ስለ “ኢኽዋን” በግጥም ከዚህ በፊት ከተፃፉት የተጨመቀ
〰
አደገኛ ቡድን - የፖለቲካ እናት፣
ለስልጣን ያደረ - የሌለው ሀይማኖት፣
ለተውሒድ ለሱና - የማይረባ ቅንጣት፣
ጭንቅ ጭንቅ የሚለው - ሺርክ ሲነካበት፣
ቢድዓ ሲመታ - የሚዋጥ በጭንቀት፣
እጅግ የሚበሳጭ - ተውሒድ ሲስፋፋበት፣
ሱና ሲያለመልም ፣ ደሙ ሚፈላበት!
ስለ ኢኽዋን ቡድን - ያልነቃ ሠው ይንቃ፣
ጥቂት ታህል እንኳ - ሊያምኑት የማይበቃ፣
የተውሒድ እንቅፋት - የሺርክ ጠበቃ፣
ስሜት የተሞላ - በብዥታ አሮንቃ!
ሱናን ተፃራሪ - የቢድዓ እግረኛ፣
የፖለቲካ አንጃ - የስልጣን ጥመኛ፣
ባ-ንድነት ስም ነጋጅ - ከፋፋይ ፅንፈኛ!
የበግ ለምድ ለብሶ - እንደሚያድን ተኩላ፣
ኢኽዋንይ ሻይረስ - የለከፈው ገላ፣
ምንም ኸይር የለውም - ሸር ነው ጠቅላላ!
አፉን ማር ቀብቶ - ውስጡን የሚወጋ፣
የመድረክ ላይ አልጋ - በእውነታው ቀጋ፣
ኢኽዋን የሚባለው - አደገኛው መንጋ፣
ቀጣይም አያርፍም - አይተኛም ላደጋ፣
አላህ ያስተካክለው - ሀገር ሳያበላሽ በመሸ በነጋ!
አዲስ ማጭበርበሪያ - ይዞ መጥቷል ኢኽዋን፣
ሰለፍይ ነኝ ብሎ - የስም መጠሪያውን፣
በዘደ ያስፋፋል - ያን ውድቅ አካሄዱን፣
ባጋጣሚ አምቻችቶ - መውጋት ሰለፍያን!
ለኢስላም ታላቅ ፀር - ኢኽዋን ብሎ ነገር፣
የፖለቲካ ጅብ - ለስልጣን የሚኖር፣
ራሱን መሸጎ - በኢስላም ጥላ ሥር!
ምንም ለውጥ የለውም - ዛሬም ይሁን ትናንት፣
አደጋ ቡድን ነው - ይሄ ኢኸዋን ማለት፣
የሺርክ ጠበቃ - የተውሒድ እንቅፋት፣
ከስር መሰረቱ - ሡፍይ ነው በእውነት፣
በርግጥ አየሩን - ሲያይ ይሻል ሱንይነት፣
ሒዝብይ ነውና - ህዝብ እንዳይሸሽበት፣
ከመሃል ላይ ቁሞ - ያንንም ይሄንም በበላይ ለመምራት!
ሌላም አደጋ አለው - ሞገደኛው ኢኽዋን፣
የእስስት ባህሪ - አለበት ተለውን፣
ያልሆነውን ሆኖ - ይሻል መታየትን፣
ማስመሰል ይወዳል - ላላወቀው ወገን፣
ልብ ብሎ ላየው - ቀርቦ ሁኔታውን፣
ሀቅን አስሸቀንጥሮ - ያነግሳል ባጢልን!
✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/9035
〰
አደገኛ ቡድን - የፖለቲካ እናት፣
ለስልጣን ያደረ - የሌለው ሀይማኖት፣
ለተውሒድ ለሱና - የማይረባ ቅንጣት፣
ጭንቅ ጭንቅ የሚለው - ሺርክ ሲነካበት፣
ቢድዓ ሲመታ - የሚዋጥ በጭንቀት፣
እጅግ የሚበሳጭ - ተውሒድ ሲስፋፋበት፣
ሱና ሲያለመልም ፣ ደሙ ሚፈላበት!
ስለ ኢኽዋን ቡድን - ያልነቃ ሠው ይንቃ፣
ጥቂት ታህል እንኳ - ሊያምኑት የማይበቃ፣
የተውሒድ እንቅፋት - የሺርክ ጠበቃ፣
ስሜት የተሞላ - በብዥታ አሮንቃ!
ሱናን ተፃራሪ - የቢድዓ እግረኛ፣
የፖለቲካ አንጃ - የስልጣን ጥመኛ፣
ባ-ንድነት ስም ነጋጅ - ከፋፋይ ፅንፈኛ!
የበግ ለምድ ለብሶ - እንደሚያድን ተኩላ፣
ኢኽዋንይ ሻይረስ - የለከፈው ገላ፣
ምንም ኸይር የለውም - ሸር ነው ጠቅላላ!
አፉን ማር ቀብቶ - ውስጡን የሚወጋ፣
የመድረክ ላይ አልጋ - በእውነታው ቀጋ፣
ኢኽዋን የሚባለው - አደገኛው መንጋ፣
ቀጣይም አያርፍም - አይተኛም ላደጋ፣
አላህ ያስተካክለው - ሀገር ሳያበላሽ በመሸ በነጋ!
አዲስ ማጭበርበሪያ - ይዞ መጥቷል ኢኽዋን፣
ሰለፍይ ነኝ ብሎ - የስም መጠሪያውን፣
በዘደ ያስፋፋል - ያን ውድቅ አካሄዱን፣
ባጋጣሚ አምቻችቶ - መውጋት ሰለፍያን!
ለኢስላም ታላቅ ፀር - ኢኽዋን ብሎ ነገር፣
የፖለቲካ ጅብ - ለስልጣን የሚኖር፣
ራሱን መሸጎ - በኢስላም ጥላ ሥር!
ምንም ለውጥ የለውም - ዛሬም ይሁን ትናንት፣
አደጋ ቡድን ነው - ይሄ ኢኸዋን ማለት፣
የሺርክ ጠበቃ - የተውሒድ እንቅፋት፣
ከስር መሰረቱ - ሡፍይ ነው በእውነት፣
በርግጥ አየሩን - ሲያይ ይሻል ሱንይነት፣
ሒዝብይ ነውና - ህዝብ እንዳይሸሽበት፣
ከመሃል ላይ ቁሞ - ያንንም ይሄንም በበላይ ለመምራት!
ሌላም አደጋ አለው - ሞገደኛው ኢኽዋን፣
የእስስት ባህሪ - አለበት ተለውን፣
ያልሆነውን ሆኖ - ይሻል መታየትን፣
ማስመሰል ይወዳል - ላላወቀው ወገን፣
ልብ ብሎ ላየው - ቀርቦ ሁኔታውን፣
ሀቅን አስሸቀንጥሮ - ያነግሳል ባጢልን!
✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/9035