የመርከዝ አል ፈላሕ የሰለፊያ ቻናል


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


⚡🎤 "ቁርኣንና ሐዲስ በሰለፎች ግንዛቤ"
ይህ ቻናል በመስጂድ አል ፈላሕ የሚሠጡ
📚 ደርሶችን ፣
🎤 የጁሙዓ ኹጥባዎችን
እንዲሁም የተለያዩ በድምፅና በፅሁፍ የሚቀርቡ ትምህርቶችንና ምክሮችን ያስተላልፋል። ⚡ 🎤
@husen41

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


📱ለልጆቻችሁ ስልክ አትስጡ ስል ያለምክንያት አይደለም። በቂ ምክንያት አለኝ።
📌ስልክ መስጠት ሲባል ገዝቶ መስጠትን ሳይሆን የራሳችሁን ስልክ ራሱ ለምንም ነገር ቢፈልጉት እንኳን አትስጧቸው። ልጆች በጣም ፈጥነው ሄደዋል የሰሙትን ያዩትን ነገር ለመተግበር ጊዜ አይፈጅባቸውም ።
ወላጆች ሁሌም ንቁ ልትሆኑ ይገባል እናንተ ከምታስቡት በላይ እነሱ ያስባሉ ቤተሰቦቻቸውንም መሸወድ ማታለል ይችሉበታል። ተጠንቀቁ❗️

የኔ ልጅ ጨዋ ነው የኔ ልጅ ጨዋ ነች ምናምን ከማለት በቻልከው አቅም ልጅህን ለመቆጣጠር መሞከር ነው።

ይህን ስል ስልክ ሰጥተህ ተከታተለው እያልኩ አይደለም ስልክ በጭራሽ እንዳትሰጥ።

በስልክ ምክንያት ስንቶች ተበላሹ
ስንትና ስንት ሴቶች ትዳራቸውን በተኑ
ጨዋ ምንም አያውቅም መልካም ልጅ ተብሎ በስልክ ምክንያት ተበላሽቶ የቀረ ቤቱ ይቁጠረው።

የዚህ ዘመን ትልቁ ሙሲባ ስልክ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም።

👉https://t.me/AbuEkrima


Forward from: አል ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ
🛌 አስቸኳይ የሰላተል ጀናዛ ጥሪ

[ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّآ إِلَيْهِ رٰجِعُونَ] ["إِنَّ لِلَّـهِ مَا أَخَذَ، وَلَهُ مَا أَعْطَى، وَكُلُّ شَيءٍ عِنْدَهُ بِأَجَلٍ مُسَمَّىً"]

💥 ዛሬ የኡስታዝ አቡ ጀሪር ሙሐመድ እናት ወደ አኼራ ሄዳለች አላህ የጀነት ያድርጋት።

🕌 በአላህ ፍቃድ ዛሬ ማክሰኞ ዝሁር ላይ [ፉርቃን መስጂድ] ሰላተል ጀናዛ ተሰግዶ...

🛣️  ዐለም ባንክ በሚገኘው መቅበራ የሚቀበሩ ይሆናል።

📮 መገኘት የምትችሉ በአጠቃላይ ተገኝታችሁ እንድትሰግዱና እንድትሸኙ ጥሪ ተላልፎላችኋል‼️

🕌 ሰላተል ጀናዛ ዝሁር ላይ ፉርቃን መስጂድ።

🛣️  ቀብር ዐለም ባንክ መቅበራ።

🔗 t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio


Forward from: ዲማስ
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🌹ቪድዮ🌹ግጥማዊ ማስታወቂያ🌹

አማራጭ በበሞላው በሰፋፊው መንገድ

ሙስሊሞች በሙሉ ወደዚያ በመሄድ

እነዘይር ወንድሞች ይታይ ስንዋደድ



መርከዝ አስሱና ቂልጦ ጎሞሮ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

jan/26/2025


በጁሀር ኡመር


https://t.me/OfficialDemas/6403


🚨የእሁድ ሙሓደራ⤵️

👅 ምላስህን ጠብቅ! 👅

🔁 በሚል ርዕስ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሓደራ።

🎙️ በኡስታዝ አቡ አብድልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ አላህ ይጠብቀው።

📅 እሁድ 18/05/2017E.C 📅

🕌 በአንዋር መስጂድ {አዲስ አበባ}

📎 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17759
👆
👇
👉https://t.me/selefya


ቁርአን መቅራት እና ማዳመጥ ያለው ትሩፋት እንዲሁም የወንድምን ሐቅ ስለመጠበቅ የተወሳበት ገሳጭ የሆነ ምክር

በኡስታዝ አቡ አሲያ አብደላህ ቢን ሑሴን
በዳለቲ መስጅደል ፈላህ

እሑድ ከመግሪብ በኋላ
27/07/1446 አመተሂጅራ

t.me/selfya


ቁርአን መቅራት እና ማዳመጥ ያለው ፈድል እንደዚሁ የወንድምን ሀቅ መጠበቅ ያለው ፈድል የተወሳበት ገሳጭ የሆነ ምክር
በወንድማች አቡ አሲያ አብደላህ ቢን ሁሴን
በዳለቲ መስጅደል ፈላህ በይነል መግሪብ ወኢሻ ሰኞ ምሽት ።
27/07/1446 አመተሂጅራ

ከተወሱ ሀዲሶች :-
١. روى إمام أحمد في مسنده عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: "من استمع إلى آية من كتاب الله كانت له حسنة مضاعفة، ومن تلاها كانت له نوراً يوم القيامة ".
٢. روى إمام مسلم في صحيحه عن عبدالله بن عمرو بن العاص - رضي الله عنهما - قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ((فمَن أحَب أن يُزحزَح عن النار ويدخل الجنة، فلتأتِه منيَّتُه وهو يؤمن بالله واليوم الآخر، وليأتِ إلى الناس الذي يحب أن يؤتى إليه))؛ 


👇👇👇👇👇
https://t.me/Muradkelifa/


Forward from: መርከዝ አስ–ሱነህ በ ጎሞሮ❕❕ (دار الحديث السلفية في غمر( الحبشة
✍ ታላቅ የዳዕዋ እና የሙሐደራ ጥሪ


📅 የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ጥር 24 / 2017 በዓይነቱ ልዩ እና ከአራቱም የሀገራችን ክፍሎች በሚመጡ ተላላቅ መሻይኾች እና ኡስታዞች ለየት ያለ የዳዕዋ እና የሙሐደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል ።

📪 እርሶም ከነቤተሰብዎ የዚህ ኸይር ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል ይምጡ ይማራሉ ይጠቀማሉ ።

📤ሌሎችንም በመጋበዝ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ ።

🚘 የሴቶች መስገጃ አንዲሁም በቂ እና አስተማማኝ የመኪና መቆሚያ ተዘጋጅቷል ።

🕌 دار الحديث السلفية قلطو ـ غمر للعلوم الشرعية.

🕌 መርከዝ አስ-ሱና ለሸሪዓዊ እውቀት ።

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين "

🔗
https://t.me/+UhQFsq-4FgB00672


🚨አዋጅ ! ግብረ-ሰዶም ሊፈጀን ነው❗️ተቀራርበን እራሳችንንም ልጆቻችንንም እናድን !!!!!

 እጅግ አሳሳቢ ሙሀደራ

በመስጂድ አል-ፈላህ ዳለቲ

ኢስማኤል ወርቁ حفظه الله

https://t.me/amr_nahy1

https://t.me/selefya


ምርጥ የጁሙዓ ኹጥባ እንጋብዛቹ
የምላስ ጣጣ በሚል
🎙በኡስታዝ አቡ ዓብድልመናን

እኛም ብለናል 🕹የሰማው ተጠቀመ ያመለጠው ተነደመ❗️

https://t.me/selefya


Forward from: መርከዝ አስ–ሱነህ በ ጎሞሮ❕❕ (دار الحديث السلفية في غمر( الحبشة
✍ بسم الله الرحمن الرحيم


   ✍ ታላቅ ብስራት በጣም በናፍቆትና በጉጉት ሚጠበቀው የአህለ ሱና ወልጀማዓ የዚያራ ኢጅቲማዕ መርከዘ አስ ሱናቂልጦ ጎሞሮ ላይ !!

       🕌 ለየት ባለ መልኩ በጣም በጉጉትና በናፍቆት ሚጠበቀው የአህለ ሱና ኢጅቲማዕ ከትልቁ የሰለፍዮች መርከዝ "መርከዝ አስ_ሱናህ" ቀጠሮ ተወስኖ ተቆርጦ አልቆዋል!!

📆 ኢንሻ አሏህ የሚመጣው ቅዳሜ ሳምንት {ጥር 24
/2017}
             ቂልጦ_ጎሞሮ !!

   🚧 ትላልቅ ኡስታዞች መሻይኾች ዱዓቶችና አስተማሪዎች ከከተማም ከገጠርም ከተለያዩ ቦታዎች ለዳዕዋ ሚመጡበት ኢጅቲማዕ ነው።

📢 አላህ ባገራላቸው ሁሉም መሻይኾች ዱዓቶች የሚካፈሉበት ስለሆነ የቻለ ሰው በጊዜ ተገኝቶ እንዲጠቀም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን !!

⏱ፕሮግራሙ ቅዳሜ ከዙሁር ጀምሮ እስከ ዒሻ በኋላ ይቀጥላል ።

📍ቅዳሜ በጠዋት ያልደረሰ ሰው ፕሮግራሙ ያመልጠዋል!!

🗳 ከጁሙዓ ኹጥባ ጀምሮ ቀደም ብለው በሚመጡ ኡስታዞች የተለያዩ ፕሮግራሞች ስለሚኖሩ ከጁመዓ ኹጥባ ጀምሮ የቻለ እንዲካፈል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!

   🚫ማሳሰቢያ ❗️❗️

📍መደበኛው ፕሮግራም ቅዳሜ ነው
እሁድ አይደለም ።

📮ዳዕዋው ጥሪው ኢንሻ አላህ ሁሉንም ሙስሊሞች ወንዶችንም ይሁን ከመሕረማቸው ጋር የሚመጡ ሴቶችንም ያካትታል!!

  የሚመጣው ቅዳሜ ሳምንት
      🗓ጥር 24
/2017 
             ቂልጦ_ጎሞሮ እንገናኝ!!

   🕌 መርከዝ አስ_ሱናህ ቂልጦ ጎሞሮ የሰለፊዮች የዓይን ማረፊያ።

📤 الدال على الخير كفاعله.

📤 የሰማችሁ ላልሰሙት ሼር በማድረግ የኸይሩ ተካፋይ ይሁኑ::






🔗
https://t.me/+UhQFsq-4FgB00672


🚨صفات عباد الرحمان
.
🚨የአርረሕማን ምርጥ ባሪያዎች መልካም  ባህሪያት
                       በሚል ርዕስ
.
          ማራኪ የሆነ የእሁድ ሙሀደራ
.
🕌.በመስጂድ አል-ፈላህ ዳለቲ
.
📻.በኡስታዝ አቡ አብድልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ حفظه الله
.
https://t.me/selefya
https://t.me/selefya


قال ابن تيمية رحمه الله :
«الناس يطلبون المجد في الملوك ولا يجدونه إلا في طاعة الله».
[مجموع الفتاوى 15/426]

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ አንዲህ አለ:–

" ሰዎች ልቅናን በንግስና ለማግኘት ይፈልጋሉ ነገር ግን አላህን በመታዘዝ ውስጥ እንጂ በሌላ አያገኙትም።"

መጅሙዑ አልፈታዋ 15/426

https://t.me/selefya


🎥ሆሊውድ በአላህ አላግጣ የጇን አገኘች።

ሆሊውድ የተባለው የአሜሪካ ቆሻሻ የፊልም ኢንዱስትሪ ከቀናት በፊት የፊልም ምርጫ አድርጎ ነበር።
በዚህ አስፀያፊ ስብስባቸው የምርጫው መድረክ መሪ የነበረች ሴት ኮሜዲ ፊልሞቹ ያገኙትን ነጥብ ስትናገር
👉1ኛው ፊልም = 11 ድምፅ አግኝቷል
👉2ኛው ደግሞ = 3 ድምፅ አግኝቷል
ካለች በኋላ
🚫3ኛው ፊልም = አምላክ (አላህ) የአለም ፈጣሪ ነው የሚለው ፊልም ዜሮ ድምፅ
ብላ ሳቀች ።
ከዚያም ይህ ቤት ፈጣሪ የለውም አለች።
መድረክ ላይ ያለ ሰው ሁላ በሷ ማሾፍ እየተደሰቱ አሽካኩ።

🔥🔥🔥
ከዚህ ስብስባቸው 1 ወይም ሁለት ቀን በኋላ አላህ በላውን አወረደባቸው።
በካሊፎርኒያ ግዛት የሚገኘው ሎስ አንጀለስና የሆሊውድ ኮረብታ በእሳት አመድ ሆነ።
በዚህም ከነዚህ የሆሊውድ ሰዎች የብዙዎቹ ቤት ወደመ።
👏 አላህ ይህን የቆሻሻ መፈብረኪያ ጨርሶ ያውድመው

☄☄ጄምስ ዉድ የተባለው ከነዚህ የሆሊውድ ፊልመኞች ውስጥ አንዱ የሆነው  የዛሬ አመት አካባቢ ኢስራኤልን ደግፎ
እዝነት የለም
ጨርሷቸው
እያለ ፖስቶ ነበር።
ዛሬ በዚህ ቃጠሎ ቅንጡ የሆነው ቤቱ ሙሉ በሙሉ ሲወድምበት ሚዲያ ላይ ወጥቶ አለቃቀሰ።
ብዙ የማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች
የእጅህን ነው ያገኘኸው በማለት ሲወቅሱት ተሰምቷል።


☄☄በሌላ በኩል ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ
የኢስራኢል እስረኞች የማይለቀቁ ከሆነ መካከለኛው ምስራቅን ገሃነም አደርጋታለሁ”
ብሎ ዝቶ ነበር።

ነገር ግን እሳቱ ቀድሞ ቤቱ ውስጥ ተቀጣጠለ።
الحمد لله
አላህ የአሜሪካን ደካማነት ከአለም ፊት አዋርደህ  አሳየኸን።

አቡ ዩሱፍ

👉https://t.me/AbuEkrima


https://t.me/selefya




📻 تسجيلات  الإسلامية السلفية بدار الحديث بمسجد الفلاح  في الحبشة: يسرها أن تقدم لكم هذه المادة وهي عبارة عن خطبة جمعة

🔖 በአላህ ታዕምራቶች መማር

🔜 በሚል ርዕስ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ የጁመዓ ኹጥባ።

🎙 لأستاذنا الفاضل الداعي إلى الله أبي عبد المنان خالد بن طيب  الحبشي حفظه الله تعالى

🎙️ በኡስታዝ አቡ አብድልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ አላህ ይጠብቀው።
.
📆.2/5/2017

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
📎https://t.me/selefya
     https://t.me/selefya


☑️ቀደምቶችና አስገራሚ ወንድማማችነት

🔹🔸ከቀደምት ሰለፎች መካከል አንድ ሰው ወደ ጓደኛው ቤት ይሄዳል።
✏️ጓደኛውም "ሞነው በዚህ ሰኣት መጣህ?'' ይለዋል።
👉እሱም "አራት መቶ ዲርሀም እዳ አለብኝና ክፈልልኝ።" ይለዋል
✏️ ጓደኛውም ቤቱ ይገባና አራት መቶ ዲርሀም መዝኖ ይሰጠዋል።
👉 ከዛም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገብቶ ማልቀስ ይ ጀ ም ራ ል ።
✏️ሚስቱሞ " ገንዘቡን የምትፈልገው ከሆነና መስጠት የማትችል ከሆነ ለምን የለኝም ብለህ ምክንያት አታቀርብም ነበር አሁን ማልቀሱ ምን ያ ደ ር ጋ ል ? " አለችው።
👉እሱሞ " እኔ የማለቅሰው እሱ እኔ ጋር መጥቶ እስከሚነግረኝ ድረስ ወንድሜ ያለበትን ሁኔታ ባለማወቄ ነው።'' አለ

☑️እኛስ ከነሱ አንፃር የት ነን እስኪ እራሳችንን እንፈትሽ ።

🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16781

t.me/selefya


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
✍نصيحة ابن عثيمين رحمه الله للمرأة الغيورة

✅‌‌‌‌‏قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله تعالى :

من طبيعة المرأة أن تغار على زوجها ، وهذا دليل على محبتها له ..

ولكني أقول : الغيرة إذا زادت صارت غبرة وليست غيرة ، وتتعب المرأة تعباً شديداً !!

لذلك أشير على المرأة أن تخفف من غيرتها ..

ታላቁ ሼይኽ

"ሴት ልጅ በባሏ ጉዳይ ያላት ቅናት ልከኛ ይሁን" ይሉናል


{ اللقاء الشهري [ ٣١ ] / ‎فتاوى_المرأة }

t.me/selefya

♻️-==-==-📘📗📕-==-==-♻️
#قناة_أبي_خالد_الدعوية
https://t.me/AbuKhlid3320/54066


🩸 አብሬት የሽርክ መናገሻ ⤵️

🔗 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17584


🩸 አብሬት የሽርክ መናገሻ ⤵️

💧 በሚል ርዕስ ከፊል አብሬት ላይ የሚሰሩ ሙኻለፍዎች በጉራጊኛ ቋንቋ የተዳሰሰበት.....

......ወቅታዊ የሆነ ሁሉም ሰው ሊያዳምጠው የሚገባ መካሪ የሆነ ሙሐደራ።

🎙በኡስታዝ አቡ ሀምዛ አብድልወዱድ አላህ ይጠብቀው።

🕌 በመስጂድ ሱና በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን {ቋንጤ}

🔗 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17584


📌ዛሬ የምንሰማቸው ጉዳጉዶች መነሻቸው ት/ቤቶች ናቸው ብል ማጋነን አይሆንብኝም።

📌ትምህርት ቤት ውስጥ የሚለመዱ መጥፎ ባህሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መልካቸውን እየቀየሩ ወደ ከፋ ደረጃ ደርሰዋል❗️እጅግ በጣም መጥፎ ስራዎች በብዙ ት/ቤቶች ይተገበራሉ። መቼም እኔ እንዲህ ብዬ ዘርዝሬ አልነግርህም።
👉አንተ ወላጆች ሆይ ፈልገህ ድረስበት ምክንያቱም ለልጅህ ስትል
ልጅህን ታጣዋለክ ለፍተህ፣ ላብህን ጠብ አድርገህ ያሳደከው ልጅ ወይም ሴት ውሏቸው አጉል ሀሳባቸው የተበላሸ ከሆነ ምን አተረፍክ❓

📍ለአብነት ያህል ስለ አንድ የግል ት/ቤት የደረሰኝ መረጃ ላካፍላችሁ ። እዚህ ት/ቤት ወስጥ ድንገት ተማሪ ለማምጣት የሄደው ሰው ያልጠበቀውን ነገር ተመልክቷል።
ቀኑ water day ( የውሃ) ቀን ይባላል በነገራችን ላይ የማይከበር ቀን የለም ጭራሽ የእብደት ቀን ሁላ ይከበራል እንደው እንደ ሸሪዓ ይቅርና እንደ ሰው ስናስበው ምን ማለት ነው ክሬዚ ዴይ( የእብደት ቀን) አላህ ይጠብቀን። ምኞት ነው ወይስ ምንድን ነው❓እብደት ፀጋ መስሏቸው ነው ❓እንዴት አስበውት እንደሆነ እኔንጃ? እንዘምን ነው ነገሩ።
🏮መቼም የነጮቹን ቆሻሻ የመሸከም አቅም ብቻ ነው ያለን መልካም መልካሙን ለሀገር ለራስም ጠቃሚ ነገሮችን መያዝ ከባድ ሆኖብናል
ለነገሩ አስሩ ቆሻሻ አይምሮ ስር የተሸገሸገበት ልጅ ከየት መጥቶ ትምህርቱን ይወዳል እንዴትስ ይገባዋል ።
ለማንኛውም ወደ ታሪኩ ልመልሳቹ 👉እናም ቀኑ እንዳልኳችሁ የውሃ ቀን ነበር ታዲያ ይህ ሰው ድንገት የግቢውን በር ከፍቶ ሲገባ ሴቶቹ በጡት ማስያዣ ሆነው እያበዱ ሙዚቃው ተከፍቶ ውሃ ይረጫጫሉ: በጣም የሚገመው የት/ ቤቱ ባለቤት ራሱ አብሯቸው ይረጫጫል ይጨፍራል ። እንግዲህ ይታያችሁ እዚህ ት/ቤት በጣም እጅግ በጣም ብዙ ሙስሊም ተማሪዎች አሉ ምን አይነት ተርቢያ ይያዙ? በዚህ መልኩ መሆን ማለት ከባድ ነው ሰው እንዴት ባደባባይ ወንጀል ይፈፅማል።ምን አይነት ጋጠወጥ ትውልድ እፈራ እንደሆነ ተመልከቱ❗️

🏮እንዴት ሆኖ ነው ግን እነዚያ ኢኽዋኖች እና ጀምዕዮች ስለዚህ ግብስብስ ህይወት ባገኙት አጋጣሚ ሚደሰኩሩን እኛ ብዙ ምናውቃቸው ትውልድ ገዳይ አስተሳሰብ ያላቸው ግን ራሳቸውን ሙፈኪረል ኢስላም አድርገው እንደፈለጉት ሰውን የሚነዱ ሰዎ እንዳሉ እናውቃለን ። አላህ ሂዳያ ይስጣቸው ።
📍ወንድሞቼ አሁን እኮ የሚማር መች ጠፋ የጠፋው እውቀት ፈላጊ እንጂ የእውነት ተማሪ ነው የጠፋው
ት/ ቤት ውስጥ ጫት ይዞ የሚገባ ተማሪ ምን ትለዋለክ ? ይህ ብቻም አይደለም አደንዛዥ እፅ ተጠቅሞ የሚገባም አለ።

የመማር ፍላጎት የሌለው ወጣት ት/ቤት ስለ ላከው እውቀት ይገበያል ማለት አይደለም።
👉 በርግጥ ሰለፍዮች ስለ ትምህርት ሲያወሩ ልጆች አይማሩ እውቀት ጎጂ ነው ምናም አይነት ሀሳብ እንዳላቸው አድርጋችሁ የምታወሩ ሰዎች አላችሁ ልክ አይደላችሁም❗️
ወደ ፊት እንደውም ከብዙ ሰዎች ፍላጎት የተነሳ መድረሳዎቻችንን አሰፋፍተን አጠቃላይ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ለመቀየር ቁርጠኛ ሀሳብ ያለን ሰዎችን መሆናችንን ተገንዘቡ

👉እንዴት ሆኖ ነው ሰለፊዮች እውቀት የሚጠሉት❓
ለዱንያ የሚጠቅም እውቀት እንደ አስፈላጊነቱ ይወሰዳል ችግር የለውም። እኛ ጋር ችግር ብለን ምናስባቸው ነገሮች በርግጥ አሉ ከችግሮቹ ውስጥ አንዱን ላንሳላችሁ የወንድ እና ሴት ተቀላቅሎ መማር ይህ ነገር ከባድ ጥፋት ነው። አሁን ላይ ተማሪዎች በብዛት ስለ ምንድን ነው ሚያወሩት ቢባል ያለ ምንም ማጋነን ስለ ተቃራኒ ፆታ ነው። ይህ ደግሞ ትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ፈፅሞ አያደርጋቸውም ።
እውቀቱ የሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች እውነት ትክክለኛ ትውልድ ይፈጥርልናል ወይ ነው ሌላኛው ጥያቄ ❓
🩸 ከኢለመንተሪ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተመልከቱ የምር መውለዳችሁን ትጠላላችሁ ።
👉አንድ ሰው ነበር ይህ ሰው ብዙ ጊዜ ሴቶች ዩኒቨርሲቲ ሄደው መማር አለባቸው ብሎ ይከራከራል ታዲያ የሆነ ወቅት ላይ ለስራ ጉዳይ ከጓደኛው ጋር ክፍለ ሀገር ሄዶ በማታ ለመመለስ ጉዞ ሲጀምሩ ብዙ ሴት ተማሪዎች አስፋልቱን ሞልተውት ቆመው ያያል ከዛም እነዚህ ምንድናቸው ሲል ጠየቀ? የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሆናቸው ይነገራዋል በዚህ ጊዜ ያ ሁላ ክርክር ቀርቶ እኔ ልጄን በተአምር ወደዚህ አልክም እስከማለት ደረጃ ላይ ደርሷል።

👉 ኡማው ሚያስፈልገው ዋና ነገር ዲን ነው ፣ ተርቢያ ነው ። የዱንያውን እውቀት ለመስጠት ጥርት ያለ አየር ፈጥረንላቸው ሲሆን እጅግ የላቀ ጥቅም ያስገኛል ካልሆነ ግን አንድ ሺ ተማሪ ልከህ የሚማረው አስሩ ነው ። በዚያ ላይ ከትምህርታቸውም ከዲናቸውም ያልሆኑ እንዝላል ይሆኑና ለቤተሰብም ለሀገርም ሸክም ይሆናሉ።

ለልጆቻችን መስተካከል ትልቁ አማራጭ በተርቢያ የተሞላ መዋያን ማመቻችት ነው።
ካልሆነ ግን… ልጆቻችሁን ቻው ቻው❗️

👉https://t.me/AbuEkrima

20 last posts shown.