ሙሁሩ!
ከቢሮው ደረጃ እየወረደ፤ ከስር ከስሩ መከታተሌን እንዳላቆምኩ ስላወቀ፤ ወደ ኋላ በመዞር "እኛም እንደ አንተ ነው፤ በድህነት ውስጥ ሆነን ተምረን እዚህ የደረስነው። በል ባለህበት ቦታ በርትተ ተማር"! በማለት ወደ መኪና ማቆሚያ ቦታ ባለውበት ትቶኝ ሄደ። የዩኒቨርሲቲ ቅያሪዬን ውድቅድቅ አድርጎብኝ። ቁብ እንዳልሰጠውት እንኳን የሚያሳየው? እንባዬን እንደ ጅረት በቆምኩበት እያፈሰስኩኝ እያየኝ እንዴት እንዳለው ለማወቅ አንዴም ስንኳ ወደ ኋላ ሳይዞር መኪናውን ከፍቶ ገብቶ መሄዱ ነው።
ንግግሩ አደራረቀኝ፤ እንቧ ፊቴ ላይ ሞላ! በእጄ የያዝኩትን የትምህርት ማስረጃ አሽቀንጥሬ ከፊት ለፊቴ ተዘርጎቶ የሚገኘው አሰፋልት ላይ ወረወርኩት።
ከዓመታት በኃላ እኔ በትምህርት ላይ እንዳለው, "እኛም እንደ አንተ በድህነት ውስጥ ነው የተማርነው ያለኝ" የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በረሃ መውጣቱንና መሸፈቱን ሰማው፤ ያሸነፈውን ድህነት ዳግም አገኘው። ድህነትም ሸምቆ ወጋው። ሸምቆ አንበረበደው! ሽምቅ ተዋጊና ድህነት አጥፍተናቸው ይነሳሉ ለካ፤ ራሳቸው በሚያውቁት ቀመር። እሱንም ድሃነት ሽምቅ ወግቶት ዳግም በረሃ ገብቶ ጠብመንጃ እንዲያነሳ አደረገው። ድህነትን በዕውቀት ሳይሆን በጠብመንጃ ዳግም ሊያሸንፈው።
እኔ ግን? እኔ ግን? ከዓመታት በኃላ እዛው ፍራሼ ላይ ነበርኩ። ዩኒቨርሲቲ ሳልቀይር! አይ ጊዜ.... አሳልፈሽ አትሽጪኝ ለባለ ጊዜኛ!
# ....., ......, 2013ዓ.ም
# ከምህረትዬ B.
@Sewmehoneth