በአፍሪካ ከወባ ነፃ የተባሉ አገራት የትኞቹ ናቸው?
ወባ ለብዙ አሥርተ ዓመታት በብዙ የአፍሪካ አገሮች ከባድ የጤና ስጋት ሆኖ ቆይቷል። የወባ በሽታ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት አሳሳቢ ቢሆንም አንዳንድ አገራት ግን በተሳካ ሁኔታ ከወባ ነፃ አገር ለመባል በቅተዋል።
ከወባ ነፃ ለመባል ሃገራት የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣውን መስፈርት ማሟላት አለባቸው።
ከመስፈርቱ ውስጥ ከወባ ነፃ ለመባል በአንድ አገር ቢያንስ ለተከታታይ ሶስት አመታት ምንም በወባ የተያዘ ሰው አለመመዝገቡ መረጋገጥ አለበት። በተጨማሪም በሽታው ዳግም እንዳይከሰት መከላከል የሚያስችል አቅም በአገሪቱ መገንባቱ ይገመገማል።
ለመሆኑ በአፍሪካ ከወባ ነፃ የተባሉ አገራት የትኞቹ ናቸው?
ሞሮኮ፦ እ.ኤ.አ. በ 2010 ሞሮኮ በዓለም ጤና ድርጅት ከወባ ነፃ የሆነች ሀገር ተብላለች። አገሪቷ የወባ መከላከል አፈፃፀሟን በማሳደግ ፈጣን የህክምና ስርዓት በመዘርጋት ውጤታማ መሆኗ ተነግሯል።
አልጄሪያ፦ የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር አልጄሪያ እ.ኤ.አ. በ2019 ከሞሮኮ በኋላ ከወባ ነፃ መሆን የቻለች አገር ናት። የአልጄሪያ ስኬት የተመሰረተው በውጤታማ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ነው። አገሪቱ በትምህርት፤ በወባ የሚያዙ ሰዎችን አስቀድሞ በመለየት እንዲሁም በማከም ላይ መጠነሰፊ ኢንቨስትመንት አድርጋለች።
ሞሪሸስ፦ በ1940ዎቹ ገደማ ሞሪሽየስ ብዙ ሰዎችን በፈጀ የወባ ትንኝ ትቸገር ነበር። ነገር ግን አገሪቱ በሽታውን ለማጥፋት የወባ ትንኝ ቁጥጥር ዘመቻዎችን፤ ጨምሮ ከፍተኛ የቁጥጥር ስራዎችን በመስራት ከወባ በሽታ ነፃ ሆናለች።
ካቦ ቬሪዴ፦ አገሪቱ በአፍሪካ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ ላይ ያለች ናት። ይህች ትንሽ ሀገር በጃንዋሪ 2024 ከወባ ነፃ ተብላለች። የካቦ ቬርዴ መንግስት የወባ ትንኝ ቁጥጥርን፣ የጤና አጠባበቅ፤ የበሽታ ትምህርት ላይ በማተኮር ወባን መዋጋት ችሏል።
ግብፅ፦ ግብፅ ከቀናት በፊት ከወባ ነፃ በመባል የአለም ጤና ድርጅት የምስክር ወረቀት አግኝታለች። አገሪቱ ወባን ለማስወገድ መስራት የጀመረችው የዛሬ 100 ዓመት ገደማ ሲሆን ከሞሮኮ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በመቀጠል በአለም ጤና ድርጅት ምስራቃዊ ሜዲትራኒያን ቀጠና ይህንን የምስክር ወረቀት ያገኘ ሶስተኛዋ ሀገር ሆናለች።
በተጨማሪም በአፍሪካ ወባ ቀድሞውንም የሌለባቸው ወይም አገራቱ ምንም ልዩ እንቅስቃሴ ሳያደርጉ ከወባ ነፃ የሆኑ አገራት መኖራቸውን የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
እነዚህ አገራት በጂኦግራፊ አቀማመጣቸውም፤ የአየር ንብረት ከሚሳድረው ተፅእኖም ነፃ በመሆናቸው የወባ ተጋላጭነት የሌለባቸው ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ሲሼልስ፣ ሌሴቶ፣ ሊቢያ፣ ቱኒሲያ እንደሆኑ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
@tikvahethmagazine