REDZEK CHANNEL ⒺⓉⒽ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Edutainment


BACK IN 24.02.2022
Quiz
NEWS
FUN GAMES
AMAZING FACTS
MUSICS AND OTHER
Bot @Redzekbot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Edutainment
Statistics
Posts filter






WRITE IN COMMENT WHO WANT BE


NEW ADMIN
Poll
  •   Yes
  •   No
15 votes


ታሪክን ትጥቅ ማስፈታት

ትውስታና ተስፋ ያለው ምድራዊ ፍጡር ሰው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ታሪክና ዕቅድ አለው፡፡ የሰው ልጅ ጥንታዊ ጥያቄ የሚባለው ‹ከየት መጣሁ› የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ስለ ትናንት ለማወቅ ጉጉታቸው የጨመረውና ትናንታቸውን መፈልፈል የፈለጉት ይሄንን ጥያቄ ለመመለስ ነበር፡፡ ታሪክ ያለው የሰው ልጅ ብቻ ስለሆነ፡፡

የታሪክ አንዱ ጠባዩ ድርጊቱ የተጠናቀቀ፣ ጣጣው ያላለቀ መሆኑ ነው፡፡ የታሪክ ሂደት ከጊዜ ጋር የተሠናሰለ በመሆኑ ድጊቱ ተከናውኖ ይጠናቀቃል፡፡ የድርጊቱ ተጽዕኖ ግን ሺ ዓመታትን እስከመሻገር ይደርሳል፡፡ ተጽዕኖው እንዳይቋረጥ የሚያደርጉት ሁለት ነገሮች ናቸው፡፡ የመጀመሪያው አዳዲስ መረጃዎችና ማስረጃዎች ስለሚገኙ የነበረውን ትረካ ይቀይሩታል፤ ሁለተኛ ደግሞ ቀድሞ ለተደረገ ድርጊት አዳዲስ ምልከታዎችና ትርጉሞች ይሰጡታል፡፡ ‹ለምን እንዲህ ሆነ? እንዲህ መሆን አልነበረበትም፤ እንዲህ ቢሆን ጥሩ ነበር› የሚሉ አእላፍ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡



ከትናንቱ ከመማርና ወደፊት ከመስፈንጠር ይልቅ ‹እህህ› እያሉ በትናንቱ የሚቆዝሙት ‹የታሪክ እሥረኞች - prisnores of history› ይባላሉ፡፡ የማንኛውም ነገር መበየኛቸው ትናንት ነው፡፡ ያ አካል ዛሬ ቢሻሻል፣ ቢቀየር፣ ግድ የላቸውም፡፡ ትናንት ያንን የፈጸሙት ሰዎች ቢኖሩ፣ ባይኖሩ ቁብ አይሰጣቸውም፡፡ በጥፋት ውኃ በጠፉ ሰብአ ትካት ላይ ቂም ይይዛሉ፡፡

ብዙ ጊዜ ታሪክ ጠቀስ ጠብ የሚፈጠረው በድርጊቱ ምክንያት ሳይሆን ለድርጊቱ በሚሰጠው አሁናዊ ትርጓሜ ነው፡፡ ከዘመናት በፊት የተፈጠሩ ድርጊቶችን አንሥተው ሀገሮች ጦርነት ገጥመዋል፡፡ ጎሳዎች ተጋጭተዋል፤ ማኅበረሰቦች ተለያይተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ብዙዎቹ በድርጊቱ የተሳተፉት አንድም የሉም፣ አለያም ጨርሰው ማንነታቸው አይታወቅም፡፡ ወንጀል ግለሰባዊ ነው፡፡ ሰዎች ተመካክረውና ወስነው ቢፈጽሙት እንኳን በየራሳቸው የነበራቸው ድርሻ ወሳኝ ነው፡፡ ታሪክን ለአሁን የፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም የሚፈልጉ አካላት ግን የወንጀልን ግለሰባዊ ባሕሪይ በመካድ ማኅበራዊ ባሕሪይ ያላብሱታል፡፡ እንደ ተቋምም ካየን መንግሥታት በሕግ ሀገራትንና ሕዝቦችን ይወክላሉ እንጂ ተተኪ ትውልድ የቀደመውን አይወክልም፡፡ ሀገሮችና ሕዝቦች የፈጸሟቸው ነገሮች አሉ ከተባሉም መንግሥታት ወይም የሕዝቡ መሪ የነበረው አካል ታሪካዊ ወይም መዋቅራዊ ወራሽ ነው የሚቀበላቸው፡፡



ታሪክን እንዲህ ካለው መከራ የሚያድነው እርሱን ራሱን ትጥቅ ማስፈታት ነው (disarmament of history)፡፡ ታሪክ የመማማሪያ፣ ከትናንት የተሻለ ዓለም ለመገንባት የመነሻ መሠረት፣ መልካሙን የማስቀጠያ፣ ክፉውን የማረሚያ መንገድ ስናደርገው ትጥቅ እናስፈታዋለን፡፡ ታሪክን መሣሪያ አስነግቶ ለመታኮሻ፣ ሆድ ለማባባሻ፣ ለማተራመሻ፣ ለጠብ መቆስቆሻ፣ ለእሳት መለኮሻ፣ ለቁስል መቀስቀሻ መጠቀም የጠላነውን ታሪካዊ ክሥተት እንደገና መድገም ነው፡፡ ይህ ከሆነ ታሪክ ቦንብና ፈንጅ፣ መትረጊስና ላውንቸር፣ ታንክና ኒውክሌር ታጥቋል ማለት ነው፡፡

በተረቶቻችን ውስጥ አያሌ አስደንጋጭ፣ አሳዛኝ፣ አስፈሪና አሰቃቂ ድርጊቶች አሉ፡፡ እነዚያን ተረቶች እንድንሰማቸው የሚያደርገን በሚተረቱበት ዓላማ ምክንያት ነው፡፡ የተረቱ ሞራላዊ ፋይዳ በጎ በመሆኑ፡፡ ታሪክንም ለተሻለ ሞራላዊ ፋይዳ ካልተጠቀምንበት ያታኩሰናል፡፡ ወደ ኋላ ተመልሰን ለመቀየር አንዳች ዐቅም ሆነ ዕድል በሌለን ድርጊት መነሻነት ዛሬያችንንና ነጋችንን እንድናበላሽ ያደርገናል፡፡ ታሪካችን ትጥቅ ይፍታ፡፡ ሌጣውን ታሪክ እንማርበት፣ እንገረምበት፣ እንናደድበት፣ እንደሰትበት፣ እንቆጭበት፣ እንወያይበት፣ እንከራከርበት፡፡ ታሪክ ባለ ትጥቅ ከሆነ ውይይትና ክርክር፣ መተራረምና መማማር ፈጽሞ አይኖርም፡፡ እየተታኮሱ ትምህርትም፣ ውይይትም፣ ክርክርም የለምና፡፡
ታሪካችን ትጥቅ ይፍታ።

ፀሀፊ- ዳንኤል ክብረት
🆁🅴🅳🆉🅴🅺




Forward from: Ethiopian New Music
💚💛❤️አድዋ💚💛❤️


What grade are you?
Poll
  •   12+
  •   12
  •   12-
37 votes


Gravity setting chambers are used in industries to remove A. SOx B. NOx C. suspended particulate matter D. CO
Poll
  •   CO
  •   suspended particulate matter
  •   NOx
  •   SOx
20 votes


The content is hidden


Eritrea, which became the 182nd member of the UN in 1993, is in the continent of
Poll
  •   ASIA
  •   AFRICA
  •   EUROPE
  •   AUSTRALIA
23 votes


1. Which one of the five is least like the other four?
Poll
  •   Dog
  •   MOUSE
  •   LION
  •   SNAKE
  •   ELEPHANT
24 votes


🅠🅤🅘🅩 🅦🅘🅛🅛 🅢🅣🅐🅡🅣 🅘🅝 3:00


#HOT100 MUSIC THIS WEEK


WORLD WIDE MUSICS










[ Album ]
"ከሚኒሊክ አደባባይ እስከ አድዋ ድልድይ"

እንደሚታቀው 126ኛ የዓድዋ ድል በዓል በነገው እለት "ዓድዋ ለኢትጵያዊያን ህብረት፤ ለአፍሪካ የነጻነት ጮራ! " በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል፡፡ የዘንድሮውን የዓድዋ ድል በዓል ከወትሮው በተሻለ ሁኔታ በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
አከባበሩም ከወትሮው በተሻለ ሁኔታ ለማክበር የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና አባት አርበኞች በቅንጅት እየሰሩ ሲሆን የፌዴራል ፣ የክልል ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስተ የስራ ሃላፊዎች፤ አባት አርበኞች እና መላው የከተማችን ነዋሪ በሚገኝበት በእግር ጉዞና በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ከሚኒሊክ አደባባይ እስከ ዓድዋ ድልድይ ይከናወናል፡፡
የዓድዋ ድል የአንድነት ውጤት መሆኑን በማስታወስ፤ እንዲሁም ከኛም አልፎ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ ስለሆነ ጥቃቅን ልዩነቶችን ለማጉላት ከመስራት ተቆጥበን ያለምንም ልዩነት እንደ አባቶቻችን በአንድነት ስሜት በጋራ ማክበር ይገባናል።
በዚሁ መሰረት በማለዳ በሚኒሊክ አደባባይ በሚደረገው የመክፈቻ ሥነስርዓት ተጀምሮ ወደ ሌላኛው ታሪካዊ ቦታ ወደ ዓድዋ ድልድይ በእግር ጉዞ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በመጨረሻም በዓድዋ ድልድይ በሚደረጉ የተለያዩ ዝግጅቶች የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!
የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ
የካቲት 22/2014 ዓ.ም

20 last posts shown.

112

subscribers
Channel statistics