📚👳‍♂🌼ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት🌼👳‍♂📚


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን የህይወት ቃል ጌታ እግዚአብሔር በገለጠልን ፀጋ መጠን የምንካፈልበት ሲሆን!
" ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤"ቲቶ ፩÷፲፩
📢ለማስታወቂ ሥራ @Mane_tekel

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter




Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
ኅዳር 12

~ ለውጦ ማክበር ~

ንግሥት ክሌዎፓትራ "ሳተርን" ለሚባል ጣዖት ያሠራችው ቤት በእስክንድርያ ነበር። ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እለ እስክንድሮስ ፓትርያርክ ዘመን 212-326 ድረስ ነበር። እለእስክንድሮስም ሊያጠፋ ሲነሣ በሕዝቡ ልቡና ገና አምልኮ ጣዖት ስላልጠፋላቸው 18 ፓትርያሪኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት። እለእስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት የነበረበትን ዕለት ወደ ቅዱስ ሚካኤል የበዓል ዕለት አደረገው። (ስንክ ሳር ኅዳር 12፣ Coptic Encyclopedia, Vi S.p 1617)።

ከእምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የእስክንድርያ ሰዎች በእለ እስክንድሮስ በኩል እየበረሩ ገቡ። የጣዖት መክበሪያ የነበረው በእለ እስክንድሮስ ጸሎት የቅዱስ ሚካኤል መክበሪያ የእግዚአብሔር መመስገኛ ኾነ። ይህን ቤተ ጣዖት ሳስብ ምናልባት በኃጢአታችን ምክንያት የእኛን ሰውነት የሚወክል ይኾን እላለሁ። ብዙዎቻችን የእግዚአብሔር መቅደስ የኾነውን ሰውነታችንን የአጋንንት መርኪያ ቤተ ዘፈን አድርገነዋልና።

የሰው ልቡና የእግዚአብሔር ቤተ መንግሥት ነው። ኾኖም ሰዎች ሰውነታቸውን እያረከሱና ከእግዚአብሔር ፍቅር እየራቁ ሲሄዱ የአጋንንት መኖሪያ ሊያደርጉት ይችላሉ። በመኾኑም የሕይወታችን ዋና ጉዳይ መኾን ያለበት መቅደስ ሰውነታችንን መጠበቅ ነው። በእለእስክንድሮስ አምሳል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ካህናትን በቅዱስ መስቀል ባርከው እንዲያነጹን መቅረብ ነው። ዝሙት የተባለ ጣዖት በልቡናችን ውስጥ የያዘውን ቦታ በካህናት ፊት ተናዘን እንድንነጻ የሚያደርገውን የንስሐን ቀኖና መቀበል ነው። ሕይወታችንን እያዛጉ ያሉትን ማናቸውንም ባዕድ የኾኑ ነገሮች በልቡናችን ውስጥ ሥር እንዳይዙ መጠንቀቅ ነው።

በእርጥም እኛ ፈቃዳችንን ለእለእስክንድሮሳዊ ፈቃድ ካስገዛን ሰውነታችን የቅዱሳን መላእክት በዓል መክበሪያ ወደ መኾን ይታደሳል። ቅዳሴ፣ ማኅሌትና ልዩ አገልግሎት ያለማቋረጥ የሚቀርብበት ንጹሕ መቅደስ ይኾናል። እንግዲያውስ ኹላችንም በሰውነታችን ውስጥ ቅዱስ ሚካኤልን እንፈልገው፤ በበዓልነት በእኛ ውስጥ እንዲከብር እንፍቀድ። ሰዎች የቅዱስ ሚካኤልን ያማረ የምልጃ ሽታ በእኛ ሰውነት ውስጥ እንዲያሸቱት እናድርግ! ወደ ቅዱስ ሚካኤላዊ የአገልግሎት ሕይወት ለመግባት እንመኝ፤ ደጋግመንም እንሻ!

( "ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው" fb የተወሰደ ።)

እንኳን አደረሳችሁ!!


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


Forward from: መንፈሳዊ የአባቶች ትምህርትና ዝማሬዎች
|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251960030506 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
ጾም በእግዚአብሔር ታዟል፤ተፈቅዷልም ።
++++++++++++++++++++++++++
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾምን እንድንጾም ባርኮ የሰጠን እሱ ነው ።ለዚህም ማረጋገጫ ፦
"ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።"
ማቴ 9:15
በዚህ መሰረት ፦
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ የጾም ህግና ስርዓት አላት ።
"ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን ።"እንዲል
1ኛ ቆሮ 14፥40
በቤተክርስቲያናችን ህግና ሥርዓት ተሰርቶላቸው
ከሚጾሙ 7 የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ነብያት ይባላል ።የጾሙ ጊዜ ከህዳር 15-እስከ ጌታ ልደት ታህሳስ 28 ድረስ ያለው ነው ።ይህን ጾም የምንጾመው ነቢያት በየዘመናቸው ስለክርስቶስ መምጣት ንጽህት ከምትሆን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን በናፍቆት ይጾሙና ይጸልዩ ስለነበር የእነርሱን አርአያ ተከትለን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ከማክበራችን ቀደም ብለን ይህን ጾም እንድንጾም በሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ሥርዓት ተሰርቷል። (ፍት.መ.ን.አንቀጽ 15)
ስለሆነም እኛም ክርስቲያኖች ይህን ተከትለን ብልቶቻችንን ሁሉ(አይን ይጹም ፤እጅ ይጹም፤ እግር ይጹም ፤አንደበት ይጹመ...እንዳለ ቅዱስ ያሬድ) ከኃጢአት ጠብቀን፤እግዚአብሔርን ከማያስደስቱ ማናቸውም ነገሮች ራሳችንን አርቀንና ፤በወንድሞቻችን በማናቸውም ላይ ቂም በቀልን በማስወገድ ይቅርም በመባባል ፤ጸሎትን ስግደትን ምጽዋትንም በመጨመር በንጹህ ልቦና መጾም ይገባናል።ይህን ካደረግን ዘወትር የሚዋጉንና የሚፈታተኑን የአጋንንት ሰራዊት በሙሉ ይደመሰሳሉ፤ኃይላቸውም ይደክማል ።ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ፍቅርን ሰላምና በረከትንም እንቀበላለን ።
"የጌታ ቃል የታመነ ነውና።"ቲቶ 3:8
".....ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
ማቴ 17:21

#ድምፀ_ተዋህዶ

        📹📹📹📹
   ✨ፊላታዎስ ሚዲያ✨
               👇👇
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
በሶሪያ ኦርቶዶክስ  ያዕቆባዊት ቤተክርስቲያን የሕንድ ሜትሮፖሊታን የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሞር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ

  ብፁዕ አቡነ ሞር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ እ.ኤ.አ ሐምሌ 22 ቀን 1929 ዓ.ም ቡቸንክሩዝ በተባለ የሕንድ ግዛት የተወለዱ ሲሆን እ.ኤ.አ ከሐምሌ 26 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የምትተዳደረውን የሕንድ ቤተ ክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በሊቀ ጵጵስና መርተዋል።

ብፁዕነታቸው በዕድሜና በሕመም ምክንያት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዕረፍት በማድረግ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት አመሻሽ ላይ በሕንድ ኮቺ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሞር አግናጢዮስ ኤፍሬም ዳግማዊ፣ ለሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ለመላው የቤተ ክርስቲያን አባላት፣ ቀሳውስትና ምእመናን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። 

የብፁዕነታቸው በረከት አይለየን !!!

© ተሚማ

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
መምህራችን መምህር ኤርሚያስ ታሟል።
አንድ ሰላም ለኪ ድገሙለት እግዚአብሔር በጤና ይመልሰው።

ሰላም ለኪ
ሰላም ለኪ፤ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ ፤ ማርያም እምነ ናስተበቊዐኪ ፤ እምአርዌ ነዓዊ ተማሕፀነ ብኪ ፤ በእንተ ሐና እምኪ ፤ ወኢያቄም አቡኪ ፤ ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ ።

ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ : -
ታዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ፤ ወትትሐሠይ መንፈስየ ፤ በአምላኪየ ወመድኃኒየ ፤ እስመ ርእየ ሕማማ ለአመቱ ፤ ናሁ እምይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኵሉ ትውልድ ፤ እስመ ገብረ ሊተ : ኃይለ ዐቢያተ ፤ ወቅዱስ ስሙ ፤ ወሣህሉኒ : ለትውልደ ትውልድ ፤ ለእለ ይፈርህዎ ፤ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ ፤ ወዘረዎሙ ለእለ የዐብዩ ኅሊና ልቦሙ ፤ ወነሠቶሙ ለኃያላን እመናብርቲሆሙ ፤ አዕበዮሙ ለትሑታን ፤ ወአጽገቦሙ እምበረከቱ ለርኁባን ፤  ወፈነዎሙ ዕራቆሙ ለብዑላን ፤ ወተወክፎ ለእስራኤል ቊልዔሁ ፤ ወተዘከረ ሣህሎ ፤ ዘይቤሎሙ ፤ ለአበዊነ : ለአብርሃም ፤ ወለዘርዑ እስከ ለዓለም ፤ አሜን ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግሥትከ። ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም። ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንህነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ። ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት። አላ አድኅነነ ወባልሓነ እምኲሉ እኩይ እስመ ዚኣከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።

በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ ድንግል በኅሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰለም ለኪ ቡርክት አንቲ እም አንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ ተፈስሒ ፍስሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ  እግዚአብሔር ምስሌኪ ሰአሊ ወጸልዪ  ምሕረተ ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
ምህረቱን ይላክሎት መምህር


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
የ ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ 3ኛ አመት የAccounting ተማሪ
የሆነችው እህታችን ሀይማኖት ደግፌ ባደረባት ህመም ምክንያት ትምህርቷን መከታተል አልቻለችም ህመሟም የጡንቻካንሰር አይነት ሲሆን በህክምና አጠራሩ Rhabdomiosarcoma ሲሆን ለዚህም በሰርጅሪ ህክምና ተድርጎላት አሁን የ chemotherapy ህክምና እየወሰደች ትገኛለች ቀጥሎም የ Radiotherapy ህክምና ያስፈልግታል ለዚህም ደግሞ የሚያስፈልገው ገንዘብ ሲሰላ ከ 100,000 ብር በላይ ድረስ ያስፈልጋታል ለዚህም እሷም ሆነ ቤታሰቦቹዋ የማሳከም አቅም ስለሌላቸው እናንተ
ወገኖቻችን ወገናዊ እጃችሁን እንድትዘረጉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
እባካችሁ እህታችንን በአቅማችን በመርዳት ወደ ቀድሞ ጤንነቷ ተመልሳ ትምህርቷን እንድትከታተል እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።


Haymanot Degife Bosen 1000191370922

በስልክም ማነጋገር ለምትፈልጉ 0986252118


"እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፡ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።" ሐዋ 20:35




Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደርሳቹ❗️

ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ 

አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰለምንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ

አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን


✝️#ድምፀ_ተዋህዶ ✝️


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን  ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።

#ድምፀ_ተዋህዶ


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
አዲስ መፅሐፍ ምረቃ

ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል የተሰኘውን መጽሐፍት ሊያስመርቁ ነው

ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም በቦሌ መድኃኔዓለም አዳራሽ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ

መጽሓፉ
ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ:
1•የእመቤታችንን  ሕይወት  የያዘ ሙሉ የነገረ ማርያም  አስትምህሮ
2•በነገረ ድኅነት ያላት ድርሻ
3•ዕርገቷን የሚመለከቱ
4•እመቤታችንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች
5•በእመቤታችን ፍቅር እንዴት መጽናትና ማደግ ይቻላል?

የሚሉትን ዓበይት ጉዳዮች የሚተነትን ነው

628 ገጾች
12 ምእራፎች አሉት
#ድምፀ_ተዋህዶ
https://t.me/dmtse_tewaedo


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
#እንኳን #ለፆመ_ጽጌ በሳላም አደረሳቹህ

✤ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው (ከሰዓትም ቅዳሴ የሚቀደሰስባቸው አካባቢዎች አሉ (ጎንደር )፡፡
በግዕዝ ጸገየ ማለት   አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡ 
በማኀሌቱም ወቅትን እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር እስከ ግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ  በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ  በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣  ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ  እያሰቡ  እና  ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡

✤እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት››
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ #ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) #ደሙ #አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡

#በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡

#ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡- ‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና›› ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ  በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡

የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን

#ማኅሌተ_ጽጌ
✤የማኅሌተ ጽጌ  የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው ፡፡
  ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡
✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤
      እጅጉን በምንወደው የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ላይ በየዓመቱ ሳይመረገዱ የማይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ
( ከማኅሌተ ጽጌ፤ ጽጌ አስተርአየ(የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብር ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡
✤ ከሰቈቃወ ድንግል፤ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡
✤ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡
✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት #የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን #በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡
( የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤
( የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት #ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን #ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም
የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ  ተጠቀሙ፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/

    #ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo




Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
ይህችን ቅደስት ቤተ ክርስቲያን ካሰባችሁላት ተዋት!

ለልጆቻችሁም ካሰባችሁ ተውን!

ይህ ሕዝብ በጦርነት ዜና፣ በኑሮ ውድነት በሌላም ብዙ ጭንቀት አለበት። እንደአባትነታችሁ ሰላምን ባትሰጡት እንኳ ሌላ ወከባ አትጨምሩበት።

እንደፖለቲከኛ የያዛችሁት ሽኩቻ ሰልችቶናል።

ተናግራችሁና ሠርታችሁ አርአያ መሆን ካልቻላችሁ ዝም በማለት አርአያ ሁኑን!

ይህ ምእመን ቤተ ክርስቲያን ላይ ለደረሰው ሁሉ ዝም ያላችሁ ከላይ እስከታች ስላላጠፋችሁ አልነበረም።

አሳልፈው የሰጡት አባቶች ከመካከል እንደነበሩ ጠፍቶትም አይደለም። ግን ስለማእተቡና ስለቀደሙት አባቶቹ የደም ሰማእትነት ሲል ብዙ እየተደረገ በብዙ ዝም አለ።

እናንተ የተቋም መሪዎቻችን እንጂ ሃይማኖታችን አይደላችሁምና መሠረቱን ክርስቶስን አስቦ ታገሰ!

እናንተ ግን ተጸፅታችሁ ወደ አንድ መጥታችሁ ከውጫዊ ጥቃት ልትጠብቁት ይቅርና እያደረ አዲስ የውስጥ ፈተና ትጠራላችሁ።

ሙስናው፣ መልካም አስተዳደር ችግርና ውጫዊ ፈተናችን ብዙ ነው አይካድም።

የእናንተ የአደባባይ ንተርክ ግን እውነት ለቤተ ክርስቲያን ለውጥ አስባችሁ ነው? ወይስ ለክብራችሁ? ወይስ ስልጣናችሁን ለማጽናት?

ራሳችሁን በጾም በጸሎት የወሰናችሁ ብፁዓን አባቶችስ እስከመቼ ጥግ ይዛችሁ ታያላችሁ? ጸሎት ከሁሉም የበለጠ ኃይል እንደሆነ ብናምንም ተስፋ እንዳንቆርጥ ተግሳጻችሁን እንመኛለን!

እናም ጽሑፉ የሚመለከታችሁ ብፁዓን አባቶች የአደባባይ መዘላለፉን ትታችሁ በውስጥ ተሟገቱ። የውጭ ፈተናችን ይበቃናል። እንደተከታታይ ድራማ እናንተን መከታተል ደክሞናል።

እንዳው በልጅነት የምጠይቃችሁ ድፍረት አይሁንብኝና ከቻላችሁ ወደ ገዳም ገብታችሁ አረፍ በሉ። የጥሞና ጊዜ ጥሩ ነው ብላችሁ አስተምራችሁን የለ?

እስኪ እኛም ካለእናንተ አይነት መሪዎች ቤቱ ምን እንደሚሆን እንየው!

(ከድፍረት ያልሆነ በመድከም የተጻፈ)

✍️ መስከረም

#ድምፀ_ተዋህዶ




Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
#እሬቻ_ላይ_የሚከብረው_እግዚአብሔር_አይደለም_ዲያብሎስ_ነዉ።

🔵 እሬቻ ከክርስትና እምነት ጋር ፈጽሞ ተጻራሪና ጸረ ነፍስ ነው። የእሬቻ የዛር መንፈስ እንጂ ከመንፈስ ቅዱስ አይደለም። ለእግዚአብሔር እንጂ ለዛፍ አትንበርከክ። ለሚያልፍ ፖለቲካ የማያልፍ እግዚአብሔርን አናስቀይም።

"በወደዳችኋት የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፥ " ኢሳይያስ 1፥29

🔵 እሬቻ ደብረ ዘይት [ቢሾፍቱ] ሆራ አርሰዲ ሓይቅ ዙርያ አርሰዲ የሚባለው መንፈስ እየተወደሰ አንዲት የአድባር ዛፍ ስር ይከበራል። ኢሬቻ የራሱ ካህናት አሉት።

🔵 ተከታዮቹም የሚገብሩት ራሱን የቻለ ግብር አለ። የአድባር ዛፏ ቅቤ ትቀባለች። ሐይቁ ውስጥ አለ ተብሎ ለሚገመተው ቆሪጥም የስለት አረቄ ይጣልለታል። ደስ እንዲለውም ከብት እየታረደለት ደም ይጠጣል። ሞራ ገላጮች "ትንቢት" ይናገራሉ። አማኞችም ተንበርክከው ተረፈ መስዋዕትን ይበላሉ።

🔵 ቪድዮውንና ፎቶውን ይመልከቱ። ቪድዮው ላይ ቁልጭ ብሎ እንደምትመለከቱት ኢሬቻ ሲደርስ አርሰዲ ለሚባለው መንፈስ የደም ግብር ይቀርብለታል። ደም ይጠጣል። የተረፈውን መስዋት ደግሞ ተከታዮቹ ይበሉታል። አርሰዲ የተባለው የኢሬቻ መንፈስ ደም ከጠጣ በኋላ - የኢሬቻ ካህን የሆኑት ወገኖች ላይ አድሮ ያስጓራቸዋል። መንፈሱ አርሰዲም "እኔ ሰው አይደለሁም። መንፈስ ነኝ። አልሞትም ወዘተ" እያለ ይፎክራል። የዛር ፈረስ በመባል የሚታወቁት ካህናቱም ለታመመ "ፈውስ" ይሰጣሉ።

🔵 እነዚህ የኢሬቻ ካህናት ኢሬቻ ሲከበር ሆራ አርሰዲ ያለችው የአድባር ዛፍ ስር እየተገናኙ ድቤ ይመታላቸዋል። ሆራ ቀውጢ ትሆናለች። ያቺ የአድባር ዛፍም ቅቤ ትቀባለች። በግምጃ ታጌጣለች። የሽቶ አይነት ይርከፈከፍላታል። ወዘተ . . . ማንም ሰው የፈለገውን ማምለክ ይችላል። መብቱ ነው። እጁን ወደሚያቃጥለው ወይም ወደ ቀዘቀዘው ውሃ የመክተት ነጻ ሕሊና አለው። መዘዙ ግን በኋላ ነው- የዛሬ ሳቅ የነገ ለቅሶ ስትሆን! ግን ኢሬቻ በሃይማኖት በተለይም በክርስትና አይን ሲታይ ምንድነው? ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ኢሬቻን ማክበር ይገባዋልን? መልሱን መፅሐፍ ቅዱስ በማያሻማ ሁኔታ እንዲህ ሲል ይነግረናል።

🔵 "በወደዳችኋት የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፥ " ኢሳይያስ 1፥29፤ እርግጥ ነው ኢሬቻ የምስጋና ቀን [thanksgiving] ነው። ግን የሚመሰገነውና የሚክብረው ማነው? አርሰዲ የሚባል ደም የሚጠጣ ክርስቲያናዊ አምላክ ወይም ቅዱስ መንፈስ የለም። የኢሬቻን ካህናት የሚያስጓራው ዛር ከክፉው እንጂ ከቅዱስ መንፈስ አይደለም። የክርስቶስም መገኛ ዛፍ ስር ወይም ሐይቅ ውስጥ አይደለም። የራሱ መመለኪያ ቦታ አለው።

🔵 ሳር የሚበተንለት፣ ስለት የሚገባለት፣ ከብት ታርዶ ደም የሚረጭለት፣ የሆራው ቆሪጥ ርኩስ መንፈስ እንጂ ቅዱስ መንፈስ አይደለም።  ዛፍ ምን ስለሆነ ነው ቅቤ የሚቀባው? እንዴት ክርስቲያን ራሱ ተክሎ ላበቀላት ዛፍ ይሰግዳል? እንዴትስ እንደ አምላክ እየታየ ቅቤ ይቀባል። ለምን ህዝብ ይንበረከካል ? ለምንስ ዛፍ ግምጃ ያለብሳል? እኛ ክርስቲያኖች በአምልኮ ልንሰግድለት፣ ልንበረከክለት የሚገባን አንድ አምላክ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ ዛፍ አይደለም።

🔵 እዚህ በዓል ላይ መገኘትም ሆነ መታደም በክርስትና ዓይን ፈጽሞ የነፍስ ስብራትን የሚያመጣ አምልኮ ባዕድ ነው። ጮክ ብዬ እደግመዋለሁ:- እሬቻን ያከበረ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፊት መጠየቁ አይቀርም። እሬቻ ላይ እግዚአብሔር አይከብርም። እርግጥ ነው:- ዛሬ ፖለቲካው ሃይማኖት ሆኗል። ብዙዎቹንም ፖለቲካ ከሃይማኖት በልጦባቸው "እሬቻ" አይነኬና አይደፈሬ ፖለቲካዊ ሃይማኖት ሆኗል። ትሰሙ እንደሆነ ለራሳችሁ ስትሉ ስሙ መቼም ቢሆን የጅብ ራስ ከመሆን ያንበሳ ጭራ እንሁን! ፖለቲከኞች ተደስተውብን እግዚአብሔር ከሚያዝንብን - መንጋው ጠልቶን እግዚአብሔር አይፈርብን። በነጻነት ስም በአምልኮ ባዕድ አተላ አንጠመድ። ወፍጮ ቤት ገብቶ ብናኝ ዱቄት ሳያገኘው የማይወጣ ሰው የለም። እንዲህ ዓይነት በዓላትም ላይ ተሳትፎ በመንፈሱ የማይወጋ አይኖርም። ወደሽ ከተደፋሽ - ቢረግጡሽ አይክፋሽ ነው ነገሩ። ዛሬ በዓል ያከበርን መስሎን ያደመቅነው የመንፈስ በዓል ነገ spiritual parasite ሆኖ እድሜ ዘመናችን ዋጋ የሚያስከፍለን እንዳንሆን!

🔵 ሞቀ ደመቀ በሚል በይሉኝታ ወይም በአድባርይነት የአምልኮ ባዕድ ሰባኪዎች የሆናችሁም - ነገ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ። የማይረባ የዘር ፖለቲካ ሰማይ ቤት ተክትሎህ አይሄድም። ዛሬ የሰበካት ውሸት ነገ ሰማይ ቤት እሳት ሆና ትበላሃለች። ዛሬ ለዛፍ እንዲሰግድ፣ ዛፍ ቅቤ እንዲቀባ ባደረከው ሕዝብ ነፍስ ነገ ለፍርድ ትቀርባለህ።

🔵 የመጨረሻው ዘመን ስለሆነ ሚሊዮኖች ይተማሉ። ርኩሰትም በተቀደሰችው ሀገር ይበዛል። ሌላው ቀርቶ መስቀል ይዞ የክርስቶስን ቀሚስ ለብሶ "እሬቻ ክርስቲያናዊ ነው" ብለው የሚሰብኩ ተረፈ ይሁዳዎች በየሚድያው ይበዛሉ። የመጨረሻው ዘመን ላይ ነን። ትንቢቱ ይደርስ ዘንድ ግድ ነው። ግን አንተ እግዚብሔርን እንጂ ዛፍን አታምልክ። ለቅዱስ መንፈስ እንጂ ለዛር አትገብር። ለክርስቶስ እንጂ ለአርሰዲ አትሸበር። "እሬቻ ኦርቶዶክሳዊ ወይን ኦሪታዊ ነው" የሚሉ በለአሞችን አትስማ። ስለበዙና መንጋ ስለሆኑ የቁጥራቸው ብዛት ያንተን እግዚአብሔርን አያስፈራውም። አንተንም በቁጥር አነስክ ብሎ አይንቅህም። ብቻህን ብትቀር እንኳን ከእውነት ጋር ብቻህን ኑር። አሸናፊው አንተ ነህ። ግን ሁሌም እውነትን እውነት በል።

🔵 እንኳን ለእሬቻ አደረሳችሁ ወይም መልካም እሬቻ ከማለታችን በፊት ደጋግመን ቃሉን እናስበው። ለማን አምልኮ በዓል አደረሳችሁ እያልን እንደሆነ እያስተዋልን።

🔵 እግዚአብሔርንም አመልካለዉ እያላችሁ ነገር ግን [ከእሬቻ፣ ከጨንበላላ፣ ከጊፋታ፣ በመስቀል ስም በሌሎች ባህላዊ አምልኮ ስም] ሰጥታችሁ ከምታመልኩት ጣዖት አምልኮ ባስትመለሱ መጨረሻችሁ ገሃነም እሳት ነው።

“ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
  — ራእይ 21፥8

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
  — 2ኛ ቆሮ 13፥14

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
🔵 መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።

16 last posts shown.