Chernet senai/ቸርነት ሰናይ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter




በዲሲ እና አካባቢው የምትኖሩ የተዋሕዶ ልጆች የጥቅምት መድኃኔዓለም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በዕለተ ቀኑ ረቡዕ ጥቅምት 27/2017 Wednesday Nov 6/2024 በታላቅ ድምቀት ስለሚከበር ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
https://gofund.me/6816c624
ሼር.......


ማርያም ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማእምንት
ሰአሊተ ምሕረት ለውሉደ ሰብእ
ሰአሊ ለነ ኀበ ክርስቶስ ወልድኪ ይስረይ ኀጢአተነ ሰአሊ ለነ ቅድስት።
ማርያም ንጽህት ድንግል የታመነች አምላክን የወለደች ናት ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት ኀጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ከልጅሽ ወደ ክርስቶስ ለምኝልን።
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84?si=_BSH34jdXeFolTBl
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84?si=_BSH34jdXeFolTBl
Subscribe Our Channel and stay updated! 🔔
ቻናላችንን ሰብስክራይብ ላይክ ኮሜንት ሼር በማድረግ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ይከታተሉ!


የሊቀ ልሣናት ቸርነት ሰናይ ተወዳጅ የሆኑ ከሁሉም ሲዲዎች የተውጣጡ የመዝሙር ስብስቦች(collection) ዝማሬዎች ሙሉ አልበም እነሆ ተጽናኑባቸው!
https://youtu.be/UbZOjAHurfI
ሰብስክራይብ,ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
፩-ስለማይነገር ስጦታው
፪-ምን ብዬ
፫-ግባ የሰላም አምላክ ግባ
፬-ይኸው እዘምራለሁ
፭-መክፈል የማልችለው
፮-ሃይሌን ጉልበቴን ታድሳለህ
፯-እንደ ቅዱስ ዳዊት
፰-ማዕበል ወጀቡን ገሰጸልኝ
፱-ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ
፲-የሰማይም የምድርም ጌታ
፲፩-ተነስቷል ጌታ ተነስቷል
፲፪-ባንተ ነው የቆምኩት ጌታዬ
፲፫-በዝተናል በዝማሪያችን
Subscribe Our Channel and stay updated! 🔔
ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ይከታተሉ!!


እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ቂርቆስ የልደቱ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

ጥቅምት - 15 - ቀን ቅዱስ ቂርቆስ የተወለደበት ቀን ነው ።
የሕፃኑ ቂርቆስ አባት ቆዝሞስ ይባላል፣
እናቱ ደግሞ ቅድስት ኢየሉጣ ትባላለች
ከርእሰ አድባራት ወገዳማት ጣና ቂርቆስ አንድነት ገዳም የተገኘው ጥንታዊ የብራና ገድለ ቂርቆስ እንደሚያስረዳው የቂርቆስ ልደት ጥቅምት 15 ቀን ሲኾን ዕረፍቱ ደግሞ ጥር 15 ቀን ነው ።
የሰማዕቱ የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ ምልጃቸው በረከታቸው አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን።
https://youtube.com/@chernetsenai?si=9HP8ctpGArLrO28_
ሰብስክራይብ ሼር ........ያድርጉ


ባንተ ነዉ የቆምኩት ጌታዬ
ሞት እኮ ነበረ እጣዬ
ለወጥከዉ ቀየርከዉ ሁሉን
ምንድነዉ ምከፍልህ አሁን

አዝ=====
እልፍኜን ዳሰስኩት ያለኝን ልከፍልህ
በምድር በረከት ጌታዬ ላከብርህ
ግን አትደሰትም በሚያልፈዉ ስጦታ
ልቤን ከፈትኩልህ ንገስበት ጌታ/2/

አዝ=====
ትምክህቴ ስለሆንክ የህይወቴ ዋስትና
በቤትህ እኖራዉ ዳግም እንደገና
ከሞት ጋር ስፋጠጥ ስንዝር ሲቀረኝ
በመካከል ገብተህ ክንድህ ሰወረኝ/2/

አዝ=====
ትዝ ይለኛል ዉዴ ያደረክልን ሁሉ
ያሻገርከኝ ባህር ተራራዉ ገደሉ
ማን ያሸንፍ ነበር ለብቻዉን ሆኖ
እኔ ግን አለፍኩት ልቤ ባንተ ታምኖ/2/

አዝ====
ክንዴ የዳዊት ነዉ ጸሎቴ የሀና
አይጠፍም ከአፌ የክብርህ ምስጋና
አትፈቅድለትም ማንም እንዲነካኝ
የአባትነት ፍቅርህ ሀይልህ ነዉ የሚያሰመካኝ/2/
https://youtu.be/LH5Bopf9Q6k?si=0ByGoiLQEz5IF3bw
https://youtu.be/O_wJBKpL9rg
*ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሰናይ*
ሰብስክራይብ,ሼር............ያድርጉ


ማዕበል ወጀቡን ገሰፀልኝ
በቤቴ ሠላም ሰፈነልኝ
ከሚያስደነግጥ ከሚያስፈራ
አዳነኝ ጌታ ከመከራ
በመንገዴ አለ በጉዞዬ
ከኔ ጋራነው በኑሮዬ
አልፈራም ከቶ በዘመኔ
የጌቶች ጌታ አለ ጎኔ
አዝ…………
አለት ነው ስሙ መሸሸጊያ
የበረታ ጦር ጠላት መውጊያ
ከሞት ከተማ ከሸለቆ
ማነው ያልወጣ ስሙን ታጥቆ
አዝ…………
አለ በልቤ የኔ ጌታ
ነብሴን ይመራል በፀጥታ
አልፍገመገም በመከራ
ያልፋል ስቃዩ በየተራ
አዝ…………
ከቋንቋ በላይ ሆኖብኛል
አፌ ሊያወራ መች ይችላል
እፁብ ድንቅ ነው ለዘላለም
ለኔ እንደ ጌታ ማንም የለም
አዝ………
ጣራው ይነደል የጎጆዬ
ጌታዬም ይግባ ከጓዳዬ
የናርዶስ ሽቱ ላፍስስለት
አምላክ ነውና ልስገድለት
https://youtu.be/DmWkeX11Tqs
ግጥም፦ሊቀ ትጉኀን መኩሪያ ጉግሣ
ዜማ፦ሊቀ ልሣናት ቸርነት ሠናይ
https://youtu.be/DmWkeX11Tqs
ሰብስክራይብ ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ


ቅዱስ አማኑኤል በምሕረት አይኖቹ ይመልከተን!

"በምሕረትህ እየን አማኑኤል"

መዝሙሩን ለማድመጥ ሊንኩን ይጫኑት

https://youtu.be/_iPGAPuLQhI
https://youtu.be/K4AGb4oYmXE
Subscribe Our Channel and stay updated! 🔔
ቻናላችንን ሰብስክራይብ ላይክ ኮሜንት ሼር በማድረግ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ይከታተሉ!




ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐገራችንን ኢትዮጵያን በምልጃው በቃልኪዳኑ ይጠብቅልን!

ፈጥነህ ቅረበን ጊዮርጊስ
ለአምላክህ የታመንክ እስከሞት
አክሊልን አገኘህ ፍጡነ ረድኤት
መዝሙሩን ለማድመጥ ሊንኩን ይጫኑ
https://youtu.be/OIh8NKjpG9E
https://youtu.be/OIh8NKjpG9E
https://youtu.be/OIh8NKjpG9E
Subscribe Our Channel and stay updated! 🔔
ቻናላችንን ሰብስክራይብ ላይክ ኮሜንት ሼር በማድረግ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ይከታተሉ!


እንኳን ለብዙኃን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የግሸኗ ማርያም በያለንበት በምልጃዋ በቃል ኪዳኗ ትጠብቀን።

"ይኸው ዘምራለሁ"
https://youtu.be/RDl4e2BufAI
"ስለረዳሽኝ እመቤቴ"
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
"ሰባቱ የእሳት መጋረጃዎቹ"
https://youtu.be/iCuRJ_W73qs
"ክብርት ነሽ"
https://youtu.be/kklDFU-jAcI
"ነይ ነይ ሱላማጢስ"
https://youtu.be/MUOe5m4x4iA
"እመቤቴ ምርኩዜ ረዳቴ"
https://youtu.be/gYFZiG6tsNk
"ብሶቴን ላንቺ እንግራለሁና"
https://youtu.be/bALJWIN8A7I
"ማርያም እጣን ናት"
https://youtu.be/Uy0M89DeIh8
"ከተለዩ የተለየሽ"
https://youtu.be/cJg9aFGRfgw
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
ሼር...ሼር...ሼር.............ያድርጉ






እንኳን አደረሳችሁ
እናታችን ቅድስት ኪዳነምሕረት  ሁላችንንም በያለንበት በምልጃዋ በቃልኪዳኗ ትጠብቀን።

"ይኸው ዘምራለሁ"
https://youtu.be/RDl4e2BufAI
"ስለረዳሽኝ እመቤቴ"
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
"ሰባቱ የእሳት መጋረጃዎቹ"
https://youtu.be/iCuRJ_W73qs
"ክብርት ነሽ"
https://youtu.be/kklDFU-jAcI
"ነይ ነይ ሱላማጢስ"
https://youtu.be/MUOe5m4x4iA
"እመቤቴ ምርኩዜ ረዳቴ"
https://youtu.be/gYFZiG6tsNk
"ብሶቴን ላንቺ እንግራለሁና"
https://youtu.be/bALJWIN8A7I
"ማርያም እጣን ናት"
https://youtu.be/Uy0M89DeIh8
"ከተለዩ የተለየሽ"
https://youtu.be/cJg9aFGRfgw
   ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
ሼር...ሼር...ሼር.............ያድርጉ


ለፆመ ፍልሰታ ተስማሚ የሆነ የእመቤታችን ጥዑም ዝማሬ!

ይኸው እዘምራለሁ ለእመቤቴ
የፍቅሯ በረከት ገብቶ ቤቴ
ስለጎበኘችው ጎስቋላው ህይወቴን
አመሰግናለሁ ድንግል እመቤቴን

አ፤ዝ====
ስላበሰችልኝ እምባዬን ከፊቴ
ይኸው እዘምራለሁ ለድንግል እናቴ
በስቃይ መከራ ቀርቷል መከፋቴ
የብዙሀን እናት ገብታለች ከቤቴ

አ፤ዝ====
በድንግዝግዝ ማየት ቀርቶልኛል ለእኔ
በፍቅር እጆቿ ተዳሶልኝ አይኔ
ሀዘኔን በእንባዬ ብነግራት ብሶቴን
ይኸው በበረከት ጎበኘችው ቤቴን

አ፤ዝ=====
ምስቅልቅሉ ወጥቶ የደፈረሰብኝ
ተስተካክሎልኛል በድንግል ጠርቶልኝ
እንባዬን ፀሎቴን ጩኸቴንም ሰምታ
ፈጥና ጎበኘችኝ በረድኤት መጥታ

አ፤ዝ=====
ቀን ከሌት ሳቃስት በከበደኝ ሸክም
አገዘችኝ ድንግል ደክሜ ሳልሰጥም
እጇ ስለሳበኝ ወጣሁን ከጉድባው
ለክብሯ ልዘምር እጆቼን አነሳው
እናታችን ቅድስት ኪዳነምሕረት በምልጃዋ በቃልኪዳኗ  አትለየን!

ሊንኩን በመጫን መዝሙሩን ያድምጡ

https://youtu.be/RDl4e2BufAI
https://youtu.be/RDl4e2BufAI
https://youtu.be/RDl4e2BufAI
   ሰብስክራይብ ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ






ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ከኔጋር ስለሆንሽ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ምስጋናሽን ይዤ ጠዋት ማታ ፊትሽ እቆማለሁ
ምስጋናሽን ይዤ እመቤቴ ፊትሽ እቆማለሁ /፪

ሀዘን ትካዜዬ ባንቺ ተወግዷል
ልመና ፀሎቴ ሀሳቤ ተሟልቷል
ያጣሁትን ሁሉ አግኝቼብሻለሁ
በእናትነትሽ ዘወትር እመልካለሁ
አዝ....

ባንቺ ደስ ይለኛል ያርፋል ልቦናዬ
ሰዓሊ ለነ ብዬ ተቃና ጉዞዬ
አልፈራም እንግዲህ ገደል እንቅፋቱን
ይዘሽኛልና ድንግል አዛኝቱ
አዝ....

የተስፋ መብራቴ አትጠፊም ከፊቴ
መድኃኒቴ አንቺ ነሽ ለብቸኝነቴ
ይች አለም ብትከፋ ፊቷን ብትመልስ
ጨክነሽ አታውቂም እናቴ በኔስ
አዝ....

ምስክር አልሻም ከእንግዲህ በኃላ
ነብሴ ትጮሀለች አማላጄ ብላ
አወድስሻለሁ እናቴ እመቤቴ
በኑሮዬ ሁሉ እስከለተ ሞቴ
አዝ....

መዝሙሩን ሊንኩን በመጫን ያድምጡ
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
የእመቤታችን ምልጃ ቃልኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን
መልካም እለተ ሰንበት!
ሰብስክራይብ ሼር...........




የሊቀ ልሣናት ቸርነት ሠናይ ቁጥር-፯ ተወዳጅ የሆኑ መዝሙራት ከሰዓታት በኋላ በይቲዩብ ይለቀቃል ሁላችሁም የተዋህዶ ልጆች ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ሰብስክራይብ በማድረግ መዝሙሩን ማግኘት ትችላላችሁ!
፩-አለኝ ውዳሴ
፪-እስኪ ላመስግንህ ተንበርክኬ
፫-ሰባቱ የእሣት መጋረጃዎቹ
፬-ለብድራትህ
፭-በፈረሰው ቦታ
፮-ይጋር ሰሀዱታ
፯-ነይ ነይ ሱላማጢስ
፰-በታች በምድር በላይ በሰማይ
፱-ኢየሱስ
፲-ክብርት ነሽ
፲፩-የነፍሴ አርነት
፲፪-የንጉሡ ልጅ ነኝ
፲፫-አንተ ነህ ሐገሬ
፲፬-ጴጥሮስ ወጳውሎስ
https://youtube.com/channel/UCvfxFdhb_mRaQ3IrHeXgOvA
ሼር.......

20 last posts shown.