ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ።
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ››
ት.ኢሳ 58÷3
https://youtu.be/csxxAMGtC4I
ለመቀላቀል
http://t.me/ortodoxtewahedo

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት
👇


ሁለት ክንፎች✝
                         
Size 48.2MB
Length 52:06

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


+ ሌላ መንገድ +

ሰብአ ሰገል ወደ ሄሮድስ ሔደው ስለተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ጠየቁ:: ከዚያም በኮከብ ተመርተው ወደ ክርስቶስ ደረሱ:: ሔደውም ሰገዱለት:: እጅ መንሻም አቀረቡ::

ከዚያ በኋላ ግን "ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ" ማቴ. 2:12

ይህ መልእክት የተነገራቸው ስለ ሁለት ነገር ነው:: የመጀመሪያው ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ስለሚፈልግ ለሄሮድስ መረጃ እንዳይሠጡ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለተወለደው የአይሁድ ንጉሥ እየመሰከሩ የመጡበትን መንገድ ትተው አየነው እያሉ በሌላ መንገድ እንዲመሰክሩና የሕፃኑ ንጉሥ ዝና እንዲሰፋ ወንጌል እንዲስፋፋ ነበር::

መልአኩ ወደ ሄሮድስ አትመለሱ አለ እንጂ “ሄሮድስ ሊገድለው ነው" አላላቸውም:: ምክንያቱም ይህን ዜና ቢሰሙ ጦር ይዘው የመጡ ነገሥታት ናቸውና "እኛ እያለን እስቲ ይሞክረን" ብለው ውጊያ ሊያነሡ ይችሉ ነበር:: የሰላም አለቃ የተባለው ህፃኑ ክርስቶስም የውጊያ መነሻ ይሆን ነበር:: ክርስቶስ ግን የምትዋጋለት ሳይሆን የሚዋጋልህ አልፎም የሚወጋልህ አምላክ ነው::

በዚህ መሠረት ሰብአ ሰገል

"ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።

ወዳጄ ክርስቶስን ሳታገኝ በፊት ሄሮድስ ጋር ብትሔድ ችግር የለውም:: ክርስቶስን ካገኘህ በኋላ ግን ወደ ሄሮድስ መመለስ ኪሳራ ነው:: እንደ ሰብአ ሰገል ለጌታ እጅ መንሻ አቅርበህ ፣ ዘምረህ ፣ የከንፈር መሥዋዕት አቅርበህ ነፍስህ መድኃኒትዋን አግኝታ ከተደሰተች በኋላ ሕይወት እንዴት ይቀጥላል?

ወደ ሄሮድስ ልትመለስ ይሆን? እንዳታደርገው! ሄሮድስ ጋር ያለው ኃጢአት ነው:: ሄሮድስ ጋር ያለው ክፋት ነው:: እመነኝ እንደ ሰብአ ሰገል ጌታህን ካገኘህ ወዲህ ወደ ሄሮድስ አትመለስ!

ወዴት ልሒድ ካልከኝ መልሱ እዚያው ላይ አለ :‐

"በሌላ መንገድ ወደ ሀገራቸው ሔዱ"

እስቲ ሌላ መንገድ ሞክር! ትናንት ያልኖርክበትን ዓይነት ኑሮ ፣ ትናንት ያልሞከርከው የንስሐ መንገድ እስቲ ዛሬ ሒድበት! ሌላ መንገድ አልነግርህም "መንገድም ሕይወትም እውነትም እኔ ነኝ" ያለህ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እርሱ ነው:: በእኔ ኑሩ እንዳለ በእርሱ ኑር:: አደራ ወደ ሄሮድስ እንዳትመለስ!

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 2 2017

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


።።።።።።።።።።+ ጥር ፩ + ።።።።።።።።
።።።።።።።። + ቅዱስ እስጢፋኖስ + ።።።።።

ጌታችን በትሕትና የዳዊትን ጸሎት በመስቀል ላይ እንደጸለየ ሁሉ እዚያው መስቀል ላይ ሆኖ የጸለያቸውን ‹‹የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው›› እና ‹‹አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሠጣለሁ›› የሚሉትን ሁለት ጸሎቶቹን ደግሞ የመጀመሪያው ሰማዕት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ጸልዮአቸዋል፡፡ ሰማዕቱ በድንጋይ ተወግሮ በሚሞትበት ሰዓት ከጌታው የተማረውን ጸሎት ‹‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል›› ‹‹ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› በማለት ሲጸልይ ተገኝቶአል፡፡
(ሉቃ. 23፡34፣46 ፤ ሐዋ. 7፡59-60)

አንዱ የጸለየውን ጸሎት መድገም ማለት ይኼም አይደል?

፲፯

ሰላም ለአስናኒከ ለለ አሐዱ አሐዱ
እምፅዕዳዌ ሐሊብ ወበረድ እለ ሠናየ ተንዕዱ
ሶበ ጸለይከ እስጢፋኖስ ለእግዚአብሔር አምሳለ ወልዱ
አስተሥረይከ አበሳሆሙ እለ ኪያከ ሮዱ
አስተሥርዮ ጌጋይ ወአበሳ ለጻድቅ ልማዱ።

ከበረድና ወተት ይልቅ እጅግ ለተደነሱ ለእያንዳንዱ ቅዱሳት ጥርሶችህ ሰላምታ የሚገባህ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ ይቅር በላቸው እንዳለ አንተም በድንጋይ ስለወገሩህ በጸሎትህ በደልንና ኃጢአትን ማስተሥረይ ይገባልና የከበቡህ ጠላቶችህን በደል ይቅር እንደ አሰኘህ የእኔንም ኃጢአት ይቅር አሰኝልኝ።

መልክዐ ማር እስጢፋኖስ

የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከቱ አይለየን!!!

ከአቤል ወልደ የሺ የፃፈው የተወሰደ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


የሚያስፈራ ግርማ
                          
Size:-16.5MB
Length:-17:48
  
    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


"በረት ኪሩቤል እንደሚሸከሙት ዙፋን ሆነ ፤ ስፍራውም እንደ ጽርሐ አርያም፤ ድንግል እንደ አብ ሆነች አንድ ልጅም በጎል ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ ተገኘ፡፡" አርጋኖን ዘሰኑይ

ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የጌታችንን መወለድ በመጽሐፈ አርጋኖን መጽሐፉ ላይ እንዲህ ሲል በማድነቅ ይናገራል...

"እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ምን ያህል ጸጋ ክብር ሰጠ፡፡ እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ተወለደ፤ ከእርሱ ልደትም ጋር ከማይተባበሩ ሦስት ልደታት ልዩ የሆነ ልደትን ተወለደ፡፡ እኔም ዐውቄ አደነቅሁ፡፡ በእርሱ ልደት እንጂ በሦስቱ የበጎ ዕረፍት አላገኘሁም፡፡

አዳም ከሕቱም ምድር የተወለደ በተፈጥሮ ነው፡፡ እኔን ግን የጠቀመኝ የለም፡፡ ሔዋንም ከአዳም ግራ ጐን ተወለደች እርሷም በተፈጥሮ ነው፡፡ ለኔ ግን የጠቀመችኝ የለም፡፡ ቃየልም እንደ ሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ የጠቀመኝ የረባኝ የለም፡፡ ስንኳን እኔን እራሱንም አልጠቀመም፡፡ እሊህ ሦስቱ ልደታትም ለማንም ለማን አይረቡም አይጠቅሙም፡፡

ክርስቶስ ግን ያለዘር ያለሩካቤ ከድንግል ተወለደ ለሁሉ የሚረባ የሚጠቅም ሆነ፡፡ ለዚህ ልደት መስገድ መገዛት ይገባል፡፡ ክብር ምስጋና ለዚህ ልደት ይገባል ጌትነትና ገናንነት ኀያልነት፣ አዚዝነት፣ እልልታ፣ ግርግታ ለዚህ ልደት ይገባል፡፡

የሔዋን ደኅንነቷ እመቤታችን ሆይ የድንግልናሽ ኃይል እጅግ የሚያስደንቅ ዕጹብ ነው፡፡ የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋሽለት እመቤታችን ሆይ የማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር ባንቺ ተደረገ፡፡ እሳትና ውሀም ባንድነት ተስማምተው መኖራቸው እጅግ ድንቅ ነው የሚያስፈራውንም የአንበሳ ደቦል ፀዓዳ በግዕት በክንዷ መታቀፏ እጅግ ድንቅ ነው፡፡

ከድንግልም ብላቴና ጡቶች ወተት መፍሰስ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በበረትም ለድኆች ልጅ የሰማይ ሠራዊት መስገድ እጅግ ድንቅ ነው፤ ዓለምን ሁሉ የመላ አምላክም ከበረት ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ መገኘቱ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በረት ከጽርሐ አርያም ቁመት ረዘመ ከሰማይም ዳርቻ ሰፋ፡፡ ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን በረት በለጠ፡፡ ይኽውም አደፍ ጉድፍ ሳይኖርበት ንጽሕት የወለደችው ንጹሕ በግ ነው፡፡ በረት ለንጹሑ መሥዋዕት ሽታ መሰብሰቢያ ሆነ፡፡

በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች እመቤታችን የተመረጠች ድንግል የሰማዩን ሠራዊት አሰገደቻቸው፡፡ የዓለም ጌጽ ሽልማት የሁሉ አባት የሚሆን መላእክትን የፈጠረ ጌታ ከርሷ ተወልዷልና፡፡ በረት ተመሰገነ ምድርን በውሃ ላይ ያጸናት እርሱ ስለተጠጋባት ድንግልም የመላእክትን አለቆች ገዛቻቸው በኪሩቤል ላይ የሚቀመጥ እሱ በማኅፀኗ ስላደረ፡፡ በረት ኪሩቤል እንደሚሸከሙት ዙፋን ሆነ ስፍራውም እንደ ጽርሐ አርያም፤ ድንግል እንደ አብ ሆነች አንድ ልጅም በጎል ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ ተገኘ፡፡ ዮሴፍና ሰሎሜ በወዲህና በወዲያ ላምና አህያም በወዲህና በወዲያ በበረቱ ጐንና ጐን በአራቱ ማዕዘን በዙፋኑ ቀኝና ግራ በጐንና በጐኑ አራቱ እንስሶች እንዳሉ፡፡ የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ተሠራ፡፡ ቤተልሔም ሰማይን መሰለች ስለ ፀሐይም በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ለዘወትርም ጨለማ የማይቃወመው ኅልፈት ጥፋትም የሌለበት ዕውነተኛ ፀሐይ በውስጧ ተገኘ፡፡ የብርሃኑም ክበብ መምላትና መጉደልን ስለሚያፈራርቅ በጨረቃ ፈንታ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች የድንግልናዋም ምስጋና በሁሉ የመላ ነው፡፡ ለዘወትርም የማይጐድል እመቤታችን የተመረፀች ድንግል ማርያም ተገኘች ስለ ከዋክብትም መላእክተ ብርሃን ታዩ፡፡..."


ወደዚህ ማኀበር አንድነት እንኖር ዘንድ ማን በከፈለን ከመላእክት ጋር እንድናመሰግን ከአዋላጅቱም ጋር እንድናደንቅ ከእረኞችም ጋር እንድናገለግል፡፡ በረቱንም እጅ እንነሣ ዘንድ ማን በከፈለን የሙታን ሕይወት የኃጥአንም ንጸሕና የቅቡፃን ተስፋ የተጨነቁትንም የሚያድን ጌታ ወደተቀመጠበት፡፡ አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ማርያም ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አናንስም ሀሳባችንንም ከዚያ እንዳለን አድርገናልና፡፡

በስጋ አልነበርንም በመንፈስ ግን አለን፡፡ ባነዋወር አልነበርንም በሃይማኖት ግን አለን በገጽ አልነበርንም በማመን ግን አለን፡፡
ሳንኖር እራሳችንን እንዳለን ያደረግን እኛ የተመሰገንን ነን ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል ሳያዩኝ የሚያምኑብኝ ግን የተመሰገኑ ናቸው፡፡ እኛ ባሪያዎችህ ስለሃይማኖታችን የተመሰገንን ነን፡፡ ስለ ዕውነታችን አይደለም ስለ መረዳታችንም የተመሰገንን ነን፡፡ ስለ ንጽህናችንም አይደለም በእግዚአብሔር ስም ስለ አመንን የተመሰገንን ነን፡፡ በእናቱም ጸሎት ስለ አመንን ንዑድ ክቡር ነን፡፡

እንኳን ለዚህ ጥበብ ፍልስፍና : አንክሮ ለሚገባው : እጅግ ዕፁብ ድንቅ ለሆነ የአምላክ ሰው መሆን ሥጋን መልበስ ዕለት በሰላም አደረሳችሁ!!!

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤

በምሉእ ፍቅሩ ሰውን ከባርነት ወደ ነጻነት ለመመለስ በሥጋ ሰብእ የተወለደው ጌታችን  አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘሠምሮ ለሰብእ፤ ክብር በሰማያት ለእግዚአብሔር ይሁን›› በምድርም እጅግ ለወደደው የሰው ልጅ ሰላም ይሁን” (ሉቃ ፪÷፲፬)
ይህ ቃለ ሰላም በጌታችን ዕለተ ልደት የተነገረ ነው፣ ቃሉ የተነገረው እንዲሁ እንደ ተራ ነገር ሳይሆን በቃለ መዝሙር እየተደጋገመ ነው፡፡ የተዘመረውም በምድራውያን ደራሲዎች ሳይሆን በሰማያውያን መላእክተ እግዚአብሔር ነው፣ የያዘው መልእክትም ሰማያውያንና ምድራውያንን ሁሉ ያካለለ ነው፡፡ የመልእክቱ ገዢ ሓሳብም አምላክ ከሰውነታችን ጋር ባለመለያየት፣ባለመጠፋፋት፣ባለመቀላቀል፣ባለመዋዋጥ፣ ባለመለዋወጥና ያለባዕድና አንድ አካል፣አንድ ክዋኔ፣አንድ ጠባይ ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጾኣልና እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡ የተዋሕዶውም ምስጢር ሰላምን ያሰፍናልና እግዚአብሔር ሰውን በእጅጉ መውደዱ ከዚህ ተዋሕዶ ዓውቀናል የሚል ነው፡፡

በእርግጥም እግዚአብሔር ሰውን ለመውደዱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ ወይም ማስረጃ የለም፤ እንከን የለሽ ንጹህ አምላክ የእኛን ኃጢአተኛ ሰውነት አካሉ አድርጎ ተወለደ ሲባል ላስተዋለው ሰው ምንኛ ቢወደን ነው የሚለው ጥልቅ አድናቆትን ያጭራልና ነው፡፡ይህ ብቻም አይደለም በዚህ ነገረ ተዋሕዶ ምክንያት ሰውነታችን አምላክ ሆኖ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ መብቃቱ የድኅነታችንና የክብራችን ከፍታ ምን ያህል አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መንፈሳችን በአንክሮ ይረዳዋል፡፡ ድምር ውጤቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ያስረዳናል፤ ሰማያውያኑ መላእክተ እግዚአብሔር በመዝሙራቸው ያበሰሩን ይህንን የምስራች ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር በእጅጉ ይወደናል ስንል እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተን ኣይደለም፡፡ በበደላችንና በኃጢአታችን ሳይጸየፈን ሰውነታችንን በረድኤት ወይም በኅድረት ያይደለ በኩነት ተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ስላደረገው  ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ፍጹምና ምሉእ ፍቅሩ ሰውነታችንን በመበረ ጸባኦት ኣስቀምጦ መላእክት ሳይቀሩ ፍጥረታትን በሙሉ እንድንገዛ አድርጎናል፤ ምክንያቱም መላእክት በዕለተ ልደት የዘመሩለት በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለቤተ ልሔሙ ሕፃን እንጂ ለመለኮት ብቻ ኣይደለምና ነው፡፡ የዕለተ ልደት መዝሙር ዛሬም በሰማያትም ሆነ በምድር በተዋሕዶ ሰውም አምላክም የሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለክበታል፣ ይመሰገንበታል፡፡ የሰማዩና የምድሩ ዕርቅ ወደ ኋላ ላይመለስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ተከናውኗል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰውም አዋጭ ምርጫ ይህ ዕርቅ ተጠብቆ እንዲኖር ነው፣ ያለ ዕርቅ ሰላም ሕይወት የለውምና፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ክብርና ሰላም በእጅጉ የተሳሰሩና የተቆራኙ ናቸው፤ እኛ እግዚአብሔርን ካከበርነው፣ ካዳመጥነው፣ ከታዘዝነውና ከተከተልነው ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ለሱ ካልታዘዝንና እሱን ካላከበርን ግን ዘላቂ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም ሰላምን ጨምሮ መልካም ነገር ሁሉ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ዛሬ በሁሉም የዓለማችን ማዕዘን የሚታየው የሰላም መደፍረስ እግዚአብሔርን ካለማክበራችንና ለእርሱ ካለመታዘዛችን የተነሣ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዓለም ከእግዚአብሔር ቃል ርቃ ለመሄድ በእጅጉ እየኳተነች ነው፤ በዚህ እኩይ ተግባርዋ ደግሞ እግዚአብሔር ለስጋትና ለጉስቁልና አሳልፎ እየሰጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌው ቢታረቃትም ዕርቁን ማክበር አቅቷታል፤ ይህንን የእግዚአብሔር ጸጋ ቸል ብላ የምታደርገው ሩጫ የትም ሊያደርሳት እንደማይችል ብታውቅና በንስሓ ብትመለስ እግጅ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ቃል “እናንተስ ከማይጠፋ ዘር ተወለዳችሁ” ብሎ ተስፋውን እንደነገረን ምድባችን ከማይጠፋ ዘር እንዲሆን ክርስቲያኖች የሆን ሁላችን በአእምሮ ጎልብተን፣ በሥነ-ምግባር አምረን፣ ጤናማ ሕይወትን ልንመራ ይገባናል፡፡

የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ነገረ ፍቅርን፣ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል፡፡
ጠቡ፣ጥላቻው፣መለያየቱ፣መጠፋፋቱ፣ ለወንድሜ  ከማለት ይልቅ ለኔ ለኔ ማለቱ ሲጎዳን እንጂ ሲጠቅመን አላየንም፡፡ አሁንም ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነውና፡፡ በሌሎቹ ክፍለ ዓለማት እንደሆነው ሁሉ በሀገራችን የተከሠተው አላስፈላጊ ግጭት ብዙዎችን አሳጥቶናል፤ ብዙዎችንም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ፈሰው የሰቆቃ ኑሮ እንዲገፉ አድርጎብናል፡፡ የሀገር ሀብት እንዲወድም ሆኗል፤ ልጆቻችን ምናለ ከእንግዲህ ወዲህ ቢበቃንና ምድሪቱን የሰላም አየር እንድትተነፍስ ብንፈቅድላት፤ ይህ የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ መልእክትና ጥሪ ነው፡፡    

በመጨረሻም፡-

በዓለ ልደት የእግዚአብሔር በዓል ነውና፣ እግዚአብሔር በምድራችን ሰላምን ያወርድ ዘንድ ካለን ከፍለን ለተፈናቃዮች፣ለነዳያን እና ለአካል ጉዳተኞች በመለገስ በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታና በሰላም እንድናከብር አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በተገኙበት እየተከናወ ነው።

ከቅዱስነታቸው ጋር ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና እጅግ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና ምእመናት ተገኝተዋል።

መርሐ ግብሩን በቀጥታ ሥርጭት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን(EOTC TV)፣ ሀገሬ ቲቪ እና አርትስ ቲቪ እያስተላላፉት ይገኛሉ።

እንኳን ለበዓለ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


#ቤዛ ኩሉ አለም ዮም ተወልደ

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በቅዱስ ላሊበላ በከፍተኛ ድምቀት ይከበራል ፡፡

መላእክት ከእኛ ጋር በእዚህ አሉ....
***

የአማናዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሚነሳበት በእዛ .... ቅዱሳን መላእክት ይነጠፋሉ።

ቤተክርስቲያን በምትዘረጋዊ ሚስጢሯ ውስጥ ሰማያውያን ተሰልፈው ከተመረጡ የአብ ተክል አመስጋኞች ተርታ በአንድነት ይቆማሉ።

የሚታዩት ከማይታዩት ፣ ሰማያውያን ከምድራውያን ጋር ለአንድ ርስት እና ለአንድ ጌታ የሚደክሙበት ንጽሁ እና ቅዱስ በዓት .....ቤተክርስቲያን ::

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo


+ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ:: ልጅም ትወልዳለች:: እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ:: በነቢይ ከጌታ ዘንድ:-'እነሆ ድንግል ትጸንሳለች:: ልጅም ትወልዳለች:: ስሙንም አማኑኤል ይሉታል:: የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል:: ትርጉዋሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው::

(ማቴ. 1:20)

+" እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራቹሃለሁና አትፍሩ:: ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት: እርሱም ክርስቶስ: ጌታ የሆነ ተወልዶላቹሃልና::

(ሉቃ. 2:10)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

12 last posts shown.