ክፍያቸውን ለፈፀሙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ዛሬ ተለቋል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት ሳይለቀቅ መዘግየቱይታወቃል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞችን ክፍያ የሚፈፅሙት ተቋማት ክፍያቸውን ሳያደርጉ በመዘግየታቸው የተፈታኞቹ ውጤት ሳይለቀቅ ቆይቷል።
ተቋማቱ ክፍያውን በመፈፀማቸው የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለየተቋማቱ መለቀቁን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።
📄
@Exitnewss