❤️RIDE (™️) Drivers Update


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Transport


ይህ ቻናል ከራይድ ሀሳብ መለዋወጫ ግሩፕ (RIDE group) በተጨማሪ ኦፊሻል የአሰራር መረጃ ሲኖር ማሰራጫ መንገድ ነው

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Transport
Statistics
Posts filter


⭐️የአፕዎ ፅሁፍ አይታይዎትም? Setting ውስጥ Font ብለው search ያድርጉ- ከዛ መጠኑን ከፍ ሲያደርጉት ስክሪንዎ ጎልቶ ይታያል::


🙏ዛሬ የትኞቹን ቻናሎች አብርተው መስራት መረጡ? በነግራችን ላይ እንደመኪናዎ አይነት, ጠቅላላ የስራ ፍሰት እና ያዋጣኛል ብለው ባመኑት ታሪፍ ለመስራት የሚፈልጉትን መርጠው ማብራት የሚፈልጉትን ደግሞ ማጥፋት ይችላሉ:: ምርጫው በእጅዎ ነው


Forward from: ❤️RIDE (™️)
የስራ ቻናልዎን በምርጫዎ ለመስራት እንደወቅቱ ይቀያይራሉ?
Poll
  •   አዎ እቀያይረዋለሁ
  •   አይ ባለበት ነው ይተውኩት
82 votes


[Survey] ከተሰጠዎት የስራ ቻናሎች ውስጥ የትኞቹን ላለመስራት በፍላጎትዎ አጥፍተዋቸዋል?
Poll
  •   RIDE Quick
  •   RIDE Midsize
  •   RIDE Minivan
  •   RIDE Minibus
  •   RIDE EV
88 votes


⭐️ከደንበኛ ሁለት ግዜ ክፍያ እንዳይቀበሉ ያስተውሉ! በውጭ ካርድ የሚከፍል ደንበኛ ጉዞውን ጨርሶ Finish ሲሉ ‘Paid with Card’ ብሎ የሚዘጋ ከሆነ ባላንሱ የDriver ባላንስዎ ውስጥ ገብቷል ማለት ነው:: በዚህ ግዜ ደንበኛውን አመስግነው ያሰናብቱ:: ስለአሰራሩ ግንዛቤ ለመጨበጥ ይህንን አጭር ቪድዮ ይመልከቱ https://youtu.be/hcmrJkUhZ_4?si=jWJ4M84m41J8saZk


Forward from: ❤️RIDE (™️) Drivers Update
⭐️አዲስ Feature ለደንበኞች ተጨመረ! ደንበኞች በጥሪ ማዕከል አዘው ሲጠቀሙ በጉዞ መጨረሻ የሂሳብ መዝገብ ማወራረጃ የTrip Summary ሊንክ በSMS ይደርሳቸዋል:: ለደንበኞችዎ ይህንን ይንገሩ


⭐️አዲስ Feature ለደንበኞች ተጨመረ! ደንበኞች በጥሪ ማዕከል አዘው ሲጠቀሙ በጉዞ መጨረሻ የሂሳብ መዝገብ ማወራረጃ የTrip Summary ሊንክ በSMS ይደርሳቸዋል:: ለደንበኞችዎ ይህንን ይንገሩ


🎉⭐️እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ:: በዓሉን በRIDE Plus ሰርተው ዳጎስ ያለ የRIDE Point ያጠራቅሙ
👉Copyright Painting by Teklemariam Zewde


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🎉ክፍያው ፈጣን ሆነ! የRIDE Plus Corporate ክፍያ መቀበያ ፕላትፎርማችን ላይ የፍጥነት ማሻሻያ አድርገናል:: በፊት ደንበኛ ይዘው ካደረሱ በሁዋላ ክፍያው እስኪገባ የነበረውን መዘግየት ቀርፈናል:: የRIDE Plus እና የDriver አፓችንን Integration በፍጥነት እያቀላጠፍን ሲሆን በየወቅቱ የምናደርገውን ማሻሻያ እናሳውቅዎታለን:: ዛሬውኑ RIDE Plus አፓችንን Download አድርገው በራይድ ስልክ ቁጥርዎ Login አድርገው ይጠቀሙ Android https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ridetm
Ios
https://apps.apple.com/us/app/ride-plus/id6443848297


⭐️RIDE ከኢትዮዽያ ቱሪዝም ሚንስቴር ጋር በጋራ ለአባላት የስልጠና መርሃ ግብር አስጀመረ! ስልጠናው የደንበኛ አያያዝን እና አገልግሎት አሰጣጥን እንዲሁም የቅሬታ አፈታትን ያካተተ ሲሆን- የትራንስፖርት ሴክተሩን ደረጃ ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል:: በመጀመርያው ዙር የስልጠና ተሳታፊዎች Level 3 እና Level 2 የRIDE Comfort እና Minivan አሽከርካሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ ሁሉም በየረድፉ የስልጠናው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እናሳውቃለን:: ከስልጠናው ባሻገር አባላቱ በቅርቡ በአፍሪካ ዩኒየን ስብሰባ ላይ የይለፍ ባጅ የሚያገኙ ሲሆን- ይህንን ባጅ ተጠቅመው ከኤይርፖርት እና ከስብሰባ ቦታዎች በነፃነት ደንበኛን እንዲያነሱ እና እንዲያወርዱ ያስችላቸዋል:: ይሳተፉ


⭐️Dynamic Pricing እንዴት ይለያል? ባጭሩ- ያሉበት አካባቢ የመኪና እጥረት ካለ አሽከርካሪውን ለማበረታታት እንደመኪና አቅርቦቱ መጠን ጠቅላላ ዋጋው በ10%, በ20% ወይም በ30% ይጨምራል:: Dynamic Pricing ያለበትን የሚጠቁምዎ ካርታዎ ላይ ያለው ደማቅ ቀይ ባለ 6 ጎን ምልክት ነው:: በጣም እየደመቀ ሲሄድ ዋጋውም የዛን ያህል ይጨምራል


⛽️የነዳጅ ጭማሪን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ:- ውድ የራይድ ቤተሰብ- በዛሬው እለት የነዳጅ ጭማሪ እንደተደረገ ተነግሯል:: ይህንን አስመልክቶ አባላት የራይድን ዋጋ ለመጨመር ወይም ባለበት ለማቆየት ከደንበኞች የመክፈል አቅም እይታ ሃሳባቸውን እየገለፁ ይገኛሉ:: በዚህም መሰረት ድርጅታችን የተገበረው የDynamic Pricing feature አማካኝነት የተደረገውን ጭማሪ እንደሚያካክስ እየገለፅን መደበኛ ታሪፋችን ባለበት እንደሚቆይ በአክብሮት እናሳውቃለን:: ይህም ማለት- እሩቅ የሆኑ ቦታዎች እና መመለሻ በማይገኝባቸው ቦታዎች ሲስተማችን ባየር ላይ ዋጋውን በ10% ወይም በ20% የሚያሳድግ ይሆናል:: መልካም በዓል ይሁንልዎ


🎉ዛሬ ስንት ብር ይሰሩ ይሆን? ቀይ ወደበዛበት ስፍራ ከተንቀሳቀሱ በDynamic Pricing መሰረት ሂሳቡ በ10% ወይም በ20% ይባዛል:: በተጨማሪም የአፕ ተጠቃሚ ሲያዝ አስቀድሞ ከ20 እስከ 50 ብር Bonus ይጨምርልዎታል! ያገኙትን ገንዘብ screenshot ያጋሩን


🎉⭐️❤️ለራይድ ቤተሰብ በሙሉ መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ/ይሁንልን::


💥ጥር ወር የስራ ነው! ያለዎትን ግዜ በሙሉ ስራ ላይ በማዋል ይህንን የስራ ወቅት በሚገባ ይጠቀሙበት:: በአንድ ቦታ ሁነው ስራ ካልገባልዎት በምንም ምክንያት ከ10 ደቂቃ በላይ እንዳይቆሙ:: የቴክኒካል ችግር ካለብዎ በፍጥነት ቢሮ በመምጣት አስተካክለው ይህንን ወር ገቢዎን ጥግ ያድርሱ:: ከራይድ ጋር ወደፊት!


⭐️ኮኮባችንን እናሳምር! በጉዞ መጨረሻ ደንበኞች አሽከርካሪዎችን rate የሚያደርጉ ሲሆን- ይህ ውጤት በጠቅላላው የስራ ፍሰትዎን ይወስናል:: በአንፃሩ እርስዎ ለደንበኛችን የሚሰጡትን ኮኮብ እያጣራን እርምት እንወስዳለን::


✨የRIDE አፖችዎን Update ያድርጉ! Latest Version መያዝ ከስራ እንዳይስተጏጎሉ ያግዛል::


Forward from: ❤️RIDE (™️) Drivers Update
👏RIDE ለረዥም ስራዎች ተመጣጣኝ ክፍያ ያስገኛል! በባዶ እንዳይመለሱም መመለሻ ስራ በBack to Back Feature ይሰጥዎታል:: ከRIDE ጋር ወደፊት!


✨ይድረስ ለታክሲ (ኮድ 1) ድርጅቶች በሙሉ:- አዲሱ በፀደቀው የግብር አዋጅ መሰረት ከ8 መቀመጫ በታች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት Vat/TOT ተመዝግበው ለተሳፋሪ ሪሲት መስጠት እንዳለባቸው አስቀምጧል:: በዚህም መሰረት ራይድ ከወረቀት ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በዲጅታል መንገድ VAT እንዲሰበስቡ ሲስተም ያዘጋጀ ሲሆን ይህንን እገዛ ለማግኘት በማህበር ስራ ሃላፊዎች በኩል በዚህ ሊንክ ቀጠሮ ማስያዝ እንደሚችሉ በአክብሮት እናሳውቃለን:: ኑ አብረን እንስራ! https://forms.gle/CdsUc4RjDZEjGLiM6


⭐️ይህንን አስተውለውታል? ተሳፋሪ በአፕ ሲያዝ አስቀድሞ ከ20-50 ብር Bonus ሂሳቡ ላይ መጨመር ይችላል:: እንዲህ የሚያበረታታን ደንበኛ እኛም በቅልጥፍና እናስተናግድ

20 last posts shown.