የኛ ነው ዋሻው እምነቱ ፀበሉ | ዘማሪ አሸናፊ አበበ
የኛ ነው ዋሻው እምነቱ ፀበሉ
አናፍርም ትምክህታችን ነው መስቀሉ/2/
የኛ ነው የኛ የኛ /2/
አዝ____
የሦስት ሺህ አመት የኛ ታሪክ ያላት የኛ
ታቦተ ፅዮን የኛ ያለችበት የኛ
የፀሎት ስፍራ የኛ የኪዳን ሀገር የኛ
ኢትዮጵያ እናቴ የኛ ሀገረ እግዚአብሔር የኛ
አዝ____
ከአንዲት ድንጋይ የኛ የተወቀረው የኛ
የላሊበላ የኛ ድንቅ ስራ ነው የኛ
ጣራው ክፍት ሆኖ የኛ ዝናብ ማይገባው የኛ
አቡነ አሮን የኛ ምንኛ ውብ ነው የኛ
አዝ____
ኢትዮጵያ ሀገሬ የኛ ልጅሽ ባኮስ የኛ
ተጠምቆልሻል የኛ በፊሊጶስ የኛ
በአምላክ ሠው መሆን የኛ ምስጢርን አውቆ የኛ
በየሱስ አምኖ የኛ መጣ ተጠምቆ የኛ
አዝ____
ትምክህታችን ነው የኛ የጌታ መስቀል የኛ
አምነን ድነናል የኛ በእምነት በፀበል የኛ
መለያችን ነው የኛ ማህተባችን የኛ
ተዋህዶ ናት የኛ እምነታችን የኛ
አዝ____
ፃድቃኔ ሂዱ የኛ ሸንኮራ ሂዱ የኛ
ግሸንም ውጡ የኛ አክሱም ውረዱ የኛ
ሽባው ተፈቶ የኛ እውሩ በርቶ የኛ
ጎባጣው ቀንቶ የኛ ደንቆሮው ሠምቶ የኛ
ፍፁም አምነናል የኛ አይናችን አይቶ የኛ
ፀንተን ቆመናል የኛ ጆሯችን ሰምቶ የኛ
@Orthodox_Mezmur_For_All@Orthodox_Mezmur_For_All