👉♻️የሰኢድ ኢብን ጁበይር አሟሟትና አስገራሚ ታሪክ ያንብቡት፡፡
``
🔷ሐጃጅ ሰኢድን “ ሸቂዩ ኢብኑ ከሲር ነህ አይደል ?” አለው፡፡(በአረብኛ ሸቅይ የሰኢድ ተቃራኒ ነው)
ሰኢድ፡- ስሜን ያወጣችልኝ እናቴ ጠንቅቃ ታውቀዋለች፡፡
🔶ሐጃጀ፡-(በቁጣ) አንተም እናትህም ፉግር እድለ ቢሶች(ሸቅይ) ናችሁ፡፡
ሰኢድ፡- ሸቅይማ የጀሀነም የሆነ ሰው ነው፡፡ የሩቅ ታውቃለህ እንዴ?
♦️ ሐጃጅ፡- ዱንያህን በአንገብጋቢ ጀሀነም ነው የምቀይርልህ፡፡
ሰኢድ፡- ወላሂ ይህን ማድረግ መቻልህን ባውቅ ከአሏህ ውጭ አምላክ አድርጌ እይዝህ ነበር፡፡
🔘ሐጃጅ፡- ለኔ ያለህ አመለካከት ምንድን ነው?
ሰኢድ፡- በሙስሊሞች ደም ተጨማልቆ አሏህን የሚገናኝ በደለኛ ነህ፡፡
◼️ ሐጃጅ፡- ይልቅ ምን አይነት አገዳደል ልግደልህ? እራስህ ምረጥ፡፡
🧿ሰኢድ፡- አንተ ራስህ መሞቻህን መንገድ ምረጥ፡ አሏህ አኔን በገደልከኘኝ መንገድ አንተንም ይገድልሃል፡፡
ሐጃጅ፡- ካንተ በፊትም ሆነ በኋላ! የማልገድልበትን አሰቃቂ ግድያ ነው የምገድልህ፡፡
ሰኢድ፡- ስለዚህ አንተ ዱንያየን ስታበላሽብኝ በኔ ምክንያት አኺራህ ይበላሻል፡፡
▪️ሐጃጅ የሰኢድን ብርታት ባለመቋቋሙ ወታደሮችን ጠርቶ እየጎተቱ ወስደው እንዲገድሉት አዘዘ፡፡
ሰኢድም በሐጃጅ እየሳቀበት ከገዳዮቹ ጋር ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ሐጃጅ በቁጣ ሰኢድን ተጣርቶ ምንድን ነው የሚያስቅህ? አለው፡፡
ሰኢድም : እኔማ የሚያስቀኝ አንተ በአሏህ ላይ ያለህ ድፍረት እና አሏህ ባንተ ስራ ያለው ትዕግስት ነው አለው፡፡
🔺ሐጃጅ ፦ ይህንን ሲሰማ በቁጣ ገንፍሎ ወታደሮቹን እረዱት ሲል አንቧረቀባቸው፡፡
ሰኢድም፦ ወደ ቂብላ አዙራችሁ እረዱኝ አለ፡፡ አንገቱ ላይ ሰይፍ እንዳስቀመጡበትም
“ وجهت وجهي للذي فطر السموات والأرض حنيفا مسلما وماأنا من المشركين
ይህንን የሚከታተለው ሐጃጅ ፊቱን ከቂብላ ወደ ሌላ አቅጣጫ አዙሩት አላቸው፡፡
ሰኢድም ፦ “ ولله المشرق والمغرب فأين ما تولوا فثم وجه الله የሚለውን አያህ ቀራ፡
🔻ሐጃጅም በፊቱ ድፉት አለ፡፡
🤌ሰኢድም منها خلقنكم وفيها نعيدكم ومنها نخرجكم تارةأخرى የሚለውን አያህ አነበበለት፡፡
ሐጃጅ፡- አንተ ሰኢድ ምላስህ እንዴት ለቁርአን ፈጣን ነው!!! እረዱት አለ፡፡
☝️በዚህ ጊዜ ሰኢድ أشهد أن لاإله إلاالله وأن محمدرسول الله
🫵ሐጃጅ ሆይ የውመል ቂያማ እስከምንገናኝ ድረስ ይህችን ንግግሬን ያዛት አለና “ አሏህ ሆይ ከኔ በኋላ ማንንም እንዳይገድል አድርገው ” ብሎ አሏህን ተማጽኖ ተገደለ፡፡
👌የሚገርመው ነገር ግን ከሰኢድ ሞት በኋላ ሐጃጅ በየሌሊቱ “ ምነው ይህ ሰኢድ ልተኛ ስል እግሬን እየያዘ እረፍት ነሳኝ ” እያለ እየባነነ ይጮህ ነበር፡፡
🙌ከሰኢድ ሞት 15 ቀናት በኋላ ሐጃጅ ማንንም ሰው ሳይገድል ሞተ፡፡ አንተ የጁበይር ልጅ ሆይ አሏህ ይዘንልህ፡፡ ካንተ ፅናት፣ አሳማኝ መረጃ እና የኢማንህ ንፅህና አንፃር እኛስ የት ነን?
🤝መልካም አዳር
👇👇👇👆👆👆
https://t.me/nurders/7638