Forward from: መፅሀፍ አለሜ📚📚📖📖
-እንዲህም አለ፦ “I am not God. I am not a Deva. I am a Human… I am the Awakened one, who has seen the Truth of the world.” በሰውነቱ ውስጥ ያሉትን አተሞች ሁሉ ለመቁጠር በሚያስችል መልኩ ስለ አእምሮው ጥልቅ ትንታኔ አድርጓል።
-“Noting in this world is solid” ለዚህ አባባሉ ዘመናዊ ትርጓሜውን ልተነትን ብነሳ ረጅም ነው። ነገር ግን አሳጥሬው እንዲህ ያለህ ነው፦ ሁሉም ነገር ባዶ ቦታ ባላቸው ጥቃቅን ቅንጣቶች ተከቧል። እና እነዚህ ቅንጣቶች በቋሚ እንቅስቃሴ እና ፍሰት ውስጥ ከሚገኙ ጥቃቅን የኃይል ኳሶች በስተቀር ምንም አይደሉም። የሰው ልጅን ጨምሮ ለትንሽ ነፍሳት የምንታየው ልክ እንዲህ ባለ ኤሌክትሮኒክስ ኃይል ተበታትነን ነው። እናም አንዲት ትንሽ ነፍሳት ስላየችው አንድ ሰው አቋም ብንጠይቃት፤ ጥቃቅን የኤሌትሪክ ኳሶች በአንድ ቦታ ተሰብስበው እንደተመለከተች ነው የምትነግረን።
-ይህ ሰው የሚያገኛቸውን ሰዎች በጠቅላላ ቋንቋቸውን በአንዴ የመልመድ ብቃት ነበረው። ነገር ግን ሁሌም ሲሰበሰቡ የሚናገረው ንግግር የፓሊ ቋንቋ ብቻ ነበር። በጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ ተመስጦ ሲያደርግ የትኛውም እንስሳ አይጎዳውም ነበር። እንስሳቱ እሱ ጋር ሲደርሱ ቦዲ ትራዛክሽናቸው እና ኬሚካል ሪአክሽናቸው ይዳከማል። በሜታ
“Amity benevolence” የተጠራቀመው ኃይሉ በእንስሳቱ ላይ እርጋታ ይለቅባቸዋል።
-“Rebirth” የዳግም የመወለድን ጽንሰ ሐሳብ በሰፊው አጋርቷል። ራሱን በራሱ ተመልክቷል እናም በዚህ ህይወት ውስጥ “ቡድሃ:የበራለት” ለመሆን የበቃው ቀደም ባሉት ህይወቶች ሁሉ በሰራቸው መልካም ስራዎች ምክንያት እንደሆነ ደጋግሞ ተናግሯል።
-እንደ አንጉሊማላ ያለ የ999 ሰዎችን ነፍስ ያጠፋ፤ እንደ አምራፓሊ ያለች የከተማዋ ዝሙተኛ ሴት፤ እንደ ሳካካ ያሉ ፀባየ ጥፉ ተከራካሪ እና ቡድሃን በየቀኑ የሚያሽጓጥጠው ሁሉም በጠቅላላ ወደ ሀይማኖቱ ገብተው “አርሃንት” ሆኑ።
-ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ቀልድ የማይቀልድ፣ ሐሜት የማይወድ እና በሰው የማያሾፍ ነገር ግን ሁልጊዜ ፊቱ ላይ በሚበራው ፈገግታ ያገኙትን ሁሉ መማረክ የሚችል፤ ድንቁ አስተማሪ ሲድሃርታ ጓተማ ቡድሃ ነበር።
-ቡድሃ አንድ ቀን ለምጽዋት ሲሄድ አንድ ትንሽ ልጅ ከፊት ለፊቱ አንድ አቧራ የለበሰ ሳህን አነሳ። ቡድሃ በቀስታ ፈገግ አለና የምጽዋውን ሳህኑን ወደ ፊቱ አስጠጋው። ደቀመዝሙሩ አናንዳ የፈገግታውን ምክንያት ምን እንደሆነ ጠየቀው። ቡድሃም፦ “ይህ ልጅ በፓታሊፑታ ከተማ የኔፓሪኒባና ሞት በማስከተል ይሞታል። ከሁለት አመት ተኩል በኋላ እንደገና ይወለዳል። እና ቻካቫቲ “wheel turning” ንጉሠ ነገሥት ይሆናል። እና ለቡድሂስት አገዛዝ ጥቅም 84,000 የብረት ቤተመቅደሶችን በመገንባት ታሪክ ይሰራል። ይሄም ልጅ በነሱ ዘንድ ታላቁ አሾካ የሚባለው ንጉስ ነበር። አሾካም በጣም ጥሩ መልክ የነበረው፣ የተመጠነ ቁመት፣ ሰፊ ትከሻዎች፣ ረጃጅም ጆሮዎች፣ ሰማያዊ አይኖች፣ ፀጉሩ ላይ መለስተኛ ጠባሳ እና በቸርነት እና ምህረት የተሞላ ንጉስ ነበር። ከአስደናቂው ገላው ውስጥ ማራኪ ጠረን እንደሚወጣው ተነግሯል።
-ከቡድሃ ብዙ ደቀ መዛሙርት መካከል አናንዳ የማስታወስ አቅሙ የጎላ እንደነበር ይነገራል። አብዛኞቹ የቀደሙት የቡድሂስት ሱታ ፒታካ ጽሑፎች በአንደኛው የቡድሂስት ምክር ቤት የቡድሃ ትምህርቶችን ጨምሮ አንድ ላይ ለአስተምህሮ ያበቃው አናንዳ ነው።
-ዛሬ የቡድሃ ሃይማኖት እጅግ በጣም ሳይንሳዊ አስምህሮ ተደርጎ ይወሰዳል። እና አንዳንድ ልዩነቶችም እንዳሉ መካድ አያስፈልግም። በጊዜ ሂደት የተከሰተ ነው። ቡድሃ የሰጠው የአዕምሮ እና የአካል እውቀት የልቡ እምነት እውነታ እንጂ ለየትኛውም የሃይማኖት ህግጋት የሚውል አስተምህሮ አልነበረም!።
-አናንዳ ከመነኩሴው ቡድሃ የህይወት ክህሎት በመነሳት፤ ሁል ጊዜ ቢሆን ይጾማል እናም እስከ ፓሪኒባና ድረስ በባዶ እግሩ ረጅም ርቀት በመጓዝ ያስተምርም ነበር። መገለጥን ካገኘ በኋላ ከቤተሰቡ ጋር ተገናኘና አባቱን፣ እናቱን፣ አሳዳጊ እናቱን፣ ሚስቱን እና ልጁን ወደ ኒባና መራቸው። የአገሩ ሰዎች ሲናገሩ እንደነሱ አይነት ደስተኛ ቤተሰብ አጋጥሞን አያውቅም ይላሉ። የዚህ ሁሉ ስነ መሠረት የሆነው መምህሩ ቡድሃ ታላቁ ሳይንቲስት ከ2600 ዓመታት በፊት የተወለደ ሲድሃርታ ጓተማ ነበር፤ የእሱን ፈለግ የተከተሉት ሰዎች በጠቅላላ የመገለል፣ የመረጋጋት አስተምህሮ እናም ደግሞ የተመስጦ ቴክኒኮችን አሁንም በመተግበር ላይ ይገኛሉ ይህም በዓለም ዙሪያ አድናቆት ያለው ስብስብ ነበር።
-በቡድሃ ውስጥ በጣም የሚያስደንቀው ነገር ከምቾት ቀጠና ወጥቶ እውነትን የፈለገ ብቸኛ ሰው መሆኑ ነው። ይህ ብሩህ አእምሮ ያለው ሰው አምላክም አይደለም፣ ነቢይም አይደለም፣ እሱ ተፈጥሮውን የተረዳ አንድ ሰው ነው። ታድያ እንደ ሰው ኖረና ሞተ። በሃይማኖቱ ውስጥ የገነት ተስፋ የለም፤ የገሃነም ስጋት አልተቀመጠም። ለመጸለይ አገልግሎት የተቀመጠ መፅሃፍ የለም። እሱንም መከተል ግዴታ አልተደረገም። ምንም አስገዳጅ የአምልኮ ሥርዓቶች አልተቀመጡም። ብቻ የቡድሃን ትምህርቶች መከተል አንድ ሰው የተሻለ ሰው ያደርገዋል። “ድሃማ” የሚባለው አስተምህሮቱን አንድ ሰው መማር ካልፈለገ አይጎዳውም፤ ነገር ግን እሱ ወይም እሷ የተሻለ ሰው የመሆን እድላቸውን ያጣሉ!።