ፀፀት!
እንደ ወትሮዬ የፀሐያን ግብዓት ተመልክቼ ለወክ(ለእግር ሽርሽር) ተሰነዳድቼ ከቤት ወጣውኝ። ከሰሞኑ የምሰማቸው "የሰዎች ስግብግብነትና ራስ ወዳድነት" ወሬዋች ራሴን አነውዘውኝ በምሄድበት(ኮብል ስቶን) የተጠረበ ምንጣፍ ድንጋይ ላይ እግሬን በቀስታ እየለቀኩኝ ከራሴ ጋር በሆዴ እያወራው እሄዳለው፤ አንዳንዴ ንግግሩ ከሆዴ አፈትልኮ በመውጣት የአደባባይ ጉዳይ ይሆንና በተናገርኩት ነገር ሰው አየኝ አላየኝ በማለት ስቅቅ እያልኩኝ ከሰሙኝ ሰዎች እስክሰወር ፈጠን ፈጠን ያለ እርምጃ እራመዳለሁ።
ሰዎቹ ከእኔ መራቃቸውን ወይም ከእኔ ጋር አለመሆናቸውን ከተረዳሁኝ በኋላ ዳግም በዝግታ እየተራመድኩኝ ቤት ውስጥ ሴቶች ሲያወሩ የሰማውትን አብሰለስላለው። በእንዲው ሙድ ውስጥ እያለሁ ከየት መጣ ያላልኩት ልጅ ፀጉሩ የተንጨፈረረ፣ ከታች ሰማያዊ የሴት ታይት ያደረገ፣ ከላይ አልፎ አልፎ ቀዳዳ ቀዳዳ የሚታይበት ወይን ጠጅ ቲሸርት የለበሰ፣ ባዶ እግሩን የሆነ፣ ፊቱ የወየበ፣ ቁመቱ ሜትር ከሰባ ሚደርሰው ከመንገድ ላይ እንቅልፍ እንዲ ብሎ ቀሰቀሰኝ "አባት አምስት ብር አለሽ"? ማነው ብዬ ስመለከተው ከላይ የገለፅኩላቹ ልጅ መሆኑን አወኩኝ። እሱ መሆኑን ሳውቅ ችላ ብየው መንገዴን ቀጠልኩኝ፤ እሱ ግን አልተወኝም ነበር። ዳግም "አባት! አባት በቃ እሺ አንድ ብር አድርጊው። ልምጣ አለኝ?" ከኋላ ኋላዬ እየተከተለኝ። ዞሬ ገላመጥኩትና መንገዴን ቀጠልኩኝ። የገረመኝ ነገር ቢኖር ፍቅረኛዬ ጋር ካርድ ሞልቼ ለመደወል ከታክሲ የተረፋኝን ሳንቲሞች የኋላ ኪሴ ውስጥ አምስት የአንድ አንድ ብር ሳንቲም መኖሩና በመጀመሪያ የጠየቀኝ የብር መጠን እኩል መሆኑ ነው። ከዛው ወርዶ አንድ ብር ማለቱ ደግሞ አናደደኝ በማላቀው ነገር? ልጁ ከነጀሰኝ በኋላ ከፊት ለፊቴ የአስር አስር ብር ኖት እየቆጠረ ከፊት ለፊቴ ልጅ እግር ልጅ መጣ። "ምናለ ልጁ እዚህ ጋ ቢሆን ኖሮ" አልኩኝ የልጁ አቆጣጠርንና የብር ብዛቱን አይቼ። ይሄን አይቼ ሳልጨርስ የተቀቀለ ድንች(ፌንቸራ) የምትሸጥ ሴትዮ የሸጠችውን ብር በዓይነት በዓይነቱ ከፌስታል ውስጥ እያወጣች ታስተካክላለች። በድጋሜ ጠያቂና ሰጪ አለመገናኘት አልኩኝ። በማያገባኝ ገብቼ በሃሳብ ከምሰቃኝ ፍቅረኛዬ ጋር ድውዬ እስቲ ላውራት በማለት አቅራቢያዬ ካለው ሱቅ ካርድ ገዝቼ መንገድ ለመንገድ እየሄድኩኝ ካርዱን ሞላውት። ከፊት ለፊቴ አንድ ሴትና ወንድ ህፃናት ልጆች ይሄዳሉ። በአምስት ብሩ የአየር የድምፅ ጥቅል አገልግሎት ገዝቼ ወደ ፍቅረኛዬ ብደውል ስልኳ አይነሳም! ደገምኩት አሁንም አይነሳም፣ ለሶስተኛ ጊዜ ሞክሬ እምቢ ሲለኝ ሞባየሌን ኪሴ ውስጥ ከተትኳት። ልጆቹ አሁንም ከፊቴ ይሄዳሉ። ሴቷ በቀኝ እጇ ነጭ ፌስታል ይዛለች። በፌስታሉ አየሩን እየቀዘፈች ውስጡ ታስገባዋለች። ወንዱ "ከየት ነው የምገዢው" ሲላት ሰማው። ዐይኔ ማን እንዳዘዘው ባላውቅም ፌስታሉ ላይ አተኮረ የልጁን ጥያቄ ተንተርሶ። ዐይኔ ከፈለገው ውጪ የዚህ ሰዓት አየ። የልጅቷ እጅ ውስጥ ሁለት አስር ብሮች። እንዴት ቅድም ሳላየው እያልኩኝ ተገርሜ ሳልጨርስ፣ ልጆቹ በስተቀኝ ባለው መታጠፍያ ታጥፈው ሲሄዱ እኔ ደሞ ግራውን መታጠፍያ ይዤ ወደ ሆስፒታሉ የሚወስደውን መንገድ ያዝኩኝ። ቀን ላይ ቸፍ ቸፍ ያለው ዝናብ መንገዱ ላይ ውሃ አቁሮ ተኝታል።
ጫማዬ እንዳይበላሽ ዳር ዳሩን ይዤ አለፍኩኝ። ግን ሌላ ትልቅ ተራራ ፊት ለፊቴ ተደቀነ። እናቴን የሚመስሉት እናት ከቀናት በኋላ ማደበሪያቸውን ዘርግተው የያጅ፣ ወራጁን እጅ ይጠባበቃሉ! በተለመደው ቦታ ሆነው። አሁን ተናደድኩኝ ካርድ በመሙላቴ፤ ንዴትን እንድጨርስ አልተፈቀደልኝም በመንገዱ ዳር ከእናቴ መሳይ እናት መቶ ሜትር ርቀት ላይ ከህፃን ልጇ ጋር በመሆን ለልመና የወጣች ባልቴት አየው። የማየውን ስላልወደድኩት ለጆሮዬ ሂርፎን አብጅቼለት ዘፈን እያዳመጥኩኝ የእግር ሽርሽሬን ማጣጣም ተያያዝኩት። የቀኑ ብርሃን ሙሉ ለሙሉ በአንፖል ሲተካ፣ በወጣ እግሬ ወደ ቤት ተመለስኩኝ። ድክም ብሎኝ ቤት ስለገባው፣ የፈረደባት ይመስል ቀን ቀን እንደ መቀመጫነትና ማታ ላይ እንደ አልጋ የምንጠቀምበት ሶፍ ላይ ለመሆን ልብሴን ለመቀየር ፈጠን ብዬ ጓዳ ገባው። የተጫማውትን ጫማ ቁጭ ባልኩበት በእግሬ የአንዱን በአንዱ አወለኩት። ሱሪዬ ጊዜውን ለመምሰል ብዬ እግሩ ጋር ስላስጠበብኩት ለማውልቅ እንዲመቸኝ በሆነ መልኩ ከወገቡ ጋር ገልብጬ እግሬ ስር አደረኩት። አንድ እግሬን አወጣውት፤ የቀረውን ለማውለቅ ታግዬ አወለኩት። የሱሪውን እግር ይዤ አጣጥፌ ለማስቀመጥ ስል ከየት መጣ የማልለው የአንዱ ብር ሳንቲም ከኪሴ ውስጥ ወድቆ "ቂልልል, ቂሊሊሊ" እያለ የቤቱ ወለል ላይ ተሽከርክሮ ፊት ለፊቴ ተቀመጠ። የኔ መሆኑን ተጠራጠርኩኝ? የት ውስጥ ተሸሽጎ ነው አሁን የወጣው? እኔ ማውቀው ባለአንድ ብሩ አምስት ሳንቲም መኖሩን ነው ኪሴ ውስጥ። ሱሬዬን ማጣጠፍ ትቼ ቁጭ ባልኩበት ልጁ ፊቴ ላይ መጥቶ በጣቱ አንድ ቁጥር ሰርቶ "አባት እሺ አንድ ብር ካለክ" ያለኝ ትዝ አለኝ! ለምንስ አንድ ብር ጠየቀኝ? አንድ ብር በአሁን ሰዓት ምን ያህል አስፈልጎት ነው እየተከተለኝ የጠየቀኝ አልኩኝ? ጊዜው ካለፈ በኋላ። በሶፍው ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ተኝቼ ዘፈን ማዳመጤን ትቼ ለፍቅረኛዬ የተከሰተውን ለመንገርና ታናፋቂ ድምፃን ሳልሰማ መተኛት ስለማልችል ደወልኩላት! ሞባየሏ ይጠራል ግን አታነሳውም። አምስት ጊዜ ሞከርኩኝ? ምንም ምላሽ የለም። ስልክ ባለመነሳቱ ተናደድኩኝ። ንዴቴ እየበረደ ሲመጣ ግን "ምን ሆኗ ነው " ብዬ መጨነቅ ጀመርኩኝ። በተኛውበት በእጄ ላይ ያለውን የአንድ ብር ሳንቲም እያገለባበጥኩ። ይሄኔ ልጁ ዐይኔ ላይ ድቅን አለ። ብሩን የጠየቀኝ ይሄ እንደሚፈጠር አስቀድሞ አውቆ ይሆን? ለሊቱን በሙላ እንቅልፍ እምቢ አለኝ! ልጁ የጠየቀኝን አለመስጠቴ ፀፀተኝ። እናቴን መሳይ ነድያንና የልጅ እናቷ እጅ እጄን ሲመለከቱኝ ትቻቸው ማለፌ በፀፀት አንገበገበኝ። ስለ ስግብግብነትና ራስ ወዳድነት ቤት የሰማውት፤ ስጋ ለብሶ በእኔ ውስጥ ሲገለጥ አገኘውት።
# ከምህረትዬ B.
# 21/1/2014 ዓ.ም
@Sewmehoneth