🆕🔴
የመልካም ስራ ጥሪ አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ
بسم الله الرحمن الرحيم
⭐️እንደሚታወቀው መረከዝ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪ ላለፉት 4 አመታት ገደማ የቁርአን ሂፍዝና ተያያዥ የተረቢያ ትምህርቶችን በተለያዩ መርሀግብሮች ማለትም በአዳሪ፣ በተመላላሽና በርቀት በርካታ ተማሪዎችን አስተምሮ ለውጤት በማብቃት ኡማውን በዲኑ የሚያገለግሉ ተተኪዎችን በማፍራት የበኩሉን አሰተዋፆ ሲያበረክት ቆይቷል ።
📸እነሆ አሁን ላይ መርከዙ ተደራሽነቱን በማስፋት በ3ቱም ቅርንጫፎች በበይነ መረብ የሚማሩትንም ጨምሮ ቁጥራቸው ወድ 400 ገደማ የሚደርሱ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል ።
✅አንዱ ቅርንጫፍ 30 አከባቢ የሚሆኑ ተማሪዎችን ያለ ምንም ክፍያ የምናስተምር ሲሆን በ2ቱ ቅርንጫፎች ላይ መክፈል ለማይችሉ የግድ መማር ያለባቸው 10ራ ምናምን ተማሪዎችን እና በ ኦንላይን በርከት ያሉ ተማሪዎች በነፃ ተቀብለን እያስተማርን እንገኛለን ።
አጠቃላይ በነፃ የምናስተምራቸው ተማሪዎች አሁን ላይ ቁጥራቸው ወድ 45 አከባቢ ደርሷል ።
☑️እኛ አቅማችን በሚችለው አላህ በረካ አድርጎልን ይሄን ያክል ርቀት ተጉዘናልና እናንተስ ለቀጣዩ ፕሮጄክታችን ልታግዙን ዝግጁ አይደላችሁም ? ዛሬ ስለሱ ይሆናል የምናወራው።
🥳ይሄንን ሁሉ ስናድርግ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖልን ሳይሆ በጣም ብዙ ቻሌንጆችን በመቋቋም መሆኑን እንድትረዱልን እንፈልጋለን ። በጣም ብዙ ውጣ ውረዶች ..
አሁን ላይ ግን አንዱንና ዋነኛውን ነው የምንነግራቹህ ።
እሱም ቋሚ የሆነ ቦታ አለማግኘታችን እና በቤት ኪራይ መሰቃየታችን ትልቁ ተግዳሮታችን ነው ።
📣ስለሆነም እነሆ ዛሬ ላይ የሙስሊሙን ማህበረሰብ እገዛ ፈልገን የመጣነው በዚሁ ጉዳይ ላይ ነውና በአላህ ፍቃድ በህይውት እስካለን ድረስ ኢስላማዊ ሀለሰፊነታችንን የምንወጣበት እና ለልጆቻችንና ለቀጣዩ ትውልድ መልካምን ነገር ያስቀጥል ዘንድ ይሄንን መርከዝ ገንብተን ለማስረከብ ሁላችንም የበኩላችንን አሰተዋፆ እንድናበረክት በአለሰህ ስም እንጠይቃለን ።
ይሄንን በማስመልከት ታላቅ የዳዕዋና የኒያ ፕሮግራም አዘጋጀተናል። እርሶም እንዳይቀሩ በክብር ተገሰብዘዋል።
😬
የእለቱ ተጋባዥ እንግዱች ▶️
✅ ሳዳት ከማል
✅ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
✅ ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
✅ ሸይኽ አወል ኬሚሴ
✅ ኡስታዝ ኸድር ኬሚሴ
✅ ኡስታዝ አቡ ሙሰሊም
😓እሁድ ማታ ከተረዊህ ሰላት በሇላ
4️⃣🔤1️⃣5️⃣
💎
ፕሮግራሙ የሚካሄድበት የተሌግራም ግሩፕ⤵️
⛓
https://t.me/merkezabumussa1 ⛓
⛓
https://t.me/merkezabumussa1 ⛓
ውድና የተከበራቹህ ሙስሊም ወንድምና እህቶች፣ የቁርአንና ሱና ወዳጆች ይሄንን ፕሮግራም ሼር በማድረግ የአጅር ተካፋይ እንድትሆኑ ለማስታወስ እንወዳለን ።