ሸይኽ አብዱልሐሚድ እና የገጠር ዳዕዋ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
🏝 የሀገራችን ህዝብ አብዛኛው መካሪ ካገኘ ያለበትን ክፍተት ለማሻሻል የሚጥር ነው። በተለይ በገጠራማ አካባቢ ሰፍሮ የሚገኘው ሙስሊም ልክ እንደህፃን በሚሰጠው መመሪያ የሚቀየር ነው።
✅ ኢትዮጵያ ላይ አብዛኛዎቹ መሻይኾች ኡስታዞች እና ዱዓቶች ትንሽ ተሰሚነት ካገኙ ፈጥነው ወደ አዲስ አበባ ወይም ወደ ክልል ትልልቅ ከተሞች ይዘምታሉ። ከዛም ለገጠሩ ህዝብ ደንታ የላቸውም።
👌 ሸይኽ አብዱልሐሚድ ያሲን ግን ምቾትን ሳይፈልጉ ድካም ሳይበግራቸው በተለያየ መልኩ የሀገራችንን ገጠራማ ክፍል ህዝብ በማንቃት የማይተካ ሚና ተጫውተዋል።
➪ ሸይኽ በዒልማቸው የላቁ ከመሆናቸው ጋር ዝቅ ብለው (በመሰረቱ ከፍታ ነው) በመንቀሳቀስ ህዝቡን ለመጥቀም ደፋ ቀና ብለዋል።
👉 ሸይኹ እስከ "ገነቴ" ድረስ በመሄድ ጥግ ካሉ የአማራ ክልል አካባቢዎች መካከል ዳዕዋ አድርገዋል። በሰሜን ወሎ በመሄድም ከሰሜን ወሎዎቹ ከዋክብት ጋር ዳዕዋ አድርገዋል።
🔎 በዚሁ በስልጤ ዞን እና ጉራጌ ዞን እንዲሁም አጎራባች ያሉ አካባቢዎችን ገጠራቸውን በማዳረስ ሊመከር የሚገባውን የገጠር ማህበረሰብ በዳዕዋ እና ኮርሶች ለመቀየር ሞክረዋል። አላህ ይቀበላቸው!
👌 የሚገርመው ይህንን ጥረት ለማደናቀፍ ደፋ ቀና የሚሉ ሚስኪኖች አላህን ሊፈሩ ይገባል።
https://t.me/AbuImranAselefy/9770