Posts filter


ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለመንፈሳዊ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም #join ሳይል እንዳያልፍ button ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇


ሰላም👋
ዘሬ በአማራ ክልል ስለሚገኘው ስለ
#ወሎ የህዝብ ክፍል እነፀልይ

#ወሎ(አማራ)
ዋና ቋንቋ፡
#አማርኛ
ትልቁ ሀይማኖት፡
#እስልምና

የህዝብ ብዛት: 6,492,000
ክርስቲያን፡ 188,282 (2.90%)
ወንጌላዊ፡ 12,985 (0.20%)

#መጽሐፍ_ቅዱስ፡ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ አለ
#ኢየሱስ_ፊልም፡- አለ
#የወንጌል_የድምጽ_ቅጂዎች፡- አለ
#የወንጌል_ሬዲዮ፡ የለም

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
- - - - - - - - - - - - - - - - - -
“ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው። እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
የዮሐንስ ወንጌል 17:1-3
- - - - - - - - - - - - - - - - - -

#የፀሎት_ረዕስ

#1 አብንና ወልድን አውቀው የዘላለም ህይወት እንዲሆንላቸው
#2 ልባቸውን እግዚአብሔር  ለወንጌል ይከፈት ዘንድ
#3 ሰራተኞችን እንዲልክ ሰራተኛ እኛን አድርጎ እንዲልከን, የተላኩ ሰራተኞች እግዚአብሔር በፍሬ እንዲባርካቸው

#Pray_for_wello ☪️
#Pray_for_wello☪️
#Pray_for_wello ☪️


ዓላማን ሳይለቁ ውጣ ውረዶችን የማስተናገድ ሰፊነት

“በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊል 4፡12-13)፡፡

አንዳንድ ጊዜ አንድን ነገር ጀምረን ገና አንድ እርምጃ ሳንራመድ ውጣውረዶች በሕይወታችን ብቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሰፊነታችን ወሳኝ ነው፡፡

በሚመጡት ውጣውረዶች በመጨናነቅ እነሱ እስከሚወገዱ ዓላማችን ይገታል ወይስ ውስጣችንን ሰፋ አድርገንና ጌታችንን አምነን በዙሪያችን ምንም አይነት ማዕበል ቢነሳ ወደፊት እንገሰግሳለን? ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ምንም እንኳን ሙታንን እስከማስነሳት የደረሰ የምነት ሰው ቢሆንም በተለያዩ ውጣ ውረዶች ማለፍ ነበረበት፡፡ ለእርሱ እምነት ማለት ካለምንም ችግር መኖር ሳይሆን በምንም ነገር ውስጥ ለማለፍ የሚያስችል ኃይል ሊሰጠው የሚችለውን ጌታ ማመን ማለት ነበር፡፡

ልበ ሰፊዎች ከሌሎቹ የሚለዩት በጊዜአዊ ደስታም ሆነ ኃዘን ከጨበጡት ዓላማቸው የአለመነቃነቃቸው ዝንባሌ ነው፡፡ ይህንን ሰፊነት ለመለማመድ ደግሞ ልክ እንደነሱ ልንገነዘባቸው የሚገቡን እውነታዎች ይኖራሉ፡፡

1. የተዛባውን አመለካከት ማስተካከል

“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ”” ዮሐ. 16፡33

ክርስቶስ እዚህ ጋር ሊያሳስበን የፈለገው እውነታ፣ ሰላማችን ከሚነጥቁ ሁኔታዎች አንዱ በአለም ሳለን ምንም መከራ እንደሌለብን ስንቆትርና መከራው ሲደርስ የሚገጥመን የመናወጥ ሁኔታ ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰላም እንዲኖራችሁ በማለት በአለም ያለውን እውነታ የሚነግረን፡፡ ስለዚህም በምንም አይነት ውጣ ውረድ ውስጥ ብናልፍም እንኳን ሳንናወጥ ለመኖር በክርስቶስ እስካለሁ ድረስ ምንም አይደርስብንም የሚለውን የተዛባ አመለካከት ማስተካከል የግድ ነው፡፡

2. የሁኔታዎችን ጊዜያዊነት መገንዘብ

“በክርስቶስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤አጽንቶም ያቆማችኋል” (1ጴጥ. 5:10)፡፡

እውነቱ አጭርና ግልጽ ነው! መከራ ለጥቂት ጊዜ ነው፡፡ መከራው ካለፈ በኋላ ግን መልሶ የሚበረታና እስከመጨረሻው የሚያጸና ጸጋ ይሰጠናል፡፡ በዚህ መለኮታዊ አሰራር ደግሞ ደስ ልንሰኝ ይገባናል፡፡ “ምክንያቱም ቀላልና ጊዜያዊ የሆነው መከራችን ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብር ያስገኝልናል” (2ቆሮ. 4:17)፡፡

3. የችግርን ጥቅም መገንዘብ

“በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ምክንያቱም ፈተናን ሲቋቋም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሰጠውን ተስፋ፣ የሕይወትን አክሊል ያገኛል” (ያዕ. 1:12)፡፡

በምንም አይነት ፈተና ውስጥ ብናልፍ ያንን ለመቋቋም ስንወስን ሽልማትን ከጌታ እንቀበላለን፡፡ ይህ ሽልማት ቀደም ብለን በተመለከትናቸው ትቅሶች መሰረት ምድራዊ ገጽታ ሲኖረው በያእቆብ መልእክት መሰረት ደግሞ ዘላለማዊ ክብርና አክሊል የሚሰጥ ሽልማት ነው፡፡ ይህንን መገንዘብ ይህ ነው የማይባል ሰፊነትን ይሰጠናል፡፡

የሚቀጥለው ትምህርት፡ “መርህን ሳይለቁ በዓለም የመሰማራት ሰፊነት”

@revealjesus


ዓላማን ሳይለቁ ውጣ ውረዶችን የማስተናገድ ሰፊነት


የእግዚአብሔር ጊዜ ከኔ ጊዜ ይለያል 🙏
         
@revealjesus


ሁሉን በማስተናገድ እውነቱ ጋር የመድረስ ሰፊነት

“ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ” (1ተሰ. 2፡20-21)፡፡

አንዳንድ ሰዎች፣ “ምንም አላይም፣ ምንም አልሰማም፣ ምንም አልሞክርም” በማለት ሁለንተናቸውን ጥርቅም አድርገው መዝጋት ብስለትና ማስተዋል ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ጥንቁቅነት ሊመስል ይችላል፣ ትክክለኛውና ሚዛናዊው መንገድ ግን አይደለም፡፡

በሳል ወደሆነ ሰፊነት አልፈን ስንሄድ ከምን አይነት ሁኔታ መሸሽ እንዳለብንና የትኛውን ደግሞ በማስተናገድ አጣርተን መቀበል እንዳለብን በሚገባ ወደመገንዘብ እንመጣለን፡፡ ስለዚህም፣ የተለያዩ ሃሳቦችን ማስተናገድ ማለት ከተለያዩ ሃሳቦችን በመሸሽ ሳይሆን አውቀናቸው ባመንንበት እውነት የመጽናት ሰፊነት ማለት ነው፡፡

ይህ ሰፊነት ግን ታላቅ ጥንቃቄ የሚጠይቅና አቅምን ማወቅ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች ይህንን መርህ እንዳዳብር ሊረዱኝ ይችላሉ፡፡

1. ባመንኩት እምነትና እውነት በሚገባ በመብሰል መደላደል

“እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደተቀበላችሁት እንዲሁ በእርሱ ኑሩ፤ በእርሱ ተተክላችሁና ታንጻችሁ፣ እንደተማራችሁት በእምነት ጸንታችሁ፣የተትረፈረፈ ምስጋና እያቀረባችሁ ኑሩ” (ቆላ. 2:6-7)፡፡

ወደ እኔ የሚመጣውን ሁሉ በሚገባ በመመዘንና በማጣራት ለመኖር በቅድሚያ በተማርኩበት ትምህርት መጽናት አስፈላጊ ነው፡፡ ክርስቶስን በማመንና በማወቅ መታነጽ፣ መተከልና፣ በተማርነው እምነት መጽናት ወደ እኛ ለሚመጣው ለማንኛውም ነገር ዝግጁ እንድንሆን ያግዘናል፡፡ ለሚነፍሰው የተለያየ የትምህርትና የፍልስፍና ነፋስ ዝግጁ የሆነን መሰረት በመጣል ራሳችንን ለዚህ አይነቱ ሰፊነት ማዘጋጀት እንችላለን፡፡

2. ወደእኔ የሚመጣውን የመለየት ስራ መስራት

“የቤርያ ሰዎች ከተሰሎንቄ ሰዎች ይልቅ አስተዋዮች ነበሩ፤ምክንያቱም ነገሩ እንደዚህ ይሆንን እያሉ መጻሕፍትን በየዕለቱ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጒጒት ተቀብለዋል” (የሐዋ. 17:11)::

የቤሪያ ሰዎች የኖሩበት ዘመን የተለያዩ የትምህርት ነፋሶች የሚነፍሱበትና የግሪክ ፍልስፍና የበዛበት ዘመን ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን በፍርሃት ራሳቸውን አልሸሸጉም፡፡ ወደ እነሱ የሚመጣውን የተለያየ ሃሳብ በመመርመር የቃሉን እውነት ብቻ ጥንፍፍ አድርገው በማውጠት ይቀበሉ ነበር፡፡ እነዚህን ሰዎች ቃሉ አስተዋዮች (ልበ ሰፊዎች) ይላቸዋል፡፡

3. የዘመኑን መንፈስን መመርመር

“ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ” (1ዮሐ. 4:1)፡፡

አንዳንድ ሰዎች “ታላቅ ነኝ፣ ተቀብቻለሁ፣ ተልኬያለሁ …” ብሎ ራሱን የሰየመውን ሁሉ ካለምንም ምርመራ የመቀበል የሞኝነት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ሆኖም፣ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጥ ይናገራል” (1ጢሞ. 4:1-2)፡፡ እንደዚህ መሰል ባለንበት ዘመን የሚገኙትን የመናፍስት አሰራር በሚገባ መመርመር አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚሰራው መናፍስትን የመለየት መለኮታዊ አሰራር በእኛ ሲያድር የዘመኑን መንፈስ እየመረመርን ትክክለናውን መውሰድን እንማራለን፡፡

የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ዓላማን ሳይለቁ ውጣ ውረዶችን የማስተናገድ ሰፊነት”


@revealjesus


ሁሉን በማስተናገድ እውነቱ ጋር የመድረስ ሰፊነት


ሰዎችን ከድካማቸው ለይቶ የማየት ሰፊነት

“በሥጋዬም ፈተና የሆነባችሁን ነገር አልናቃችሁትምና አልተጸየፋችሁትም ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ አዎን እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ” (ገላ. 4፡14)፡፡

በቅርባችን የሚገኙ በማንኛውም ደረጃ የምናገናቸው ሰዎች አንድ ድካም ስላገኘንባቸው ብቻ የምንለያቸው ቢሆን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብቻችንን እንደምንቀር ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት ከሰዎች ጋር ጥቂት ካሳለፍን በኋላ አንዳንድ ደካማ ጎናቸውን ማየት ስለምንጀምር ነው፡፡

ሰዎችን ከድካማቸው ለይቶ በመመልከት ማስተናገድ ማለት ድካማቸውንና ማንነታቸውን በማወቃችን ምክንያት ሳንንቃቸውና ሳናቃልላቸው ሰዎቹን የመቀበል ሰፊነት ማለት ነው፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን አይነቱን ተቀባይነት ከገላትያ ሰዎች እንዳገኘ ነው ከላይ ባሰፈርነው ክፍል ውስጥ የሚናገረው፡፡ የገላትያ ሰዎች በጳውሎስ ላይ የሚፈትናቸው ሁኔታ እንደነበረ በግልጽ ተናግሯል፡፡

ሆኖም፣ የገላትያ ሰዎች ልክ ምንም ደካማ ባይኖረው ኖሮ ሊቀበሉት በሚችሉበት ሁኔታ ሲቀበሉት እናያለን፡፡

ይህንን እውነታ ለመለማመድ እንድንችል አንዳንድ እውነቶችን ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡

1. ፍጹም የሆነ ሰው እንደሌለ ማስታወስ

“ጻድቅ ማንም የለም፤ አንድም እንኳ” (ሮሜ 3:10)፡፡

ስፍራ ቢበቃን ኖሮ የመጽሐፍ ቅዱስን ኃያላን ሰዎች በመዘርዘር መመልከት እንችላለን፡፡ ሙሴ በቁጣ ጽላቱን ሰብሯል፡፡ ዳዊት በምንዝርናና በነፍስ ግድያ ተገኝቷል፣ ኤልያስ መሞትን እስከሚመኝ ድረስ ፈርቶ ነበር፡፡ ጴጥሮስ በጳውሎስ እስከሚገሰጽ ድረስ ግብዝ ነበር፣ እንዲሁም ክርስቶስን ክዶ ነበር፡፡

እነዚህና መሰል ታላላቅ ሰዎች ድካማቸውን አልፈው ከተቀበሏቸው ሰዎች የተነሳ አሸንፈው ጌታን አክብረዋል፡፡

2. ደካሞችን መርዳት

“ደካሞችን እርዷቸው” (1ተሰ. 5፡14)፡፡

የዕብራውያን ጸሐፊ “በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህን የለንምና” (ዕብ. 4፡15) በማለት ክርስቶስ ኢየሱስ የቀደደልን መንገድ ይጠቁመናል፡፡

ስለዚህም፣ ሰዎች ድካም እንዳለባቸው በማወቅ ከእነሱ ፍጽምናን ከመጠበቅ ይልቅ እነሱን የመርዳት ዝንባሌ ሊኖረን እንደሚገባ ያስታውሰናል፡፡

“መንፈስ በድካማችን ያግዘናል” (ሮሜ 8፡26) የሚለውም ቃል ቢሆን በውስጣችን ያደረው የጌታ መንፈስ ድካምን የሚያግዝ መንፈስ እንደሆነና እኛም ያንን መንፈስ የጠጣን ሰዎች ከድካማቸው የተነሳ መተው ሳይሆን በድካማቸው ማገዝ እንደሚገባን ያሳስበናል፡፡

3. የእኛን ደስታ ማዘግየት

“እኛ ብርቱዎች የሆንን፣ የደካሞችን ጉድለት መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም” (ሮሜ 15፡1)፡፡

ሰዎችን በድካማቸው ለማገዝ ለጊዜው የእኛን ደስታ ማዘግየትን ይጠይቀናል፡፡ ለምሳሌ በእውቀት አሁን የደረስንበት ደረጃ ከመድረሳችን በፊት እስከሚገባን ድረስ የታገሱንን ሰዎች ማስታወስ ከባድ አይደለም፡፡

አንድን በህመም የደከመን ሰው ለመርዳት ከእርሱ ቀስታ እኩል መራመድና የመፍጠን ፍላጎታችንን መግታት የግድ ነው፡፡ ይህ አመለካከት ግን ሰፊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚለማመዱት አመለካከት ነው፡፡ “ደካሞችን እመስል ዘንድ፣ ከደካሞች ጋር እንደ ደካማ ሆንኩ” (1ቆሮ. 9:22)፡፡

የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ሁሉን በማስተናገድ እውነቱ ጋር የመድረስ ሰፊነት”


ሰዎችን ከድካማቸው ለይቶ የማየት ሰፊነት


ሰላም ለሁላችሁ!

“የታደሰ አእምሮ” በተሰኘው ርእስ ስር ባለፈው የተመለከትናቸው ሃሳቦች “ሰማያዊ አመለካከት”“ንጹህ አመለካከት” እና “ስልታዊ አመለካከት” የሚሉትን ነው፡፡ ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት ደግም የምንመለከተው፣ “ሰፊ አመለካከት” የሚለውን ሃሳብ ነው፡፡

ሰፊ አመለካከት

ጠቢቡ ሰሎሞንን በአለም ዙሪያ ታዋቂ ካደረጉት ባህሪዎቹ አንዱ ልበ ሰፊነቱ ወይም የአመለካከቱ ሰፊነት ነው፡፡

“አምላክ ለሰሎሞን ጥበብንና እጅግ ታላቅ ማስተዋልን እንዲሁም በባሕርዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋትን ሰጠው” (ምሳ. 4፡29)፡፡

ከዚህ ሰፊነቱ የተነሳ ነበር ከተለያዩ ክፍላተ-አለማት የእርሱን ጥበብና ፍርድ ለማየትና ለማድመጥ ሰዎች ይመጡ የነበረው፡፡ ይህ ሰፊነቱ ከተለያዩ ነገስታት ጋር ላለው የፖለቲካም ሆነ የንግድ ግንኙነት መሰረታዊና አስፈላጊ ነበር፡፡ ይህ ሰፊነቱ በሕዝቡ መካከል በትክክል እንዲፈርድ አስችሎትም ነበር፡፡

በተለያዩ የሕይወት አቅጣጫዎች ከጠባብነት ወጥተን አመለካከታችንን ስናሰፋ የተሳካ ሕይወት ውስጥ እንገባለን፡፡ ይህ የብልሆችና የጥበበኞች መንገድ ነውና፡፡ “ተላላ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤ የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል” (ምሳ. 18፡2)፡፡

ሁል ጊዜ በአንድ ጉዳይ ላይ ግራና ቀኙን በሚገባ ሳንገነዘብ ያቀባበልነውን ሃሳብ ብቻ ለመልቀቅ ከመዘጋጀት የወረደ ሕይወት ወጥተን ወደ አስተዋይነት እንድንገባ ሰፊ አመለካከት ወሳን ነው፡፡

የዚህ ክፍል አላማ አንድ አማኝ ስለ ሰፊ አመለካከት ሊያውቃቸው የሚገባውን መሰረታዊ እውነታዎች መግለጽ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የምናጠናቸው አምስት ዋና ዋና እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ሰዎችን ከድካማቸው ለይቶ የማየት ሰፊነት

“በሥጋዬም ፈተና የሆነባችሁን ነገር አልናቃችሁትምና አልተጸየፋችሁትም ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ አዎን እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ” (ገላ. 4፡14)፡፡

2. ሁሉን በማስተናገድ እውነቱ ጋር የመድረስ ሰፊነት

“ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ” (1ተሰ. 2፡20-21)፡፡

3. ዓላማን ሳይለቁ ውጣ ውረዶችን የማስተናገድ ሰፊነት

“በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊል 4፡12-13)፡፡

4. መርህን ሳይለቁ በዓለም የመሰማራት ሰፊነት

“ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም። እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም” (ዮሐ. 17፡15-

5 ትህትናን ሳይለቁ ምስጋናን የመቀበል ሰፊነት

“ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም” (ምሳ. 27:2)፡፡

Will See you tomorrow morning!


https://youtu.be/3igcTI9JPd8?si=cgW8UF6iwmfy0PBk

🚀 Best online investment platform for gold🚀
Celebrating Our Members’ Successful Withdrawals!
Join Allied Gold Today – Your Success Story Starts Here!
💡 Online Earnings Made Effortless
💡 Partner with Excellence, Grow with Gold
Why Choose Allied Gold?
✅ Trusted by 100,000+ Investors Worldwide
✅ Secure Gold-Backed Investments with 24/7 Transparency
✅ Instant Withdrawals & Dedicated Support
https://t.me/Allied_Gold
https://www.alliedgoldinvestment.com/?invitation_code=B6897


☝️አንድ የፀሎት ርዕስ => #ነብሳት
☝️የዛሬው የፀሎት ርዕስ => በ
#ፓኪስታን ለሚገኙ ላልተደረሱ #ሰዪድ ነብሳት

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
- - - - - - - - - - - - - - - - - -
“ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን ሁሉ፣ #ምድርም_የእግዚአብሔርን_ክብር_በማወቅ_ትሞላለችና።”
ዕንባቆም 2:14
- - - - - - - - - - - - - - - - - -

#Pray_for_sayyid ☪️🕋
#Pray_for_sayyid☪️🕋
#Pray_for_sayyid ☪️🕋


ተልእኳችን ማለዳ
መጋቢት 6- 2017

ረመዷን ጾም ቀን -15-
የመጸሐፍ ቅዱስ ምንባብ፡- ዩሐንስ ወንጌል 14፡ 6

ኢየሱስም፡— እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።


ብዙ ሰዎች ሲሞቱ ወደ መንግሥተ ሰማያት መሄድ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ—ገነት የዘላለም መዳረሻቸው ተስፋ ነው። ነገር ግን ብዙዎቹ ተመሳሳይ ሰዎች ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚወስደው መንገድ እንደ ጎግል ካርታ ነው ብለው ያምናሉ - እዚያ ለመድረስ ብዙ መንገዶች አሉ እና እርስዎ የመረጡትን ለመምረጥ ነፃ ነዎት። ይሁን እንጂ በዮሐንስ 14፡6 ላይ ኢየሱስ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። በሌላ አነጋገር፣ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት በሚወስደው መንገድ ላይ ምንም አማራጮች የሉም ብቸኛው አማራጭ አንድ አለ እርሱም ኢየሱስ ነው።

ኢየሱስ ይህን ግልጽ በሆነ መንገድ የተናገረዉ አንዳንድ ግራ በሚያጋቡ ጊዜያት ነዉ። በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13 ላይ፣ ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት በነበረው ምሽት ለደቀ መዛሙርቱ ከመካከላቸው አንዱ አሳልፎ እንደሚሰጠው (ዮሐንስ 13፡21)፣ ሊተዋቸው እንደሆነ (ዮሐንስ 13፡33) እና ጴጥሮስ እንደሚክደው ነገራቸው (ዮሐንስ 13፡38)። ደቀ መዛሙርቱ ሕይወታቸውን ያዋሉበት ነገር ሁሉ በዙሪያቸው እየፈራረሰ ሲሄድ ምን ያህል የጠፉ፣ ግራ የተጋቡ እና ተስፋ ቢስ እንደሆኑ መገመት እችላለሁ።
እንግዲያው ኢየሱስ በጽሑፋችን ላይ የተናገረው ሐሳብ ምን ያህል አጽናኝ ሊሆን እንደሚችል አስቡ! ኢየሱስ ታላቅ ፍርሃታቸውን ለማቃለል ወሳኝ ማረጋገጫ ሰጥቷቸዋል—መለያየታቸው ጊዜያዊ ነው፣ እንደገና መገናኘታቸው ዘላለማዊ ይሆናል፣ እና እሱ፣ ኢየሱስ እነሱን ለማግኘት ተመልሶ ይመጣል፡-

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በዳግም ምጽአቱ (በትንሳኤው ብቻ ሳይሆን በዳግም ምጽአቱ 1) እና ዘላለማዊ መገናኘታቸውን ካጽናና በኋላ፣ ግራ መጋባትን የሚያቃልልባቸውን ቃላት ተናግሯል፡- እኔ የምሄድበትን ብቻ ሳይሆን ወደምሄድበት ቦታ መድረሻ መንገዱንም ታውቃላችሁ። የጠፉ አልነበሩም፣ የሚተውም አይሆኑም ነበር ከዚያም ሲያልፍ መንገዱን ያውቁ ነበር።

ዛሬ በዓለማችን የሚገኙ ሙስሊሞች እንዲህ ይጸልያሉ፤ አላህ ሆይ በዚህ ቀን የትሁታንን ታዛዥነት ስጠኝ፤ በትሑታን ንስሃ ደረቴን አስፋ፤ በአንተ ደህንነት የፈሪዎች መጠጊያ የሆንክ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሰውን ብቸኛውን መንገድ ልጁን ኢየሱስን በማመን፤ በልጁ በኩል የሐጢያትን ይቅርታ ያገኙ ዘንድ እግዚአብሔር ይገናኛቸው ዘንድ እንጸልይ፡፡


🔹ብዙ ጊዜ የአብዛኞቻችን ችግር የሚሆነው በትንሽ ነገር የምንረካ ነን ። በትንሽ ፀሎት ፡ በትንሽ ቃል ማንበብ ፡ ትንሽ በሆነ እግዚአብሔርን መፈለግ ቶሎ እንጠግባለን ትንሽ ፈልገን ብዙ እንደደከምን ይሰማናል ግን ያ ልክ ያልሆነ ርሀብ ነው ።

🔹መንፈስ ቅዱስ ዕለት ዕለት በሆነ ርሀብ እና ጥማት የሚፈለግ እና የሚናፈቅ ነው ። አንድ ጊዜ አግኝተን የምንረካው ሳይሆን እያገኘነው የሚናፍቀን ከመንፈሱ እያረካን የሚጠማን ነው።

✨መንፈስቅዱስ የእውነት ርሀባችንን ይፈውሰው ።🙏🙏




Forward from: REVEAL JESUS
ትልቅ ራእይ አለኝ!

ሰዎች ላይ መልካም ተፅእኖን ለመፍጠር እና ራእያችሁን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጋችሁ ብዙ ብር፣ የብዙ ሰው ድጋፍ፣ ትልቅ እውቅና፣ እና የመሳሰሉት ነገሮች ብቻ አይደሉም እነዚህና መሰል ሁኔታዎች በጊዜያቸው አስፈላጊ መሆናቸውን የማይካድ ሀቅ ነው ይሁን እንጂ የመነሻው ነጥብ ግን እሱ አይደለም፡፡ እነዚህን “ትልልቅ” ነገሮች ይዘው ከትንሽነትና ከተራ አመለካት ያልወጡ ጊዜያቸውንና ያላቸውን ትልቅ ነገር በከንቱ የሚያባክኑ ብዙዎች አሉ፡፡

ትልልቅ ክንዋኔዎች የሚጀመሩት በትልቅ ልብና በትንንሽ ተግባራዊ እርመጃዎች ነው ትልቅ አስቡና በትንሹ ጅምሩት ፍጥነታችሁን እየጨመራችሁ በየለቱ ለትልቁ ሀሳባችሁ ተራመዱ ያኔ አንድ ቀን ካሰባችሁበት ደርሳችሁ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ::

ቅዱስ ቃሉም ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል እዮብ 8-7 ይለናል ትንንሽ ነገሮችን ትልቅ የሚያደርጋቸው የትልቅ ልብ አመለካከት እና ቀጣይነት ያላቸው ትንንሽ እርምጃዎች ናቸው::

ለዚህም ነው ከትንሽ መጀመር የማልፈራው እስከቀጠልኩ ድረስ ትልቅ መሆኔ እንደማይቀር እና ትልቅነት ከትንሽ የመጀመር እና በትጋት የመቀጠል ውጤት መሆኑን በሚገባ አውቃለሁ::

@revealjesus


እንዴት እንሙት? እንዴት እንኑር?

በምድር ላይ ረጅም ዕድሜ አልኖረም፤ የኖረበት ጥቂት ዕድሜ ግን እስከ ዛሬ ያላባራ የለውጥ፣ የተሐድሶ፣ የፍስሓ፣ የጸጋ ሞገድ አስነሥቷል። ‘ከኖርኩ አይቀር እንደ እርሱ ልኑር’ የሚያሰኝ ትርጉም ያለው ሕይወት ኖረ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚኖር ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደሚሞትም አሳየን። ከኑሮው ለመቅዳት የምንሻማ ሁሉ ከሞቱም ለመማር ብንዘጋጅ እጅግ እንጠቀማለን።

እውነቱን ለመናገር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሞት የመጣ ነዋሪ ነበር። “በሥጋና በደም የተካፈለው” (ሰው ሆኖ የተወለደው) በሞቱ አማካይነት በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስን ለመሻር ነው። እና በመሞት አሸነፈው፤ በንጹሕ ሞት ድል ነሣው፤ ታይቶ በማይታወቅ ዐይነት መሥዋዕታዊ ሞት ሞትንና አለቃውን ቀጣቸው። ቅርንጫፉን በመቁረጥ ሳይሆን፣ የሞትን ሥሩን በጥሶ አመከነው። የሞት መነሻ ሥሩ ኀጢአት ነበረና የኀጢአትን ሰንኮፍ ሲነቅል ሞት ተልፈሰፈሰ። የእግዚአብሔር ስም ይመስገን። ይህ ሟች ልዩ ሟች ነው። ማንም ይሞታል በኀጢአቱ፣ በአዳምነቱ፤ ይህኛው ግን ያለ ኀጢአት ሞቶ ኀጢአተኛኞች ሟቾችን አጸደቀ። አቤት ጥበቡ!

ይህስ ይሁን፣ ታዲያ ትምህርቱ ምንድን ነው? ከአሟሟቱ ምን እንማራለን?

የወንጌላቱ ትራኬ በሕይወት ታሪክ አጻጻፍ ደንብ ሲቃኝ አድልዎ ያሳያል። ስለ ሕይወቱ፣ ስለ አገልግሎቱ፣ ስለ ትምህርቱ፣ ከጻፉት ጋር በማይመጣጠን መንገድ ስለ ሞቱ የጻፉት ይበልጣል። ምናልባት የመጽሐፋቸውን እርቦ ያህል የጻፉት ስለዚህ ሰው የመጨረሻ ሳምንት ሳይሆን አይቀርም። በከንቱ አላደረጉትም፤ ሞቱ ግዙፍ ሞት ነበርና።

የመጀመሪያው ትምህርት
ኢየሱስ ክርስቶስ ኑሮው የተለካ ዐጭር ጊዜ እንደ ነበረ ዐውቆ፣ ይህንኑ እየተናገረ፣ በዚሁ ዕይታ ይኖር የነበረ ሰው ነበር። በታላቅ መረጋጋት ውስጥ ሆኖ እያለ አንዳች የተልእኮ ጥድፊያ ደግሞ ይጎተጉተው እንደ ነበር ያስታውቃል። “…ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ፤ ወደ ላከኝም እሄዳለሁ። ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም…” ዮሐ 7፥33-34፤ “ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል” (ዮሐ 9፥4)፤ ለመሞት ተዘጋጅቶ በተልእኮ ልቡና ውስጥ ይኖር ነበር።

የእኛስ እድሜ ልክ የለሽ ነው እንዴ? ‘ሌሎች ሊሞቱ ይችላሉ፤ እኔ እንኳ ሳልቆይ አልቀርም’ ማለት ከፍተኛ ሽንገላ አይደለምን? የሞትን እውነታ ገፋ ገፋ ማድረግ ሰብአዊ ጨዋታ ሳይሆን አይቀርም። የምር ስንነጋገር ግን ይህን ዐረፍተ ነገር እንኳ አንብበን ሳንጨርስ ሕይወት ልትቋረጥ እንደምትችል አንዘነጋውም። እንግዲያው አንዱ የጌታ ትምህርት ሕይወት ጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚጠፋ እንፋሎት መሆኑን ተገንዝቦ በተልእኮ ልቡና እንዲሁም በሥራ ትጋት መኖር ነው። ሕይወት ከቸሩ ጌታ የተሰጠችን ጥሪት ናት። ሙዐለ ሕይወት ትርፋማ እንዲሆን ሳንጨነቅ፣ በብርቱ ትጋት እንድንሠራ ያሻል።

ሁለተኛው ትምህርት
ጌታችን ሞትን እንደ ክብር መሸጋገሪያ መንገድ አድርጎ የቆጠረበት አተያይ ነው። የሞቱ ጊዜ ደረሰ ማለት ለጌታችን የክብሩ ጊዜ ደረሰ የማለት ያህል ነበር። አሟሟቱ ላይ ላዩን ሲያዩት የታላቅ ውርደት ይመስል ነበር። በሐሰተኛ ምስክሮች ተከስሶ፣ በቅርብ ጓደኞቹ ተከድቶ፣ አጠገቡ በነበረ ተማሪው በገንዘብ ተሸጦ፣ በወታደሮች ጥፊና ድብደባ፣ በጅራፍ ግርፊያና በስላቅ እየተነዳ፣ እርቃኑን በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ዐላፊ አግዳሚ እያላገጠበት የሞተውን ሞት እንዴት ነው የክብር መንገድ የሚለው?

ነገሩ እንዲህ ነው፤ መሬት ሲሳለቅበት ሰማይ ያጨበጭብለት ነበር፤ ጲላጦስ እንዲሰቀል ሲፈርድበት አባቱ ትንሣኤውን ያዘጋጅለት ነበር፤ ብቻውን ቀርቶ እየጮኸ ሲሞት ለአእላፍ አማኞቹ የሰማይ በር ያስከፍት ነበር። ሞቱ ታላቅ ዐላማ ስለ ነበረው ጻድቅ አምላክ ያከበረው ሞት ነበረ። አባቱን እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ታዝዞ፣ የሰውን ልጅ እስከ መጨረሻው ድረስ ወድዶ ስለ ሞተ ታላቅ ክብር ተጎናጸፈ። “… በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው” ብሎ ይለናል ሐዋርያው ጳውሎስ (ፊል 2፥9)። እንግዲያው ለእኛ ለምናምነው ሁሉ የመታዘዝና የፍቅር አርኣያ ሆነልን፤ የክብርን መንገድ አሳየን። እና እኛ ከመሞታችን በፊት በዚህ በጠረገልን መንገድ ስንጓዝ፣ በሕመም ብንሞት፣ በአደጋ፣ በእርጅና በሌላ በማናቸውም “አሰቃቂ” ይሁን “ለስላሳ” አሟሟት ብንሞት ግሥገሳችን ወደ ክብር እንደ ሆነ እንድናስብ ያሻል። ‘ጎሽ፤ አንተ ታማኝ ባሪያ እንኳን ደኅና መጣህ!’ ወደሚለን ቸር አባት እየቀረብን መሆናችንን እናስብ።

ሦስተኛ ትምህርት
ኢየሱስ ክርስቶስ የሞቱን እውነት አስቀድሞ ቢረዳም እጅ አጣጥፎ፣ ጉልበቱን ኮርትሞ በሰቀቀንና በድንጋጤ ሞትን አልተጠባበቀም። እስከ መጨረሻ ትንፋሹ ሕቅታ ድረስ በጎ እየሠራ፣ የያዙትን ወታደሮች እየፈወሰ፣ ለሰቀሉት ምሕረት እየለመነ፣ ከአባቱ ጋር በጸሎት እየተነጋገረ “ተፈጸመ” ብሎ ነፍሱን ሰጠ።

እስክንሞት ድረስ ቦዝዘን እንዳንቀመጥ፣ ከበጎ ሥራ እንዳንታክት፣ ከጸሎት እንዳናፈገፍግ፣ ‘ወይኔ ጉዴ’ እያልን በሰቀቀን እንዳናልቅ አስተማረን። እያንዳንዷን ሰዓት በዘላለም መዝገብ ውስጥ የሚገባ የሰላምና የፍቅር ዘር እየዘራን እንሙት (ያው መሞታችን አይቀርም ብዬ ነው)። የምንወድዳቸውን በጣም እንውደዳቸው፤ ለሚጠሉን እንጸልይላቸው፤ ለአገርና ለሕዝብ መልካሙን ሁሉ እንመኝ፤ እንናገር፤ እንባርክ። እንደዚያ ሀኬተኛ ባሪያ መክሊታችንን ቀብረን የቁጥጥሩን ቀን በድንጋጤ አንጠብቅ። በተሰጠን ትንሽ ትንፋሽ እንኳ በመክሊታችን እየነገድን እንሙት።

አራተኛ ትምህርት
ለሞቱ ቀን ተማሪዎችን እያዘጋጃቸው ሳለ፣ ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መዝሙር ዘመረ (ማቴ 26፥30)። ምን እንደ ዘመሩ ባይጻፍልንም፣ የእኔ ግምት የፋሲካ ሰሞን ስለ ነበረ እስራኤል ከግብፅ ባርነት ነጻ የወጣበትን፣ የእግዚአብሔርን ትድግናና ግርማ የሚናገር የነጻነትና የምስጋና መዝሙር ሳይሆን አይቀርም። በሞት ሰሞን መዝሙር አልተከለከለም። የሚሠራውን የሚያውቀውና የፍጥረት ሁሉ ገዥ የሆነውን፣ የነፍስ ሁሉ ባለቤት የሆነውን ጌታ እያመሰገንነው እንሙት። ሮበርት ፍሮስት ስመጥር አሜሪካዊ ባለ ቅኔ ነበረ። እንጨት አጥር ላይ ቆማ በጧት የምትዘምር ወፍ፣ ሥራ በፈታ አንድ ልጅ በተወረወረ ድንጋይ ተመትታ ጸጥ ስትል አዝኖ እንዲህ አለ፦

There must be some wrong;
in silencing any song!
መዝሙር የሚያዳፍን ዜማ የሚከለክል፣
ጤና ሰው አይደለም ሠርቷል ትልቅ በደል!

ሌላም ብዙ ትምህርት አለው። ለምሳሌ፣ በመስቀል ላይ እየሞተ ሳለ ስለ ወላጅ እናቱ አስቦ ለዮሐንስ ዐደራ መስጠቱ ትልቅ የኀላፊነት አብነት ነው።

የመጨረሻው እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲበላ፣ ህብስቱንና ወይኑን ሲሰጣቸው “በእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ጋር አዲሷን ወይን እስክንጠጣ ከዚህ በኋላ አልጠጣውም” ማለቱ የትንሣኤንና የዳግም ምፅዐቱን ተስፋ የሚያለመልም የተረጋጋ ንግግር ነው። ከዚህ ሕይወት በኋላ ሌላ የከበረ ሕይወት አለ፤ ይህንን እየተናገረ የሞተ ሰው ነበረ።

ሁሉን ትምህርት ዘርዝረን አንጨርስም …

ነገር ግን ይህ አስገራሚ ሞት የሞተው ትሑቱ ኢየሱስ የገሃነም ኀይሎች ሊቋቋሙት በማይችሉት ታላቅ ኀይል ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። በእርሱ የምናምን የሁላችንን ዕንባ የሚያብስ፣ ነፍሳችንን የሚመልስ፣ የመጽናናት ብሥራት ሰጠን። እና ወዳጆቼ እንደ ጳውሎስ፣ “ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነው” የማለት ጸጋ ያድለን።


Nigussie Bulcha

@revealjesus


ከታንኳው ውረዱ

ከአገልጋይ ብሩክ ሚልኪያስ ጋር


ልባም ሴት ማን ናት ?

1. ልባም ሴት ራሷን ለክርስቶስ አሳልፋ ትሰጣለች ። አምላኳን ኢየሱስን ታመልካለች ለባሏ ትገዛለች
2.ልባም ሴት ፋሽን ተከታይ አይደለችም ። ልታይ ልታይ አትልም ሰውነቷን ታስከብራለች
3.ልባም ሴት በትዳሯ ላይ በገንዘብ እና በንብረት አስተዳደር ጠንቃቃ ናት ስለዚህ ባሏ ያምናታል
4.ልባም ሴት ለሀሜት ፥ አሉባልታ እና ለወሬ ጊዜ የላትም ልቧ በቃል የተሞላ ነው ።
5.ልባም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት
6. ልባም ሴት ንግግሯ በጨው እንደተቀመመ ነው ።
7.ልባም ሴት ዓላማ አላት ።
8.ልባም ሴት ጊዜዋን በአግባቡ ትጠቀማለች ።
9.ልባም ሴት ይቅርታ አድራጊ ነች ቂም ጥላቻ አትይዝም ።
10. ልባም ሴት ለድሀ እና ለምስኪኖች ትራራለች ።

“ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል።”
  — ምሳሌ 31፥10


     



20 last posts shown.