orthodox new mezmur


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን የህይወት ቃል ጌታ እግዚአብሔር በገለጠልን ፀጋ መጠን የምንካፈልበት ሲሆን!
" ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤"ቲቶ 2÷11
ስለዚህ ፀጋ ያየነውን የዳሰስነውን በስልጣን ቃል ለትውልድ ሁሉ በእምነት እናውጃለን!! ቤተሰባችን ስለሆናችሁ በክርስቶስ ፍቅር እንወዳችኃለን!!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙በዘማሪ የአብቃል ደሳለኝ

🎙የአፎሚያ እረዳት

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙ጠባቂዬ

🎙ዘማሪ እስ-ከዳር

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙 ሚካኤል_ሥዩም

🎙ዘማሪት_ፀሐይ ሽብሩ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


#የተቀደደ_መጽሐፍ

መጽሐፍት ሙሉ መልዕክት የሚኖራቸው ሙሉውን ክፍል እስካነበብን ድረስ ነው። የአንድን መጽሐፍ አንድ ገጽ መቅደድ የመልዕክቱን ሙሉነት ያሳንሰዋል። ብዙ መጽሐፍ ማንበብ የሚወዱ ሰዎች መጽሐፍ ሲቀደድ ሲያዩ የመታገስ ጽዋቸው ሞልቶ ለቁጣ ይጋበዛሉ። ያነበብቱ በዚህ ልክ ከተሰማቸው የመጽሐፉ ጸሓፊ ደግሞ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም። አንዳንድ ጸሓፊዎች መጽሐፋቸውን ልጄ ብለው በመጥራት ለልጃቸው የሚያደርጉትን ጥንቃቄ ሁሉ ለመጽሐፋቸው ሲያደርጉ ይስተዋላሉ።

እግዚአብሔር ቃሉ እንዲጻፍ ለምን የፈለገ ይመስላችኋል? ሳይጻፍ ቀርቶ በንግርት ወይም ከሰዎች ምላስ ላይ እንዲደመጥ አድርጎስ ቢሆን? እንዲ ቢሆን ኖሮ በዚህ ዘመን የምንሰማው ቃል ጥቂት የእግዚአብሔር ይሆንና እልፍ የሰዎች ይሆናል። የተወሰኑ 20 ሰዎችን ደርድረን ለመጀመሪያው ረዘም ያለ መልዕክት ነግረነው ለሁለተኛው እንዲነግረው ሁለተኛውም ለሶስተኛው..... 20ኛው ሰው እስኪ የሰማኸውን ንገረን ብንለው ከዋናው መልዕክት በጣም ጥቂት ቃላት ከ19ኙ ሰዎች ብዙ ስህተት የሆነ ቃላትን ገጣጥሞ ይነግረናል።

በንግርት የሚያልፍ መልዕክት አይደለም ከትውልድ ወደ ትውልድ በሙሉነቱ ሊሸጋገር ቀርቶ በአንድ ትውልድ ውስጥ ባሉ ሰዎች እንኳን በትክክል ለመተላለፍ ይቸገራል። የእግዚአብሔር ቃሉ በንግርት የተቀመጠ ቢሆን ነገስታት ያራቸውን ክብር ለመጨመር ቃሉ ላይ በጨመሩ ነበር፣ ተናጋሪዎቹ የሰሙትን እንደሚረዱት መጠን ባስተላለፉት ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል መጻፍ ዋና ጉዳይ መልዕክቱ ትክክለኛነቱን እንደጠበቀ ዘመናትን እንዲሻገር ነው።

ይኸው ስለተጻፈ በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች በዛ ዘመን የተሰበከውን የእውነት ቃል ለማንበብ እና በቅዱሱ መንፈስ አማካኝነት ደግሞ ለመረዳት በቅተናል። እረ እንኳንም ተጻፈ። የመልዕክቱ ርዕስ የተቀደደ መጽሐፍ ስለሚል ከርዕሴ እንዳልወጣ ስለመጻፉ አስፈላጊነት ብዙ አልበል። ብዙ ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ቅዱሱን የእግዚአብሔር ቃል በመቅደድ ተግባር ላይ ናቸው። መርጠው ይሰማሉ፣ ከፍለው ያነባሉ፣ ቆንጽለው ይረዳሉ፣ የተመቻቸውን ክፍል ብቻ ልክ ይላሉ፣ እንደልባቸው ይተረጉማሉ ይሄ ነው መጽሐፉን መቅደድ የሚባለው።

አሁን አሁንማ ከሰዎችም አልፎ ተርፎ ቤተ እምነቶችም ለራሳቸው አስተምህሮ እንዲመች አድርገው መጽሐፉን ይቀዳሉ ግሪኩ እንዲ ይላል በማለት የራሳቸውን ያስቀምጣሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ የአፍ መፍቻ ቋንቋ የዕብራስጥ እና የግሪክ ቋንቋ እንደሆነ መረዳት ያሻል። መጽሐፉ ልክ ሲጻፍ እንዲ ይላል ብሎ ሌላ መጽሐፍ መጽሐፉን መቅደድ ካልተባለ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም።

ከመሃል መርጠን የተረዳነውን ቃል እስኪ ከነሙሉ መልዕክቱ ለመረዳት ልባችንን ክፍት እናድርግ ያኔ የቀደድናቸው ክፍሎች ይታዩናል። አንድ ጸሓፊ የጻፈው መጽሐፍ ሲቀደድበት ማያትን ካልፈለገ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር መጽሐፉ ሲቀደድ ምን ይሰማው ይሆን? የእግዚአብሔር ከሆነው ነገር ከመጉደል በላይ መጉደል ወዴት አለ? የእግዚአብሔርን ሃሳብ በሙሉነቱ ካልመረዳት በላይ መጎዳትስ ከዬት ይገኛል?

ስለእግዚአብሔር ቃል ያለን መረዳት ስለዘላለማችን ይወስናልና መረዳታችን በተገቢው መልኩ መፈተሽ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ሆኖ የማይገባን ነገር እንዳይኖር መትጋት በጣም አስፈላጊ ነው። የእግዚአብሔር የልቡ ሃሳብ ያለው የትም አይደለም ቅዱሱ መጽሐፍ ላይ ነው። ከዚህ ክፍል አንዱን ገጽ መቅደድ በእግዚአብሔር በልቡ ሃሳብ ላይ ማሾፍ ነው። እናማ አትቅደዱ አንቅደድ። በተቻለን ሁሉ ከዚህ ቃል የማይገባን እንዳይኖር እግዚአብሔር መረዳታችንን እንዲረዳው መጸለይ እና ቃሉን ማንበብ የሁል ጊዜ ስራችን ይሁን።

✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙ዳዊት መዝሙረኛው

🎙ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙የምናምንሽ

🎙ዘማሪት ዶክተር ቤዛዊት ወንድሙ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙ትንሣኤና_ሕይወት

🎙ዘማሪት ሔርሜላ ሲሳይ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙ይደንቀኛል_መኖሬ

🎙ዘማሪት እጹብድንቅ አዲሱ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


#ትላንት_ዛሬ_ነገ

ዘመን ሳይዘምን ገና፣ ጸሐይ ሳትታይ በፊት፣ ጨረቃም ሳትወጣ ቀድሞ፣ ሰማይ ሳይዘረጋ፣ ምድርም ሳትቆም፣ ከዋክብት ሳይታዩ፣ ወንዞች ሳይፈሱ፣ ውቂያኖስ ሳይሞላ፣ አዕዋፋት ሳይበሩ፣ ፍጥረታት ሳይፈጠሩ፣ አራዊት ሳይኖሩ፣ ሰውም በምድር ላይ ሳይታይ፣ የሚታዩ እና የማይታዩት ፍጥረታት ሳይኖሩ፣ አመታት ሳይቆጠሩ፣ ወራት ሳይፈራረቁ፣ ሳምንታት ሳይቀያየሩ፣ ቀናትም አሃዱ ሳይባሉ፣ ሰዓታት ሳይቆጥሩ፣ ደቂቃና ሰከንዶች ሳይጀምሩ ብቸውን የነበረ፣ ከዘላለም በፊት የከበረ፣ ከመጀመሪያ በፊት ሆኖ መጀመሪያን ያስጀመረ፣ ከሁሉ ነገረ በፊት የነበረ፣ አንድ ተብሎ ቁጥር የማይጀመርለት፣ ለዘመኑ ቁጥር የሌለው እርሱ እግዚአብሔር ነው። ትላንት የነበረ እርሱ አምላካችን ነው።

አለም በኃጢያት ወደቃ፣ በሴሰኝነት ወጥመድ ገብታ፣ ሰው ክብሩን ጥሎ ቀሎ እየኖረ፣ ለአምላኩ ትቶ ለሆዱ እያደረ፣ ጽድቅ የሆነውን ለቆ ለበደል እየኳተነ፣ ፍቅርን ከመየዝ ይልቅ ጥላቻን እያነገበ፣ ቅን የሆነውን ረስቶ ለተንኮል እየነቃ፣ ሰው በብዙ ልከ በልሆነ ነገር ውስጥ ሆኖ እርሱ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ እያየ በዙፋኑ ላይ አለ። ትላንትን አሳልፎ አሁንን የሰራ፣ ያለፈውን የሚያውቅ ያለውን የሚያኖር፣ ዛሬን ከዘላለም በፊት የሚያውቃት፣ ሁሉን የሚገዛ ሁሉን የሚያስተዳድር፣ ሁሉን የሚመገብ ደግሞ ሁሉን የሚጠብቅ፣ ዛሬ በምንለው በየትኛውም  ዛሬ ላይ ሁሌ ያለ እርሱ ፈጣሪያችን ነው።

ሁሉ ካለፈ በኋላ የማያልፍ ፣ ሁሉም ነበር ከሆነ በኋላ ነበር የማይባልለት፣ ከዘላለም በኃላ የሚኖር፣ እስከ ተብሎ የማይገደብ፣ በቃ ተብሎ የማይቋጭለት፣ ሁሉን በነበር መጥራት የሚችል፣ አሁን የለም የማይባልለት፣ የዘመን  ቁጥር የማይሰላለት፣ የጊዜ ቀመር የማይቀመርለት፣ የእድሜ ገደብ የማይበጅለት፣ ሁሉ አልፎ የሚኖር እርሱ እግዚአብሔር ጠባቂያችን ነው። ነገን ያያት ነገን የሚያውቃት ነገም የሚኖር እረሱ መድሃኒታችን ነው።

ትላንት የነበረ አሁንም ያለ ዘመናትን አሰልፎ የሚኖር እርሱ እግዚአብሔር ነው። ስሙ ይክበር ይመስገን። አሜን

✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur


🔔አዲስ የዝማሬ አልበም

🎙በዘማሪት ፀጌሬዳ ጥላሁን

🎙የጸሎቴ ልዕስ ነህ ሙሉ አልበም

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


#ሺ_ጊዜ

ሺ ጊዜ ኃጢያት ስራ ነገር ግን ንስሃ ከመግባት አትቦዝን። የፈጠረህ እግዚአብሔር ጨርሶ አንተን መማር አይሰለችምና። እልፍ ጊዜ በድል ነገር ግን ከእግዚአብሔር አትኮብልል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የደበሉ ወደ እርሱ የሚሸሸጉበት ዕሩሩህ እንጂ የሚሸሹት ጨካኝ አይደለምና።

በጣም ለቁጥር እንኳን በሚታክት ጥፋት ውስጥ ሁን ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከእግሩ ስር አትጥፋ። እግሩ ስር ስትሆን ክብር አለህና በጥፋትህ ብዛት እኔ እንዴት ወደ እግዚአብሔር እቀርባለሁ ብለህ አትራቅ። እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንድትቀርብ ልጁን ለአንተ ሲል በመስቀል ሰውቶታልና።

ጉድ የሚያስብል ጉድ ውስጥም ሁን ነገር ግን ገበናህን ከሚሸሸግልህ ከእግዚአብሔር አትሸፍት። የሁሉ ሰው ተግባር በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ ነው። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገርህን እያወቀ ዝም የሚልህ ስለሚምርህ ነው እንጂ ለኃጢአትህ መዝገብ አዘጋጅቶ አይደለም።

ኃጢአቴ ብዙ ነው ብትልም የኃጢአትህ ክምር በጭራሽ እግዚአብሔርን እንዳይሸሽግህ። ከበደልህ ይልቅ የሞተልህን ተመልከት። እግዚአብሔር የኃጥዓን መፍትሔ ነው። ችግር ውስጥ እንዳለህ በተሰማ ቁጥር ወደ ባለመፍትሔው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እጅግ ማትረፊያ ነው። ኃጢአት የሰው ልጅ ሁሉ ችግር ነውና።

የራስህን መንገድ ብትከተል ጨርሶ ልትወጣው ወደማትችለው መስመር ልትገባ ትችላለህ ከዚህ ይልቅ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” (ማቴዎስ 11፥28) የሚለውን መለኮታዊ ቃል አምነህ ከነሸክምህ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ። እርሱ እንዳለውም ያሳርፍሃልና።

የራስህን ኃጢአት እና የእግዚአብሔርን ጽድቅ እያመዛዘንክ አትኑር። በምንም መልኩ በእግዚአብሔር ልክ ጻድቅ ልትሆን እና የእርሱን የጽድቅ ጥማትም ልታረክ አትችልም። እንዲህ እስክሆን ወደ እርሱ አልቀርብም፣ ይሄንን ልማዴን እስከተው አልጠጋውም አትበል ያንን ልማድህን የሚያስክድ እና የሚያስተው አቅም እና ጸጋ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ እራስህ ጋር አታገኘውምና።

እና ወዳጄ እሩጫ የሚሻለው ወደ እግዚአብሔር ሲሆን ነው። ጌታ እግዚአብሔር የማያሳፍርህ ተቀባይ፣ የማያሸማቀቅህ አዛኝ፣ ፊት የማይነሳህ አቃፊ ነው። እና ወደ እርሱ መምጣት የሁሉ ነገር መፍትሔ ነው።

✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur




🔔አዲስ ዝማሬ

🎙መዝገበ ርህራኄ

🎙ዘማሪ ኤርምያስ_ታደሰ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙ኃጥያት ያልሰራ እሳት የተሸከመ

🎙 ዘማሪት ኢ፡ር ፋሲካ አሰፋ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙የልቤን ሁሉ የማዋይሽ

🎙ዲያቆን_አሸናፊ_በላይ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024


#ዋናው_እኔ_ነኝ

ብዙ የበደሉህ ዋኖች ይኖራሉ እንደ እኔ ግን አልበደለሁም፣ አንተን ያስከፉህ ቢሰለፉ ከፊት የምገኘው እኔ ነኝ፣ በኃጢአት ባህር መዋኘት ድሎት የሆናቸው ብዙ አሉ ዋናው ግን እኔ ነኝ፣ ልክ ባልሆነው ጎዳና የሚራመዱ አሉ መሪያቸው ግን እኔ ነኝ፣ አንተን በመቅረብ ፈንታ ጀርባ የሰጡህ አሉ እኔ ግን እብሳለሁ፣ ጌታዬ መድሃኒቴ ኢየሱስ አንተን የምትል ነፍሴ በስጋ ድካም ውስጥ ሳለ አለሁሽ ያልካት አንተ ነህ።

እኔ መማርህ እንዴት ያለ ምህረት ነው። የምህረትህ ድልድልነት ለእያንዳንዱ መንገዴ መሸጋገሪያ ሆኖኛል። እኔን ለማዳን ወደዚች አለም የመጣ አስታዋሼ አንተ ነህ። ከነ ኃጢያቴ እንዳልጠፋ እኔ ባለሁበት ተገኝተህ ያገኘኸን ፈላጊዬ ነህ፣ በሞት ጥላ ውስጥ ያለሁትን በደምህ ድምጽ የጠራኸኝ ባለውለታዬ አንተ ነህ፣ በምድረበዳው ብቻዬን ስባዝን ና ወደ እኔ ያልከኝ አስጠጊዬ አንተ ነህ።

እኔ ብቻ እንኳን በኃጢያት የጠፋው ብሆን የራስህ ጉዳይ ብለህ ከነበደሌ የማትተወኝ ለእኔ ብቻ እንኳን ብለህ ልትሞትልኝ የምትመጣ አፍቃሪዬ ነህ። ለእኔ ስትል ሰው የሆንክ አምላኬ ክርስቶስ ሆይ ክበር ተመስገን። እኔን ዋናውን ለማዳን ስትል ከሰው ተርታ ተገኝተህ በሰው ልክ የተመላለስክ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ተመስገን።

ወደ ክብሬ ልትመልሰኝ ክብርህን እንደመቀመት ሳትቆጥር ከላይ ከሰማያት የመጣህልኝ አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ። እኔን ከማርከኝማ እኔን ይቅር ካልከኝማ ማንም ትምራለህ። እኔን ዋናውን ከተቀበልክማ መዳፍህ ሰፊ ነው ሁሉን ይቀበላል።

ለእኔ ስለሆነው በጎነትህ ክብር ይሁንልህ። አሜን

“ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤”  1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥15

✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur


#የምትነበብብኝ

ሰው የሚያውቀኝ በጎደፈው ግብሬ፣ በጠለሸው ማንነቴ፣ ከአዳፋው ሰውነቴ እና በበደለው እኔነቴ ነው። ወደ እኔም ሲመለከተ የሚታወሰው በጎ ሳይሆን መጥፎ ብቻ ነው። ይህን ማንነቴን ልተወው ብዙ ታግያለሁ ነገር ግን ከድካምና ከቁስል በቀር ምንም ትርፍ አልነበረኝም። ለካ ሳውቀው ያለ እርዳታህ ለካ ስረዳው ያለ አብሮነትህ የሚቻል አይደለም።

የህይወቴን አቅጣጫ እንድትመራው ፍቃድ ስሰጥህ እና ከአንተ ጋር ስስማማ የምታገለው ቀለለኝ። ደስታ ይሆነኝ የነበረው መጥፎ ግብሬ መጥፎነቱ ፍንትው ብሎ የታየኝ ትክክል የሆንከውን አንተን ሳገኝ ነው። እንደቀድሞው ሆ ብዬ ለተንኮል እንዳልዘምት አንተ ገንዘብህ አደረከኝ።

ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ በኃጢያት ልማድ ለተንከራተተች ነፍሴ አለሁኝ ብለህ በምህረትህ ምረህ በይቅርታህ አቅፈህ ታሪኬን የቀየርከው አንተ ነህ። መተላለፌን ደመሰስክ በደለኛነቴን ይቅር አልክ ለዚህም በእያንዳንዱ ግብሬ እና እርምጃዬ የምትነበብብኝ ነህ።

ሰዎች ሲመለከቱኝ ይቅር ባይ መሆንህ ይታይብኛል። እርሱንም እግዚአብሔር ይምራል ለካ እያሉ በእኔ መቆም ውስጥ ምህረትህን ያስተውላሉ። የህይወቴ ምዕራፉ ቢገለጥ ምንም የረባ ነገር የሌለኝን እኔን ይረባኛል ብለህ ስለተቀበልከኝ በእኔ ላይ አዛኝነትህ ይነበባል።

በእኔ መራድ ሰዎች የአንተን ምህረት ይናገሩ በመኖሬ ይቅርታህን ያደናንቁ። እኔ የምህርትህ ውጤት፣ የይቅርታህ ፍሬ ነኝ። ያቆመኝ የጉልበቴ መጠንከር እና የአቅሜ ጽናት አይደለም ያቆምከኝ አንተ ነህ እንጂ። አንተ ስላለኸኝ እኔም ኖርኩኝ እንጂ ግብሬ አላኖረኝም።

ብዙ ዕለታትን የማለፌ፣ ብዙ ምሽቶችን የማንጋቴ ምክንያቱ ከእኔ የሆነ ምንም ነገር ሳይሆን ከአንተው የሚመነጨው የምህረትህ ጉልበት ነው። ሰዎች እሱም እስከ ዛሬ በህይወት አለ ብለው ቢደነቁ አስደናቂው ምህረትህ ከልሎኝ እንደቆምኩኝ ይወቁ።

ለመሃሪነትህ ምስክሩ እንሆኝ ባርያህ አለሁኝ። ሰው እኔን ሲያይ እንደፈወስከኝ ይቃወቅልኝ። ሰው እኔን ሲያይ እንደማርከኝ ይቃወቅልኝ።  እንምትምር ምረኸኝ አይቻለሁኝ። በአፈ ታሪክ እግዚአብሔር ይምራል ሲባል ሰማሁኝ አሁነ ግን በህይወቴ ሆኖ አየሁት።

በምልኬ ውስጥ የምትታየው አንተ ሁን። በመቆሜ ውስጥ ምህረትህ ይነገር። በድርጊቴ ውስጥ አንተ ተነበብብኝ። ምክንያቱም እንደ አንተ እንጂ እንደ እራሴ ዛሬ የኔ አልነበረችምና። ክብር እና ምስጋና አምላኮና ውዳሴ ከምድር እሰከ አርያም ድረስ ለአንተ ይሁን። አሜን

✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ከአንድ አመት በፊት ተጻፈ

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur


🔔አዲስ ዝማሬ

🎙ያለ አንተ ማን አስቦኛል

🎙በዘማሪት_ሳራ_መንግሥቱ_

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024

54k 0 238 146



🔔እንኳን አደረሳችሁ

🎙የማትረግፍ_አበባ

🎙ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ግርማ አዳነ

💒Ethiopian Orthodox Mezmur 

@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur

         👆 ይቀላቀሉን   👆

📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024

20 last posts shown.