#የኦሾ እይታዎች
* * *
#መስጠትና መበተን
"አንድ ለማኝ ከመንገድ ዳር እየለመነ ሳለ ከአጠገቡ መኪና ይመለከትና ሄዶ ያስቆመዋል ። ይኽ ለማኝ ለሦስት ቀናት ምግብ አልበላም ነበር እና ባለመኪናው ገንዘብ እንዲሠጠው ይጠይቃል ። ባለመኪናው ሠውዬ የሎተሪ እጣ አሸንፎ ሀብታም ከሆነ ጥቂት ቀናቶችን አስቆጥሯል። ወደ ለማኙ ሲመለከት የሚያየውን ነገር ማመን አልቻለም። የለማኙ ልብስ ምንም እንኳን ያረጀ ቢሆንም ሰውዬው ከደህና ቤተሠብ የመጣ እንደሆነ ደም ግባቱ ያስታውቅ ነበር ፤ ከዚያም በላይ በሚገባ የተማረ ሰው እንደሆነ ንግግሩ ያስታውቃል። "
" ባለመኪናው በጊዜው በገንዘብ የተንበሸበሸ ሰው
በመሆኑ ባለ መቶ ኖት ሩፒ (ገንዘብ) በማውጣት በለማኙ እጅ ላይ ያስቀምጣል። ይኽን ጊዜ ለመኙ ሠው ባለመኪናው የሠጠውን ገንዘብ ተመልክቶ መሳቅ ጀመረ።"
"በሁኔታው ግራ የተጋባው ባለመኪና፦ "ለምን ትስቅብኛለህ ?" ሲል ለማኙን ይጠይቃል ። "
"ይኽን ጊዜ ለማኙ ፦ " የምስቀውማ በአጭር ጊዜ
ውስጥ ዛሬ እኔ የቆምኩበት ቦታ ቆመህ እንደማይህ
ስለታወቀኝ ነው ። እኔም ለማኝ የሆነኩት በዚህ መንገድ
ነው ። በአንድ ወቅት የራሴ መኪና ፣ ንብረትና በብዙ ሺ
ዎች የሚቆጠር ገንዘብ ነበረኝ ። ነገር ግን እንዳሻኝ
ስበትን ኖሬ የምታየኝ ቦታ ለመቆም በቃሁ ። ወዳጄ!
መበተንም ሆነ መሰሰት አጥያት ነውና መስጠትን እንጂ
መበተንን አትማር ፣አታስተምር " ብሎት ሄደ ። " ይለናል
#ኦሾ/OSHO