የ51 ተሳፋሪዎቹን ሕይዎት የታደገው ጀግና ሹፌር
እጁን በጥይት ተመትቶ ንፁህ ደሙን እያዘራ የ51 ተሳፋሪዎቹን ህይዎት የታደገው ጀግና
ጀግናው ሹፌር አየለ እውነቱ በሙያው የተመሰገነና የተከበረ የህዝብ ማመላለሻ ሀገር አቋራጭ አውቶብስ አሽከርካሪ ነው ።
መጋቢት 03 ቀን 2017 ዓ/ም ምድቡ ወደሆነው ወልድያ ከተማ ፣ እንደወትሮው ሁሉ 51 ተጏዦቹን አሳፍሮ ከሌሊቱ 10:30 ሰዓት ከአዲስ አበባ ላምበረት ተነስቶ በጭፍራ በኩል ወደ ወልዲያ ጉዞ ጀመረ ።
ይሁን እንጅ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ አፋር ገዋኔ አካባቢ እንደደረሱ አምነውት የተሳፈሩ ወገኖችን እንደያዘ ሀገር አማን ብሎ ወደፊት እየከነፈ ባለበት ወቅት ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ሀይሎች ጀግናው (ሽፍቶች) ሹፌር አየለ እውነቱ ላይ አነጣጥረው የጥይት እሩምታ ያወርዱበት ጀመር።
በዚህ የጥይት እሩምታ ቀኝ እጁ ላይ ከባድና ግራ እጁ ላይ ቀላል ጉዳት ቢደርስበትም ህመሙን ዋጥ አድርጎ ንፁህ ደሙን እያዘራ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ የሁለት ልጆቹና መላው ቤተሰቡ አምላክ ጥበቃ ፣ የሚያሽከረክረውን አውቶብስ በብስለት ተቆጣጥሮ እንዳይወድቅ አድርጓል ፣ በዚህም አውቶብስ ውስጥ የሚጏዙ 51 ተሳፋሪዎችን ህይዎት ታድጏል።
ረዳቱ ተስፋዬም የሚፈሰውን ደም በጨርቅ አስሮ በአካባቢው ወደሚገኝ ህክምና ቦታ እንዲደርስ አድርጓል። ሹፌር አየለ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛል።
ክብር በሞትና በህይዎት መካከል በስንት ፈተና እያለፉ ህዝብንና ሀገርን ለሚያገለግሉ ፣ ክብር ጥቃታቸው ጉዳታቸው ሞታቸው ውለታቸው ቢዘነጋም እነሱ በየመንገዱ እየወደቁ ፣ እየሞቱ አካላቸውን እያጡ ነፍሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው ለሙያቸው ለታመኑ ጀግና የሀገራችን አሽከርካሪዎች ። ...
ክብር ለሹፌሮች።
@sheger_press@sheger_press