ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


✞✞✞ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ፅሁፎች ለማግኘኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞✞✞
@orthodox1
ሁሉም እንዲያነበው share ያርጉ

ለማንኛውም መረጃዎች ለመጠየቅ @drshaye
ማናገር ይችላሉ
🇪🇹 ✝✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር 🇪🇹
Join Us Today And Lets learn Together ✝✝✝
@orthodox1

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🙏 በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት ✅JOIN✅ የምትለውን ብቻ ይንኳት።🙏


👑'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN


"The woman who left her water jar: The Samaritan Woman"
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°•◇•°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
[A theological discourse on a woman from Samaria, often referred to as the Samaritan woman. It delves into her encounter with Jesus Christ as described in the Gospel of John, chapter 4. The text highlights her significance in Christian theology and her role as an evangelist.]


         From the Samaritan village, the noble stories of the good Samaritan and the good Samaritan woman stand out. In our Book of Synaxarium , on the 5th of Megabit, we read about Saint Eudoxia, a Samaritan woman whose name means 'peace and tranquility,' who achieved great martyrdom.

The story of the good Samaritan is a lesson [Luke 10:33], but hers is real story. Her dwelling place was Sychar, the great "Samaritan" woman [John 4:7].

       This woman was a precious witness, causing the name 'Savior of the World' to be first spoken by human lips in the Gospel through her preaching.

"Martyrs testify to us that this is truly Christ, the Savior of the world."

The Gospel narrates her final mission thus: "And the woman left her water jar and went into the city and told the people, saying, ‘Come, see a man who told me all that I ever did. Could this be the Christ?’

The golden-mouthed preacher, Saint John Chrysostom, elaborates on her apostolic work: "While the other apostles left their nets to follow Him, she too, as an apostle, left her water jar and followed Him. While they witnessed to Philip, Andrew, and others to follow Him, she preached to the whole village to follow Him."

Who is the Samaritan woman?
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
        Beside our 81 books of the Holy Bible , other 'holy' traditions also mention her with various names and additional stories.
Early Greek texts describe her as having five sisters and two children, martyred for her faith, and a follower of Saints Paul and Peter. She is revered as the great martyr, Saint Photine of Samaria.

Our Teamre Iyesus (Miracle of Lord Jesus) also mentions her name and narrates her story as follows : "And when the Samaritan woman, named #BERFISENIYA, heard the word of the Lord Jesus, she went into the city and told the people, saying, ‘Come, see a man who told me all that I ever did. Could this be the Christ?’"

         Saint Berfiseniya, the Samaritan woman, left her water jar and returned to the village, calling all to the living water, to salvation. Her mouth became a fountain of life. "The mouth of the righteous is a fountain of life, but the mouth of the wicked conceals violence." [Proverbs 10:11]

         For the people of Sychar, Saint Photinia served as a "water jar" leading them to the living water, Christ. Though they followed her preaching, they denied her role, saying:  "And they said to the woman, ‘It is no longer because of your words that we believe, for we have heard ourselves and know that this is indeed the Christ, the Savior of the world."

           May the blessing of the Samaritan woman Saint Berfiseniya (Photinia) be upon us all!


"ብእሲት ዘኃደገት ቀሱታ ⇨  መቅጃዋን የተወችው ሴት"
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°•◇•°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

ከሰማርያ መንደር ከወጡ ደገኛ የቅዱስ መጽሐፍ ባለ ታሪኮች ደጉ ሳምራዊ እና ደጓ ሳምራዊት ጎልተው ይጠቀሳሉ። በመጽሐፈ ስንክሳራችንም መጋቢት ፭ ቀን የስሟ ትርጓሜ ሰላምና ሥምረት የሆነ ቅድስት አውዶክስያ የምትባል አንዲት ሳምራዊት ሴት በታላቅ ተጋድሎ ማረፏን ይነግረናል።

የደጉ ሳምራዊ ታሪክ ለትምህርት ምሳሌ ነው [የሉቃስ ወንጌል 10:33] ፤ የእርሷ ግን በአምላካችን ዘመነ ሥጋዌ የተፈጸመ አስተማሪ ኩነት አዝሏል።  መኖርያዋ ሲካር ነው  ታላቋ «ሳምራዊት» ሴት [የዮሐንስ ወንጌል 4:7]

ይህች ሴት መድኃኔዓለም የሚለውን ስም በወንጌል ቀድሞ በሰው አፍ እንዲጠራ በስብከቷ ምክንያት የሆነች የከበረች ምስክር ናት።

ሰማዕነ ወጠየቅነ ከመ ዝንቱ ውእቱ ክርስቶስ በአማን #መድኅነ_ዓለም
            ↳  ይህ በእውነት የዓለሙ መድኅን ክርስቶስ እንደሆነ ሰምተናል ተረድተናል

ወንጌል ስለመጨረሻው ተልእኮዋ ሲነግረን እንዲህ ይተርከዋል፦
            ☞  "ወኃደገት ቀሱታ ይእቲ ብእሲት ወአተወት ሀገረ ወነገረት ለሰብአ ቤታ ።  ወትቤ ንዑ ትርአዩ ብእሲ ዘነገረኒ ኵሎ ዘገበርኩ እንዳዒ ለእመኑ ውእቱ ክርስቶስ "
            ↳ ሴቲቱም ማድጋዋን ትታ ወደ ሀገር ገብታ ለቤተሰቦቿ ነገረች ። የሠራሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፡ ክርስቶስም እንደሆነ እንጃ አለች ።

መምህረ ዓለም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሐዋርያዊ ሥራዋን በላቀ መንገድ ሲነግረን "ሌሎቹ ሐዋርያት መረባቸውን ጥለው ሲከተሉት እርሷም በሐዋርያነቷ መቅጃዋን ጥላ ተከተለችው ከእነርሱ እነ ፊልጶስ እነ እንድርያስ ሌላውንም እንዲከተለው በአንድ በሁለቱ ፊት ሲመሰክሩ እርሷ ግን መንደሩ ሁሉ እንዲከተለው ሰበከች" አለን ፤ አቤት መታደሏ!


ሳምራዊቷ ሴት ማናት?
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ከ፹፩ዱ ቅዱስ መጽሐፋችን በተጨማሪ በሌሎች የትውፊት መጻሕፍት አዋልድም ጭምር በተለያዩ  መጠሪያዎች ተጠርታ  ከተጨማሪ ታሪኮች ጋር እናገኛታለን።

       ቀደምት የግሪክ ክታቦች አምስት እኅቶችና ሁለት ልጆች የነበሯት በሰማዕትነት ክብር ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስን ተከትላ የጽድቅ ምስክር ሆና ያረፈች እንደሆነች አስረድተው ስሟ የከበረ ታላቋ ሰማዒት (ምስክር) ሳምራዊቷ ቅድስት #ፎጢን (holy and glorious Great-martyr #Photine of Samaria) እያሉ ገልጠዋታል።

የ’ኛውም ተአምረ ኢየሱስ  ደግሞ ስሟን በመጥቀስ የታሪኳን ፍጻሜ እንዲህ አስቀምጦልናል ፦

             ☞ "ወሶበ ሰምአት ብእሲት ሳምራዊት ዘስማ #ብርፍሴንያ ነገሮ ለእግዚእ ኢየሱስ ሖረት ወዜነወት ለሰብእ እንዘ ትብል ንዑ ኀቤየ አርእየክሙ ብእሴ ዘየአምር ኅቡአተ እስመ ውእቱ ዜነወኒ ግብርየ ዘአኀብኦ እም ሰብእ"
            ↳   ይህችም ብርፍሴንያ የምትባል ሳምራዊት ሴት የጌታ ኢየሱስን ነገር በሰማች ጊዜ ወደሀገር ገብታ ለሰዎቹ ሁሉ በሆዴ ውስጥ ያለውን ምሥጢር ሁሉ የሚናገር ሰው አሳያችሁ ዘንድ ኑ እኔ ከሰው ደብቄ የያዝኩትን ምሥጢር ነግሮኛልና አለቻቸው ።


        ሳምራዊቷ ሴት ቅድስት ብርፍሴንያ መቅጃዋን ጥላ ወደ መንደር ተመልሳ በሀገሩ ያሉትን ሁሉ ወደ ድኅነት ወደ ሕይወት ውኃ ጠራች የበረከት ቃል ከአንደበቷ እየተቀዳ አፏ የሕይወት ውኃ ምንጭ ሆነ።  "ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ" ትላለች። ጠቢቡ “የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ናት፤ የኀጥኣንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል።”  【ምሳሌ 10፥11】

         ለሲካር መንደር ሕዝብ ቅድስት ብርፍሴንያ ለሕይወት ውኃ ክርስቶስ "መቅጃቸው" ናት። እነርሱ ግን የሴት ደቀ መዝሙር ለመባል አፍረው በእርሷ ስብከት ተከትለው ቢያምኑበትም የእርሷን ድርሻ ግን እንዲህ እያሉ ካዱ ፦

             ☞ "ወይቤልዋ ለይእቲ ብእሲት አኮ እንከ በነገረ ዚአኪ ዘአመነ ቦቱ አላ ለሊነ ሰማዕነ ወጠየቅነ ከመ ዝንቱ ውእቱ ክርስቶስ በአማን መድኅነ ዓለም ።"
            ↳ ሴትዮዋንም አሁን በእርሱ ያመን ፡ አንቺ በተናገርሽው አይደለም እኛ ራሳችን ይህ በእውነት የዓለሙ መድኅን ክርስቶስ እንደሆነ ሰምተንና ተረድተን ነው እንጂ አሏት።

የሳምራዊቷን ሴት የቅድስት ብርፍሴንያ [Great-martyr St. Photine]
      ✧ በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር!  ✧


"ብእሲት ዘኃደገት ቀሱታ ⇨ መቅጃዋን የተወችው ሴት"
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°•◇•°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
"The woman who left her water jar: The Samaritan Woman"


(መሥዋዕት ለማቅረብ) ወደ ቤተ መቅደስ ሔዷል፡፡ ከዚህም እርሱ አምላክ ነኝ እና በተአምራቴ የማዳን ሥራዬን ልፈጽም ሳይል ከኀጢአትና ከፈቃደ ሥጋ በስተቀር በሰው ሥርዓት ማደጉን፤ እንደዚሁም የትሕትና ጌታ መኾኑን እንማራለን፡፡ ዛሬም ምእመናን ልጅ ሲወልዱ ወንዶችን በዐርባ፤ ሴቶች ደግሞ በሰማንያ ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን በመውሰድ ክርስትና የሚያስነሡት በዚህ ሥርዓት መሠረት ነው፡፡

ከነቢዩ ስምዖን ታሪክም በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ የማይፈጽመውን የማይናገር፤ የተናገረውንም የማያስቀር የእውነት ባለቤት እንደ ኾነ፤ እንደዚሁም እኛ አይደረግም ያልነው ከባድ የሚመስለን ምሥጢር ጊዜውን ጠብቆ መፈጸሙ እንደማይቀር፤ በተጨማሪም እግዚአብሔር በጥበብ የሚገሥፅ፣ የሚያስተምር የፍቅር አምላክ እንደ ኾነ እንገነዘባለን፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም በሥርዓተ ጋብቻ እስኪወሰኑ ድረስ ወንድሞችም እኅቶችም ክብረ ንፅሕናቸውን ጠብቀው መቆየት እንዳለባቸው፤ ከጋብቻ በኋላ ከሁለቱ ጥንዶች አንዱ በሞት ቢለይ ፈቃደ ሥጋቸውን መግታትና ሰውነታቸውን መቈጣጠር የሚቻላቸው ከኾነ እስከ ምድራዊ ሕይወታቸው ፍጻሜ ራሳቸውን ጠብቀው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ቢኖሩ በጸጋ ላይ ጸጋን፤ በበረከት ላይ በረከትን እንደሚታደሉ ከነቢዪት ሐና ታሪክ የምናገኘው ትምህርት ነው፡፡

በእርግጥ በሞት ወይም በዝሙት ምክንያት ከትዳር አጋሮቻችን ጋር የተለያየን ምእመናን ፈቃደ ሥጋችንን መቋቋም የማይቻለን ከኾነ በሥርዓተ ቍርባን በድጋሜ ጋብቻ መመሥረት እንደምንችል በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተደንግጓል፡፡ እናም በሞት ለተለያዩ ጥንዶች ሁለተኛ ጋብቻ ባይከለከልም ሳያገቡ እንደ ነቢዪት ሐና ራሳቸውን ጠብቀው መኖር ለሚፈልጉ ግን አለማግባት ይቻላል፡፡ ራስን ጠብቆ መኖር በእግዚአብሔር ለተመረጡ ሰዎች እንጂ ለዅላችን አይቻለንምና፡፡ ‹‹… እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ አደለው ጸጋ ይኑር፤ ግብሩ እንዲህ የኾነ አለና፡፡ ገብሩ ሌላ የኾነም አለና፡፡ ነገር ግን ያላገቡትንና አግብተው የፈቱትን እንደ እኔ ኾነው ቢኖሩ ይሻላቸዋል እላቸዋለሁ፡፡ በፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና …፤›› እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ /፩ኛ ቀሮ.፯፥፯-፱/፡፡

ነቢዪት ሐና በድንግልና ከመኖሯ እና ሁለተኛ ባል ካለማግባቷ ባሻገር ዓለማዊ ተድላና ደስታን ንቃ፣ ሰውነቷን ጠብቃ፣ ከምኵራብ ሳትወጣ ሰማንያ ዓመት ሙሉ እግዚአብሔርን ስታገለግል መኖሯ ከእርሷ የምንማረው ሌላኛው ቁም ነገር ነው፡፡ እኛም እንደ ነቢዪቷ ሙሉ ጊዜአችንን ለቤተ ክርስቲያን መስጠት ባይቻለን እንኳን ከሥጋዊው ሥራችን ጎን ለጎን ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሔድን ትምህርተ ወንጌል ብንሰማ፣ ብንጸልይ፣ ብንሰግድ፣ ከምሥጢራት ብንሳተፍ፤ እንደዚሁም ለአቅማችን በሚመጥን ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ተልእኮ ብናገለግል የእግዚአብሔር ጸጋ በእኛ ላይ ይበዛል፤ እጥፍ ድርብም ይኾናል፡፡ ከዅሉም በላይ በምድራዊው ሕይወታችን የክርስቶስ ቤተ መቅደስ የኾነውን ሰውነታችንን ከኀጢአት ለይተን፣ ራሳችንን ለጽድቅ ሥራ አስገዝተን፣ በመንፈሳዊ ምግባር ጸንተን፣ ስንበድል ተጸጽተን (ንስሐ ገብተን)፣ ቅዱስ ሥጋውን በልተን፣ ክቡር ደሙን ጠጥተን ብንኖር የማያልፈውን መንግሥቱን ለመውረስ እንበቃለን፡፡

የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የነቢዩ ስምዖን እና የነቢዪት ሐና፣ የሌሎችም ቅዱሳን በረከት ይደርብን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው ☞ የካቲት ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም


« ልደተ ስምዖን ነቢይ »
°°°°°°°°°ተ°°°°°°°°°°°°

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የካቲት ፰ ቀን ከሚከበሩ በዓላት መካከል የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት፣ የነቢዩ ስምዖን ልደት (መታደስ) እና የነቢዪት ሐና ዕረፍት በስፋት ይነገራል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በስምንተኛው ቀን (ጥር ፮ ቀን) በኦሪቱ ሕግ መሠረት ሥርዓተ ግዝረትን ፈጽሟል፡፡ በተወለደ በዐርባኛ ቀኑ (የካቲት ፰ ቀን) ደግሞ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቷል፡፡ (ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደበት ከታኅሣሥ ፳፱ ቀን ጀምረን ስንቈጥር የካቲት ፰ ዐርባኛው ቀን ነው፡፡)

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተመዘገበው ከሕርስ ደም የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ ‹‹የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ (የበኵር ልጅ) ዅሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ እንደ ኦሪቱ ሥርዓት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ጠባቂዋ ጻድቁ ዮሴፍ ለመሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሳትን ይዘው ጌታችንን በዚህች ዕለት ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡ ‹‹ከሕርስ ደም የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ›› ሲልም በሌሎች ሴቶች ልማድ ለመናገር ነው እንጂ በእመቤታችንስ ይህ ዅሉ ጣጣ የለባትም፡፡ ከሴቶች ተለይታ የተመረጠች ቅድስት የአምላክ እናት እንደ መኾኗ ለድንግል ማርያም ርስሐት በፍጹም አይስማማትም፡፡ በሌላ በኩል ‹‹ከሕርስ ደም የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ›› ማለት ከሰው የሚለዩበትን ጊዜ ያመለክታል፡፡ ወንዶች በተወለዱ በዐርባ፣ ሴቶች በሰማንያ ቀናቸው ከሰው ይለያሉና፡፡

ጌታችን ወደ ቤተ መቅደስ በሔደ ጊዜም አረጋዊው ነቢዩ ስምዖን ታቅፎት ሰውነቱ ታድሷል፡፡ ይህ ዕለት (የካቲት ፰ ቀን) ‹‹ልደተ ስምዖን›› እየተባለ የሚጠራውም ዕለቱ ነቢዩ ጌታችንን ታቅፎ ከእርግናው (ሽምግልናው) የታደሰበት፤ ከደዌው የተፈወሰበት፤ አምላኩን በሥጋ ያየበት በአጠቃላይ ዳግም የተወለደበት ዕለት በመኾኑ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ስምዖን›› በሚለው ስም ከሚጠሩ ቅዱሳን መካከል ነቢዩ ስምዖን አንዱ ነው፡፡ የነቢዩን ታሪክ ለማስታዎስ ያህል አባታችን አዳም በተፈጠረ በአምስት ሺሕ ሁለት መቶ ዓመት በንጉሥ በጥሊሞስ ዘመነ መንግሥት የኦሪት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ እንዲተረጕሙ ከታዘዙ ሰብዓ ሰዎች (ሊቃናት) መካከል አንዱ ነቢዩ ስምዖን ነው፡፡

ይህ ነቢይ ትንቢተ ኢሳይያስ ደረሰውና እየተረጐመ ሳለ ‹‹እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፡፡ ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች፤›› ከሚለው ኀይለ ቃል በደረሰ ጊዜ በቀጥታ ቢተረጕመው ንጉሡ እንደማይቀበለው በማሰቡ፤ እርሱም ‹‹ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል?›› ብሎ በመጠራጠሩ ‹‹ድንግል›› የሚለውን ቃል ‹‹ወለት›› (ሴት ልጅ) ብሎ ተረጐመው፡፡ ተኝቶ በነቃ ጊዜም ‹‹ወለት›› የሚለው ቃል ተፍቆ ‹‹ድንግል›› ተብሎ ተጽፎ አገኘና እርሱም ‹‹ድንግል››ን ፍቆ ‹‹ወለት›› ብሎ ይጽፋል፡፡ ዳግመኛም ለሁለተኛና ጊዜ ተኝቶ ሲነቃ ቃሉ እንደ ነበረ ኾኖ ያገኘዋል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ቃሉን እፍቃለሁ ሲልም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ‹‹የተጠራጠርኸውን፣ ከድንግል የሚወለደው ክርስቶስን እስከምታየውና እስከምትታቀፈው ድረስ ሞትን አትቀምስም፤›› ብሎታል፡፡

‹‹መሲሑን ሳታይ አትሞት›› የተባለው ነቢዩ ስምዖን አርጅቶ ከአልጋ ተጣብቆ ለሦስት መቶ ዓመታት ያህል ከኖረ በኋላ ትንቢቱ ተፈጽሞ፣ ዘመኑ ደርሶ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በዐርባኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ እስከ በገባበት ዕለት መንፈስ ቅዱስ አነሳሥቶ ወደ ምኵራብ ወሰደው፡፡ በዚያም ጌታችንን ከእመቤታችን ተቀብሎ ለመታቀፍ ታድሏል፡፡ ‹‹የምትጠብቀው ሕፃን ይህ ነው›› ብሎ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በነገረው ጊዜም ታውረው የነበሩ ዓይኖቹ ተገልጠዋል፤ ሰውነቱም ታደሷል፡፡

ነቢዩም የእግዚአብሔርን ማዳን በዓይኑ በማየቱ፣ ከደዌው በመፈወሱ እና ከእርጅናው በመታደሱ በአጠቃላይ በተደረገለት ድንቅ ተአምር ዅሉ በመደሰቱ እግዚአብሔርን አመስግኗል፡፡ ‹‹አቤቱ ባሪያህን ዛሬ አሰናብተኝ፤ ዓይኖቼ ትድግናህን አይተዋልና፤›› በሚለው ትንቢታዊ መዝሙሩም ‹‹የእግዚአብሔርን ማዳን በዓይኔ ስላየሁ እንግዲህስ ልረፍ›› በማለት ሞቱን ተማጽኗል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም የክርስቶስን የዓለም ቤዛነትና ክርስቶስ በሥጋው በሚቀበለው መከራ እመቤታችን መራራ ኀዘን እንደሚደርስባት፤ እንደዚሁም ጌታችን ለሚያምኑበት ድኅነትን፣ ለሚክዱት ደግሞ ሞትን የሚያመጣ አምላክ እንደ ኾነ የሚያስገነዝብ ትንቢት ተናግሯል፡፡

የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ለነቢዩ ስምዖን የተደረገለትን ታላቅ ሥራ ሲያደንቁ እንዲህ ይገልጹታል፤ ‹‹ሰላም እብል እንዘ እዌድሶ ወእንዕዶ፤ መዝሙረ ማኅሌት በአስተዋድዶ፤ ክብረ ስምዖን ነቢይ ለክብረ ሱራፌል ዘይፈደፍዶ፤ እስመ ሐቀፈ መለኮተ ወገሠሠ ነዶ፤ እኤምኅ ሕፅኖ ወእስዕም እዶ፤ የማኅሌት መዝሙርን በማዘጋጀት እያከበርሁትና እያደነቅሁት ከሱራፌል ክብር ለሚበልጠው ለስምዖን ክብር ሰላም እላለሁ፡፡ እርሱ መለኮትን በእጁ ታቅፏል፤ እሳቱንም ዳሷልና እቅፎቹን እጅ እነሳለሁ፤ እጆቹንም እስማለሁ፤›› /መጽሐፈ ስንክሳር፣ የየካቲት ፰ ቀን አርኬ/፡፡ የዚህ አርኬ መልእክት ኪሩቤል፣ ሱራፌል (ሰማያውያን መላእክት) በእጃቸው የማይነኩት፣ ከግርማው የተነሣ የሚንቀጠቀጡለት፣ እሳተ መለኮቱ የሚቃጥል እግዚአብሔር ወልድን ነቢዩ ስምዖን በክንዱ ለመታቀፍ በመታደሉ ክብሩ ከመላእክት እንደሚበልጥ፤ ለክብሩም የጸጋ ምስጋና እና እጅ መንሻ ማቅረብ እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ነው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የነቢዪት ሐና ዕፍትም በዛሬው ዕለት ይታሰባል፡፡ ይህቺ ቅድስት ከአሴር ነገድ የተገኘች ደግ እናት ስትኾን አባቷም ፋኑኤል ይባላል፡፡ ክብረ ንጽሕናዋን ጠብቃ በድንግልና ኾና ዐሥራ አምስት ዓመት ሲሞላት ባል አግብታ ሰባት ዓመት ከባሏ ጋር ቆይታለች፡፡ ከባሏ ጋር ከተፋታች በኋላ ራሷን ጠብቃ ቀንም ሌትም ከምኵራብ ሳትወጣ በጾም በጸሎት ተወስና በሚቻላት ዅሉ እግዚአብሔርን እያገለገለች ሰማንያ አራት ዓመት ኖራለች፡፡ ይህቺ የአንድ መቶ ስድስት ዓመቷ አረጋዊት ጌታችን ወደ ቤተ መቅደስ በገባበት ዕለት በምኵራብ ተገኝታ አምላኳን በዓይኗ ለማየት በማታደሏ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት እና የዓለም ቤዛነት አመነች፡፡ ለዚህ ቀን ያደረሳትን እግዚአብሔርንም አመሰገነች፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝታም የክርስቶስን ሥራ እያደነቀች የሰውን ድኅነት በተስፋ ለሚጠባበቁ ለኢየሩሳሌም ሕዝቦች አዳኝነቱን መሰከረች /ሉቃ.፪፥፴፮-፴፱/፡፡ በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ዐርፋለች፡፡

ምንጭ፡-

መጽሐፈ ስንክሳር፣ የካቲት ፰ ቀን፡፡

የሉቃስ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ፣ ሉቃ.፪፥፳፪-፴፱፡፡

ከዚህ ታሪክ ከምንገነዘባቸው በርካታ ቁም ነገሮች መካከል ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሦስቱ አካላት (አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) አንዱ (ወልድ) ነው፡፡ እንደ አምላክነቱ በዅሉም ቦታ የመላ ነውና መሔድ መምጣት፣ መራብ መጠማት የባሕርዩ አይደለም፡፡ ስለዚህም ‹‹ሔደ፤ መጣ፤ ተራበ፤ ተጠማ፤ ተገረዘ፤ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደ፤ ወዘተ.›› የመሳሰሉ ለፍጡራን የሚስማሙ ቃላት አይነገሩለትም፡፡ ነገር ግን መድኀኒታችን ክርስቶስ መገረዝ፣ መሔድ፣ መምጣት፣ መራብ፣ መጠማት የሚስማማው ሥጋን ለብሷልና የሰውነቱን ሥራ ይፈጽም ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ በተቀመጠው ሕግ መሠረት በተወለደ በስምንተኛው ቀን ለመገረዝ፤ በዐርባኛው ቀን ደግሞ ለመቀደስ


« ልደተ ስምዖን ነቢይ »
°°°°°°°°°ተ°°°°°°°°°°°°


⇨ ቀኝን እብራይስጡም ( יָמִין yaw-meen ) የውሚን የሚለው ግእዛችን የማን ያለውን ነው፤ በትርጉም the right hand or side (the south) ቀኝ እጅና አቅጣጫ ሆኖ ደቡብን ጠቋሚ ነው!
↳ ቴማን የሚለው የኤሳው የልጅ ልጅ ወይም የኤልፋዝ ልጅ መጠሪያና የቦታ ስም ትርጉሙ #ቴማን እንተየማን ወይም ደቡብ በሚል ተተርጉሟል

⇨ ግራን ዳግመኛም በሂብሩ ( שְׂמֹאול⇝ sem-ole') ሴምኦሌ የሚለው ግእዙ ፀጋም የሚለውን ሲሆን በፍቺው ; the left hand or side (the north) ሰሜን የሚለውን ዐቢይ ማእዘን የሚገልጥ ግራ እጅና የግራ አቅጣጫ ነው፤ በዚህም ለአቅጣጫው የግራ ሀካይነትና ድኩምነት መገለጫው ሆኖ የጽኑ ጥፋትና የክፉ ነገር መነሻ መሆኑ ተነግሯል፤
↳ "ወንሥኡ ጽዮነ ወአምስጡ ውስተ ጽዮን እስመ አመጽእ እኪተ ‘እምሰሜን’ … ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ጽዮንን ያዙ ወደ ጽዮን ሽሹ" (ኤር ፬፥፮) ይላል…


ስለዚህ እኛም ፦ ወደ «ጽዮን» በመሸሽ ከጠቢቡ ሰሎሞን ጋር ሁነን ⇨ ሰሜን ሆይ ተነሥ፣ ደቡብ ሆይ ና እንበለው "ተንሥእ ሰሜን ወነዐ ደቡብ" ( መኃ ፬፥፲፮)

② #ጌባል እና #ገሪዛን (ጌባል ፀጋማይ ተራራ፣ ገሪዛን የማናይ ተራራ)
. ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈

ኹለቱም ተራሮች የዮሴፍ ልጅ የኤፍሬም ነገድ ርስት ውስጥ ይገኛሉ፤
⇨ ጌባል ፦ በስተሰሜን ያለ የተራራ ስም ሲሆን የገሪዛን አንፃር የርግማን ቃሎች የሚነገሩበት ፀጋማይ ተራራ ነው ( ዘዳ ፳፯፥ ፲፫)፡፡
⇨ ገሪዛን፦ በስተደቡብ ያለ ቍርጥ የኾኑ የቡራኬ ቃሎች የሚነገሩበት በጌባል አንጻር ያለ ተራራ ነው (ዘዳ ፳፯፥ ፲፪)፡፡

ስለዚህ እኛም ፦ "አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ።" (ዘዳ፲፩ ፥፳፱) እንደሚል ከግራው ናባል ርቀን በበረከቱ ተራራ በገሪዛን ያለውን በቍዔተ ነፍስ ደጅ እንጠናለን።

③ #ዳክርስ እና #ጥጦስ (Dumachus and Titus)
. ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈

ከመድኃኔዓለም ቀኝና ግራ የተሰቀሉ ወንበዴዎች መጠሪያ ስም ነው፤ ፈያታዊ ዘፀጋምና ፈያታዊ ዘየማን ይላቸዋል (Dumachus on left hand and Titus on right hand) የመጠሪያ ስማቸው (ስመ ተጸውኦ) ስያሜ በእኛ ሀገር ተአምረ ኢየሱስን ጨምሮ በሌሎች ቀደምት አዋልድ መጻሕፍት የተመለከተ ሲሆን በሌሎቹም ሀገራት ቀደምት መጻሕፍትም ጭምር በተመሳሳይ አገባብ ተገልጧል፤ ለምሳሌ በሶርያ የቀደመ መዝገብ (በልሳነ ሱርስት) ጌታችን በልጅነቱ የፈፀማቸው ገቢረ ተአምራት በተዘገበበት ወንጌል "The Syriac Infancy Gospel" ወይም "Arabic Infancy Gospel" ላይ ጌታችን ገና በልጅነቱ ከእናቱ ጋር ወደግብፅ ሲሰደድ ሁለቱን ሽፍቶች እንዳገኘ እና ትንቢት እንደተናገረላቸውም ጭምር የሚዘግብ ታሪክናና በየስማቸው የሚጠቅስ አመልካች ሀተታ ይገኛል።

⇨ ዳክርስ (Dumachus) ፈያታዊ ዘፀጋምና በግራ የተሰቀለው ያልተጸጸተው ወንበዴ( Impenitent thief) ነው!
⇨ ጥጦስ (Titus) ፈያታዊ ዘየማን በቀኝ የተሰቀለው የተጸጸተው ወንበዴ (Penitent thief) ነው!

ከአበው ይኽን ገላጭ እንዲህ የምትል ረቂቅ ቅኔ እናገኛለን
. "የማናይ ርጎ ፀጋማይ ጐመን
. ወማእከሎሙ ኢየሱስ ዝግን "

ስለዚህ እኛም፦ መናዝዝ ወደሆነ የሚገባ ጸጸት ተሻግረን እንደ ጥጦስ በቀኙ ውለን "በመንግሥትህ አስበኝ" በማለት የቀኙ ጥላ እንዲያርፍብን እንትጋ።

④ #ፍየል እና #በግ (ጠሊ ወበግዕ)
. ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈

ስለ ትንሳኤ ዘጉባኤ በተነገረው የቅዱስ መጽሐፋችን ክፍል «የሰው ልጅ» ክርስቶስ በክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ በአውደ ፍትሕ
"በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።" ይላል (ማቴ ፳፭፥፴፫) መጽሐፈ ግንዘትም " ምቅዋመ አጣሊ ርጉማን ወምቅዋመ አባግዕ ብሩካን፡፡" ብሎ ይፈታልናል።

⇨ ፍየል (ጠሊ) በምሥጢር ሽቅብ አንጋጠው ስለሚሔዱ በላታቸው ነውራቸውን ስለማይሸፍኑ ኀፍረታቸው ስለተገለጠ… ትዕቢትን በሚያበዙ ነውራቸውን በንስሐ በማይሸፍኑ ባለ "ጠዋይ ፍኖት" ( ጠማማ መንገድ) ፣ "ገብር ፀዋግ" (ክፉ ባርያ) ምሳሌ ነው!
ጠሊ ለሚለው አብዢ አጣሊ በማለት ፈንታ « አ» ን ትቶ በ“ን”ና በ“የ” ሲበዛ ግን #ጣልያን (አጣሊ ኢጣሊ አጣልያን ‘ጣልያን) ይላል ይኽንንም ብዙ ሊቃውንት ሀገር ወራሪውን ለመዝለፍ በቅኔ ሲራቀቁበት ታይቷል።

⇨ በግ (በግዕ) በአንፃሩ አቀርቅረው የሚጓዙ በላታቸው ኀፍረታቸው የሚሰውሩ መሆናቸው በትህትና ለሚኖሩ በንስሐ ኀጢአታቸውን ለሚሰውሩ "በርትዐተ ልብ" እና "በጽድቅ ምሕዋር" ለሚሔዱ ኄራን አግብርት ምሳሌ ነው!

ስለዚህ እኛም በትህትና ራሳችንን በመግዛት ወደ ነፍሳችን ጠባቂና እረኛ እንመለስ ተቆጥቶ "ከእኔ ራቁ" ሳይሆን ከበጎቹ ጋር በቀኙ የሚያውለውን "ወደ እኔ ኑ" የሚለውን ወደመስማት የሚያደርሰውን ጥበብ በማስተዋል ገንዘብ እናድርግ፤ በአስተዋይ ዘንድ ጥበብ በቀኝ እጅ ያለ በጥንቃቄና በቅንነት የተያዘን አምባር ትመስላለችና "ከመ ድጕልማ ውስተ እደ የማን ከማሁ ጥበብ በኀበ ለባዊ " እንዲል ( ሲራ ፳፩፥፳፩)

ቀኝ ያውላችሁ!

(ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ለጾመ ነነዌ ፳፻፲፩ ዓ.ም. በመንገድ የተጻፈ )


#እለ_ኢፈለጡ_ፀጋሞሙ_እም_የማኖሙ
. (ግራቸውን ከቀኛቸው ያልለዩ) ☞ ዮና ፬፥፲፩

እንደምን አላችሁ? ለተቀረው ደግሞ ቅን በሆነ ቀን፣ በቀኝ ያውላችሁ!

በዚያን ወቅት የአሦራውያን ግዛትና የጤግሮስ ወንዝ መዳረሻ ሆና ስልምናሶር የሚያስተዳድራት ከአሥራሁለት እልፍ (መቶ ሃያ ሺህ) በላይ ሕዝብ እና ብዙ እንሰሳት ያሉባት ከተማ ነበረች፤ ይህች ከተማ ነነዌ ትባላለች፤

ቀድሞ ግን የሴም ልጅ አሦር የመሠረታት ከስልምናሶር በተጨማሪ ሰናክሬምና ሌሎችም ነገሥታት ያስተዳደሯት ለአሦራውያን ግዛት መዲና ሆና የኖረችው ጥንታዊቷ ‘እመ አህጉር’ ዛሬ በባግዳድ አንፃር በሰሜን ኢራቅ የምትገኝ “ታላቅ” ከተማ ናት ፦ ይኽችው ነነዌ።

እግዚአብሔር የአማቴ እና የሶና ልጅ የሆነውን ነቢዩ ዮናስን ስለሕዝቡ ክፋት የከተማዋን በሦስት ቀን መጥፋት ‘እንዲሰብክላቸው’ ቢልከውም እርሱ ግን ከተርሴስ ወደብ ተነስቶ ወደ ኢዮጴ በሚሔድ መርከብ መሸሽን መረጠ፤ የታዘዘ ዓሣ አንበሪ (አሳነባሪ) ግን በተኣምራት ዮናስን ከአንቀጸ ነነዌ (ወደ ነነዌ መግቢያ) በሦስት ቀን አደረሰው … "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታዕ ነነዌ" እያለ አስተማረ፤

ያን ጊዜ ልጅ ከእናት ላም ከጥጃ እንዳይገናኙ ከብቶቻቸውም ሳር እንዳይነጩ ውኃ እንዳይጎነጩ እንዳይሰማሩ ጭምር የአዋጅ ጾም አዘዘ በንስሐ በጾም የ፫ ቀን ‘ሱባዔ’ ወደ ፈጣሪያቸው ተመለሱ እንሰሳቱም ሳይቀር ተባበሩ እግዚአብሔርም አዘነላቸው፤ ቀድሞውኑ ዮናስም ይኼን ነበር ‘የፈራው’
⇢ አንተ በመሐሪነትህ እንድትመለስ የሕዝቡ ንስሐ (ጸጸት) እንድትጸጸትም ያደርግሃል "ወነስሐ በከመ ብዝኀ ምሕረቱ … እንደ ምሕረቱም ብዛት ተጸጸተ " እንዲል (መዝ ፻፭፥፵፭) እኔንም ነቢየ ሀሰት አስባልከኝ፤ ብሎ እሳት ባለመውረዱ አዝኖ ከከተማው በአፍአ (ውጪ) ጎጆ ሰርቶ ተቀመጠ በአንድ ሌሊት የበቀለች ቅል ዋዕየ ፀሐዩን ትከለክልለታለች፤ ይኼኔ በደስታ ከጥላው ሥር ተኝቶ ሳለ የታዘዘ ትል ቆርጦ ቅሊቱን ጣላት ደረቀችም … ያኔ ዋዕየ ፀሐይ (የፀሐዩ ንዳድ) ራሱን ቢመታው "አዳጊት" (ራስምታት) ተነሳችበት አዘነ፤ ‘እግዜሩም’ ⇒ ላልተከልካት፣ ባዛ ላይ ውሃ እንኳ አጠጥተህ ላልደከምክባት ሌሊት በቅላ ሌሊቱን ለደረቀች አንዲት ቅል አንተ ካዘንክ ↳
"ወአንሰ ፡ ኢይምሕካ ፡ ለነነዌ ፡ ሀገር ፡ ዐቢይ ፡ ዘሀለወ ፡ ውስቴታ ፡ ሰብእ ፡ ፈድፋደ ፡ እምዐሠርቱ ፡ ወክልኤቱ ፡ እልፍ ፡ እለ ፡ ኢፈለጡ ፡ ፀጋሞሙ ፡ እምየማኖሙ ፡ ወእንስሳ ፡ ብዙኅ … እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው።" (ዮና ፬፥፲፩)

በትንቢተ ዮናስ የመጨረሻ ምዕራፍና የመጨረሻ ቁጥር ላይ የምናገኘው የዐረፍተ ነገሩ ሐረግ ፦
⇝ እለ ኢፈለጡ ፀጋሞሙ እምየማኖሙ (ቀኛቸውን ከግራቸውን ያልለዩ) የሚል ነው፤ ይኽ አገባብ ነነዌን ለጥፋት የዳረጋት ከእንሰሳቱ ጋር ያስቆጠራት ልክ እንደ እንሰሳቱ ግራና ቀኝ አለመለየት ነበርና፤ በአንድ ላይ ሰዉን ከእንሰሳው ጋር ግራና ቀኝ ስለማይለዩ ሊያጠፋቸው ብሎ ዮናስን ላከ… ነገር ግን የነነዌ ሰዎች ይኽን ሰምተው "በእግዚአብሔር አመኑ" (፫፥፭) ያኔ ከግራቸው ላይ ቀኛቸውን ለዩ ወደሚያድናቸው አምላክ ጸለዩ። በርቱዕ ምግባር በጾም ለቅን ሥራ አደሩ በቀኝም ዋሉ!

#ቀኝ (የማን) እና #ግራ (ፀጋም) ምንድነው ?
. ┈┈┈◦◎ ⇆⇡⇄ ◎◦┈┈┈

በቁሙ የማን ፦ ቀኝ፣ የቀኝ እጅ፣ የቀኝ ጐን እንዲሁም ፀጋም ፦ የቀኝ አንጻር፣ የግራ እጅ፣ የግራ ጐን በሚል አቅጣጫ የሚጠቆምበት ነው፤ በዘይቤው ግን በጎውን ከክፉ መልካሙን ከመጥፎ ለይተን የምናመለክትበትም መገለጫ ነው!

የሚን ፦ መቅናት ቅን ቀኝ መኾን፣ መጽናት (መበርደድ) ፣ መብዛት (መፈድፈድ) ፣ መክበር (መወደድ) ፣ በቀኝ መቀጥቀጥ ወደ ቀኝ መኼድ ማለትን ይወክላል።

ፀጊም ፦ መጥመም መጕበጥ ጠማማ መኾን ወደ ግራ መኼድ መገልበጥ ማለት ነው ። ከዚህም በመነሳት ፀጋም ወይም ግራ ሀካይ ድኩም የሚለውን ተክቷል።

መጽሐፍም ጥበብና ስንፍናን ፣ ብርታትና ድክመትን ፣ ቅንነትና ጥመትን… ቀኝና ግራ እያለ ይገልጣል፤
↦ "ልበ ጠቢብ ውስተ የማኑ ወልቡ ለአብድ ውስተ ፀጋሙ … የጠቢብ ልብ በስተ ቀኙ ነው፥ የሰነፍ ልብ ግን በስተ ግራው ነው።" እንዲል (መክ ፲፥፪) ይኽንኑ ለማጉላት በተለየ አተያይም #ሀይመነ የሚለው የሃይማኖት መነሻ አመነ ታመነ ማለት ሲሆን ንባቡ #ከየማን ፍችው ከአሚን የወጣ ነው ይሉናል ሊቃውንቱ።

‘እግዜሩም’ ጥንቱን አክብሮ በአምሳያው ሰውን ሲፈጥረው በእውቀትና በሕይወት በዚያ ውም ላይ በነጻ ፈቃድ ከሌላው የከበረ አድርጎታል። ግራና ቀኙን የሚለይበትን እውቀት ከነጻ ፈቃድ ጋር አድሎታል ፤ ይሁንና «እንዳሻኝ» ብሎ አምላኩን በድሎ ከክብር እንዳይርቅ ከማዕረጉ እንዳይወድቅ «ቀኝ ከግራ እያወላወለ በመንታ እንዳይቅበዘበዝ በግራው ድካም ጠፍቶም እንዳይቀር» በምትሻው ለመሔድ ፈቃድ አለህ ግን የሚጠቅምህ ቀኙ ነው እያለ መልካሙን ያመለክተዋል፣ የሚጠቀምበትን ይነግረዋል።

" ወኢትትገኀስ ኢለየማን ወኢለፀጋም በከመ አዘዘ ሙሴ ለደቂቀ እስራኤል። አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ ኀበ ዘፈቀድከ ደይ እዴከ። ☞ እሳትንና ውኃን አቀረብኩልህ፤ እጅህን ወደ ወደድኸው ጨምር ብሎ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዛቸው ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበል" [፩. መቃ ፯፥፯]

ተጨማሪ ምክርም መቃቢያኑ አክለዋል እንዲህ ሲሉ " ቃሉን ትሰማ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ታደርግ ዘንድ የምነግርህን ቃሉን ስማ፤ በባሕር ማዶ፥ ወይም በጥልቁ ማዶ፥ ወይም በወንዙ ማዶ ቃሉ አለች፤ አያት ዘንድ፥ ቃሉንም እሰማ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርንም  ትእዛዙን አደርግ ዘንድ ማን ያመጣልኛል? እንዳትል፥  ዳግመኛም ሰምቼ አደርጋት ዘንድ ወደ ሰማይ ወጥቶ ያቺን የእግዚአብሔርን ቃል ማን ያወርድልኛል? እንዳትል እነሆ ቃሉ በአፍህ ቅርብ ነው። በእጅህም ውስጥ ነው።  መጽሐፉንም ካልሰማኸው አምላክህ እግዚአብሔርን  አልሰማኸውም፤ ቃሉንም ካልጠበቅህ እርሱን አልወደድኸውም፤ ትእዛዙንም አላደረግህም። አንተም ትእዛዙን ካልወደድህ በእውነትም ትጠብቃቸው ዘንድ ከወገኖችህ ሁሉ ለይቶ ያከበረህንና ያገነነህን ፈቃድ ካላደረግህ ለዘለዓለም ወደ ፍርድ ትገባለህ።"

እሳት ከውኃ ለይተን ቀኛችንን ከግራችን አንስተን እንደቃሉ ኖረን ለመክበር ያብቃን!

ከዚህ ዘይቤ በበለጠው ምሥጢር ደግሞ ቅዱስ መጽሐፍ ግራ እና ቀኝ በሚለው ሰሜንና ደቡብን ፣ ጌባልና ገሪዛንን ፣ ዳክርስ እና ጥጦስን፣ ፍየልና በግን… ይህን የመሰለውን ሁሉ እያስተያየ የሚገልጥ አስተማሪ ቃል ነው፤

① #ሰሜን እና #ደቡብ (ሰሜን የግራ ደቡብ የቀኝ አቅጣጫ )
. ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈

ከአራቱ ዐበይት ማእዘንት ምዕራብ እና ምሥራቅ ውጪ ያሉትን ሰሜንና ደቡብ እንላቸዋለን፤ ገጻችንን(ፊታችንን) ወደ ሥርቀተ ፀሐይ ምሥራቅ (ወደ ፀሐይ መውጫ) አዙረን እጆቻችንን ስንዘረጋ በቀኝ አቅጣጫ ደቡብን በግራ ደግሞ ሰሜንን እናገኛለን ከዚኽ በመነሳት ሰሜን ግራ ደቡብ ቀኝ ተሰኝቷል ይህም ከቀኙ ደቡብ ከግራው ሰሜኑ ተገምቷልና።


#እለ_ኢፈለጡ_ፀጋሞሙ_እም_የማኖሙ
. (ግራቸውን ከቀኛቸው ያልለዩ) ☞ ዮና ፬፥፲፩


ስለዚህ ጾማችን ከምጽዋት ጋር መሆን አለበት፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ምጽዋት አይለያዩምና እነዚህን ገንዘብ እናድርግ፡፡
በረከተ ሥጋ፣ በረከተ ነፍስ እንድናገኝ ጾማችን በቅንነትና በንጹሕ ልብ ይሁን ጾማችን ከምጽዋት ጋር ይሁን፡፡ ለዚህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ቅዱሳን በአማላጅነታቸው ይርዱን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አዘጋጅ፡- ላእከ ወንጌል በእደማርያም ይትባረክ (ቀሲስ) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ትምህርት ሥርጭት ኃላፊ


#ጾም_በክርስትና_ሕይወት

በዚህ ትምህርታዊ ጹሑፍ ስለ ጾም አራት ነጥቦችን እናያለን
1.የጾም ትርጉም
2.ጾም ያስፈለገበት ምክንያት
3.የጾም ጥቅሞች
4.በምን ዓይነት መንገድ መጾም እንዳለብን፡፡
ከላይ ከ1-4 ተራ ቊጥር የተገለጹትን እንደሚከተለው በዝርዝር እናያለን፡፡

1ኛ/ የጾም ትርጉም
ጾም፡- ማለት ክርስቲያን የሆነ ሰው ሁሉ ለተወሰነ ጊዜና ሰዓት ከእህል ከውኃ ተከልክሎ መቆየት ማለት ሲሆን ከሥጋ፣ ከቅቤና፣ ከእንቁላል ደግሞ እንድንጾምባቸው የተወሰኑ የአጽዋማት ሳምንታት እስኪጠናቀቁ የምንከለከልበት ማለት ነው፡፡ /ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 15/
ከዚህም ጋር ጾም ማለት፡- ዓይን ክፉ ከማየት ጆሮ ክፉ ከመስማት፣ አንደበት ክፉ ከመናገር፣ እጅ ክፉ ከመሥራት በአጠቃላይ ሰውነት የኃጢአት ሥራ ከመሥራት የሚገታበት፣ የሚከለከልበት ማለት ነው፡፡ /ቅዱስ ያሬድ/

ጾም፡- ሁለት ዓይነት ነው ይኸውም
ሀ. የአዋጅ ጾም ነው፡- ይህም በስውር ሳይሆን ሁሉ አውቆት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የሚጾመው ጾም ነው፡፡ ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው፡፡ “በጽዮን መለከትን ንፉ ጾምንም ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ” /ኢዩ. 2፡15/
ሰባቱ አጽዋማት የአዋጅ ጾሞች ናቸው፡፡ እነዚህም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
1. የነቢያት ጾም
2. የገሀድ ጾም
3. የነነዌ ጾም
4. ዐቢይ ጾም
5. የሐዋርያት ጾም
6. ጾመ ድኅነት /ረቡዕና ዓርብ/
7.ጾመ ፍልሰታ
ለ. የግል ጾም ነው፡- የግል ጾም ስንል አንድ ሰው በሠራው ኃጢአት ምክንያት ለንስሓ አባቱ ተናግሮ የሚሰጠው የንስሓ ጾም ሲሆን እንዲሁም አንድ ሰው ስለደረሰበትና በእርሱ ላይ ስለሆነ ነገር ስለሚፈልገው ጉዳይ እግዚአብሔር ተገቢውን መልስ እንዲሰጠው የሚጾመው ጾም ነው፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ልጁ በታመመ ጊዜ ጹሟል፡፡ /2ኛ.ሳሙ. 12፡16/
ነገር ግን በግል ጾም ጊዜ ጾሙ ይፋ ስላልሆነ ራስን መሰወር እንደሚያስፈልግ ታዟል፡፡
ይህንንም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ “ስትጾሙም እንደ ግብዞች አትጠውልጉ ለሰዎች ሊታዩ እንደ ጾመኛ ፊታቸውን ያጠወልጋሉና አንተ ግን ስትጾም ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ በስውር የሚያይህ አባትህ በግልጥ ይከፍልሃል” /ማቴ. 6፡16-18/ ይህ ቅዱስ ቃል ስለግል ጾም የተነገረ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የግል ጾምን ከጿሚው ሰው እና ከእግዚአብሔር ውጭ ማንም ማወቅ የለበትም፡፡

2ኛ/ ጾም ያስፈለገበት ምክንያት
ጾም፡- ያስፈለገበት ምክንያት ልጓመ ሥጋ ስለሆነ ነው፡፡ ሰው ሁልጊዜ የጣመ የላመ ምግብ የማይለየውና እንደልቡ እየበላ እየጠጣ ሳይጾም የሚኖር ከሆነ ለኃጢአት ይጋለጣል፡፡ ይህም በፍትሐ ነገሥት ተጽፏል፡፡ “ከመ ያድክም ኃይለ ፍትወት” (ኃይለ ፍትወትን፣ ሥጋዊ ፍትወትን ያደክም ዘንድ ጾም ታዘዘ) /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/ እንዲሁም በምንጾምበት ጊዜ ረሀብን፣ ችግርን እናውቃለን፡፡ “ከመ ያእምር ጸዋሚ ሕማመ ረኀብ ወይምሐሮሙ ለርኁባን” (ጿሚ ሰው የረኀብን ችግር ያውቅ ዘንድና ለተራቡ ይራራ ዘንድ ጾም ታዘዘ) /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/ እንዲሁም “ችግርን የቀመሰ ችግርን ያውቃል” እንዲሉ አባቶቻችን፡፡

3ኛ/ የጾም ጥቅሞች
የጾም ጥቅሞች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
1.በጾም መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን፡፡
ይህንንም የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ “ስለጽድቅ ብለው የሚራቡና የሚጠሙ ንዑዳን ክቡራን ናቸው እነርሱ ይጠግባሉና” /ማቴ. 5፡6/ ሲል ተናግሯል፡፡
2.በጾም በአገር ላይ የታዘዘው መቅሠፍት ይርቃል፡፡
የነነዌ ሰዎች የዮናስን ትምህርት መሠረት በማድረግ ሦስት ቀን ጾሙ፡፡ ለእነርሱ የታዘዘው እሳት የዛፉን ጫፍ ጫፍ አቃጥሎ ተመልሷል፡፡ /ትን ዮናስ ም. 3 በሙሉ/

3.በጾም ሰይጣን ድል ይሆናል፡፡
“እንዲህ ዓይነት አብሮ አደግ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም” /ማቴ. 17፡21/ ሲል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል የተናገረው ቃል ሰይጣን በጾም ድል እንደሚሆን የሚገልጽ ነው፡፡
4.ጾም ከፈተና፣ ከመከራ ያድናል፡፡
ነቢዩ ዳንኤል በጾም ከአፈ አናብስት (ከአንበሶች አፍ) ድኗል፡፡ /ትን. ዳን. ም. 6 በሙሉ/ ሶስና በጾም ከሐሰት ምስክሮች ድናለች፡፡ /መጽ. ሶስና ም. 1 ሙሉ/ ሌሎችም ቅዱሳን በጾም ከፈተና፣ ከመከራ ድነዋል፡፡
5.ጾም ዕድሜን ያረዝማል፡፡
ጾም የመልካም ሥራ ሁሉ መሠረት በመሆኑ ዕድሜን ያረዝማል፡፡
ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በገድላቸው እንደተጻፈው ዕድሜልካቸውን በጾም ነው የኖሩት የእናታቸውን ጡት እንኳን አልጠቡም፡፡ በዚህ ዓለም የኖሩት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ዓመት ነው፡፡ ሌሎችም ቅዱሳን በጾም የዕድሜ ባለጸጎች ሆነዋል፡፡
6.በጾም ምስጢር ይገለጻል፡፡
አይሁድ አርባ ስድስቱን መጻሕፍተ ብሉያት ቆነጻጽለው ባጠፏቸው ጊዜ ዕዝራ ሱቱኤል አዝኖ አርባ ቀን ጾመ ከዚህ በኋላ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ሰማያዊ መጠጥ በብርሃን ጽዋ (ጽዋዓ እሳት) ለዕዝራ አጠጣው ዕዝራም ምስጢር ተገልጾለት አርባ ስድስቱን መጻሕፍተ ብሉያት ጽፏል፡፡ /መጽ. ዕዝ. ሱቱ. 13፡36-41/ ሌሎችም ደጋግ ሰዎች በጾም ምስጢር ተገልጾላቸዋል፡፡
7.በጾም ኃጢአት ይሠረያል፡፡
የነነዌ ሰዎች የዮናስን ትምህርት መሠረት በማድረግ ሦስት ቀን ጾመው ኃጢአታቸው ተሠርዮላቸዋል፡፡ /ትን. ዮናስ ም. 3 በሙሉ/ ሌሎችም ሰዎች በጾም ኃጢአታቸው ተሠርዮላቸዋል፡፡ ይህንንም ታላቁ ሊቅ መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በዜማ ድርሰቱ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ “በጾም ወበጸሎት ይሠረይ ኃጢአት” (በጾምና በጸሎት ኃጢአት ይሠረያል)
8.በጾም ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ይቻላል፡፡
ሊቀ ነቢያት ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሞ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል በቃል ተነጋግሯል፡፡ /ዘዳግም. 9፡9-14/
ነቢዩ ኤልያስም በጾም ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሯል፡፡ /1ኛ. መጽ. ነገ. 17፡2/
9.በጾም ልመናችን ይፈጸማል፡፡
እስራኤል በጾም የለመኑትን አግኝተዋል፡፡ /1ኛ ሳሙ. 7፡6-14/ ሌሎችም ቅዱሳን በጾም ልመናቸው ተፈጽሞላቸዋል፡፡
የጾም ጥቅሞች ከላይ ከ1-9 ተራ ቊጥር የተገለጹ ሲሆን ከላይ በርእሱ እንደተገለጸው ጾም የመልካም ሥራ ሁሉ መሠረት ሲሆን በአንጻሩ አለመጾም ደግሞ የኃጢአት ሁሉ መሠረት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ካልጾመ ለብዙ ኃጢአት ይጋለጣል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰዎች የተሰጠው የጾም ትእዛዝ ነው፡፡ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን፡- ይህን ዕፀ በለስ አትብሉ ሲል ከዕፀ በለሱ ተከልከሉ ጹሙ ማለቱ ነው፡፡ እነርሱ ግን አትብሉ የተባሉትን በሉ ከገነት ወጡ ተጎዱ አለመጾም ያስጎዳል፡፡ በዚህ መሠረት ኃጢአት በመብል ምክንያት ወደዓለም ገባ፡፡

4ኛ/ በምን ዓይነት መንገድ መጾም እንዳለብን እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡
ጾም፡- ከትርጉሙ እንደተረዳነው ከእህል ከውኃ ከመከልከሉ ጋር ከክፉ ነገር ከኃጢአት መራቅ ስለሆነ ጾማችን ከክፉ ነገር በመራቅ፣ በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ነቢዩ ኢሳይያስ “በምትጾምበት ጊዜ እንጀራህን ለተራበ ብትቆርስ ብርሃንህ እንደንጋት ይበራል የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል ትጮሀለህ እርሱም እነሆ ይልሃል” /ኢሳ. 58፡6-9/ ባለው መሠረት በጾም ጊዜ የጧት ቁርሳችን ለድሆች ከተሰጠ ሰማያዊ ዋጋ እናገኛለን፡፡


#ጾም_በክርስትና_ሕይወት

በዚህ ትምህርታዊ ጹሑፍ ስለ ጾም አራት ነጥቦችን እናያለን
1.የጾም ትርጉም
2.ጾም ያስፈለገበት ምክንያት
3.የጾም ጥቅሞች
4.በምን ዓይነት መንገድ መጾም እንዳለብን፡፡
ከላይ ከ1-4 ተራ ቊጥር የተገለጹትን እንደሚከተለው በዝርዝር እናያለን፡፡


                  ☞ ያእቆብ ከዚሁ ቦታ ተነስቶ ወደላባ ሄደ ላባ የናቱ ወንድም አጉቱ ነው። በመንገዱም የበጎች ዓዘቅት ጉድጓድ አየ። ይህም ዓዘቅት በከባድ ድንጋይ የተዘጋ ነበር። በቀላሉ ለመክፈት አይቻልም ነበር።  የላባ ልጅ ራሄል ከዚያ ቁማ ነበር። (በጎቿን ለማጠጣት) ያዕቆብ የውኃውን ጉድጓድ የተከደነበትን ድንጋይ ከፈተና የውሃ መቅጃ ከራሄል እጅ ተቀብሎ በጎቹን ከጉድጓዱ ውሃ በመቅዳት አጠጣቸው በጎቹን አጠጥቶ ሲያበቃ ያዕቆብ ራሄልን ተመለከታት ወደሷም ቀርቦ ሳማት።  ያዕቆብ የውሃውን ጥልቅ ጉድጓድ መክፈቱ የቅድስት ጥምቀት ምሳሌ ነው የጥምቀት ምስጢር ረቂቅ ነውና ።

     ✧   ለቡኬ ኦ ወልድየ ቀሌሚንጦስ ከመ ኢክህለ ያዕቆብ ይስዓማ ለራሔል ዘእንበለ ዳእሙ እምድኅረከሰተ አፉሃ ለዓዘቅት ወአስተየ አባግዓ እምኔሃ ወከማሁ ይቤ አነኒ ኢርቱዕ ለሕዝብ ይባኡ ቤተ ክርስቲያን  እንበለይጠመቁ እስመ እምድኅረ ተጠምቁ ይከውኑ አበግዒሁ ለክርስቶስ።
           ☞ ልጄ ቀሌሚንጦስ ሆይ የውሃውን ጥልቅ ጉድጓድ ከፍቶ በጎቹን ከማጠጣቱ በፊት ያዕቆብ ራሄልን ሊስማት አልቻለም የጥልቅ ጉድጓዱን መክደኛ ከፍቶ በጎቹን ካጠጣ በኋላ ግን ራሄልን ሳማት እኔም የዚሁን ምሳሌ እነግርሃለሁ ሰዎች በቅድስት ጥምቀት መንፈስ ቅዱስን ሳይቀበሉ ወደቅድስት ቤተክርስቲያን መግባት ክልክል ነው። በጥምቀት የክርስቶስ በጎች ይሆናሉና።

የጥልቅ ጉድጓዱ መክደኛ መርገምን፣  ያዕቆብ ክርስቶስን፣  ውኃው ጥምቀትን፣  በጎቹ ምእመናንን መስለው መተርጎማቸውን ልብ ይሏል!

አበ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድም ወብዙኃን ባለው የቀበላ ዝማሬው  ይህን እንዲህ በማለት ተርጉሞልናል፦
       ✧ ወብዙኃን ኖሎት መጽኡ ወስዕኑ ከሢቶታ ለዕብን እምአፈ አዘቅት እስከ ይመጽእ ያዕቆብ ዘክቡት ውስተ ሐቌሁ ዘሀሎ ይሠጎ እምሰብእ ከሠተ ወአስተየ መርዔቶ ወከማሁ መጽኡ ብዙኃን ነቢያት ወስዕኑ ከሢቶታ ለጥምቀት እስከ ይመጽእ ዓቢይ ኖላዊ እምሰማይ ከሠተ ወአጥመቀ ብዙኃነ አሕዛበ በውስቴታ መንክር ተአምሪሁ ለመድኃኒነ በከመ ወጽአት በትር እምሥርወ ዕሤይ በአምሳለ በትረ ያዕቆብ በዘይርዒ አባግዒሁ ይእቲኬ ማርያም ይእቲ ወበእንተ ዘይቤ ትወጽእ በትር ወየዓርግ ጽጌ ውእቱኬ ዋህድ ውእቱ ውእቱኬ ወልደ አምላክ ውእቱ።
      [ብዙ እረኞች መጡ ከጉድጓዱ አፍ ላይ የተገጠመችዋን ድንጋይ ለማንሳት አልቻሉም ሰው ይሆን ዘንድ ያለው በወገቡ ያለ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ። እሱ ከፍቶ በጎቹን አጠጣ እንደዚሁ ብዙ ነቢያት መጡ ጥምቀትን መግለጥ አልቻሉም ዓቢይ ኖላዊ ከሰማይ እስኪመጣ ድረስ። እሱ ጥምቀትን ገለጠ በውስጧ ብዙ አሕዛብን አጠመቀ። የመድኃኒታችን ምልክቱ የሚያስደንቅ ነው ከዕሤይ ሥር በትር እንደወጣች፤ በጎቹን በሚጠብቅበት በያዕቆብ በትር አምሳል፤ ይህችውም ማርያም ናት በትር ትወጣለች አበባውም ከፍ ከፍ ይላል ማለቱ ወልድ ዋህድ ነው። እርሱ የአምላክ ልጅ ነው።]

፪ኛ】  በዘፍጥረቱ ትርጓሜ ላይ ያዕቆብ በላባ ቤት ስለ ራሔልና ልያ ፲፬ ዓመታት ተገዝቶ አገልግሏል። “ወይእዜኒ ማዕዜኑመ አንሰ እገብር ቤተ ለርእስየ?  ☞  እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?”  【ዘፍ. ፴፥፴】  ሲል ጠይቆ  ንብረት ተካፍሎ ተለይቷል። ከሚጠብቀው መንጋም ሽመልመሌ ዝንጉርጉሩን ለራሱ ሲያደርግ ከሚወለዱትም መኃል ያን የመሰለውን እንዲወስድ ላባ ፈቅዶለታል።

በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እንዲህ አደረገ  ዘፍጥረት ፴፥፴፯–፵፪
        " ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው። የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ በበጎቹ ፊት አኖራቸው፤ በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይጎመጁ ነበር።  በጎቹም በትሮቹን አይተው ከመጎምጀታቸው የተነሣ ፀነሱ፤ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጕርጕር ነቍጣም ያለበቱን ወለዱ። ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በላባ በጎች ፊት ለፊት አኖረ፤ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም።  እንዲህም ሆነ፤ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፤ በደከሙ በጎችም ፊት በትሩን አያደርገውም ነበር፤ የደከሙትም ለላባ፥ የበረቱትም ለያዕቆብ ሆኑ።"

ታሪኩ በጥላነት የያዘው ምሥጢርና  በምሳሌነት የሚያስተምረንን አማናዊ የምሥጢረ ጥምቀት ፍቺ መተርጉማን እንደሚከተለው አመሥጥረውልናል

      ☞ አብትር (በትሮቹ) የሦስቱ አካላት ፣ የተላጡት የአብ የመንፈስ ቅዱስ ፣  ቅጥልጣል የሆነው የወልድ አምሳል [አምላክ ወሰብእ ነውና] ፣  አባሕኵ የመምህራን፣ አባግዕ የምእመናን፣ ውኃ የጥምቀት፤
     ☞ አባግዕ አብትርን እየመሰሉ መወለዳቸው ፦ ምእመናንም በጥምቀት ምክንያት ሥላሴን መስለው ይወለዳሉና፤
     ☞ ላባ የዲያብሎስ፣ ያዕቆብ የጌታ ምሳሌ፤
     ☞ ምልክት ያለው ለያዕቆብ፣ ምልክት የሌለው ለላባ እንደሆነ፦  ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ያለው ለጌታ እንዲሁም ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና የሌለው ለዲያብሎስ ሁኗልና፤

ይኽነረኑ ይዞ የመልክዓ ሥላሴ ደራሲ በምሥጢር አስማምተው እንዲህ ብለዋል

      ሰላም ለአዕዛኒክሙ አናቅጸ ጸሎት ሠናይ
       ምሥጢራተ ሰሚዕ ሥላሴ ዘይተልዎ ርእይ
       በአብትረ ያዕቆብ በርሃ ሥላሴክሙ ፀሐይ
      ወተመሰሉ ሰብአ ዓይን አባግዓ ላባ ወማይ
          ለኀበ አባግዕ ዘዮም ወጥምቀት ዓባይ

       ☞ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ርዕይ የሚከተለው ምሥጢራትን ለሚሰማ የበጎ ጸሎት በር ለሆነ መለኮታዊ አእዛናችሁ (ዦሮዎቻችሁ) ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ የሦትታችሁ ፀሐይ በያዕቆብ በትሮች ላይ አበራ። ስለሆነም ለአሁኑ የታላቂቱ የጥምቀት ልጆች የቀድሞ የላባ በጎችና የሚጠጡበት የወንዝ ውሀ መልካም ምሳሌ ሆኑ።

ከዚህ ባሻገር በዛሬውም ቅዳሴ በዓሉን በሚመለከት የተሰበከው ቃለ ዳዊት ካነሳነው ምሥጢር ጋር በተገናኘ እንዲህ የሚል ነበር ፧
                       ወምስካይነ አምላኩ ለያዕቆብ
                    ንዑ ትርአዩ ግብሮ ለእግዚአብሔር
                         ዘገብረ መንክረ በዲበ ምድር
   ☞ (የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው) የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ። 【መዝ ፵፮፥፯】

አስቀድሞ በያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ላይ አድሮ ፣ ኋላ በገሊላ ቃና በሰርግ ቤት በአካል ተገኝቶ ፣ በየዘመናቱም ወደ ፍጥረቱ ጠባቂ መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ልኮ…  ድንቅ  ድንቁን ታላላቅ መንክራት ያደረገ የያዕቆብ አምላክ እግዚኣ ኃያላን 
✧ ተግባራቱን የምሥጢረ ጥምቀት ምሳሌ ካደረገለት ከቅዱሱ ያዕቆብ፣
✧  ከልጅነቱ ጀምሮ ያዕቆብን ከታደገውና ካዳነው  ከቅዱስ ሚካኤልና
✧ ከበዓለ ቃና ዘገለሊላ ረድዔት በረከት ሁላችንን ያሳትፈን 🙏

እንደ ያዕቆብ መከራና መገፋት ለሚፈራረቅባት ተዋህዶ ሃይማኖታችና በውስጧ ለተጠለልን ምእመናን እውነተኛውና ብቸኛው ንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ #በፍርዱ እስኪገለጥ ዋጋ እንዳናጣና እንዳንናወጽ #መቻል ያድለን።

✍️ ቃናዘገሊላ ፳፻፲፮ ዓ.ም. ደቡብ ሱዳን ጁባ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን የተጻፈ


. ለምን  ቃና ዘገሊላ በቅዱስ ሚካኤል ቀን ዋለ? 
°°°°°°°[#ነገረ_ያዕቆብ_ወልደ_ይስሐቅ]°°°°°°°°

       ዛሬ የየካቲት ፳፫ቱን በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር የተደረገ ተዓምር የምናስብበት የተውላጥ በዓል ነው።
[ተውላጥ ማለት ቅያሪ ልዋጭ ማለት ነው] አንድን ክብረ በዓል ከዕለቱ ውጪ በሌላ ቀን ለማሰብ ከሚያ’ዙ የቀኖና መንገዶች  መኃል እኒኽ ሦስቱ በዋናነት ይጠቀሳሉ፤

① ራሱን ለማስቻል
         ይኸውም በዕለቱ ሌላ ከብሮና ገንኖ የሚነገር ክብረ በዓል ካለ ራሱን ችሎ እንዲዘከር በተለየ ትኩረት ታስቦ እንዲከበር የዕለት ለውጥ ይደረግለታል፤
ለምሳሌ፦  የዮሐንስ አፈወርቅ ፍልሰቱን ከመስከረም ፲፯ ወደ ኅዳር ፲፯ ለማሳለፍ እንደ ምክንያት  «…ይህም (ፍልሰቱ)  በመድኃኒታችን በመስቀሉ በዓል መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን ነው ። ስለዚህም ራሱን ለማስቻል ወደ ኅዳር ዐሥራ ሰባት ቀን ለወጡት» ይለናል። እንደዚሁ ሁሉ ሌሎችም በጌታ ልደት ቀንና በሰሙነ ሕማማት የሚዘከሩ የቅዱሳኑ በዓላት ከተደራቢነት ይልቅ በተውላጥ ይከብራሉ።

② ምሥጢር ለማገናኘት
         ክብረ በዓሉን የበለጠ ለማጉላት ምቹ ኩነቶች ካሉ አያይዞ በሌላ ቀን በመዘከር ስለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ያደርጋል።

ለምሳሌ ፦ የመጋቢት ፳፱ኙን ብሥራት ወደ ታኅሳስ ፳፪ ማምጣት በዐቢይ ጾም በሰሙነ ሕማማት ከመዋሉ ባሻገር ተወለደ ለማለት ተጸነሰ የማለትን ምሥጢር እንድንዘክር ከልደቱ ፯ ቀን ቀድመን እንድንዘክር በተውላት ብሥራት ብለን እናስበዋለን፣ በተጨመሰሪም በበጋ ወራት ወደ በረሃ  መሰደዷ የተነገረውን እመቤታችንን በበረሃ ያለች የማትጠወልግ አበባ ከሚል ምሥጢር እያገናኙ ሊቃውንት ዘመነ ጽጌን የስደቷ መታሰቢያ ያደርጋሉ። ያነሳነውን የዛሬ በዓልም  የካቲት ፳፫ ቀን የተፈጸመ ሲሆን የቃና ዘገሊላ ተአምር በጥር ፲፪ ቀን የውኃን በዓል ከውኃ አገናኝቶ ቀኖና ቤተክርስቲያን  የጥምቀት ማግሥት ይዘክረዋል።

③ ቀኖና ቤተክርስቲያን
       አዋጅ  ሆኖ በጉባኤ ቤተክርስቲያን  የተደነገገ ቀን ሲኖር በተለይ ዐበይት በዓላትንና አጽዋማትን የሚመለከት ውሳኔዎች
ለምሳሌ፦ የመጋቢት ፬ቱ የአሞር ደሴት ጉባኤ የፋሲካ በዓል በሰንበት እንዲውል ለመጋቢት ፳፱ ተውላጥ እንዲኖረው መደንገጉ የዚህ አካል ነው። ይህ ድንጋጌ ከላይ ያሉትንም ሊያቅፍ የሚችል በተለይም በዓላት በቀን ቁጥር ከሚውሉበት እዕዋዳት ሌላ ዕለት እንዳይለቁ በማሰብ እንዲሁም በዐቢይ ጾምና ሰሙነ ሕማማት ዕረፍተ ሰማዕታት ልደተ ጻድቃን ሢመተ መላእክት እንዳይዘከር ታውጇል  ይህን በመሰለው መንገድና  ሌሎችም ብዙ ምክንያቶች ለለውጥ በዓላት ሊጠቀሱ ይችላሉ።
ጥምቀትና ቃና ዘገሊላ የኤጲፋንያ ክፍሎች ናቸው። ወመዋዕለ አስተርእዮ ውእቱ ኤጲፋንያ እንዲል 【ሃይ አበ ዘ፫፻ ፳፥፲፰】

ኤጲፋንያ የተባለውን አስተርእዮን ከሦስት የመገለጥ ታሪክ ጋር አያይዘው የሚያቀርቡ አሉና
፩】 የክርስቶስ ጥምቀት (the baptism of Jesus)
፪】 የሰብአ ሰገል ወደ ቤተልሔም ተጉዞ አምላክን ማየት (the visit of the Wise Men to Bethlehem) 
፫】 የቃና ዘገሊላው ተአምር (the miracle at Cana)

💦 የቃና ዘገሊላውን ተኣምር ከጥምቀቱ ጋር የሚያገናኙ አያሌ ምሥጢራት እንዳሉት ሁሉ በዓለ ቅዱስ ሚካኤልን ከጥምቀትና ከቃና ዘገሊላው በዓል ጋር ምን ያዛምደዋል?
💦 ለተውላጡ ፲፪ ለምን ተመረጠ?
💦 ከቀናቱ ለምን አልቀደመ? ለምንስ አልዘገየ? 
💦 ታቦተ ሚካኤልስ ምን አገናኝቶት በተለየ ዛሬ ክብረ በዓሉ ሆኖ ዋለ?

ቅዱስ ሚካኤልን በሚመለከት በስንክሳሩና በድርሳኑ ዛሬ የሚከብርበት ምክንያት እንዲህ ተዘግቦልናል።

            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፤ አመ ዐሡሩ ወሰኑዩ ለወርኃ ጥር ፡ በዛቲ ዕለት ተዝካረ በዓሉ ለመልዐክ ክቡር ሚካኤል ሊቀ መላዕክት እስመ በዛቲ ዕለት ፈነዎ እግዚአብሔር ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ኀበ ያዕቆብ እሥራኤል እንዘይፈርሕ እሁ ዔሳውሃ ፡ ወአድኀኖ እምኔሁ ወአኅለፎ ፈለገ ዮርዳኖስ።
              ☞ በአብና በወልድ በመንፈስቅዱስም ስም አንድ አምላክ ብለን አምነን ጥር በባተ ፲፪ ቀን የሊቀመላዕክት ቅዱስ ሚካኤል በዓል ይከበር ዘንድ እንናገራለን በዚች ቀን እግዚአብሔር ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤልን ዕሥራኤል ወደተባለ ያዕቆብ ልኮት ከሚፈራው ወንድሙ ዔሳው ታድጐ የዮርዳኖስን ወንዝ አሻግሮታልና ::

           ወሖረ ያዕቆብ ኀበ ላባ እኁሃ ለእሙ ፡ ወአስተዋሰቦ ክልዔ አዋልዲሁ ልያሃ ወራኄልሃ ። ወአግብኦ እንዘ ይጸይሕ ፍኖቶ በዳኅና ወበሰላም ምስለ ሰብኡ ወንዋዩ ወውሉዱ ወተቀበሉ እኁሁ ዔሳው በሰላም ወፍቅር
          ☞ ያዕቆብም ወደእናቱ ወን ድም ላባ ዘንድ በደረሰ ጊዜ ላባም ኹለቱ ልጆቹን ልያንና ራሔልን አጋባው ፡፡ መንገዱ ንም አቅንቶ በደኅና በፍቅር ከቤተሰቡና ከንብረቱ ጋራ መለሰው ፡፡ ወንድሙ በፍቅር አንድነት ተቀበለው፡፡

         ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ቅዱሳን ሐዋርያት ሥዩማን ዲበ ማኅበረ ምእመናን ከመ ንግበር ተዝካረ በዓሉ ለመልዐክ ክቡር ሚካኤል ሊቀ መላዕክት አመ ዐሠሩ ወሰኑዩ ለለወርኁ ትን ብልናሁ ወአስተብቊዖቱ የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን
        ☞ ስለዚህ በማኅበረ ምእመናን ላይ የተሾሙ ቅዱሳን አበው በእየወሩ ዐሥራ ሐዋርያት ኹለት ቀን የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤልን ዝክረ በዓል እናደርግ ዘንድ አዘውናል ። ፍጹም አማላጅነቱ  ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋራ ይኹን አሜን 🙏

ስንክሳሩም ቢሆን የሚደግመው ይኽንኑ ነው።

ቅዱስ ሚካኤል ለያዕቆብ ስለዋለለት ውለታና ስለፈጸመለት ትድግና ራሱ እስራኤል የተባለ ያዕቆብ በአንደበቱ እንዲህ እያለ ምስክርነቱን ሠጥቷል።
“ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ” 【ዘፍ ፵፰፥፲፮】

ያዕቆብን ጌታችን የተጠመቀበትን ፈለገ ዮርዳኖስ አሻግሮ በመንገዱ የመራ ያሳደገው የመገበው የጠበቀው ከክፉ የታደገው ቅዱስ ሚካኤል ዛሬ በዚህ መንገድ ከታሰበ ከጥምቀት ጋር ምን አገናኝቶት ነው?    የያዕቆብ ሕይወት በጥላነት ለአካሉ በምሳሌነትም ለአማናዊው ጥምቀት የጎላ ምሥጢራዊ ማነጻጸርያ ሆኖ በሊቃውንት ተተርጉሟል።

ዮርዳኖስን በመልአኩ ከመሻገሩ ባለፈ ከሁለት ክፍሎች ያገኘነውን በየተራ እንመልከት፦

፩ኛ】 ያዕቆብ ወደ ምሥራቅ ሀገር ሰዎች ሄዲ በውኃው ጉድጓድ አጠገብ ስለፈጸመው ሥራ 【ዘፍ ፳፱፥ ፪】 የምሥጢሩን ፍቺ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም በመጽሐፉ የተገለጠለትን የተነገረውን【መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ፭ ፥፳፰–፴፩ 】 ከጥምቀት ጋር አገናኝቶ እንዲህ ተርጉሞታል

        ✧ ወሖረ ያዕቆብ እምውስተ ውእቱ መካን ኀበ ላባ እሁሃ ለእሙ ወርእየ በፍኖት ዓዘቅተ አባግዕ ወክዱን አፉሃ ለዓዘቅት በዓባይ እብን። ወራሄል ወለተላባ ትቀውም ህየ ምስለ እሉ አባግዕ ኀበ ዓዘቅት ወነሥአ ያዕቆብ ወከሰታ ለይእቲ እብን እምአፈ ዓዘቅት ወነሥአ ማሕየበ ወአስተዮን ለእሉ ፅሙዓን አባግዕ እለሐለዋ ምለስ ራሄል ወእምዝ ቀርበ ኀቤሃ ለራኄል ወሰዓመ። ወከስተ ያዕቆብ አፈዓዘቅት አምሳለ ጥምቀት ቅድስት እንተ ኮነት ኀብእተ እምትካት ዘለዓለም።


. ለምን ቃና ዘገሊላ በቅዱስ ሚካኤል ቀን ዋለ?
°°°°°°°[#ነገረ_ያዕቆብ_ወልደ_ይስሐቅ]°°°°°°°°


☞ መቼ ይሆን በቤተልሔም ተሰናድቶ በመቅደስ ቀራንዮ ተሰውቶ የምናየውን የዓለም መድኃኒት በንሰሐ በታደሰ ሰውነታችን ተቀብለን በክብር የምናኖረው? መቼ ይሆን ከመንፈሳዊው መአድ ተሳትፈን የእርሱን ሥጋ በልተን የእርሱን ደም ጠጥተን እርሱኑ ለብሰን እርቃናችንን የምንሰውረው?

☞ መቼ ይሆን «ታርዤኮ አላለበሳችሁኝም» ከሚል ወቀሳና ከሰሳ ለመዳን በደጃችን የወደቁትን ዕሩቃን ነዳያን አልብሰን እርሱን ነው ያለበስነው ብለን ለብሰነው የምንከብረው?

☞ መቼ ይሆን … እንዲህ የምንለው

መኑ ይሁበኒ ሥጋሁ ለኢየሱስ
ከመ እክድን ዕቃርኖ በልብስ
ለዘከደነ ዕርቃንየ በዮርዳኖስ

[ በዮርዳኖስ እርቃኔን የሸፈነውን እርቃኑን በልብስ እሸፍን ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ማን በስጠኝ]

በልደቱ እናቱ ዕርቃኑን በጨርቅ የጠቀለለችው ሰብአ ሰገልም ቀሚስ ሰጥተው ያለበሱት ወልደ እግዚአብሔር አማኑኤል ፣ በጥምቀቱ መላእክት በክብር የጋረዱት መሲህ ክርስቶስ፣ በስቅለቱ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአዲስ በፍታ የሸፈኑት መድኅን ኢየሱስ ራቁቱን ተወልዶ ተጠምቆና ተሰቅሎ የካሰን ከመራቆት የሸፈነን ዳግመኛ ከእርሱ ተለይተን እንዳንራቆት እርቃኑን አይተነው እንዳንርቀው በቸርነቱ ይጠብቀን!

🌴Яερôšтεd ƒяô๓ ጥር ከተራ ፳፻፲፫ ዓ.ም. ✍ አዲስ አበባ


ቤተልሔም ፣ ዮርዳኖስና ቀራንዮ
በልደት ፣ በጥምቀትና በስቅለት
የአምላክ «መራቆት»
━━━✦༒⛪༒✦━━━

መኑ ይሁበኒ ሥጋሁ ለኢየሱስ
ከመ እክድን ዕርቃኖ በልብስ
ለዘከደነ ዕርቃንየ በዮርዳኖስ

[ በዮርዳኖስ እርቃኔን የሸፈነውን እርቃኑን በልብስ እሸፍን ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ማን በስጠኝ ?]

የዘፍጥረት መጽሐፍ ቀዳሚ መልእክት እንዲህ የሚል ነው «ወምድርሰ ሀለወት እምትካት ዕራቃ ☞ ምድር ግን ከቀድሞው ራቁትዋን ነበረች» ይህም ከአዝርዕት ከአትክል ከሰው የተራቆተች ሆና ባዶ ፣ ከንቱ ሆና ምድረ በዳ ነበረች ማለቱ ነው [ዘፍ ፩፥፪]

የፍጥረቱ አክሊልና የምድራችን ጌጥ ሆነን የተፈጠርነው እኛ የሰው ልጆችም ራቁትነታችን በብርሃን መጋረጃ የተሸፈነ ነበር ፤ ኋላ በበደላችን ምክንያት ከጸጋ ልጅነት ከአምላክ ባለሟልነት ስንርቅ ተራቁተን ቀረን እንጂ "አእመሩ ከመ ዕራቃኒሆሙ እሙንቱ ☞ ዕራቁታቸውን እንደሆኑ አወቁ" እንዲል [ዘፍ ፫፥፮]

እግዚአብሔርን ለመምሰል ብርሃን ተጎናጽፎ ይኖር የነበረው ሰብእናችን በበደሉ ምክንያት ዕርቃናቸውን የሚኖሩ እንሰሳትን መሰለ።

አባ ጊዮርጊስ ይህን ርደት እንዲህ ገልጦታል ፦ “ምንት ውእቱ ተመስሎ እንስሳ ዘእንበለ ተከሥቶ ዕርቃኑ ማእከለ ዕፀዊሃ ለገነት ሶበ ነፍጸ አጽፈ ብርሃን ዘላዕሌሁ ኀደጎ አጽፈ ብርሃን ⇨ በገነት ዛፎች መካከል ዕርቃኑን ሆኖ ከመተየት በስተቀር እንስሳን መምሰል ምንድ ነው? የብርሃን ልብስ ከበላዩ ላይ በተገፈፈ ጊዜ የብርሃን መጐናጸፊየው ተለየው” (መጽሐፈ ምሥጢር)

በፍና ሠርክ በድምጸ ሰኮና ብእሲ ‘እንደምን ባለ አነዋዋር አላችሁ ይሆን ? በክብር ወይስ በኃሣር ? ’ እያለ ፈልጎ አገኘንና ስለመተላለፋችን ፈርዶ ከቀደመ ክብራችን አውርዶ ከገነት አስወጣን፤ ያን ጊዜ በጊዜአዊነትም ቢሆን ሐፍረት መክደኛ ዕርቃን መሸፈኛ አበጀልን! "ወገብረ እግዚአብሔር ለአዳም ወለብእሲቱ አእዳለ ዘማእስ ወአልበሶሙ … እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፥ አለበሳቸውም።” [ዘፍ ፫፥፳፩]

ኋላ በምስጋና መብረቅ የተጋረደና በእሳት ደመና የተሸፈነ አምላክ ወልደ አምላክ የተስፋውን ቃል ለመፈጸም ከውድቀታችን ሊያነሳን ያን የተራቆተ ሥጋችንን ለበሰልን። የሚካኤል ሠራዊት በፍርኃት የገብርኤል ሠራዊት በመንቀጥቀጥ የሚያመሰግኑት እርሱ ዕርቃኑን በመካከላችን ተገኘ።

🍁 ወበቤተልሔም ወጽአ እምከርሰ እሙ ዕራቁ (በቤተልሔም ከእናቱ ማሕፀን ዕርቃኑን ተወለደ)

መጽሐፍ "ዕራቅየ ወፃእኩ እምከርሠ እምየ" እንዳለ እኛን በሚመስልበት የተዋህዶ ግብር ከድንግል እናቱ ማሕፀን ዕርቃኑን ተወለደ፤ ከመለኮቱ ሳይራቆት (ዕሩቅ ብእሲ ሳይሰኝ) ከሥጋ ልብስ ባዶ ሆኖ ተራቁቶ ፣ ክብሩን በፈቃዱ ትቶ በትህትና ወደምድራችን መጣ። ይህን ሥጋችንን ለብሶ የሰው ልጅ መባሉ ያንን የሰማይ ክብር እርሱን በጸጋ ለብሰን ትርሲተ ወልድ / የሥጦታ ልጆቹ ሊያሰኘን ነውና።

የመጽሐፉም ምስክርነት እንዲህ የሚል ነው "አሰረቶ መንኮብያቲሁ ወአስከበቶ ውስተ ጎል ወጠብለለቶ በጽርቅት ⇨ አውራ ጣቱን አሰረችው ፣ በግርግም አስተኛችው፣ በመጠቅለያም ጠቀለለችው” [ሉቃ ፪፥፯]

የ፲፭ ዓመቷ ገሊላዊት ብላቴና እናቱ ድንግል ማርያም በከብቶቹ ማደርያ ስትወልደው ለብኩርናው አውራ ጣቱን አሥራ፣ የተራቆተ ሰውነቱን በጨርቅ ጠቅላላ ፣ ለመኝታው ግርግም አሰናድታ ባላትና ባገኘችው ተቀበለችው። ይህም ለእኛ የተከፈለው ካሣ እረኞችም ምልክት እንዲሆናቸው በመልአኩ በኩል ‘እሱረ መንኮብያት ፣ ስኩብ ውስተ ጎል ፣ ጥብሉል በአጽርቅት (አውራ ጣቱ የታሠረ ፣ ከግርግም የተኛ ፣ በጨርቅ የተጠቀለለ) ሕፃን በበረቱ ታገኛላችሁ’ ተባሉ። [ሉቃ ፪፥፲፪]

ልጇን ጌታዬ የምትል ብቸኛዋ የፈጣሪ እናቱ የአምላክ ወላዲቱ ለዕርቃኑ መክደኛ የበለስ ቅጠል ስላገኘችበት ተኣምራታዊ መንገድ በቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት
እንዲህ የሚል አብነት አለ
«በለሶን ዕፀ አእምሮ የሚባለው ነው፤ ይህ የገነት በለስ አዳምና ሔዋን ፍሬውን በልተው ቅጠሉን የለበሱት ኋላም የልደት ዕለት በተኣምራት መልአክ (ቅዱስ ገብርኤል) አምጥቶላት ዳግሚት ሔዋን ድንግል ማርያም ለልጇ ለዳግማይ አዳም ሥግው ቃል ክርስቶስ ያለበሰችው ነው፤ ቅዱስ ያሬድ በድጓው "ከደነቶ እሙ ቄጽለ በሰሶን" እንዳለው። ስለዚህ ምሥጢር ብዙዎች ብዙ ብለዋል!

ባለቅኔው ፦
በለሰ ገነት ለአዳም ወሔዋን መቲሮቶሙ
መንክረ ልደት አምላከ መንገሌሆሙ ሰሐበ
ወገብርኤልሃ ዜናዊ ቀጸበ
እንተ ከመዝሰ ግብር እምከመ ለአዳም ተውህበ
ወረከበት ሔዋን ዘኢተረክበ
ካዕበ ይስሐብ ኀቤሆሙ አበ
ለበለሰ ይምትርዎ ካዕበ

ደራሲው ፦
ሰላም ለኵልያቲክሙ ዕሩያነ አካል ወአምሳል፥
አቅርንተ ነቢያት ሥላሴ ዘድምጽክሙ ወንጌል፥
ኢሳይያስ ጸርሐ ወይቤ ውስተ መካነ ላሕም ጎል፥
ገብርኤል አወፈየኒ ሕፃነ ማርያም ድንግል፥
በቆጽለ በለሶን ክዱን ወበጸርቅ ጥብሉል

🍁 ወበዮርዳኖስ ተጠምቀ በማይ ዕራቁ (በዮርዳኖስ ዕርቃኑን በውኃ ተጠመቀ)

ለኃጢዓታችን ሥርየት የሚሆን በግዕ ዘመስዋዕት፣ ለነፍሳችን ጠባቂዋ እረኛ ሊቀ ኖሎት፤ ወልዱ ለቡሩክ: ከሣቴ ብርሃን የዓለም መድኃኒት በባርያው በዮሐንስ እጅ እንዲጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ከልብሱ መራቆቱን የአበው መጽሐፍ እንዲህ ይገልጣል

"አስተርአየ በውስተ ዮርዳኖስ እንዘ ክሡት ዕርቃኑ ለተጠምቆ ⇨ ለመጠመቅ ራቁቱን በዮርዳኖስ ባሕር ውስጥ ታየ" (መጽሐፈ ምሥጢር)

የዮርዳኖስ ጥምቀት የሁላችን ዕርቃን የተከደነበት ነው።

🍁 ወበቀራንዮ ሰቀልዎ ዲበ ዕፅ ዕራቆ (በቀራንዮ በእንጨት ላይ ዕርቃኑን ሰቀሉት)

አባ ጊዮርጊስ ስለዚህም እንዲህ ብሏል “ወበከመ ተከሥተ ዕርቃነ አዳም ማእከለ ዕፀዊሃ ለገነት ከማሁ ተከሥተ ዕርቃነ ትስብእቱ ለመድኃኒነ ማዕከለ ጉባኤሆሙ ለማኅበረ እስራኤል ⇨ አዳም በገነት ዛፎች መካከል ርቃኑን እንደታየ እንደሁም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በሰውነቱ በአይሁድ ጉባኤ መካከል ዕርቃኑን ሆኖ ታየ” (መጽሐፈ ምሥጢር)
በደራስያኑም የመልክእ ምስጋና እንዲህ ተገልጧል፦

ሰላም ለዕርቃንክ እምልብሰ እልታሕ ወሰንዱን
እስከነ ሰሐቁ ላዕሌከ ሐራ ጲላጦስ መስፍን
ክርስቶስ ክቡር በቅድመ አይሁድ ምኑን
ክድነኒ እግዚኦ ልብሰ ተፋቅሮ ብርሃን
እስመ ፍቅር ተዓቢ እምኵሉ ሥልጣን
[መልክኣ ማኅየዊ ዘውእቱ መልክአ ኢየሱስ ካልእ]

ሰላም ለዕርቃንከ ዘአዕረቅዎ አይሁድ፤
እምልብሰ ምድራዊ ግዙፋነ ክሣድ፤
ዕሥራኤል እሙንቱ ሕዝብ ክቡድ፤
ተማኅፀነ በዕርቃንከ ከመ ትዕቀበነ ወልድ፤
አንተ አቡነ ወንሕነ ውሉድ። [መልክኣ ቅንዋት]

ቅዱስ ያሬድም በፋሲካው ድጓ እንዲህ ይላል
“ሰአሎ ዮሴፍ ለጲላጦስ ወይቤሎ
#ሀበኒ_በድኖ_ለኢየሱስ
#ከመ_እክድን_ዕቃርኖ_በልብስ
#ለዘከደነ_ዕርቃንየ_በዮርዳኖስ - ዮሴፍ ለጲላጦስ እንዲህ አለው፡- በዮርዳኖስ እርቃኔን የሸፈነውን እርቃኑን በልብስ እሸፍን ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ስጠኝ”

ዮሴፍና ኒቆዲሞስ እንደ ሰብአ ሰገል ምንኛ እድለኞች ናቸው? የአምላኩን እርቃን የሚሸፍን የራሱን ዕርቃን የሚከድን ነው።

እነርሱስ ከመስቀል ለማውረድ በአዲስ መቃብር ለማኖር ዕርቃኑን ለመክደን ሰውነቱን ለመሸፈን ጠይቀው ተፈቀደላቸው!

ታዲያ እኛስ …


ቤተልሔም ፣ ዮርዳኖስና ቀራንዮ
በልደት ፣ በጥምቀትና በስቅለት
የአምላክ «መራቆት»
━━━✦༒⛪༒✦━━━

20 last posts shown.