"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ድንግል ሆይ
በድካሜ ጊዜ ኀይል አደረኩሽ
የኤፍራታ ርግብ ማርያም ሆይ ነፍሴ ብቻዋን እንዳትኖር ከሕይወትሽ ጋራ አንድ አድርጊኝ። የሰላምና የፍቅር ንግሥት ድንግል ማርያም ሆይ ለክብርሽ ምስጋናን አነሣለሁ፤ ለስምሽ ምስጋናን በማቀርብበት ጊዜ ከበሮን አነሣለሁ። የሽቱ ሙዳይ ድንግል ማርያም ሆይ በውዳሴ ቃል አመሰግንሽ ዘንድ የአንደበቴን አልጫነት በጨው አጣፍጪ። የነዳያንን ልመና የምትሰሚ ማርያም ሆይ ጠላት በእኔ ላይ እንዳይበረታ ሰይፍሽን አንሺ።
ከሽቱ ይልቅ የምትሸቺ አበባ ማርያም ሆይ አንበሳ አራዊትን ሁሉ እንደሚያሸንፍ ያንቺም ጽድቅ የእኔን አበሳ ያሸንፈው።
ለእግዚአብሔር እናት የሆንሽ ማርያም ሆይ የተጠማች ምድር ዝናምን ተስፋ እንደምታደርግ በፊትሽ ቆሜ ምሕረትሽን ተስፋ አድርጋለሁ።
የሕይወት ፍሬ ክርስቶስን የተሸከምሽ ማርያም ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ወልደሽልናልና፤ በምደኸይበት ጊዜ ብልፅግናን፤ በድካሜ ጊዜ ኀይል አደረኩሽ። የጉባኤ መመኪያ ድንግል ማርያም ሆይ በውድቀቴ ጊዜ ረዳት ባጣሁ ጊዜ ባንቺ ቃል ትንሣኤን ተስፋ አደርጋለሁ።
ሙሴ በደብረ ሲና ያየሽ የማስተዋልና የጥበብ ዕፅ አንቺ ነሽ በቅድስና ፈጽሞ የተጐናጸፍሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ ጥፋትን እንዳላይ ብርሃናዊ መጽሐፍንና የተሰወረ መናን ስጪኝ።
ሕያውና ማኅያዊ የሚሆን ጌታ ካንቺ የተወለደ የሰማያዊ ንጉሥ እርሻ አንቺ ነሽ፤ የሌዊና የይሁዳ ልጅ ድንግል ማርያም ሆይ በምልጃሽ የችግርን በር ዝጊ የምሕረትሽንም በር ክፈቺ።
የመላእክት ተድላ ደስታቸው የጌታ እናት ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ፈጽሞ የተመሰገንሽ ማርያም ሆይ ከምርጦችሽ አትለይኝ ንግሥት ሆይ በሕይወቴም በሞቴም አትተይኝ (አትለይኝ)። ፈቃድን የምትፈጽሚ ድንግል ማርያም ሆይ የስምሽ መታሰቢያ ለሕሙማን ፈውስን ለተራቆቱት ልብስን ሰጣቸው።
ድንግል ሆይ ልዕልናሽ በመናገርም በመተርጐምም ሊነገር አይቻልም፤ የእግዚአብሔር ማደሪያው የሆንሽ ማርያም ሆይ የዓለምን ፍቅር እንዳልከተል ከዕውቀትሽ ዕውቀትን አድይኝ።
ከረጅም ተራራ የሰው እጅ ሳይነካው የተፈነቀለው ይህ ድንጋይ አንድ ልጅሽ ነው፤ ማለሟልነትሽ የበዛ ድንግል ማርያም ሆይ ከቀዳማዊና ከደኀራዊ ትውልድ ሁሉ ለስምሽ አጠራር ስግደት ይገባል።
የአባቶቻችን የቅዱሳን የጸናች የቀናች ሃይማኖታቸው እመቤታችን ሆይ የሕይወት አጽቅ አንቺ ነሽ፤ በዘመናችን ነፍሳችን ምስጋናን ይዛ ለልደትሽ ቊርባንን ታገባለች (ታቀርባለች)።
የታላቅ ብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ ይኸውም ለዐይን የሚታይ ቃል ነው፤ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋቸው የሆንሽ ድንግል ማርያም ሆይ ባርኪኝ፤ እንደ ለብሐዊ ምእመን (ቅዱስ ፍሬም) ከወይን ይልቅ በሚያስደስቱ ከናፍሮችሽ ባርኪኝ።
ጭንቅን የምታቃልዪ ድንግል ማርያም ሆይ በየዋሕነትሽ በርግብ ተመሰልሽ፤ በንጽሕናሽም ጥበበኛ ድንግል ተባልሽ።
እናትነትን ከአገልጋይነት አስተባብረሽ የያዝሽ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በእቅፍሽ የያዝሽውን ጌታ መላእክት ያመሰገኑታል፤ ንጽሕትና የተባረክሽ ማርያም ሆይ በንጉሥ ቀኝ የምትቆሚ ንግሥት ሆይ ስላንቺ ዳዊት ዘመረ እኔም እዘምርልሻለሁ።
(መልክአ ውዳሴ)


#ድንግል_ሆይ_ዝም_አትበይ🙏🙏😢😢
ጨለማችን ጨልሟል ውስጣችን ቃል በሌለው ኃዘን ውስጥ ወድቋል ። አሰገራሚው መድኃኒት በውስጥሸ የተገኘ ፡ ምድርን የሸፈነ ፀሐይ የተገለጠብሽ የዳዊት ልጅ እናታችን ማርያም ሆይ ዝም አትበይ በእውነት ዝም አትበይ ። ትላንት ልመናሽ እንደጋረደን ዛሬም ቃል ኪዳንሽ ጥላ ይሁነን ።
ድንግል ሆይ....የመጣብንን እሳት ፡ከፊታችን
የቆመውን ደንቃራ በቃህ እንዲለው በልጅሽ ፈት ቁሚልን ።
እናታችን ሆይ ...አለማችን የዶኪማስን ቤት ሆኗል ፡ ሠርጉ ወደ ሙሾ ጠጁም ወደ መርዝነት ተቀይሯልና ....እንደ ልማድሽ ልጄ ሆይ በይልን ።
ከቀኝ ከግራ የሌለው የቃል ኪዳን ሕዝብሽን ሞት እንዳይበላው መድኃኒት ተብሎ ከተጠራው ልጅሽ ለምኚልን ። አንቺ በሥላሴ ፊት ሞገስ ያለሽ ሙሽራ ማርያም ሆይ ሠዓሊ ለነ እያልን በፊትሽ የመረረ እንባችንን እናፈሳላን ። ሚረዳን የልጅሽ እጅ ሚፈውሰንም እርሱ ብቻ ነውና ዝም አትበይ ።
ኢየሩሳሌምን ስለ ዳዊት የጋረድካት ጌታ ሆይ ስለ እናትህ ብለህ የሚሮጠውን መልአከ ሞት ያዘው።
ደምህ ይጋርደን ኃጢዓታችንን አታስብብን🙏🙏

734 0 10 5 33

Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
🌷መልክአ ቅዱስ ራጉኤል📗

አቤቱ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል አምላክ ሆይ ! እኔን ባሪያህን .ወለተ ሥላሴ...ይልቁን ሙሉ ህዝበ ክርስቲያንን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ዘወትር በየጊዜውና በየሰአቱ አድነን ጠብቀንም ለዘለዓለሙ አሜን።


Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
🌷መልክአ ቅድስት ልደታ ለማርያም📗

እመቤቴ ማርያም ሆይ እኔ ኃጢዓተኛ ልጅሽን ወለተ ሥላሴን ለመንግሥተ ሰማያት እንድታበቂኝ በዚህ ዓለምም ከክፉ ነገር ኹሉ እንድትሰውሪኝ ዕለተ ልደትሽ ተስፋና አለኝታ አድርጌ እማፀንሻለሁና በፊት በኋላዬ ከእኔ ሳትለዪ ጠብቂኝ ዛሬም ነገም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።🤲


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ የካቲት ፩/1

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊




አንቺን የያዘ ሰዉ ምን ይጎልበታል በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል።

🌷እመብርሃን ትጠብቃችሁ🌹🤲


እግዚአብሔር ይመስገን
እንሆ ወርኅ ጥር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈፀመ!ወርኅ የካቲትን የተባረከ መልካም ፍሬ የምናፈራበት ወደ ንስሃ የምንቀርብበት ያድረግልን!ሰይጣይ ከሸመቀው እኛ ከማናውቀው እግዚአብሔር ከሚያውቀው ክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን ይጠብቀን አሜን 🤲🌸


ነገ የካቲት 1 እናታችን እመቤታችን  ቅድስት ልደታ ለማርያም ናት። ድንግል አዛኚቱ ወልልዲተ አምላክ እናታችን ወቶ ከመቅረት ከክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን።🙏❤


Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
✝️🌹ልደታ ለማርያም እናቴ አለው ትበለን❤

💫የልዑል ማደሪያ እናቱ ለጌታ
💫የጸሎት መዝገብ ነሽ የወንጌል አንድምታ
❤የአባ ጽጌ ድንግል የደስታ መዓዛ
❤የአባ ሕርያቆስ የቅዳሴው ለዛ
❤የአባ ጊዮርጊስ የምስጋናው ደብተር
❤የኤፍሬም ውዳሴ የቅዱሳን ክብር
❤አንቺ ነሽ ማርያም የማሕተብ ፍቅር💖

🌸እናታችን ምልጃዋ አይለየን አሜን🌹🙏


Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
📒#ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት †††🌹

†††••ወር በገባ በ1 የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ራጉኤል ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡፡ጸሎቱ በረከቱ ለዘአለሙ ይደርብንና ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ራጉኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡

☞በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀራንዮ በሚባል ቦታ በሰቀሉት ጊዜ
☞ለንጊኖስ የተባለ አንድ ጭፍራ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሣለ ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፡፡

☞በዚያም ጊዜ መልአኩ ዑራኤል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደሙን
ይቀዳ ዘንድ በእጁ የብርሃን ጽዋ ይዞ ቀረበ፡፡
☞እንደዚሁ መልአኩ ዑራኤል የክርስቶስን ደም በሚቀዳበት ጊዜ ለአይሁድ
አልተገለጸላቸውም ነበር ይህም የመላእክት አለቃ ዑራኤል የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስን ደም በምድር ላይ ከጽንፍ ረጨው፡፡
☞በዚያን ጊዜም በመላአከ ብርሃናት ራጉኤል እጅ ፀሀይ ጨለመ ጨረቃም ደም
መሰለ ከዋክብትም ረገፋ እሱ ራጉኤል መልአክ በፀሐይና በጨረቃ በከዋክብትና
በሌሎችም ብርሃናት ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጥቶታልና፡፡
☞ከብርሃናት አለቃ ከራጉኤል በቀር ፀሐይና ጨረቃን ከዋክብትንም
የሚያዠዛቸዉም የለም፡፡ ፀሐይን በጠፈረ ሰማይ ላይ በቀን ያበራ ዘንድ
አሠለጠነው፡፡ ጨረቃንም ብርሃኑን በሊት ይሰጥ ዘንድ አሠለጠነው፡፡ከዋክብትም
እንዲሁ ለሰማይ የፈረጥ ጌት ናቸው፡፡
☞ዳግመኛም መልአከ ብርሃናት ራጉኤል በከዋክብት ላይ ሰባት አለቆችን ሾመ፡፡
☞የኒህ የብርሃናት አለቆች የመላእክት ሰማቸው ነቢዮ፤ኢሳይያስ እንደስማቸው
ሸረህ መሽተሪህ አጣርድ ዝኁራ፤ዙኃል፤ቀመር ይባላል፡፡
☞እነዚህ የከዋክብት አለቆች ታዛዥነታቸው ለመላእክት አለቃ ለራጉኤል ነው፡፡
እሱ በብርሃናት ሁሉ ላይ የሠለጠኀ ነውና፡፡
☞ልመናው አማላጅነቱ ለሁላችን ይደረግልን፡፡
☞የጽሑፍ ምንጭ (ድርሳነ ራጉኤል)
☞ቅዱስ ራጉኤል ህይወት ለጨለማችሁ ሁሉ ብርሃን ይሆናችሁ፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc




Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
††† እንኳን ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ዼጥሮስ እና ለ150ው ቅዱሳን ሊቃውንት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት †††

††† የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ነው::

ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት (የሰማዕታት መጨረሻ)" በሚለው ስሙ ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ዼጥሮስ ወዻውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ዼጥሮስ" አለችው::

ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ዻዻሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ዼጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::

ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::

አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ዽዽስናው ላይ አልተቀመጠም:: በሁዋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::

ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ዼጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ:: ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::

††† የቅዱሳንን ዝክር ከማንበብ ባለፈ በስማቸው መጸለይ (ዘፀ. 32:13): በምጽዋትም ማሰብ (ማቴ. 10:41) ይገባል::

††† ወርኀ የካቲትን ይባርክልን!

††† የካቲት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."150"ቅዱሳን ሊቃውንት ዻዻሳት (በቁስጥንጥንያ ተሠብሥበው መናፍቃንን ያወገዙበት: ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ያፀኑበት /ጉባዔ ቁስጥንጥንያ/ በ381 ዓ/ም::
ከወቅቱ ቅዱሳን ሊቃውንት እነዚህ ይጠቀሳሉ:-
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ
*ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት
*ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም)
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
3.ታላቁ ቴዎዶስዮስ ጻድቅ (ንጉሠ ቁስጥንጥንያ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም እግዝእትነ
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
5.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቁዋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" †††
(ሐዋ. 20:28)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††




አንድ ቀን!
ዛሬ በጠዋት ወደ ስራ እየገባሁኝ መስሪያ ቤቴ አካባቢ ስደርስ ሁለት ሶስት የሚሆኑ ሰዎች ተደናግጠው ቆመው አየሁ ምን ይሆን ብየ እኔም ስጠጋቸው ፖሊሶችም ሲመጡ ተመለከትኩኝ።
ይሄን ነገር ማወቅ አለብኝ አልኩና ጠጋ ስል አንድ ከ40 -50 አመት እድሜ የሚሆን ሰው ቁጭ ባለበት ከዚህ አለም በሞ ት ተለይቷል። ይሄ ምን ይገርማል ቁጭ ሲል እያዩት ነው የሞ ተው። ተመልከቱ ሁሉ ነገር አንድ ቀን ላይ ይቆማል።
ስኬታችን አንድ ቀን ላይ ግቡን ይመታል
ማጣት አንድ ቀን ላይ ይፈትነናል
ጥጋብም አንድ ቀን ይፈትነናል
ሁሉም ምድር ላይ ያሉ ነገሮች አንድ ቀን ነው ፍፃሜያቸው። ስለዚህ ከመናከስ ከመጠላላት ከመረጋገም ከመሰዳደብ እንውጣ።በተቻለን መጠን የተሰጠንን እድሜ በፍቅርና በደግነት እንፈፅመው። ምክንያቱም አንድ ቀን ሁሉም ነገር ይፈፀማል። ሰላም ዋሉልኝ።

ለሟቹም ነፍሱን በገነት ያኑርልን።


ስትኖር ለብቻህ አትኑር
የሌሎችን ችግር በመፍታት ኑር
ገንዘብ ካለህ በገንዘብህ ደሃውን በመርዳት ኑር
ጉልበት ካለህ በጉልበትህ ደካመውን በመርዳት ኑር
እውቀት ካለህ እውቀትህን ሌላው በማካፈል ኑር
ሥልጣን ካለህ ለተበደሉት በመፍረድ ኑር
ቤት ካለህ ጎዳና ላይ ወድቆ የሚያድረውን ወንድምህን በማስጠጋት ኑር
ልብስ ካለህ ራቁቱን ላለው ወንድምህ በማልበስ ኑር
ምግብ ካለህ የሚበለው ላጣው ወንድምህ በማብላት ኑር
ገንዘብ ካለህ ለሌላው አካፍል የአንተ ገንዘብ ባንክ ተጨናንቆ ደሃ ሲቸገር
እግዚአብሔር ይታዘብሃል
ጠንካራ ጉልበት እያለህ ደካማውን ወንድምህን ሳትረዳ ስትቀር ጉልበት
የሰጠህ አምላክህ ይመለከትሃል ጠንካራው ጉልበትህ ደካማ ይሆናል አንተም
በጊዜህ አንሱኝ ጣሉኝ ትላለህ የአንተ ጠንካራ ጉልበት ደካማውን ለማሸነፍ
አይደለም የተፈጠረው ደሃውን ለመርዳት ነው እንጂ
እውቀትህ ሌላ ካላስተማርክበት እውቀቱን የሰጠህ ፈጣሪህ እውቀትህን
እንደሚነሳህ አስብ እውቀት ችግር መፍቻ ነው እንጂ ችግር ማምጫ አይደለም
እውቀት ወደብርሃን የሚመራ እንጂ ወደጨለማ የሚወስድ አይደለም የአንተ
እውቀት የዶክትሪት የማስትሪት የድግሪ የዲፕሎማ የመጽሐፍ የቅኔ የድጓ
የአቋቋም የዝማሬ የቅዳሴ እውቀትህ ላላወቁት ለማሳወቅ እንጂ ለመወደስ
ለመከበር ለመፈራት አይደለም
በስልጣንህ የምታዳላ ከሆነ ሰማያዊ ስልጣን ባለው
ፊት ተከሰህ ስትቀርብ መልስ ታጣለህ ስልጣንህ ለተበደለ ፈራጂ ለተቀማ
አስመላሽ የድኀ እንባ አባሽ መሆን አለበት ዛሬ ሰዎች ተከሰው ወደአንተ ፊት
እንደቀረቡ ሁሉ አንተም ተከሰህ በፈጣሪህ ፊት ትቀርባለህና
ልብስህ ቁም ሳጥን ሞልቶ ሻንጣ አጨናንቆ አንተ በሰላሳ ቀን ሰላሳ ልብስ
እየቀየርህ እንዳንተ ገላ ያለው ሰው ራቁቱን ሁኖ ብርድና ሙቀት ሲፈራረቅበት
የማታለብሰው ከሆነ ሰማይን በደመና የሚያለብሰው ምድርን በእሳር የሚሸፍነው
አምላክህ ያዝንብሃል
አንተ ምን ልብላ ብለህ አማርጠህ ትበላለህ በቀን አራት አምስት ጊዜ
ትበላለህ እንዳንተ ምግብ የሚፈልገው ወንድምህ የሚበለው አጥቶ ሲራብ
ትተኸው ስትበላ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብህ አምላክ
የሰጠህን ምግብ ይነሰሃል ታመህ ያየሀውን ሁሉ እንዳትበላ ያደርግሃል
ስትቆርጠው የነበረው ጮማ ስትጎነጨው የነበረው ውስኪ ሁሉ ይቀራል
ገንዘብህ በባንክ እየደለበ ሌላውን ካረዳህበት ስትሞት አብሮህ አይቀበርም
ወደመቃብር ስትወርድ በአንድ ነጭ ነጠላ ተጠቅልለህ ነው ሀብትህ ሁሉ
አይከተልህም እግዚአብሔር ሀብት የሰጠህ አንተ ለዳሀው ሰጥተህ እንድትጸድቅ
ዳሀው ተቀብሎ እግዚአብሔርን እንዲአመሰግን ነው
ሰው ሆይ በትክክለኛው መንገድ ኑር
ለኳስ ሁለት ሰአት ጊዜ ሰጥተህ ለቅዳሴ አንድ ሰአት አልሰጠህም
ለፊልም ረጅም ጊዜ ሰጥተህ ለወንጌል አጭር ጊዜ አጥተሃል
ለኳስ ጨዋታ ተወራርደህ ብር ትሰጣለህ ለቤተ ክርስቲያን ማሰሪያ እጅህ
ይታሰራል
ለፊልም እስፖንሰር ትሆናለህ ለወንጌል ግን አምስት ሳንቲም ለማውጣት
ትቆረቆራለህ
የፊል አክተሮችን አንድ በአንድ ታውቃቸዋለህ የኳስ ኮከቦችን በደረጃ
ትጠራቸዋለህ
ወንጌሉን የጻፉት አነማናቸው ስትባል መልስ ታጣለህ
ሰው ሆይ አንተ ለዘለዓለም በምድር አትኖርም በሰማይ ለመኖር የተፈጠርህ ነህ
ወደምድር ያወረደህ የአባትህ የአዳም የናትህ የሄዋን ኀጢአት ነው እንጂ ሀገርህ
በሰማይ ነው ለተወሰነ ጊዜ በምድር ትቆያለህ ሇላ ከምድር ወደላይ ትወሰዳለህ
በሰማይ በበጎ ቦታ ለመኖር በምድር ሳለህ መልካም ስራ ስራ ከጎንህ
የምታውቀው ሰው ሲሞት ከማልቀስ ባሿገር ነገ አንተ እነደምትሞት ተማርበት
ጎረቤትህ ዛሬ ሲሞት ነገ ተረው የአንተ መሆኑን አትርሳ
ዓለም ጨለማ ናት ወደጨለማ ሳትወስድህ ወደብርሃን ተጉዘህ ቅደማት
የምታልፈው ዓለም እድሜህን በከንቱ ሳትጨርስብህ ማለፏን አውቀህ ቅደማት
ዓለም የዛሬ ናት ዛሬ አስደስታ ነገ ታስለቅስሃለች
ዛሬ አሳይታ ነገ ታሳጣሀለች
ዛሬ አጥግባ ነገ ታስርብሐለች
ዛሬ ሹማ ነገ ትሽርሃለች
ዛሬ አክብራ ነገ ታዋርድሃለች
ዛሬ አሳምራ ነገ ታጠቁርሐለች
ዛሬ አድንቃ ነገ ትንቅሃለች
ዛሬ አጨብጭባለህ ነገ ድንጋይ ትወረውርብሐለች
ዛሬ ከፍ ከፍ አድርጋ ነገ ዝቅ ዝቅ ታረግሃለች
ለአንተ አባቶች አልሆነችም መቃብር ከታቸዋለች ከቀደሙት አባቶችህ ተማር የምታውቃቸው ካንተ ቀድመው የነበሩ ዝነኞች ባለ ሀብቶች አርቲስቶች
የሃይማኖት አባቶች ባለ ስልጣናት ሁሉ መቃብር ውስጥ እንደሆኑ ተረዳ
ስማቸው ከመቃብር በላይ ቀርቷል መልካም የሰሩት በመልካም ስም ክፉ የሰሩት በክፉ ስም ይታወሳሉ
ሰው ሆይ ለሰው ችግር ሳትሆን ሰውን በመርዳት ኑር።

መልካም ቀን✝


እለተ አርብ የፍቅር ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ብሎ መስቀል ላይ የዋለበት ቀን ነው እንኳን አደረሳችሁ ።የዓለም መድኃኒት ጌታዬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በቀራንዮ በተሰቀልክበት መስቀል እማጸንሃለው። ከመስቀሉ ስር ተደፍታ በምታነባው እናትህ እለምንሃለሁ ከኃጢዓቴ አንፃኝ መተላለፌን አትቁጠርብኝ በእምነት በምግባር አፅናኝ አቤቱ ማረኝ! ምህረትህ ቸርነትህ አይለየን አሜን በእውነት ።🤲🥰✝


🌷መልክአ መጥምቀ ዮሐንስ✝

ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ሰላም እልሃለሀ/፫/

በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዩሐንስ አለው ይበላችሁ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይሰዉራችሁ።

🥰🙏🥰


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥር ፴/30

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊



20 last posts shown.