አሜን አሜን አሜን ልበል እስኪ አሜን
አምላክ ፍቅሬን አንቺን ቢሰጠኝ አልኩ አሜን
አሜን አሜን አሜን እስኪ ልበል አሜን
ሰላምን ጽናትን ፍቅርን ባንቺ አየሁ ህይወትን
ክፉ አይንካሽ በምድር ክፉ አይንካሽ ባለም
ኑሪልኝ ዘላለም ዘላለም
አንቺ የህመሜ ሀኪም አንቺ በጭንቅ የፈተንኩሽ
አንቺ ክፉ ቀን መወጫ አንቺ ጉልበቴ ያረኩሽ
መጽናኛዬ ያልኩሽ እህህ ብዬ እህህ ብዬ
እህህ ብዬ የልቤን ልንገርሽ
አንቺ የህይወት ምስክር አንቺ የሄዋን ጉልበታም
አንቺ አንቺ አንቺ የእናት የእህት ምትክ
አንቺ የደግነት ሀብታም ነሽ ምግባረ መልካም
በደስታሽ በሳቅሽ እረካለሁ ሲከፋሽ ስታዝኚም አዝናለሁ
ፍቅርን ህይወትን አስተምረሽኛል አመሰግናለሁ ውለታሽ ከብዶኛል
👇👇👇
@old_musicaሼር🙏