ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን።
YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8
Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ሖረ ኢየሱስ

ሖረ ኢየሱስ /4/
ዕም ገሊላ /3/ ኃበ ዮርዳኖስ /2/
 
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ጥር ፯ /7/


በዚች ቀን የከበረ አባት የሮሜ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት ሶል ጴጥሮስ አረፈ።

ይህንንም አባት ስለ ተጋድሎው ገናናነት ስለ አገልግሎቱም ስለ ትሩፋቱ ስለ አዋቂነቱና ስለ ደግነቱ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ መልጥያኖስ ከአረፈ በኋላ መርጠው ሊቀ ጵጵስና በሮሜ ሀገር ላይ ሾሙት። በሐዋርያት አለቃ በጴጥሮስ ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የዕሌኒ ልጅ የሆነ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ከከሀድያን ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ምክንያት ገና አልተጠመቀም ነበርና የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሶ የእግዚአብሔርን አብያተ ክርስቲያናት ሠራቸው።

የዚህም አባት የሶል ጴጥሮስ ገድሉ እጅግ ብሩህ የሆነ ነው እርሱ ሁል ጊዜ ሕዝቡን ያስተምራቸዋልና ከልቡናቸውም ከሰይጣን የሆነ ጥርጥርንና ክፉ ሐሳብን ያርቃል። ከእነርሳቸው ሥውር የሆነውንም የመጻሕፍት ምሥጢር ተርጕሞ ያስገነዝባቸዋል። አይሁድንና ዮናናውያንን ሁል ጊዜ ይከራከራቸው ነበር ከእርሳቸውም ብዙዎችን መልሶ ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ስሙም በምእመናን ዘንድ ፈጽሞ የሚያስፈራ ሆነ።

እግዚአብሔርን ስለ ማወቅና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ብዙ ድርሳናትን ደረሰ። በተሾመ በሰባተኛውም ዓመት ስለ አርዮስ በኒቅያ ከተማ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት የከበሩ አባቶች የአንድነት ስብሰባ ሆነ ይህም አባት ሶል ጴጥሮስ ከእርሳቸው አንዱ ነበር አርዮስንም ከተከታዮቹ ጋር ረገመው አውግዞም ለየው። በሹመቱም ዐሥራ አንድ ዓመት ኖረ መልካም ተጋድሎውን ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ጥምቀተ ባሕር

ጥምቀተ ባሕር  ዮርዳኖስ ነያ/2/
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ/2/

ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ፊት ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዞች ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ  ቀረ ወደ ኋላ
አዝ

አብ ነበር የመጣው ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና
ቃሉን ወረወረ ሆኖ በደመና
አዝ

ጌታችን ሲጠመቅ በሰላሳ ዓመት
ባህር ኮበለለች ግዑዟ መሬት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀዐዳ
ከሩቅ መቷልና አብ ታላቁ እንግዳ
አዝ

እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት  መገኛ
የፃድቃን መሰላል ድህነታችን ለኛ
ቀላያት አብርኅት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ

ዘማሪት አዜብ ከበደ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


​​​​​​✞ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም "ሥላሴ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ሥሉስ ቅዱስ

ምሥጢራት በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም::

እግዚአብሔር አንድም ነው: ሦስትም ነው:: ጊዜ ሣይሠፈር ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም: በአካል: በግብር ሦስትነቱ: በባሕርይ: በሕልውና: በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው::

ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው:: ዓለምን ከፈጠረ በሁዋላም ምሥጢረ ሥላሴ (መለኮት) ብለን የምንማረው ትምሕርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው::

ይኼውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው:: ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርሕ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት: ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም::

እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ:- ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው:: ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ያውቃል::

በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ: ወልድ: መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን : በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል::

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት::

ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

በዓለ ሥላሴ በዚህ ቀን የሚከበረው ስለ 2 ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን 2ኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

ሕንጻ ሰናዖር

ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

ቅዳሴ ቤት

ልክ የዛሬ 324 ዓመት: አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት: (በ1684 ዓ/ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ/ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

8.9k 0 130 2 137

ጥያቄ❓ከመመለስዎ በፊት የእለቱን ስንክሳር ይመልከቱ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በስንተኛው ቀን ወደ ቤተ ግዝረት ገብቶ የኦሪት ሕግን ፈጸመ?
Poll
  •   ሀ. 6
  •   ለ. 7
  •   ሐ. 8
  •   መ. 5
513 votes

9.1k 0 19 19 46

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ /2/
ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ /2/

አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በጥምቀትህ
አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በልደትህ

አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በልደትህ
አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በጥምቀትህ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


የጥምቀት መዝሙራት2.pdf
436.4Kb
የጥምቀት መዝሙር ስብስብ #2
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


የጥምቀት መዝሙራት.pdf
555.5Kb
የጥምቀት መዝሙር ስብስብ #1
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ጥር ፮ /6/

በዚች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ።

የከበረ ወንጌል ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቄ ያዙት አላቸው።

ሕፃን ጌታ ኢየሱስም ባለሙያውን ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዕለተ ዓርብ ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና አለው።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችንን ማርያምን ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው አላት።

ሕፃኑ ኢየሱስም እኔ ነኝ ትገዝረኛለህን ወይስ ተውከኝ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ አለው። ያም ባለሙያ የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው አለው ሕፃን ጌታችንም አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው ባለሙያውም እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና አለው።

በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ አባት ሆይ ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

13.6k 0 82 15 177

ዮሐንስኒ

ዮሐንስኒ ያጠምቅ/4/
በሄኖን /4/ በማዕዶተ ዮርዳኖስ
አዝ

እዩት ትህትናውን     ያጠምቅ
ፅድቁን ተመልከቱ   ያጠምቅ
በባሪያው እጅ ሆኖ   ያጠምቅ
የጌታ ጥምቀቱ       ያጠምቅ
አዝ

አንተ መናኙ ሰው    ያጠምቅ
ቅዱስ ባህታዊ       ያጠምቅ
በእጅህ ተጠምቆ    ያጠምቅ
ኢየሱስ ናዝራዊ      ያጠምቅ
አዝ

ተሰውሮ ሳለ          ያጠምቅ
ከዓለም ተለይቶ      ያጠምቅ
አዋጁን ስሙ አለ    ያጠምቅ
በጉን አሳይቶ      ያጠምቅ
አዝ

ንስሀ እየገቡ              ያጠምቅ
እየተናዘዙ                 ያጠምቅ
በዮሐንስ ስብከት        ያጠምቅ
ለእግዚአብሔር ተገዙ  ያጠምቅ
አዝ

የሰማዩን ጌታ                 ያጠምቅ
ምድራዊ ሲያጠምቀው   ያጠምቅ
ምሥጢር ተገለጠ          ያጠምቅ
ዓለም ሁሉ አወቀው        ያጠምቅ

ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ተለቀቀ

🔴አዲስ ዝማሬ “አምላክን ሳትወልጅው
” ዘማሪት ዘውድነሽ አክሊል - “Amlakin Satiweljiw” an Orthodox mezmur by Zemarit Zewdnesh Aklil

በዚህ ያገኙታል
https://youtu.be/ZqJ8QSnPCSA?si=fm5YfX_KFY7sFzDp


​​​​​​እንኳን አደረሳችሁ ጥር 6 ግዝረት

ግዝረት ከጌታችን ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው፡፡ እነዚህ ንዑሳን በዓላት የሚባሉትም ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ፣ ግዝረት፣ ቃና ዘገሊላ፣ ልደተ ስምዖን፣ ደብረ ዘይት፣ የመጋቢት መስቀልና መስቀል ናቸው፡፡ ነቢያት ይወርዳል፤ ይወለዳል ብለው በትንቢት ይጠባበቁት የነበረው መሲሕ የዓለም ብርሃን፣ የነፍሳት ጠባቂ መሆኑን አምነን የምናከብራቸው ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡

ከእናቱና ከደቀመዛሙርቱ ጋር በሰርግ ቤት የተገኙበት ቃና ዘገሊላ፣ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትና አረጋዊ ስምዖንን የሰላሳ ዓመት ጎልማሳ የሆነበት “ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ዐይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና” በማለት የተናገረበት ልደተ ስምዖን ከንዑሳን በዓላት ይመደባሉ፡፡ የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግዝረት በመሆኑ ሀተታዬን ወደ እሱ እመልሳለሁ፡፡

ፍቅር ወልድን ከዙፋኑ ስቦት ወርዶ ሥጋ ማርያምን ተዋሕዶ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ማሕፀኗን ዓለም አድርጎ ከቆየ በኋላ ታኅሣሥ ሃያ ዘጠኝ በዘመነ ማቴዎስ ተወለደ፡፡ በተወለደ በስምንተኛ ቀኑ ሥርዓተ ኦሪትን ሊፈጽም ተገረዘ፡፡ ግዝረትን በስምንተኛው ቀን መፈጸሙ፣ በተወለደ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ መሔዱ ሕገ ኦሪትን ሊያጸና፣ ሊፈጽም፣ ምሳሌውን በአማናዊው ሊተካ እንጂ ኦሪትን ሊሽር ላለመምጣቱ እማኝ ምስክር ነው፡፡ የተሻረ ነገር መታሰቢያ የለውም የተፈጸመ፣ በምሳሌና በትዕምርታዊነት የተወከለ ግን ጥንተ ታሪኩን፣ ትንቢቱን ጠይቀን ምሳሌውን ከትርጓሜ መጻሕፍት እንረዳለን፡፡

ግዝረት አይሁድ የአብርሃም ልጅ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማኅተም ነው፡፡ በሕግና በሥርዐት የሚመሩ መሆናቸውን አንድ አምላክ ማመናቸውን የገለጡበት ነው፡፡ አይሁድ በግዝረት የአብርሃም ልጅነታቸውን እንዳረጋገጡ፣ ክርስቲያኖችም በጥምቀት የሥላሴ ልጅነታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ይህም የሚሆነው ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ መሆኑን ያስረዳል፡፡ በሐዲስ ኪዳን ጥምቀት እንጂ መገረዝ፣ አለመገረዝ አይጠቅምም፡፡ በሐዲስ ኪዳን ግዝረት በፍቃድ እንጂ እንደ አይሁድ እኛም የአብርሃም ልጆች እንድንባል የምንገረዝ አይደለም፡፡

ለእኛ ለክርስቲያኖች ከሥላሴ በመንፈስ ቅዱስ መወለድ እንጂ መገረዝ የአብርሃም ልጆች አያሰኘንም፡፡ አለመገረዝ እንደማይጠቅም ቢያውቅም ጌታችን መገረዝ ያስፈለገው ሕገ ኦሪትን ለመፈጸም ሲሆን በእኔ ግን ምስጢረ ጥምቀትን ፈጽሜ አድናችኋለሁ ሲለን ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የማይጠቅምና ለነገረ ድኅነት የማያበቃ ነገር ቢያጋጥመን እንኳ በጥበብና በማስተዋል እንድናደርገው ሲያስተምረን ነው፡፡ ሥርዐተ ኦሪታችንን ስላፈረሰብን ለሞት አበቃነው ብለው ምክንያት እንዳያገኙና ይህንን ስበብ አድርገው ከነገረ ድኅነት ተለይተው እንዳይቀሩ የሚያደርጉትን በማድረግ፣ የሚወዱትን በመውደድና አብሯቸው የሥርዐታቸው ተካፋይ በመሆን በፍቅር ስቦ ወደ አማናዊው ድኅነት፣ ወደ ጥምቀትና የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ወደማመን መልሷቸዋል፡፡

የመምህሩን አሰረፍኖት የሚከተለው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በደርቤን በሚያስተምርበት ወቅት ጢሞቴዎስ ሲከተለው መገረዝ አለመገረዝ ጥቅምም ጉዳትም እንደሌለው እያወቀ የገዘረው በዙሪያው ብዙ አይሁድ ስለነበሩ እነርሱን ላለማስከፋትና ላለማስደንበር መሆኑን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ “.. የኦሪት ሕግ ለማዳን ብቁ አለመሆኗን እየደጋገመ በድፍረት ይሰብክ የነበረው መምህረ አሕዛብ ቅዱስ ጳውሎስ እንኳ አይሁድን ላለማስደንበር ሲል ሥርዐተ ኦሪትን ይፈጽም ነበር፡፡” /1978፣ 29/ በማለት ገልጸዋል፡፡

ግዝረት ለእስራኤል ከአብርሃም ለመወለዳቸው ምልክት ብቻ ሳይሆን የአብርሃምን ሃይማኖት ለመያዛቸውም መታወቂያ ነበረች፡፡ ጌታችንም ምንም እንኳ የባሕርይ አምላክ ቢሆን በሥጋ የአብርሃም ልጅ ነውና የአብርሃም ልጅነቱን የአብርሃምን ሃይማኖት ማጽናቱን ለማስረገጥ ግዝረትን ፈጸመ፡፡

አንድም በግዝረት ደም ይፈስሳለና አብርሃም በዘጠና ዘጠኝ ዓመቱ በመገረዝና ደሙን በማፍሰስ አበ ሰማዕታት ተብሏልና ግዝረት የሰማዕትነት ምሳሌም ነው፡፡

ጥር ስድስት በሚነበበው ስንክሳር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አረጋዊ ዮሴፍን ሕፃኑን የሚገርዝ ባለሙያ ፈልጎ እንዲያመጣ እንደነገረችው፣ አረጋዊውም ባለሙያውን ፈልጎ እንዳመጣ ይናገራል፡፡ ባለሙያውም ሕፃንን በደምብ ያዙልኝ ብሎ ለመግረዝ ሲሰናዳ ባለሙያ ሆይ ደሜ ሳይፈስ መግረዝ ትችላለህን ብሎ እንደጠየቀው፣ ከስቅለቱ በፊት ደሙ እንደማይፈስ እንዳስተማረው፣ በዚህም ምክንያት ለመግረዝ የመጣው ባለሙያ፣ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን አምኖ እንደሰገደለት ለመግረዣ ያዘጋጀው ምላጭም እሳት ላይ እንደተጣደ ቅቤ መቅለጡን ይተርካል፡፡

በመቀጠልም ክርስቶስ ዘር ምክንያት ሳይሆነው እንደተፀነሰ፣ ማኅተመ ድንግልናዋን ሳይለውጥ እንደተወለደ እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል “ሳይከፈት ገብቶ ሳይከፍት እንደወጣ” ስለት ምክንያት ሳይሆነው፣ በግዝረት ምክንያት ደም ሳይፈስ በተአምራት ተገረዘ፡፡

በአጠቃላይ ግዝረት በኦሪት የአብርሃም ልጅነትን፣ የአብርሃምን ሃይማኖት መያዝን ማረጋጋጫ ማኅተም ሲሆን በሐዲስ ኪዳን በጥምቀት ተተክቷል፡፡ ለአማናዊው ግዝረት /ለጥምቀት/ ምሳሌ በመሆኑም በሥራ የአብርሃም ልጅነትን፣ በእምነት የሥላሴ ልጅነትን አግኝተንበታል፡፡ ወርደህ ተወልደህ፣ በነፍስ በሥጋ፣ ከተቆራኘን ባለጋራ አድነን ብለን የተጣራነው ተሰመቶ፣ ሥርዓተ ኦሪትን ፈጽሞ ወደ ሥርዓተ ሐዲስ የሚያሸጋግረን መሆኑን ያመንበት፣ በጥምቀቱ ቦታ በዮርዳኖስ የተቀበረው የባርነታችን ደብደቤ የሚቀደድ መሆኑን በምሳሌ ያወቅንበት ግዝረት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

13.1k 0 135 5 112

ጥያቄ❓ከመመለስዎ በፊት የእለቱን ስንክሳር ይመልከቱ። የከበረ ቅዱስ አውስግንዮስ ስንት ዓመት በውትድርና ኖረ?
Poll
  •   ሀ. 30
  •   ለ. 25
  •   ሐ. 20
  •   መ. 50
267 votes


​​የእግዚአብሔር ባህርይ

የእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህርይ በሰው አእምሮ የማይመረመርና የማይወሰን ረቂቅ ነው። በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር መመራመርም ሆነ ለሌላውም ማስረዳት ይቻላል። የመለኮትን ባህርይ ግን ሙሉ በሙሉ ተመራምሮ የሚያውቅም ሆነ የሚያስረዳ ማንም የለም። ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት በገለጹልን መሠረት እንደሚከተለው ለመግለጽ እንሞክራለን።

እግዚአብሔር መንፈስ (ረቂቅ) ነው እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእምነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ዮሐ 4 ፥ 24። በማለት ጌታችን እንደተናገረ እግዚአብሔርን ስናምን በዓይናችን አይተን ፣ በእጃችን ዳስሰን አረጋግጠን ሳይሆን በመለኮታዊ ባህርዩ በሥጋ ዓይን የማይታይ አምላክ መሆኑን አምነን በመቀበል ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ነው ስንልም። በእኛ አእምሮ የማይታወቅ ፤ መጠን የማይሰጠው ፤ በላብራቶሪ ምርመራ የማይደረስበት ፤ከምርምር ውጭ የሆነ አምላክ ማለታችን ነው። እግዚአብሔር የፈጠረው ነፋስን እንኳን ከረቂቅነቱ የተነሳ በዓይናችን ማየት እንደማንችል ሁሉ። ዮሐ 3 ፥ 8። ረቂቃን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ መለኮታዊ ባህርዩ ሊመረመርና ሊገመት የማይችል ረቂቅ ነው።

እግዚአብሔር በሁሉም ሙሉ ነው
ሰው በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ መገኘት የማይችል በተወሰነ ቦታ ብቻ የሚወሰን ነው። ኤር 23 ፥ 23። እግዚአብሔር ግን ፍጡር የማይወስነው ፣ በሁሉም ቦታ የሚገኝ ፣ (ምሉዕ በኩለሄ የሆነ) አምላክ ነው። እግዚአብሔር በዓለም ሙሉ ነው ሲባል በዓለም ውስጥ ብቻ ተወስኖ ይኖራል ማለት ሳይሆን ዓለምን በውስጡ ይወስናል ማለት ነው። በኢሳ 8 ፥ 1። “ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት።” የሚለው ቃል እግዚአብሔር በዚህ አካባቢ ብቻ አለ ተብሎ ቦታ የማይወሰንበት ፡ ሰማይም ምድርም ዓለማት በሙሉ ግዛቱ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው።

እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው ሰዎች በዚህ ዓለም መኖር የሚችሉት በሕይወት እስካሉ ድረስ ብቻ ነው። ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊ ኑሯቸው በሞት ይለወጣል። ዘፍ 3 ፥ 19። እግዚአብሔር ግን ዓለማት ሳይፈጠሩ የነበረ ፣ አሁንም እየገዛ ያለ ፣ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ፣ በባህርዩ ሞት ፣በመንግሥቱ ሽረት የሌለበት ዘለዓለማዊ አምላክ ነው። እኛ ሰዎች የተወለድንበት ቀን መጀመሪያችን ፤ የምንሞትበት ቀን መጨረሻችን ነው ፤ አምላክ ግን ሰው በመሆኑ ዘመን ቢቆ ጠርለትም ፤ ሥጋ ፡ የመለኮትን ባህርይ በተዋሕዶ ገንዘቡ ስላደረገ “ስለተዋሃደ” ፤ ዘመናት የማይቀድሙት ቀዳማዊ ዘመናትን አሳልፎ የሚኖር ደኃራዊ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማዊ አምላክ ነው ። ራዕ 1 ፥ ፲፰ ለነበረበት መጀመሪያ ፤ የማይኖርበት መጨረሻ የለውም ፤ ለሁሉም ነገር መጀመሪያውም ሆነ መጨረሻው ራሱ ነው። ዘፍ 18 ፥ 14 ዘፀ 3 ፥ 14:

እግዚአብሔር ጥበበኛ (አዋቂ) ነው የሰው ልጅ ይዞት የተወለደው ልቅሶ ብቻ ነው። ሌላውን ሁሉ ፡ በማየት፣ በመስማት ፣ በመማር ፤ ከሰዎች ያገኘው ነው። ያውም ቢሆን ያለፈውን ታሪክ ከማውራትና አሁን የሚደረገውን ከማየት በቀር ወደ ፊት የሚሆነውን ለማወቅ የሚያስችል ዕው ቀትና ጥበብ የለውም። ዕውቀቱም ቢሆን የአንዱ ዕውቀት ከሌላው ይበልጣል ፤ በዚህ ዓለም ፍፁም የሆነ ዕውቀት የለም የተከፈለውም ቢሆን በጊዜው ያልፋል። 1ቆሮ 13 ፥ 8። እግዚአብሔር ጥበቡ የባህርዩ የሆነ ፣ ያለፈውን የማይረሳ ፣የሚያውቅ ፣ ለሰዎች ዕውቀትንና ጥበብን የሚገልጽ አምላክ ነው። ሰው ሊያውቅና ሊመራመር የሚችለው ውጫዊውንና ግዙፉን ነገር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ግን ልብና ኩላሊትን (በሰው ህሊና የታሰበውን) አስቀድሞ የሚያውቅ አምላክ ነው። መዝ 7 ፥ 9።

እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ቅድስና የእግዚአብሔር የባህርዩ ሲሆን “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ዘሌዋ 19 ፥ 2። 1 ጴጥ 1 ፥ 15። ባለው ቃል መሠረት ቅዱሳን መላእክትና በሥራቸው ለቅድስና የበቁ ሰዎችም ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ። የመላእክትና የሰዎች ቅድስና ግን ፡ በሥራ የሚገኝ ፣ በሃይማኖት የተፈተነ ፣ከእግዚአብሔር የሚሰጥ የፀጋ ቅድስና ነው። የፍጡራን ቅድስና ደረጃ አለው ከአንዱ የሌላው ይበልጣል። 1 ቆሮ 15 ፥ 41። የእግዚአብሔር ቅድስና በመጠን አይወሰንም ፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለምና ። ኢሳ 6 ፥ 3። ዕንባ 1 ፥ 13።

እግዚአብሔር ቸር ነው የሰው ልጅ ቸርነቱ (ልግስናው) በኪሱ ያለው ሳንቲም እስኪያልቅ ፤ እሱንም ቢሆን የሚሰጠው ተለምኖ ነው። እግዚአብ ሔር ሁሉ ያለው ፣ ያለ ንፍገትና ያለ መሰሰት ለጋስ ፣ ስጦታው የማያልቅበት ፣ ኃጥዕ ጻድቅ ሳይል በቸርነቱ ለሁሉ ያለ አድልዎ የሚያድል ማቴ 5 ፥ 41። ሳንለምነው የሚያስፈልገንን አውቆ የሚሰጠን ፣ቸር አምላክ ነው። ማቴ 6 32። ሰው የሚሰጠው ከሌላው ያገኘውን ነው ፤ወደዚህ ዓለም የመጣው ራቁቱን ነው ፤ወደ ምድር ሲመለስም የሚያስከትለው ነገር የለውም። ኢዮ 1 ፥ 21። 1ጢሞ 6 ፥ 7። እኛ ለሌሌሎች የምንሰጠው ከተረፈን ብቻ ነው አምላካችን ግን ለእኛ የሰጠን ራሱን ነው። ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሐ 15 ፥ 13። ሰው የሚሰጠው ለወዳጁ ፣ ለወገኑ ፣ ለሚመስለው… ነው እግዚአብሔር ግን ጠላቶቹ ሳለን ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ከራሱ ጋር አስታረቀን ፤ ከዘለዓለም ሞትም አዳነን። ሮሜ 5 ፥ 10።

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ሰው ወዳጁን ይወዳል ለማይወደው ግን ቦታ አይሰጥም ፤ እንዲያውም ከተመቸው ከመበቀል ወደኋላ አይልም። እግዚአብ ሔር ግን እየበደልነው ለንስሐ እስክንዘጋጅ በብዙ ታግሶ ይወደናል። ሮሜ 2 ፥4። የሰው ፍቅሩ ተለዋዋጭ ፣ ወረት ያለበት ፣ ጊዜያዊ ነው። ሰው ለጥቅም ብሎ ወዳጁን ይገድላል። አምላካችን ፍቅሩ የማይለካ ፣ ለእኛ ለጠላቶቹ የሞተ ፤ ኢሳ 53 ፥ 1 ፥12። የሠራነውን ሁሉ በቸርነቱ ይቅር ብሎ ከበደል የሚያነጻን አምላክ ነው። ኢሳ 1 ፥ 18። እግዚአብሔር ፈቅደን እንድንገዛለት ይፈልጋል እንጅ ፤ ማንኛችንንም አስጨንቆ አይገዛንም። 1 ዮሐ 18

እግዚአብሔር በእውነት የሚፈርድ እውነተኛ ዳኛ (ፈራጅ) ነው እግዚአብሔር ለሰዎች የዳኝነት ሥልጣን የሰጣቸው ትክክለኛ ፍርድ እንዲፈረዱ ነው። ማንም ቢሆን እውነት መፍረድ እንዳለበት ህሊናው ይነግረዋል። በሐሰት ስንፈርድ በመጀመሪያ የሚወቅሰን ህሊናችን ነው። የህሊና ወቀሳን የማይፈራ ማንንም ሊፈራ አይችልም። ዳኞች ፡ በዘመድ ፣ በጥቅማ ጥቅም ፣ በዓላማ መመሳሰል ፡ እና በሌላም ፍርድ ሊያዛቡ ይችላሉ። እግዚአብሔር ግን ከማንም ምንም የማይፈልግ ፣ ከእውነት ጋር ደስ የሚለው ፣ ፍርዱ ትክክለኛ የሆነ አምላክ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያደላም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል። ራዕ 22 ፥ 12። መዝ 36 ፥ 28

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  ሀልወተ እግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ግነዩ ለእግዚአብሔር

ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር /2/
እስመ ለዓለም ምሕረቱ እስመ ለዓለም /4/

እናመስግንሽ የአምላክ እናት በዝማሬ /2/
የዓለም ቤዛ ነውና የማኅፀንሽ ፍሬ /4/
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ካንቺ ተወልዶ /2/
መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ /4/
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ /2/
በቸርነቱ አወቀን ከበደል አራቀን /4/
በድንግልና የወለድሽው የአንቺ ፅንስ /2/
የድኩማኖች ብርታት ነው የሕሙማን ፈውስ /4/
ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም ያዘከረ /2/
በመንግሥተ ሰማይ ይኖራል እንደ ተከበረ /4/
ብርሃነ መለኮት ያደረብሽ አዳራሽ /2/
ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ /4/
እመቤታችን እናታችን ማርያም /2/
የተማፀነሽ ይኖራል ለዘለዓለም /4/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ጥር ፭ /5/


በዚች ቀን በከሀዲው ዑልያኖስ ዘመን የከበረ አውስግንዮስ ምስክር ሁኖ ሞተ።

ይህም ቅዱስ አውስግንዮስ እድሜው መቶ ዐሥር ዐመት እስከ ሆነው ከቈስጠንጢኖስና ከልጆቹ ዘመነ መንግሥት በኋላ እስከ ከሀዲው ዑልያኖስ ዘመን ኖረ።

በአንዲት ዕለትም በአንጾኪያ ከተማ በአደባባይ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሲመላለስ ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አግኝቷቸው ሊአስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላም ሊያአደርግ ወዶ አስታረቃቸው በመታረቃቸውም ደስታ አደረጉ እርሱ የከበረ አረጋዊ ሰው ነውና።

ከዚያም አንድ ክፉ ሰው ወደ ንጉሥ ዑልያኖስ ሒዶ ነገር ሠራበት እንዲህም አለው አውስግንዮስ በራሱ ፈቃድ ገዥና ፈራጅ ዳኛ ሆነ። ንጉሥም ይህን ቅዱስ ወደርሱ አቅርቦ ገሠጸው ገዥና ፈራጅ ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማነው አለው።

የከበረ አውስግንዮስ መልሶ ነፍስህ በእጁ የተያዘች የእግዚአብሔርን አምልኮት ትተህ አንተ ለረከሱ ጣዖታት ለምን ሰገድክ ከአንተ በፊት የነበሩ ነገሥታትን ለምን አልተከተልካቸውም እኔም እንዳንተ ወታደር ሁኜ ከቈስጠንጢኖስ ጋር ሃያ ዓመት ኖርኩ ከልጆቹም ጋር ነበርኩ ከእነርሱ ውስጥ እንዳንተ ያለ ጠባየ ክፉ የለም አለው።

ዑልያኖስም በቅዱስ አውስግንዮስ ላይ እጅግ ተቆጣ ይሰቅሉት ዘንድ በጐኖቹም ውስጥ መብራቶችን አስገብተው እንዲለበልቡት አዘዘ እርሱም ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህን ሁሉ ታገሠ።

ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ወታደሮችም ሊቆርጡት በመጡ ጊዜ እስኪጸልይ ይታገሡት ዘንድ ለመናቸው ጸሎቱንም ሲፈጽም የከበረች ራሱን ቆረጡት የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


የዓለምን በደል

የዓለምን በደል የሠውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ
አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ/2/
ልጁ በዮርዳኖስ ፅድቅን ሲመሠርት
መጣ በደመና ሰማያዊ አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ/2/
ምድር ስትጨነቅ ተራራው ሲጨፍር
ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር
ዓለም በዛሬው ቀን አየች ልዩ ምሥጢር
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ/2/
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደ ተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ/2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


​​ጥር ፭

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር አምስት በዚህች ዕለት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ የለውጥ በዓል ነው።

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ጥር አምስት በዚህች ዕለት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ የለውጥ በዓል ነው። ትውልድ አገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው፡፡አባታቸው ስም ቅዱስ ስምዖን  እናታቸው ስም ቅድስት አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ "ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ ከፍ የሚል፣ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ ንጽሕናው እንደ እንደ ነቢይ ኤልያስ፣እንደ መጥምቁ ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ አሏት። ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ። ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት"። እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡

ቅድስት አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ "የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን"አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ ዳግመኛም ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን" አለ፡፡

የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ ልደት ታህሳስ 29 በጌታችን ልደት ነው:: ነገር ግን ዕለቱ ትልቅ ሚስጥር የያዘ ነውና አባቶቻችን የጌታ ልደት ዘምረው ጣዕሙ ሳያልቅ ቅዳሴ ይገባሉ:: ስለዚህ የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ከሚቀር ልደታቸው ጥር 5 እንዲከበር ስርዓት ሰርተዋልና በዓለ ልደታቸው በዚህች ቀን ተከብሮ ይውላል፡፡

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ጥያቄ❓ከመመለስዎ በፊት የእለቱን ስንክሳር ይመልከቱ። ቅዱስ ዮሐንስ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ የመረጣቸው ደቀ መዛሙርት ስንት ናቸው?
Poll
  •   ሀ. 7
  •   ለ. 3
  •   ሐ. 9
  •   መ. 2
394 votes


ነገረ ቅዱሳን
ቅዱሳን ስግደት ይገባል?
ክፍል አራት

በዲ/ን ዳግም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

20 last posts shown.