ተገደሉ‼️
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ለገሰ ሥዩም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን ተገደሉ
ከፖሊስ አዛዡ በተጨማሪ የወረዳው የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ሲሳይ በሻዳ ተመትተው ጫንጮ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል፡፡
በጥቃቱ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አንድ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል በድምሩ አራት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
አማጺ ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን ጠዋት 3 ሰዓት አካባቢ ልዩ ስሙ ሮብ ገበያ በተባለ ስፍራ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ ፖሊስ አዛዡና የጸጥታ ኃይሎቹ ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊው ወደ ጫንጮ ሆስፒታል መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።
አማጺ ቡድኑ በማለት ቀድመው ማሳወቃቸውን ተከትሎ አመራሮቹና የጸጥታ ኃይሎቹ ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።
ሆኖም በስፍራው ሲደርሱ በአማጺ ቡድኑ በኩል በተከፈተባቸው ድንገተኛ የእሩምታ ተኩስ የፖሊስ አዛዡና የጸጥታ አባላቱ ሕይወታቸው ማለፉት ምንጮች ተናግረዋል። (ዋዜማ)
@Sheger_press