Thoughts ™


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Blogs


contact us @hisandphilobot
Group https://t.me/thoughtschatgr

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Blogs
Statistics
Posts filter


Forward from: BOOK SHELF
ይህንን ስራ ብዙዎቻችሁ አልጀመራችሁም።

የሚከፍለው በ Toncoin ነው።አሁን ላይ 1 ton በ 7 ዶላር እየተሸጠ ነው።

ምን ትጠብቃላችሁ ታዲያ አሁኑኑ ጀምሩ።

ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ
ከዛ የሚያመጣውን ቻናል ጆይን አድርጉ

ከዛ ጓደኞቻችሁን በመጋበዝ ብሩን መስራት

https://t.me/preton_drop_bot?start=b2f95fa3-9b7d-4c86-a1cf-ad9b3b3f19ae


ለፈገግታ

አንድ ሽማግሌ ጥቅጥቅ ያለ አውቶብስ ውስጥ ገብተው ወደ ቤታቸው ሲጓዙ በግምት 14 ዓመት የሚሞላው ልጅ ደሞ ለብቻው ተስፋፍቶ ወንበር ይዞ ተቀምጦ ሰውየው ከነምርኩዛቸው ሲንገዳገዱ ዝም ብሎ ያያቸዋል።

ባሱ አራት ኪሎ አደባባይን ሲያጠማዝዝ በጣም ስለዞረ ሽማግሌው ሚዛናቸውን መጠበቅ ተስኗቸው ባፍጢማቸው ይደፋሉ።

ይሄኔ ልጁ ከተቀመጠበት እንኳን ሳይነሳላቸው በዛ ሙጢ ድምፁ :- "ፋዘር ዱላው ጫፍ ላይኮ እንደ ጎማ አይነት ላስቲክ ቢያደርጉበት ኖሮ እንደዚህ አይፈጠፈጡም ነበር!" ..ሲላቸው ከመውደቃቸው በላይ በልጁ መሞላፈጥ ብስጭት ያሉት ሽማግሌው ምን ብለው ቢመልሱለት ጥሩ ነው ?

"አባትህም ያኔ ላስቲክ አርጎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ እኔ መቀመጫ አላጣም ነበር"

Join us @philosophyeth 


Lampros Digital Magazine will be back after some days.

Thank you all of you guys for your Support.

Stay tuned here!


#ሳይኮሎጂ_እንዲህ_ይላል

አእምሯችን አደጋን የማወቅና የመለየት አቅም አለው።

ደመ ነፍስህ የሆነ የተሳሳተ ነገር እንዳለ ከነገረህ፣ ያንን ስሜት ችላ አትበለው።


ትስማሙበታላችሁ? ሀሳብ አስተያየቶቻቹሁን አካፍሉን።


በርካታ ሀገር በቀል እውቀቶች "ስነ-ቃል" ተብለው ተረት ማሳመሪያና ጨዋታ ማድመቂያ ሆነው ቀርተዋል፣ ለምሳሌ "ሴት በዛ ጎመን ጠነዛ" በኢኮኖሚክስ አለም ያለቀለትና ለህግ የበቃ እውቀት ነው፣ "The law of diminishing marginal productivity" ተብሎ ይታወቃል፣

አንዱ ግብአት (input) ውስን ሆኖ ሌላኛውን ግብአት እየጨመርክ በመጣህ ቁጥር እያንዳንዱ ተጨማሪ ግብአት የሚያስገኝው ተጨማሪ ምርት/ ምርታማነት [marginal productivity] ከተወሰነ ደረጃ በኋላ [after reaching optimal level] እያሽቆለቆለ ይመጣል፣

ለምሳሌ ሁለት እስር ጎመን አንድ ሴት በአንድ ሰዓት ውስጥ አጣፍጣ ሰርታ ልታቀርበው ትችላለች፣ ሴቶቹን ሁለት ብታደርጋቸው የተሻለ ጣፍቶ በ45 ደቂቃ ሊቀርብ ይችል ይሆናል፣ ሴቶቹ አስር ሲሆኑ ጎመኑ ይባክናል፣ ይጠነዛል፣ ይጎመዝዛል፣ ገበታ ላይ ለመቅረብ ሁለት ሰዓት ሊወስድ ይችላል፣ ሁለት እስር ጎመን አቅርበህ በአንድ መክተፍያና አንድ ድስት ዙሪያ ሴቶቹ ስታበዛ ቦታ ይጨናነቃል፣ ሀሳብ ይበዛል፣ ወሬ ይጨምራል ወዘተ፣

* "ሴት" የሚለው ቃል የሚወክለው ጉልበትን (labour) እንጂ ፆታን አይደለም፣ for that matter አስር ወንዶችም ቢሆኑ ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፣ ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል፣ ስነ ቃል ተብለው እንዲባክኑ የሆኑ እውቀቶችን ወዲህ በሉና ትርጉም እንፈልግላቸው እስኪ፣

* "ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም" የሚለ አባባል figurative interpretation ልክክ ያለ ኢኮኖሚክስ ነው፣ ስለ human capital ነው የሚያስረዳው፣

ᴄʀᴇᴅɪᴛ ካሳ አንበሳው


እግር ኳስን ለማትመለከቱ ይህ ሰው ሮድሪ ይባላል....ስፔናዊ ሲሆን የማንችስተር ሲቲ ተጫዋች ነው።

ሮድሪና ኮንቴ ቦታቸው ብቻ ሳይሆን አኗኗራቸውም ያስገርማል

ሮድሪ ከማንችስተር ሲቲ በደሞዝ መልክ በሳምንት 220,000 ዩሮ ያገኛል(በዛሬ የብሄራዊ ባንክ ምንዛሬ 13 ሚሊየን ብር) ያገኛል።

ከደሞዙ ላይ 25% ለበጎ አድራጎት የሚሰጠው ሮድሪ፤ምንም አይነት የማህበራዊ ሚዲያ እንደዚሁም በሰውነቱ ላይ ምንም አይነት ንቅሳት የለም።

ከኳስ ጨዋታ ውጪ ሮድሪ ጊዜውን የሚያሳልፈው ወይ ሲያነብ ወይ ከቤተሰቡ ጋር ነው።

በኢኮኖሚክስ ዲግሪ ያለው ሮድሪ የቅንጦት ነገሮችን አይጠቀምም።
የሚነዳው መኪና እንኳን ሰው የተገለገለበት(used car)ነው።

Join us @philosophyeth
Group https://t.me/thoughtschatgr


''.....ሰው ሲታመም የምንጠይቀው ከቋጠሮ ሰሐን ጋር ነው... ሰው ሲታሰር ' እግዚአብሔር ያውጣህ ' የምንለው ከፍትፍት አገልግል ጋር ነው ....አራስ የምትጠይቀው ከፔርሙዝ አጥሚት ጋር ነው ... የክርስትና አባታችን ለፋሲካ አክፋዩን የሚጠብቀው ድፎ ዳቦ ና አረቄ ነው ...እዝንተኛ የምናስተዛዝነው ሰባት እንጀራ ከአንድ ሰሐን ወጥ ጋር ነው ...ሟች የምንሸኘው ከገንቦ ጠላና ከለምለም እንጀራ ጋር ነው ...የቅዱሳንና የመልአክታት ተራዳኢነት የሚጎበኘን በስማቸው ከዘከርን ነው...ሰዕለታችን በሬ ወይም በግ ነው ...ሰርጋችን ፣ ልደታችን፣ እርቃችን፣ ሹመታችን፣ አምልኳችን፣ የሚበላ ነገርን ሙጥኝ ያሉ ናቸው ...
....ሌላው ቀርቶ አንድ ሰው ተምሮ ሲመረቅ ይዘን የምንሄደለት ስጦታ ብዕር ወይንም መጽሐፍ አይደለም ፤ ኬክ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ...ነው ። በሽተኛ ስትጠይቅ ከብርቱካንና ከሙዝ ይልቅ መጽሐፍ መውሰድ እንደማላገጥ ይቆጠራል ። ጊዜውን ይገፋበት ዘንድ መጽሐፍ ማበርከት በሽተኛው እንዳይድን ከመመኘት እኩል ነው ።
ለኛ ለኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ከባዶ ገበታችን በስተዚያ የተቀመጡ ትርፍ ነገሮች ናቸው ። መጻሕፍት የሚያስፈልጉት ገበታችን ሞልቶ ከገነፈለ በኃላ ነው ብለን በይነናል። ገበታችንም አይሞላ ፤ መጻሕፍቱም አይነሱም ። ያልተረዳነው ቢኖር ለገበታ መትረፍረፍ ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ መጻሕፍት አቋራጭ መንገድ መሆናቸውን ነው ።
እንዴት ታዲያ ማንበብ መብላትን ይቅደም ? መቼ ይሆን ከምንኮራባቸው ባህሎቻችን በላይ ማንበብ ባህላችን ሆኖ የምንታወቅበት ና የምንኮራበት?......'''''
.
አለማየሁ ገላጋይ ፤ ኔሽን


የመሃመድ አሊን "ውሃና ወርቅ"ፊልም ያየ እስቲ
የመሃመድ አሊ...ሁለቱም ድንቅ ፊልሞች ናቸው።

ፊልሞቹን ለማየት የምትፈልጉ

አለም በቃኝ
ውሃና ወርቅ


በአንድ መንደር ውስጥ ሥዕል እየሳለ በውድ ዋጋ በመሸጥ የሚተዳደር ሽማግሌ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን አንድ የመንደሩ ነዋሪ የሆነ የኔ ቢጤ መጣና "አንተ ሠዓሊ ነህ። ሥዕል
እየሳልክ ብዙ ስለምታገኝ ሀብተም ሆነሀል፤ ግን ለድሆች አትሰጥም፤ ባለ ልኳንዳ ቤቱ እንኳ ሁሌ ሥጋ ለድሆች በነጻ ያድላል።"
አለው ሽማግሌው ሠዓሊም ፈገግ ከማለት ውጪ ምንም መልስ አልሰጠውም . ድሀው ሰውዬም በመንደሩ እየዞረ ሽማግሌው ሀብታም እንደሆነና ግን ስስታም እንደሆነ አናፈሰ።
የመንደሩ ሰዎች አዛውንቱን ጠሉት . . ከጊዚያት በኃላ አዛውንቱ ታመመ። አንድ እንኳ የሚያስታምመው ሰው አጥቶ ሞተ . ከዚያን ቀን በኋላ ባለ ልኳንዳው ሥጋ ማደሉን አቆመ።
ለምን እንዳቆመ የመንደሩ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁት . "እስከ ዛሬ የማድላችሁ እኮ ሠዓሊው ስለሚከፍለኝ ነው" ብሎ መለሰላቸው።
□  አንዳንዴ ነገሮችን ሳናረጋግጥ


Forward from: BOOK SHELF
የአማኑኤል_ሆስፒታል_ታሪኮች.pdf
16.5Mb
Join us for more books @bookshelfeth1

ለመፅሐፎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን @bookshelfeth1


አንድ ሰው አለ ሚስተር ሳይ ይባላል ። የሆነ ጊዜ ወደአውሮፓ መሄድ ፈልጎ በ500 ሺ ዶላር የገዛትን ሮል ሮይስ መኪናውን አስይዞ 500 ዶላር ብድር እንዲሰጠው ጠየቀ ። ተፈቀድለትና ዶላሩ ተሰጠው ። እሱም የመኪናዋን ቁልፍ ሰጥቶ ሄደ ። የባንኩ ሰራተኛም መኪናዋን እየነዳ ወደባንኩ የመኪና ማቆሚያ አስገብቶ አቆማት ። ከሳምንት በኃላ የባንኩ ማናጀርና የብድር መኮነኑ የሚስተር ሳይን አካውንት ሲያዩት ብዙ ሚሊዮን ዶላር አለው ። ይሄ ሁሉ ገንዘብ እያለው 500 ዶላር ብቻ ለምን ተበደረ የሚለው ግራ ገባቸው ።

ከ2 ሳምንት በኃላ ከነወለዱ 506.50 ዶላር ከፍሎ መኪናውን ይዞ ሲወጣ ማናጀሩና ሌሎች የባንኩ ሰራተኞች "ሚስተር ሳይ! ያ ሁሉ ሚሊዮን ዶላር እያለህ ይችን ዶላር ብቻ የተበደርከው ለምንድን ነው?" አሉት ። ሚስተር ሳይ ፈገግ ብሎ፡- "በዚህ ወቅት በ6.50 ዶላር መኪናየን ለ2 ሳምንት የሚጠብቅልኝ ከዚህ የተሻለ ታማኝ ቦታ የት አገኛለሁ?" አላቸውና ወደቤቱ ቆሰቆሰው....

📢 telegram: @philosophyeth
🤖 Bot: @hisandphilobot
📚 book channel: @bookshelfeth1


Thoughts

Screenshot ሲላክልኝ እኔ ብቻ ነኝ እነዚህን ነገሮች ማየት የሚያስደስተኝ😂


ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

ሁዋዌ ኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮ ቴሌኮምን ማስፋፊያ በሚያደርግበት ጊዜ ቻይኖቹ ጋር ተቀጥሬ እሰራ ነበር።በዚያን ወቅት ቻይኖቹ የሚበሳጩት በእኛ በኢትዮጵያውያኑ የበዓል ብዛት ነበር።

አዲስ አመት ልናከብር ነው ብለን ፍቃድ ጠይቀናቸው በሁለተኛው ሳምንት መስቀል ለማክበር ወደ ክፍለ ሀገር ልንሄድ ነው አልናቸው።ምክንያቱን ጠየቁን፤እኛም ስለ መስቀሉ መገኘት ነገርናቸው ፈቀዱልን።

ታህሳስ ላይ ገና ልናከብር ነው አልናቸው፤ምንድን ነው አሉን -የኢየሱስ ልደት ብለን መለስን እናም ፈቀዱልን ድጋሚ ከ2 ሳምንት በኋላ ጥምቀት አልናቸው...ምንድን ነው ሲሉን የኢየሱስ ጥምቀት አልናቸው....አመነጫጭቀውም ቢሆን ፍቃድ ሰጡን።

ሚያዚያ ደረሰ....ለፋሲካ ልናስፈቅዳቸው ሄድን...አሁን ደግሞ ምንድን ነው አሉን ....የኢየሱስ ስቅለት አልናቸው .....ቻይናው ሃላፊያችን ተገላገልን ሲል....ከጎኔ የነበረው ሐበሻ እሁድ ይነሳል አለው።

📢 telegram: @philosophyeth
🤖 Bot: @hisandphilobot
🤳 contact us: @FREDOBASN
📚 book channel: @bookshelfeth1


"የክብር ሽልማት"የአመቱ ምርጥ የረዥም ልቦለድ መፅሐፍ ፀሐፊ በመሆን አለማየሁ ገላጋይ በቤባንያ መፅሐፉ ተመርጧል።

በጋዜጠኝነት ደግሞ የእግር ኳስ ጋዜጠኛው መንሱር አብዱልቀኒ ተመርጧል።

📢 telegram: @philosophyeth
🤖 Bot: @hisandphilobot
🤳 contact us: @FREDOBASN
📚 book channel: @bookshelfeth1


Thoughts....

ምን ጉድ ነው?

የዜማ ጠበብቱ የያሬድ ሃውልት ነው አሉ።

ኧረ እያፈርን


LOL 😂
መንታ ሳይሆኑ እንዴት በዚህ ደረጃ ይመሳሰላል የሰው ልጅ?

አንዱ ዘማሪ አንዱ ዘፋኝ

📢 telegram: @philosophyeth
🤖 Bot: @hisandphilobot
🤳 contact us: @FREDOBASN
📚 book channel: @bookshelfeth1
ነገ  ዘረኝነት በባህላዊነት ይተካ ይሆናል። በቀደመው ጊዜ 'የኛ ዘር የተለየ ነው' ብለው ያመኑቱ ዘራቸውን ለመጠበቅ ዋጋ ከፍለዋል። ሌሎችን ዝቅ አድርገዋል። እስከመገዳደልም ደርሰዋል። አዶልፍ ሂትለር አይሁዳውያንን ለመጨፍጨፍ የዘር ካርድ መዟል። ይህን የእብድ ሃሳብ ፊደል የቆጠሩቱም ደግፈዋል።
ትላንት የተማሩ፥ የተመራመሩ ወገኖች የዘራቸውን ምርጥነት በሳይንሳዊ ማስረጃ ለማስደገፍ ታትረዋል።በዚህ ዘመን ግን 'የኔ ዘር የተለየ ተፈጥሮ አለው' ብሎ የሚሟገት ቂል ቢመጣ ሳይንስ በቀላሉ ሙግቱን ፉርሽ ያደርግበታል። ጥቁሮች ከነጭ ያነሰ ተፈጥሮ  እንደሌላቸው ግልፅ ሆናል።  እንዲህ ያለ ጨዋታ ሳይንሳዊ አይደለም።

ዛሬ ዛሬ ዘረኝነት በባህላዊነት እየተለወጠ ይመስላል። ካልቸሪዝም ገንግኖ በሬሲዝም መንበር ለመቀመጥ እያደባ ነው።

ኹሉም ወገን የራሱን ባህል ልዩ መሆን ይሰብካል። የባሰው ነገር ደግሞ ባህልን ከመጤ ባህል መጠበቅ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነገር ሆኗል። ትላንት "በዘር  የተለየን ነን" ብለው ያሰቡቱ በአመራር ደረጃ የከበረ ዘራቸውን "ከብክለት እንጠብቅ" ብለው ደም አፍስሰዋል። ምናልባት ደግሞ ነገ ምርጡን ባህል ከመጤ ባህል ለመጠበቅ በሚል የሰው ልጅ ደም ይፋሰስ ይሆናል።

በእርግጥም የሰው ልጅ ኢምክንያታዊነት የማይናቅ ጉልበት አለው!

ከ #ነገን_ፍለጋ መፅሐፍ የተወሰደ
ተስፋብአብ ተሾመ


What's your thought?
ሀሳባችሁ ምንድን ነው?

📢 telegram: @philosophyeth
🤖 Bot: @hisandphilobot
🤳 contact us: @FREDOBASN
📚 book channel: @bookshelfeth1


አሜሪካዊው ቢሊዬነር #ስቲቭ_ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው አስደናቂ መልዕክት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
((ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው))

በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው፣
,
አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ  ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ፥፥
,
✔አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀጥረው ትችላለህ፣ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን ልትቀጥረው አትችልም፥
,
✔ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው፥
,
✔አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፣
,
✔በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን  የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም፣
,
★ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፣
,
★ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ
,
👉እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል
,
👉በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም ፣
,
👉የኣንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥፥የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው ፣
,
👉ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና  አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፣
,
👉ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፣
,
…የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል
,
👉አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል  ቁልቁል ትወርዳለህ፣
,
✋እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው፥፥
ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ ፣
,
5 ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ …
☝ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው፥፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው፥፥ ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል፣
,
☝ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ ፣
,
☝የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል፣
,
☝"ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፥
,
☝ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው፣
,
☝በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ

Credit ህብረ ቀለማት

📢 telegram: @philosophyeth
🤖 Bot: @hisandphilobot
🤳 contact us: @FREDOBASN
📚 book channel: @bookshelfeth1


ሳይኮሎጂ_እንዲህ_ይላል፦

ሁልጊዜም ከሰዎች ጋር ስትገናኝ አንድ ምክንያት ይኖራል።

ሕይወትህን እንዲቀይሩልህ ትፈልጋለህ አልያም የእነሱ እንዲቀየር የምታግዛቸው ሰው ነህ!

ትስማሙበታላችሁ? ..

📢 telegram: @philosophyeth
🤖 Bot: @hisandphilobot
🤳 contact us: @FREDOBASN
📚 book channel: @bookshelfeth1

20 last posts shown.