቶማስ ጄፈርሰን

💬
❝ሰው የገዛ ራሱ ወዳጅም ጠላትም ነው።❞
          ባጋቫድ ጊታ

💬
❝ቃልህን ከሚያሳጥፍህና ክብርህን ከሚያጎድፍብህ ድርጊት አንዳች ጠቀሜታ አገኛለሁ ብለህ አታስብ።❞
          ማርክስ ኦሪሊየስ

💬
❝ለገዛ ራስህ ክቡር ዓላማዎች ታማኝ ሁን።❞
          ዊልያም ቻኒንግ

💬
❝የሰው አዕምሮ በአትክልት ስፍራ ይመሰላል። በጥበብ ይኮተኮታል፤ ወይ ዳዋ ይለብሳል። የሚያበቅለውም የሰጡትን ነው። ጠቃሚ ዘር ካልተዘራበት አረም ይውጠዋል።❞
          ጀምስ አለን

      💬  💬
      ጥቅሶች
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


"ሰውን እብድ የሚያሰኘው እብድ የሚያደርገውን ማድረግ አይደለም።
እብድ የሚያደርገውን ሲያደርጉ መታየቱ ነው! ''

📖....ፍቅር እስከ መቃብር ...📖
ከ ሀዲስ ዓለማየሁ
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


The Metaphysics - Aristotle

Penguin Classic Edition

What the book is about...

✅ The book investigates the nature of being, including what it means to exist, how things change, and what is necessary for other things to exist 

✅ It also explores the relationship between form and matter, and the concepts of potentiality and actuality

✅ Aristotle argues that the reality of things is found in their concrete forms, rather than in a Platonic idea of reality as a reflection of something else 

Price 1750 birr
⛵️⛵️⛵️
ለማዘዝ
📚የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።

Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


#ራጅኒሽ/ኦሾ
ኦሾ ቤቱ ዉስጥ እያነበበ እያለ አንድ ወዳጁ ዘዉ ብሎ ገባና ዘርፈጥ ብሎ ተቀመጠ:እንዲህም አለዉ "አንተኮ ቅዱስ ነህ ጥበብህና እዉቀትህ ሁሌም ያስደንቀኛል" አለዉ። "ልክ ነህ!" አለዉና ማንበቡን ቀጠለ ኦሾ።ከደቂቃዎች ቆይታ አንድ ኦሾን አምርሮ የሚጠላ ሰዉዬ ገባና "አንተኮ አለምን ሰላም የነሳህ አምሳያ የሌለህ ዲያብሎስ ነህ" ሲል ኦሾ ላይ ወረደበት። ኦሾም መፅሀፉ ላይ እንደተተከለ "ልክ ነህ!" አለዉ።ይህን የሰማ የመጀመርያዉ ሰዉዬዉ "እኔ ቅዱስ ስልህ 'ልክ ነህ' ብለህኝ ነበር: አሁን ደግሞ ይሄ እብድ ሰዉዬ ዲያብሎስ ሲልህ ሰምተህ ተቀበልከዉ: እንዴት ሊሆን ይችላል?" ሲል ጠየቀዉ: ኦሾን።ኦሾም "ሰማኝ ወዳጄ የተለያዩ ሰዎች እየመጡ እኔን  ሺ አይነት ስም ቢሰጡኝ: እኔ እነሱ እንዳሉት ሺ አይነት ማንነት ያለዉ ሰዉ ልሆን አልችልም: ሰዎች ለኔ የሚሰጡኝ ሰም የራሳቸዉን ነዉ እኔን በዉስጣቸዉ     ካለዉ ባህሪንጋ እንደማስተዋወቅ ነዉ።አንተ እኔን ቁዱስ ያልከኝ ቅዱስ ስለሆንኩኝ አይደለም: በዉስጥህ ያለችዉ ትንሽዬ ቅድስና ነዉ የነገርከኝ።ሰዉየዉም የነገረኝ በዉስጡ ስላለ ዲያብሎስነት ነዉ።እኔም ሁለታችሁንም ልክ እንደሆናቹ ነገርካቹ: ምክንያቱም ስለራሳቹ ከናንተ በላይ ስለማላዉቅ ነዉ።" ብሎ መለሰለት።

1.Intelligence

2.Joy

3.Forgiveness

4.Courage

5.Creativity

6.Awareness

7.Intuiotion

8.Trust

9.Intimacy

10.Maturity

Total price 6750

ማሳሰቢያ፦ለየብቻ አይሸጥም።🙏
⛵️⛵️⛵️
ለማዘዝ
📚የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።

Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ኖኀ Book Delivery ለተወሰነ ጊዜ በመጥፋታችን ስልካችን ዝግ በመሆኑ ይቅርታ እየጠየቅን። ለእናተ ደንበኞቻችን አዳዲስ መጽሐፎችን ይዘን ለመምጣት ደፋ ቀና እያልን ነው ። ከሰኞ በኋላ በተለመደው መሰረት አዲስ እና ከዚህ በፊት ኑረው ያለቁ የተለያዩ መጽሐፎችን ይዘን የምንመጣ ይሆናል። 🙏

እስዛው ድረስ ፈገግ እያላቹ ጠብቁን 😊
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


we must bring
our own light
to the
darkness.

nobody is going
to do it
for us.

~ Bukowski
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


የሱሪ ቀዳዳውን እንዲሰፋበት መርፌ ስታሳየው፤ ቁጭ ብሎ ሹልነቱን እንደ አስገራሚ ግኝት እየፈተሸ ቂጥህን ሊወጋበት ቀን የሚጠብቅ አይጠፋም፡፡ 😂😂😂

የስንብት ቀለማት

አዳም ረታ ✍✍✍
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ጀምበሯ ለመጥለቅ አቆልቁላለች፡፡ አድማሱ ቀልቷል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ቀለበቷን ብቻ
አልነበረም በጫማው ረግጦ የለጋው ፣
የገዛ ሕይወቷን ነበር እንጂ፡፡
ቻው ፊያሜታ አለ በልቡ፡፡
መቃብሯ ጸጥ ብሎአል፡፡
ከመቃብር ጸጥታ ባሻገር የናቅፋ
ተኩስ ተሰማው፣ የጀግኖችን ደም ጩኸት እየሰማ ልቡ ወደዚያ ሔደ ፡፡

" ሁሉን ትወዳለህ በመጨረሻም ሁሉን ታጣለህ "
         ሴላቪ ኦሮማይ !
                                                  (በዓሉ ግርማ )

" በመጨረሻም ሁላችንም ታሪክ እንሆናለን "
  In the end , We'll all become Stories  ,
                     'Margaret Atwood'
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery

16 last posts shown.