የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር👏


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮንና ስርዓትን የጠበቁ ያሬዳዊ መዝሙሮች ግጥማቸውን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።@abnat19

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter




|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 25 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከነ የምስክር ወረቀቱ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 25 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከነ የምስክር ወረቀቱ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ታሪክ 🥺


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 25 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከነ የምስክር ወረቀቱ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


መጋቢት 29 በኩረ በዓላት

ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልዩ ናት።

በዚህ ዕለት፦
ጥንተ ፍጥረት ነው፦ በዚህች ቀን እግዚአብሔር ፍጥረታትን መፍጠር ጀመረ። "....ሰማይና ምድርን ፈጠረ።" ዘፍ. 1፥1)
በዓለ ጽንሰት ( በዓለ ትስብእት) ነው፦ (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብሥራተ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ተጸነሰ።) ሉቃ. 1፥26
ጥንተ ትንሳኤ ነው (የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ነው) ማቴ. 28፥1
ዳግም ምጽአት በዚህች ዕለት ነው፦ (በዚህች ዕለት ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚህች ቀን ይመጣል።) ማቴ. 24፥1

በእነዚህ በዓላት ምክንያት ዕለቱ "ርዕሰ በዓላት፣ በኩረ በዓላት" ይባላል።



የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን በእንተ ጾም


....ወርቅ በእሳት ውስጥ ሲጨመር ዝገቱ እንደሚርቅ ኹሉ፥ የእነዚህ ኃይላተ ቃላት ፍርሐት በልቡናችን ጽላት ላይ ሲቀረፅም ይህን ያህልና ከዚህ በላይ የዝሙት ዝገትን (ኃጢአትን) ኹሉ እናርቃለን፡፡ ስለዚህ በወዲያኛው ዓለም በእሳተ ገሃነም እንዳንቃጠል በዚህ ዓለም በቃሉ ትምህርት ይህን እሳት በልቡናችን ላይ እናንድደው፡፡ በዚህ ዓለም ሕሊናቸውን ንጹህ ያደረጉ ሰዎች፥ በወዲያኛው ዓለም ያለው እሳት አያቃጥላቸውምና፡፡ ከእነ ኃጢአታቸው ወደዚያ ከኼዱ ግን ያ እሳት ያገኛቸዋልና፡፡ “በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መኾኑን እሳቱ ይፈትነዋል” ይላልና (1ኛ ቆሮ. 3፥13)፡፡ ስለዚህ በወዲያኛው ዓለም በሕማም በዋይታ እንዳንመረመር በዚህ ዓለም ያለ ሕማም ያለ ዋይታ ራሳችንን እንመርምር፡፡

“ምንም ብትል ምን ግን ሕጉ (ትእዛዙ) አስጨናቂ ነው" የሚል ሰው አለ፡፡ እንግዲህ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ማድረግ የማይቻለንን ነገር እንድናደርግ አዝዞናልን? በፍጹም ማድረግ የማይቻለንን ሕግ (ትእዛዝ) እንድንፈጽም አላዘዘንም ብዬ እመልስልሃለሁ፡፡

ዝም በል! በዚህ አትጸድቅምና ወይም ደግሞ ከቅድሙ ይልቅ የባሰ በደል ትሠራለህና አምላክንም አትውቀስ፡፡ ደጋግመው ኃጢአት የሚሠሩ ሰዎች ለፈጸሙት በደል እነርሱ ራሳቸው ባለ ዕዳ እንደ ኾኑ አድምጥ፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ባሪያ ሌላ አምስት አትርፎ መጣ፡፡ ኹለት መክሊት የተቀበለውም ሌላ ኹለት አትርፎ ይዞ መጣ፡፡ አንድ መክሊት የተሰጠው ሰው ግን ሳያተርፍ ያቺኑ ይዞ መጣ፡፡ ይባስ ብሎም አትርፎ እንደ መምጣት “ጨካኝ ሰው መኾንህን ዐውቃለሁ” ብሎ በጌታው ላይ የነቀፋ ቃልን ሰነዘረ (ማቴ.25፥24)፡፡

ወዮ! አእምሮ የጎደለው ባሪያ! የገዛ ራሱ ኃጢአት ሳይበቃው እንደ ገና በጌታው ላይ የነቀፋ ቃልን ጨመረበት፡፡ “ያላኖርኸውን ትወስዳለህ፤ ያልዘራኸውም ታጭዳለህ' ብሎአልና (ሉቃ.19፥21)፡፡ ልክ እንደዚሁ ብዙ ሰዎች በዚህ ዓለም በጎ ሥራን ካለመሥራታቸው በላይ እንደ ገና በጌታ ላይ የነቀፋ ቃልን በመናገር ሌላ በደል ይጨምሩበታል፡፡ ኾኖም ግን ጌታችን የማንችለውን ነገር አላዘዘንም፡፡

እግዚአብሔር ማድረግ የማንችለውን ሕግ እንድንፈጽም እንዳላዘዘን ልታውቅ ትወድዳለህን? ብዙዎች ከታዘዙት በላይ አትርፈው ፈጽመዋል፡፡ የተሰጠን ትእዛዝ ጥንቱንም የማይቻል ቢኾን ኖሮ ትሩፋትን መሥራት ባልተቻለ ነበርና፡፡ የድንግልና ሕይወትን በግድ እንድንፈጽመው አላዘዘንም። ብዙዎች ግን ይህ ተችሏቸዋል፡፡ መንኖ ጥሪትን በግድ ገንዘብ እንድናደርገው አለዘዘንም፡፡ ብዙዎች ግን ሀብታቸውን ንቀዋል፤ ትእዛዛተ ወንጌል ለማድረግ እጅግ ቀሊላን መኾናቸውም በሥራቸው መስክረዋል፡፡ የድንግልና ሕይወትን አላዘዘም፤ ድንግልናን እንደ ግዴታ የሚያዝዝ ይህን የማይፈልገውን ሰውንም የግድ ይህን ሕግ እንዲፈጽም ያዝዘዋልና፡፡'' ምክርን ብቻ የሚሰጥ ግን ሰማዒው ምርጫ እንዲኖረው ይፈቅድለታል፡፡ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ፡- “ስለ ደናግልም የጌታ ትእዛዝ የለኝም፥ ነገር ግን ምክር እመክራለሁ” ያለበት ምክንያትም ይህ ነው (1ኛ ቆሮ.7፡25)፡፡ እንግዲህ ምክር እንጂ ትእዛዝ እንዳልኾነ ትመለከታለህን? በትእዛዝና በምክር መካከልም ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ ትእዛዝ ግዴታ ሲኾን ምክር ግን እንደ ምርጫ የሚከናወን ነውና፡፡ “አስተምር ዘንድ እመክራለሁ እንጂ ሸክም እንዳልኾንባችሁ ትእዛዝን አላዝዝም" አለ፡፡ እንዲህም በመኾኑ ጌታችን ክርስቶስ፦ “ኹላችሁም የድንግልና ሕይወትን ኑሩ" አላለም፡፡ ሰዎች ኹሉ በድንግልና እንዲኖሩ አዝዞና ምክሩን ትእዛዝ አድርጎት ቢኾን ኖሮ ያን ሕይወት መኖር የሚችሉትም ቢኾኑ እንደ አሁኑ በድንግልና መኖራቸው ታላቅ ክብርን ባላስገኘላቸው ነበርና፡፡ በድንግልና የማይኖር ስውም ጽኑ ቅጣት ባገኘው ነበርና፡፡

ይቀጥላል..

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ንስሓና ምጽዋት ገጽ 96-116 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)



የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን በእንተ ጾም

....በዚህ ዓለም ሕይወት የነገሮች አከዋወን እንደዚህ ነውና፡፡ ትኩረትህን ልታመጣው ባለህ ነገር አድካሚነት ላይ የምታደርግ ከኾነ፡ ነገሩን ለማግኘት እጅግ ከባድና አስቸጋሪ ይኾንብሃል፡፡ ትርፉን የምታስብ ከኾነ ግን በፊትህ ያለው ነገር ቀላል ነው፡፡ አንድ የመርከብ አለቃም ማዕበሎችን ብቻ የሚመለከት ከኾነ መርከቢቱን ወደ ወደቡ ሊያደርሳት አይችልም:: ማዕበሎቹን ሳይኾን ንግዱን የሚመለከት ከኾነ ግን ተበረታትቶ ግዙፉን ባሕር ደፍሮ ይሻገረዋል፡፡ አንድ ወታደርም ስለሚያጋጥሙት ቁስሎችና ሞት የሚያስብ ከኾነ ጋሻ ጦር አይታጠቅም፡፡ ከቁስሎቹ ይልቅ ስለሚያገኛቸው ድሎችና ማሸነፎች የሚያስብ ከኾነ ግን ለምለም መስክ እንደሚሮጥ ሰው ኾኖ ወደ ዓውደ ውጊያው እየተፋጠነ ይኼዳል። ማንኛውም በተፈጥሮው ከባድ የኾነ ነገር ቀላል የሚኾነው አስቸጋሪነቱንና ከባድነቱን ብቻ ሳይኾን ከዚያ የሚገኘው ሽልማትንም ጭምር የተመለከትን እንደ ኾነ ነውና፡፡

በተፈጥሯቸው ከባድና አስቸጋሪ የኾኑ ነገሮች እንዴት ቀላል እንደሚኾኑ መማር ትወድዳለህን? ቅዱስ ጳውሎስን አድምጠው፤ እንዲህ ያለውን "የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የኾነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘለዓለም ብዛት ከኹሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና” (2ኛ ቆሮ.4፥17)። የተናገረው ነገር ረቂቅ ነው፡፡ “መከራ ከኾነ ቀላል የሚኾነው እንዴት ነው? ቀላል ከኾነስ - እነዚህ ነገሮች ተቃራኒ ናቸውና - እንዴት መከራ ሊኾን ይችላል?" ሊባል ይችላልና፡፡ ቀላል መኾኑን በምን መንገድ እንደ ኾነ ቀጥሎ በተናገረው ነገር ረቂቁን (የተሰወረውን) ግልፅ አድርጎታል፡፡ እንዴት? "የሚታየውን እንመልከት" በማለት! ቅዱስ ጳውሎስ መጀመሪያ የክብር አክሊሉን አመጣና ቀጥሎም ተጋድሎውን ቀላል አደረገው፡፡ አስቀድሞ ሽልማቱን አሳየና አድካሚነቱን አራቀ፡፡ ስለዚህ አንተም መልከ መልካምና ተሸላልማ የለበሰች ሴትን ስትመለከትና ምኞት ቢመጣብህ፤ ልብህም ሴትዋን ማየት ደስ እንዳሰኘው ብታስተውል ዓይንህን ከዚህ ነቅለህ ከላይ ከሰማይ ያለውን አክሊል ወደ ማየት ከፍ ከፍ አድርገው፡፡ እንደ አንተ ባሪያ የኾነችን ሴት አየህን? ጌታህን አስብ፤ በቀላሉም በሽታህን ማራቅ ይቻልሃል፡፡

የሚማሩ ሕፃናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሁ ያለ ዓላማ የማይኼዱና ተምረው የማይመጡ ከኾነ፣ በስንፍና የማይመላለሱ ከኾነ፣ ይህን ማድረግ የማይሰለቻቸው ከኾነ እንተ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ክርስቶስን በዓይነ ሕሊናህ በፊትህ የምትመለከተው ከኾነ እንደዚህ ያለ ነገር አያገኝህም፡፡ "ወደ ሴት ያየ ኹሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል" (ማቴ. 5፥28)፡፡ እኔ እጅግ ደስ ብሎኝና አዘውትሬ የሕግ መልእክታትን (መጽሐፍ ቅዱስን) አነባ'ለሁ፡፡ በዚህ በሽታ በቀላሉ የሚጠቁ ሰዎች ሳይቀሩ ቀኑን ሙሉ ይህን ማድረግ እንደሚቻላቸው ልነግራችሁ እወድዳለሁ፡፡ እናንተ ግን በርግጥ ከዚህ መጠበቅ እንደሚቻላችሁ ልነግራችሁ እወድዳለሁ፡፡ በዚህም ብዙዎች ወደ ጤንነታቸው ይመለሳሉ፡፡ “ወደ ሴት ያየ ኹሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል፡፡”

እነዚህን ኃይላተ ቃላት ማንበብ ብቻ የኃጢአትን ብክለት ኹሉ ማንጻት ይቻላል፡፡ ቁስሎች የሚነጹት (የሚድኑት) በዚህ መንገድ ነውና፡፡ ቁስሎችን የሚያነጻ ሰው አስቀድሞ ጽኑ መድኃኒቶችን ይጨምራል፡፡ እናንተም እነዚህን ኃይላተ ቃላት ስትቀበሉአቸውና ስትተገብሩአቸው፥ ይህን ያህልና ከዚህ በላይ የዝሙትን መርዝ ከእናንተ ታርቃላችሁ፡፡

ይቀጥላል..

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ንስሓና ምጽዋት ገጽ 96-116 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)


የሌሊቱ ተማሪ ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በዮሐ. 3÷1 ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ 1÷2) በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው ኒቆዲሞስ “መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርገ የሚችል የለምና።" በማለት ተናገረ።(ዮሐ3፥2) በዚህ ጊዜ ጌታችን የገነት በር ስለሆነው ስለ ምስጢረ ጥምቀት አስፍቶና አምልቶ በምሳሌ ጭምር አስረዳው። "እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” (ዮሐ 3፥3) በማለት መንፈሳዊ እውቀት የጎደለው መሆኑን አሳይቶ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ከእግዚአብሔር መንግሥት ውጪ እንደሚሆን አስርግጦ ነገረው።

በዚህም ታላቅ ምስጢርን ሊገልጥለት ወደደ። ይህ አነጋገር ከአይሁድ አለቆች አንዱ ለሆነው ፈሪሳዊ ሰው ከባድ ነበር። ምሥጢሩም ቢጸናበት ጊዜ ጌታን እንዲህ በማለት ጠየቀው “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንደምን ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማሕጸን ተመልሶ ሊገባ ይችላልን?“። (ዮሐ 3፥4) ጌታችንም ለኒቆዲሞስ መልሶ የአዳም ልጆች ሁሉ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ካልተወለዱ (በመንፈስ ቅዱስ መታደስን በሚያሰጥ ጥምቀት ካልተጠመቁ) መንግሥተ ሰማያትን መውረስ እንደማይችሉ ነገረው።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር!!


የጌታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ ታሪክ🥺


​​​​​​​​ኒቆዲሞስ
የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት።


''እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። (ዮሐ 3:3-6)

ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር። በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡

ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች። ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡

ኒቆዲሞስ ማነው?

፩. ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው《ዮሐ 3-1》
፪. ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው《ዮሐ 3-1》
፫. ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው《ዮሐ 3-10》
፬. ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው 《ዮሐ 7-51》

ኒቆዲሞስ ምን አደረገ?

ለምስጢረ ጥምቀት መገለጥ ምክንያት ሆነ《ዮሐ 3:1-21)
አዋቂ ነን የሚሉትን አሳፈራቸው 《ዮሐ 7-51》
ጌታን ለመገነዝ በቃ《ዮሐ 19-38》

=> ከኒቆዲሞስ ምን እንማር?
አትኅቶ ርእስ ጎደሎን ማወቅ የእውነት ምስክር《ስምዐ ጽድቅ》መሆን ትግሃ ሌሊት እስከ መጨረሻ መጽናት በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡

የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን ምክንያት ነውና በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


♡ ኒቆዲሞስ ክቡር ♡


ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር


በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትህትና ተዋርዶ አደረቀ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቶ አከበረ
ከመቅደሱ አንቀፅ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ


ለሊትም ለሊት ዕውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማ ሀጢያት ነግታ ብርሃን ከአየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

ዲያቆን ዘማሪ ቀዳሚፀጋ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
  @maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


♡ ኒቆዲሞስ ♡


ሥውር ወዳጅ ምሁረ ኦሪት
ኒቆዲሞስ ክቡር ኒቆዲሞስ ትሑት
ባለጸጋ ሳለ በበጎ ሕሊና
ዝቅ ብሎ ተማረ በሚደንቅ ትሕትና ፪


የአይሁድ አለቃ ኒቆዲሞስ ምሁር
ጌታችን እንዳለ የእስራኤል መምህር
ከፈሪሳውያን ልቡ የቀናለት
በሌሊቱ ሲጓዝ ብርሀን በራለት፪
በመቅደስህ ቆሜ ስምህን ላሞግስ
መንገዴን አብራልኝ በሌሊት ልገስግስ፪

 
አዝ= = = = =

እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነለት በቀር
ማንም አያደርግም የእጅህን ተአምር
ብሎ ባንደበቱ እንደመሰከረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ፪
በመቅደስህ ቆሜ ስምህን ላሞግስ
መንገዴን አብራልኝ በሌሊት ልገስግስ፪

አዝ= = = = =

ዳግማዊ ልደትን ከጌታ ተማረ
ከምድራዊ እውቀት ሰማይ ተሻገረ
በምሽት ጨረቃ በመመላለሱ
ይበራለት ነበር ከፀሐይ ከራሱ፪
በመቅደስህ ቆሜ ስምህን ላሞግስ
መንገዴን አብራልኝ በሌሊት ልገስግስ፪

አዝ= = = = =    

ኒቆዲሞስ ልሁን ሌሊት የማይፈራ
ሠላሳና ስልሳ መቶ የሚያፈራ
እንቅልፍ አርቅልኝ በጽናት ልበርታ
እግሮቼን ታቅናልኝ ትእዛዝህ አብርታ፪
በመቅደስህ ቆሜ ስምህን ላሞግስ
መንገዴን አብራልኝ በሌሊት ልገስግስ፪

 
አዝ= = = = =      

ጎጆዬ ሲጨልም ሰማይ ሲደፋብኝ
ውስጤ ብርሀን ሲያጣ ተስፋ ሲርቅብኝ
በልቤ ላይ ውረድ በብሩህ ደመና
ጨለማው ያላንተ አይገፋምና፪
በመቅደስህ ቆሜ ስምህን ላሞግስ
መንገዴን አብራልኝ በሌሊት ልገስግስ፪


ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
  @maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✥ በእምባዬ የማመልክህ ✥



በእንባዬ የማመልክህ ጌታዬ
ከክፋ ቀን መወጫ አንባዬ
ኀዘኔን በደስታ ለውጠው
አንተን በመታመን ልለፈው

በእናቴ ማህፀን እያለሁኝ ገና
የተደገፍኩብህ አምላኬ ነህና
አውጣኝ ከመከራ እያልኩኝ ቀን ሌሊት
ምንጣፌን ዘወትር በአንባዬ አራስኩት

አዝ= = = = =
የምትታመነው ሁልጊዜ ምትጠራው
እያሉ ሲወቅሱኝ አምላክህ ወዴት ነው
ለአፌ ምግብ ሆነኝ የማነባው እንባ
እባክህ አምላኬ ወደ 'ረፍቴ ልግባ

አዝ= = = = =
እስክትጎበኘኝ ከሰማዩ መቅደስ
ማዳንህን እስካይ እንባዬ እስኪታበስ
ሳታቋርጥ እንባን ታፈሳለች ዐይኔ
እንደቀድሞ ይሁን ይታደስ ዘመኔ

አዝ= = = = =
ከአንደበቴ ጠፍቷል የጽዮን ዝማሬ
በባቢሎን ምርኮ ሳለው አቀርቅሬ
በዚያ የማረኩን ፈስን እንድንዘምር
እንዴት ይቻለናል በባዕዳን ምድር


መዝሙር
ዘማሪ አቤል መክብብ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
     @maedot_ze_orthodox
    ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✟በውስጥ ሰውነቴ✟

እኔ ምነኛ ጎስቃላ  ሰው ነኝ.... በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን። እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ህግ በስጋዬ ግን ለሀጢያት ህግ እገዛለሁ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 7÷24-25


በውስጥ ሰውነቴ በትዛዝህ ደስ ይለኛል
በስጋዬ በኩል ሀጥያትም ይስበኛል
ምነኛ ጎስቋላ ደካማ ነው ሰውነቴ
ማን ይታደገዋል ያድነዋል ይህ ህይወቴ


መልካሙን ለማድረግ አስብና እነሳለሁ
ክፉን በሚያሰራ በሌላ ህግ እያዛለሁ
በውስጥ ሰውነቴ ለትዛዝህ ተገዝቼ
በስጋ እደክማለሁ ቃልህንም እረስቼ

አዝ____

ያነበብኩትና የሰማሁት ቅዱስ ቃልህ
የቀመስኩትና ያጣጣምኩት ይህ ፍቅርህ
በዚህ መኖር ለኔ መልካም ነውም ያሰኘኛል
ብዙም ሳልቆይ ፈጥኖ ስምህንም ያስክደኛል

አዝ____

ፍቅርህን አስቤ ሁሉን ንቄ ሁሉን ትቼ
በውሀ ላይ ልሄድ ለመራመድ ተነስቼ
ካንተ ጋራ ሳልደርስ በፍጥነትም እሰጥማለሁ
መጥፋቴ ነው ጌታ አንተ አድነኝ እልሃለሁ

አዝ____

አምላክ ሆይ እባክህ ፍጻሜዬን አሳምረው
የሚያድነኝ ቸርነትህና ምህረትህ ነው
ስለእማአምላክ ብለህ ድል መንሳትን አድለኝ
ለምኞቴ እና ለፈቃዴ አትስጠኝ


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 25 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከነ የምስክር ወረቀቱ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 25 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከነ የምስክር ወረቀቱ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


#ዘጠኝ_ሰዓት_ሲሆን

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ
በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ
ድምጽህን በማሰማት አባት ሆይ
ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ

ከዋክብተ ሰማይ በሙሉ ረገፉ
ጨረቃና ፀሐይ ደምን አጎረፉ
ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ
ሥጋህን በመስቀል ተገልጦ ስላዩ
#አዝ
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ
ማርና ወተትን ለሚመግበው
ሐሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው
#አዝ
አካሉ ሲወጋ ውኃ ደም ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ
የእሥራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክም
#አዝ
እናትህ ስታለቅስ በመስቃል ሥር ሆና
ዮሐንስን ሰጠህ ጠብቆ እንዲያፅናና
መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ

ሊቀ-መዘምራን
ኪነ-ጥበብ ወልደ-ቂርቆስ


ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ

➮ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ጌታየ ሆነ ደም ግባት አልባ፤
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገርፍ እረሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/፣


በሀሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ፣
ጌታ ተያዘ ህይወቴን ፈቅዶ፣
ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ፣
ለኔ ግን ሆኗል መዉጫ መንገዴ/2/፣


ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣
ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣


ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ፣
ጅርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/፣


ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ፣
የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ፣
በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ፣
እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ/2/፣


ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣
ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ ፣


ጌታዬ ሆነ ድም ግባት አልባ፣
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔደማ፣
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/


ህይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑን
ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ፣
እጅ እግሩን ምስማር ሲቸነክርዉ
የሞትን እሾህ ከኔ ነቀለዉ/2/፣


ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣
ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣


ጌታዬሆነ ደም ግባት አልባ፣
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገረፍ አርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ አርሱ ተገፎ/2/፣


እርቃኑን ሆኖ ፈተነዉ ልብሴን፣
አንዲሁ ወዶኝ ጠጣ ቆምጣጤ፣
በምህረቱ ጥል ነብሴን አርክቶ፣
አለመለመኝ አርሱ ተጠምቶ/2/፣

ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ ፣
ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 25 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከነ የምስክር ወረቀቱ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓

20 last posts shown.