❥:::::::::::የአሹራ ፆም:::::::::::❥
👉ከአሹራ ቀን በፊት አንድ ቀን አስቀድሞ መፃም የተወደደ ተግባር ነው። ትልቅ ምንዳንም ያስገኛል። የአሹራ ቀን ብቻ ነጥሎ ከሚፃም ሰውም የተሻለ ይሆናል።
✅ አብደላህ ኢብኑ አባስ ስራው አላህ ይውደድለትና እንዲህ አለ። የአላህ መልእክተኛ የአሹራን ቀን ፁመው ሰሀባዎቻቸውንም እንዲፃሙ ባዘዙ ጊዜ፦ ይህ ቀን እኮ አይሁዶችና ነሳራዎች የሚያልቁት ቀን ነው ተባሉ። እሳቸውም፦ የአላህ ፍቃድ ሆኖ ቀጣይ አመት ከኖርን ዘጠነኛውንም ቀን አስቀድመን እንፃማለን አሉ። ነገር ግን የቀጣዩ አመት አሹራ ከመድረሳቸው በፊት ወደ አሄራ ሄዱ።
📚(ኢማሙ ሙስሊም ሰግቦታል)
✅ ይህን በተመለከተ ኢማሙ ሻፍእይ፣ ባልደረቦቻቸው፣ ኢማሙ አህመድ፣ ኢስሀቅና ሌሎችም ኡለማዎች የዘጠነኛውና የአስረኛው ቀን በተከታታይ መፃም ይወደዳል ብለዋል። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ አስረኛውን ቀን ፁመውታል። የዘጠነኛው ቀን ግን ደርሰው ባይፃሙትም ከኖርኩ እፃመዋለሁ ብለው ነይተውታልና።
የ አሹራ ጾም👇👇👇#ነገ
የዘጠነኛው ቀን = ሮብ ኦገስት 18/2021
የአስረኛው ቀን = ሀሙስ ኦገስት 19/2021
የአስራ አንደኛው ቀን = ጁምዓ ኦገስት 20/2021
ይሆናል አላይ የወፍቀን አላህ ይወፍቃችሁ መልከቱን በፍጥነት #ሼር በማድረግ ሌላዉን ያስታዉሱ 👇👇
https://t.me/joinchat/WoR2ZKBuiN8wODBk