Shewa press


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter




ወንድማማችነት👥
ፋኖነት💪💪✊

@showapress


ጠቃሚ ነገር ልጠቁማችሁ👉 በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን #star ብላችሁ ጀምሩ👇👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl


ሕዳር 07 ቀን 2017 ዓ.ም
ባሕር ዳር

ብርሃኑ ጁላ ከብአዴን የተሸለመው ካባ ከትከሻው ሳይወልቅ ተዓምር ተሰርቷል!

ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ ሁለት ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከባህርዳር ኤርፖርት ተነስተው የተለመደውን የንፁሃን ጭፍጨፋ ሲያደርጉ ከዋሉ በኋላ ያልገመቱት ነገር ገጥሟቸዋል።

ከወጡበት ስምሪት ሲመለሱ ባህርዳር ኤርፖርት ለማረፍ ዝቅ ብለው በሚበሩበት ወቅት የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር በረጅም ርቀት መሳሪያ ለመምታት ባደረገው ርብርብ አንደኛዋ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ ችሏል:: በዚሁ ምክንያት የተመታችዉ ተዋጊ አውሮፕላን የሲቪል አውሮፕላን ማኮብከኮቢያው ላይ ተከስክሳለች።

በስፍራው የነበረው የመከላከያ ምዕራብ ዕዝ እስታፍ ሙሉ ኤርፖርቱን በቁጥጥሩ ስር በማዋሉ ምክንያት የእሳት አደጋ መኪኖች እና አምቡላንሶችም ወደ ስፍራው እንዳይገቡ ተከልክለዋል:: አብራሪውን ጨምሮ በረራው ላይ የነበሩት በሙሉ መሞታቸው ተረጋግጧል። መደበኛ በረራም ተቋርጧል::

የአብይ አህመድ ወራሪ ጦር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርፖርቶችን እና የሲቪል አውሮፕላኖችን ለሰራዊቱ መጠቀም ካላቆመ ፋኖ የበረራ ክልከላ (No Fly Zone) ወደ ማወጁ ይሸጋገራል።

ይኸኛው ትዉልድ አሸናፊ ነው!

አዲስ ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

©አስረስ ማረ ዳምጤ

@showapress


ህዳር 7/2017 ዓ_ም
ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ
በኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ ዋና መሪነት በፊት አውራሪ ባዪ አለባቸው የጦር አዛዥነት የሚመራው ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋታውና መብረቁ ብርጌድ የተዎሰኑ ሺ አለቃዎች ከጣይቱ ብርጌድ ጋር ጥምረት በመፍጠር ከጠዋቱ 2:00 ሰአት ጀምሮ ታላቅ ተጋድሎ እያደረጉ ሲሆን ጠላት ሀይል በአራት አቅጣጫ የተከበበ በመሆኑ መውጫና መግቢያ አጥቶ እየተቃተተ ይገኛል።

በሌላ በኩል ከመራቤቴ አለም ከተማ በመነሳት ወደ ጎረንዳዮ ሰርቃ ማርያም ያቀናው የጠላት ሀይል አይበገሬዎቹ የናደው ክፍለጦር አባላት አሰላለፍና ዎትሮ ዝግጁነት ከተመለአተ በኋላ ከባድ መሳሪያ ከርቀት በመዎርዎር የአካባቢው ማህበረሰብ በመዝረፍ ንፁሀንን በማፈን ወደመጣበት አለም ከተማ ፈርጥጧል።

ይህ እዲህ እዳለ መነሻውን እነዋሪ ከተማ መዳረሻውን ታሪካዊቷን ጅሁር ከተማ ያደረገ የጠላት ሀይል ወይራንባ ጨሶ ከተማን ከማለፉ በፊት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር መብረቁ ብርጌድ እየተዎቃ ይገኛል።

በሌላ በኩል በትናትናው እለትየአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ጀግናው ፊታውራሪ አስማረ ዳኘ ብርጌድ ተዎርዋሪ የፋኖ አባላት ትናት ህዳር 6/2017 ዓ_ም ሌሊት ጊና አገር ከተማ ሰርገው ገብተው በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት አሳግርት ዎረዳ በሚሊሻ ጠርናፊነት የዎረዳውን ህዝብ ሲገድል ሲያስገድል የነበረው ሀምሳ አለቃ አስናቀው ዎድማገኝ ማን አለብኝ ብሎ እቤቱ እንደተኛ የማያዳግም እርምጃ ተዎስዶበት እስከ ዎዲያኛው ተሸኝቷል።

ድላችን በክንዳችን
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሸዋ ዕዝ

@showapress


ባህርዳር አየር ማረፊያ ላይ ሄሊኮፕተር መውደቁን ተከትሎ ወደ አማራ ክልል መድና ባህር ዳር በረራ ተቋርጧል።

@showapress


በቅርቡ ሊስት የሚደረግ እና ጥሩ ዋጋ ይወጣለታል ተብሎ የሚጠበቅ በቴሌግራም የሚደገፍ አሪፍ Ardrop ነው። ያልጀመራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ፣start it ብላችሁ ጀምሩ👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl


በ ሸዋ መንዝ ባሽ  ተፈናቃይ ካምፕ ላይ   አገዛዙ ባደረገው የድሮን ጥቃት ብዙ ንፁሀን ወገኖች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@showapress


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የይፋትን ወጣት እየመራ የምስራቅ አማራ ፋኖን ተቀላቅሎ አስደናቂ ጀብዱዎችን የፈፀመው የሸዋው ጀግና ሰማዕት ፋኖ ስንታየሁ ማሞ (ራምቦ) በጓዶቹ እንዲህ ስሙ ሲጠራ መስማት የእሱን ህያውነት ማሳያ ነው:: በሸዋም የራምቦ መታሰቢያ ፕሮግራም ተከናውኗል::

ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ/ም ነበር የተሰዋው:: ነፍስ ኄር ጀግናችን::

ቪድዮ:- ራምቦ ክፍለ ጦር - ወሎ ቤተ አማራ

@Showapress


ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ

ዛሬ በፍርድ ቤት ያደረገው ታሪካዊ ንግግር

ከዚህ በመቀጠል በተከሰስኩበት ክስ የእምነት ክህደት ቃሌን እሰጣለሁ።
በቀዳሚነት የተከሰስኩት ጉዳይ የአማራ ህዝብ እኩል ከሌሎች ብሄሮችና ህዝቦች ጋር የአገር ባለቤት ሆኖ እያለ አገር ተወስዶበታል ብሎ ተናግሯል የሚል ነዉ።ክሴ ይሄን የሚል በመሆኑ አሁን ለፍርድ የቀረበዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ነዉ ማለት ነዉ።

የአማራ ህዝብ ላለፉት ሰላሳ አራት አመታት ፀረ አማራ ሀይሎች ተደራጅተው እና ተቀናጅተው ስልታዊ እና መንግስታዊ ጥቃት እያደረሱበት ያሉ ህዝብ ነዉ።
የአማራ ህዝብ የአገር ባለቤትነቱንበግልፅ በአደባባይ የተነጠቀዉ በ1983 ዓ.ም አማራ ጠል ሀይሎች የመንግስት ስልጣንን ተቆጣጥረዉ ባደረጉት የ ሰኔ 1983ቱ የቻርተሩ ጉባኤ ነበር።
ጉባኤው ያለምንም የአማራ ህዝብ ዉክልና የተካሄደ መሆኑን የስርአቱ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በአደባባይ የመሰከረው ሀቅ ነዉ።በዚህ የቻርተር ጉባኤ የተመሰረተው የሽግግር መንግስት  ባደረገው የክልል አከላለል ዉስጥ ምንም አይነት የአማራ ህዝብ ዉክልና  ያልነበረው ሲሆን በዚህ የሽግግር መንግስት ዘመን የተዘጋጀው ህገመንግስትም የአማራን ህዝብ በማዉገዝ ተጀምሮ በማዉገዝ ያለቀ መሆኑን የቻርተሩ ጉባኤ ቃለጉባኤዎች ,የሽግግር ም/ቤቱ ቃለጉባኤዎች,የህገመንግስት ጉባኤ ቃለጉባኤዎች ዘላለማዊ ምስክር በመሆኑ ያስረዳሉ ።
በዘመኑ ትህነግ/ኢህአዴግ በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙት አድሏዊ ድርጊቶች ,መፈናቀሎች,የንብረት ዉድመት,የዘር ፍጅትእና አገር አልባነት ልለፈዉና የዛ ስርአት ቀጥተኛ ወራሽ የሆነውን የብልፅግና ፓርቲ እና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመዉን እና እየፈጸመ ያለዉን በደል ልግለፅ።

የብልግና መንግስት በአማራ ህዝብ ተጋድሎ ወደ ስልጣን የመጣ ቢሆነም ህገመንግስታዊ ማሻሻያን ጨምሮ ፀረ አማራ የሆኑትን የመንግስት ፖሊሲዎች አስተካክላለሁ ብሎ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም በተግባር ግን አማራ ጠል መሆኑን ያስመሰከረዉ ጊዜ ሳይወስድ ነበር።
የብልፅግና መንግስት ከ ትህነግ ኢህአዴግ የወረሰውን የፌደራል እና የክልል ህገመንግስቶች ,ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ይዞ ቀጥሏል።ከ 50 በላይ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም ፀረ አማራነትን የሚቀሰቅሱ መፃህፍት አሳትሟል ።በምርምር መፅሄቶች ስም አማራ ጠልነትን ሰብኳል።በመንግስትነቱ በሚያስተዳድራቸው በኦሮምያ ቱሪዝም ቢሮ,በኦሮምያ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት,በኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅቱ ስር በሚታተሙ መፅሄትና ጋዜጦቹ በአማራ ህዝብ ላይ ለአመታት የቆየ የጥላቻ ዘመቻ አካሂዷል ።ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፀረ አማረ ንግግሮች እና ትንኮሳዎች ተደርገዋል።

በተጨማሪም የብልፅግና መንግስት የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ዉክልና እንዳይኖረው በማድረግ ዛሬ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠረው ከአማራ ክልል ዉጭ የሚኖረው የአማራ ህዝብ ምንም አይነት የፖለቲካ ዉክልና የለዉም ።

ከመንግሥት የስራ ሀላፊነት ጠርጎ በማዉጣት አድሎአዊ አሰራርን በማስፈን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በማፈናቀል ፣ በቢሊዮኖች የሚገመት የአማራን ህዝብ ሀብትና ንብረት በማውደም እንዲሁም ዘግናኝ የሆነ እንኳን ሊያዩት ሊሰሙት እንኳ የሚከብድ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም አድርጓል ። ይህ የዘር ፍጅትበመላው ኢትዮጵያ በሶማሌ ፣ በኦሮሚያ ፣ በትግራይ ፣ በሲዳማ ፣ በቀድሞ የደቡብ ክልል ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች የተፈፀመ ነው ።
ለዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአይን ምስክሮች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ ጥምረት እንዲሁም አለም አቀፍ የሆኑት የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የሂውማን ራይትዎችን ዘገባዎች በማየት መረዳት ይቻላል ።
  ጉዳዩን ሊከታተል ይችላል ተብሎ ይታሰብ የነበረው የብልፅግናው የአማራ ክልል መንግሥት ደግሞ እንኳን የአማራን ህዝብ ሊታደግ የገዛ ስልጣኑን የማያውቅ ፣ የፖለቲካ ነፃነቱን አሳልፎ የሰጠ እንዲሁም ከውሳኔ ሰጪነት ወደ ፈፃሚነት የወረደ ነው ። (ከክልሉ ውጪ ያሉ አማራዎች እንታገላቸዋለን እንጂ አንታገልላቸውም)ከማለት የደረሰ ሎሌ ነዉ።

   በተደጋጋሚ ባጋጠሙ ጉዳዮችም ተፈትኖ የወደቀ ለምሳሌ በአማራ ልዩ ሃይል መፍረስ ፣ በፕሪቶሪያ ድርድር ፣ በሱዳን ወረራ ፣ በአጣዬ እና ሸዋሮቢት ፍጅት የአማራን ህዝብ መብት ማስከበር ያልቻለ ለተፈናቃይ ዱላ ለዘር ፈጂዎች ግን ካባ የሚሸልም ስብስብ ነው ።

     የፌደራል መንግሥቱ ደግሞ ያለምንም እፍረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ፣ አቃቢ ህጉ ፣ መርማሪው ፣ ደህንነቱ ፣ የፍርድ ቤት አስተዳደር በአጠቃላይ የአንድ ብሔር/ሀይማኖት አባላት በመሆን ህግን የማጥቂያ መሣሪያ በማድረግ የአማርን ሕዝብ ልጆች ያጠቃል ።
   የአማራ ሕዝብ ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያት የሀገር ባለቤትነቱ የተወሰደበት ፣ ሀገሩን የተቀማ በመሆኑ ፣ ድርጊቱም ሥርአታዊና መንግሥታዊ ለመሆኑ የሚመሠክሩ በርካታ ማስረጃዎች ያሉ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ከዚህ የህልውና አደጋ ለመውጣት መንቃት ፣ መደራጀትና እራስን ከጥቃቶች መከላከል ይገባዋል የሚል የፀና አቋም ያለኝ በመሆኑ ይሄንን ዘረኛ እና ነውረኛ አንባገነን ሥርዓት ለመጣል ትግል እንደሚያስፈልግ እምነቴ ነው ።

በጭብጦቹም ላይ

   * የሸዋ ፋኖን በማደራጀት በኩል የራሴን አስተዋፅኦ አድርጊያለሁ
  *የአማራ ፋኖን ወደ አንድነት ለማምጣት ሲባል የተመሠረተው አመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኜ ሠርቻለሁ
  *የአማራ ፋኖ ምክርቤት እንዲመሠረት የራሴን አስተዋፅኦ አድርጊያለሁ

  * አገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችና የብልፅግና መንግሥት እመራበታለሁ በሚለው ህገመንግስት በሰፈሩት ሰብአዊና እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹን መሰረት በማድረግ የህዝቤን ግፍ እና በደል ለማስቆም በህቡዕ ሳይሆን በአደባባይ ታግያለሁ።

*የሰራሁት በሙሉ በግልጽ በአደባባይ የተፈፀመ እንጂ ምንም አይነት ህቡዕ ድርጅት አቋቁሜ አልሰራሁ።

*በህቡዕ አደረጃጀት ተፈፀሙ የሚሉትን ተግባራት አላዉቅም።አልፈፀምኩም

የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራን ህዝብ በደል በደንብ ይገነዘባል ብዬ አምናለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ "የአማራ ህዝብ እንባ በዋንጫ"ቢሰጣቸዉ የማይጎፈንናቸዉን የብልፅግና ስርአት ቁንጮዎች በቃችሁ ሊላቸዉ ይገባል።

በተጨማሪም የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ለነፃነት ለእኩልነትና ለፍትህ የሚደረግ ትግል እንጅ ጠላቶቻችን እንደሚያወሩት ሌላዉን ለመጨፍለቅ የሚደረግ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ደግፎ እንዲቆም እጠይቃለሁ።

አለማቀፉ ማህበረሰብም የአማራ ህዝብ እየተፈፀመበት ያለዉን የዘር ፍጅትና መፈናቀል ቸል በማለቱ በጣም እያዘንኩ ለአምባገነኑ መንግስት ጅምላ ጨራሽ ድሮዎኖች እና ተተኳሾችን የሚያቀብሉ አገራት ታሪክና እና እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣችኋል እላለሁ።

አመሰግናለሁ ።
ኅዳር 5/2017 ዓ.ም

ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ
https://t.me/showapress


የአማራ ፋኖ በጎጃም ዘሪሁን 13 የጦር መሳሪያዎች ማምረቻ ተቋም የሰራው ፀረ ተሽከርካሪ መሳሪያ 💪💪💪።

@Showapress


በቅርቡ ሊስት የሚደረግ እና ጥሩ ዋጋ ይወጣለታል ተብሎ የሚጠበቅ በቴሌግራም የሚደገፍ አሪፍ Ardrop ነው። ያልጀመራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ፣start it ብላችሁ ጀምሩ👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl


የድል ዜና

ከ400 በላይ ሀይል ታንክና ሞርተር ተሸክሞ ፋኖ ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ቡድን በአንድ ሻለቃ የፋኖ አባላት አይቀጡ ቅጣት ተቀጣ።

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ የፋኖ አባላት ላይ ከረፋዱ 4 ሰዓት ጥቃት ለመፈፀም አስቦ ከበረኸት ወረዳ መዲና መጥተህ ብላ ከተማና ከምንታምር ከተማ በሁለት አቅጣጫ ሞቱ ጠርቶት ታንክና ሞርተር ተሸክሞ ወደ 07 ቀበሌ ያመራው ከ400 በላይ የአገዛዙ ፀረ አማራ ቡድን በክንደ ነበልባሎቹ የተስፋ ገብረስላሴ ብርሬድ የፋኖ አባላት ለተከታታይ 2 ሰዓት በቆየ ውጊያ ተቀጥቅጦ ሙትና ቁስለኛ በመሆን ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናግዶ ከቀኑ 6 ሰዓት ወደየመጣበት ተመለሰ።

ህዳር 2/2017 ዓ.ም በፋኖ ቁጥጥር ስር የነበረን ሎቤድ መኪና በሀይል ለማስለቀቅ ያለ የሌለ ሀይሉን አግተልትሎ አለኝ ያለውን ከባድ መሳሪያ አንግቦ በስህተት የጀግኖችን ምድር ለመርገጥ ያሰበው የብልፅግናው ወንበር ጠባቂ ቡድን የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ የፋኖ አባላት ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ውጊያ የጠላት ሀይል ለመውሰድ ያሰበውን ሎቤድ ትቶ በምትኩ ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ሔዷል።

ድል ለአማራ ህዝብ!
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ህዳር 2/2017 ዓ.ም

@Showapress


ወሎ ቤተ-አምሐራ
የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ

የአማራ ፋኖ በወሎ የምዕራብ ወሎ ኮር ቅርንጫፎች የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ክንፍ የሆነው አትሮንስ ብርጌድ እና የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለጦር በጋራ በመሆን የአገዛዙን አራዊት ሰራዊት ሲያደባዩት መዋላቸው ተገልጿል!!

ዛሬ ማለትም በዕለተ ሰኞ በቀን 02/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4:30 እስከ እኩለ ቀን ድረስ በ036 ወዠድ ቀበሌ ላይ በተደረገ ውጊያ የፋሽስቱ አብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን አምስት (5) ሙት እና ሶስት (3) ቁስለኛ ተደርጓል።  በዚህም አውደ ውጊያ ላይ  የአትሮንስ ብርጌድ እና የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለጦር የበላይነት ወስደው  ውለዋል። የአገዛዙ ጥምር ጦርም  እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጦ ወደ ከተማ ገብቷል።

የሰው በላው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ወንበደ ቡድን ሽንፈቱን ለማካካስ ደንሳ መሃል ከተማ ላይ ንፁሃንን እያንገላታና እየደበደበ መሆኑን  የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ይህ በእንድህ እንዳለ በጥምር ጦሩ ላይ ከቀን ወደ ቀን እየደረሰበት ያለውን ጉዳት የተመለከቱ የሚሊሻ አባላት ከድተው ወደ ወንድሞቻቸው  እየተመለሱ መሆኑን የአትሮንስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ ጎሹ ሳይንቴው ገልጿል። አዛዡ አክሎም ከቀን 27/02/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ቀን 02/03/2017 ዓ/ም ድረስ ከስምንት በላይ ሚሊሾች ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው እንደተመለሱ ተናግሯል።

የተቀሩትም በቅርቡ ወደኛ እንድመጡ እያልን ወንድማዊ ጥሪያችንን አስተላልፈናል ብሏል ፋኖ ጎሹ::
የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ህዳር 2/2017 ዓ.ም

@showapress


በቅርቡ ሊስት የሚደረግ እና ጥሩ ዋጋ ይወጣለታል ተብሎ የሚጠበቅ በቴሌግራም የሚደገፍ አሪፍ Ardrop ነው። ያልጀመራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ፣start it ብላችሁ ጀምሩ👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl


በጭንቀት ላይ ለሰነበታችሁ ዘመድ ወዳጆቸ እና የትግል አጋሮቸ በሙሉ።

ለገጠመኝ የጤና ችግር ከአንድ ቀን በፊት የተካሄደልኝ የቀዶ ጥገና ህክምና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል። የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ አሁን ላይ ጤናየ በጥሩ ሁኔታ ስለሚገኝም ከሆስፒታል ወጥቸ ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ። ስለ ደህንነቴ ተጨንቃችሁ በፀሎትና በሀሳብ ስታግዙኝ ለሰነበታችሁ ወዳጅ ዘመዶቸ በሙሉ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ። አሁን ረዥም ጊዜ የፈጀው የህክምናየ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ነው። ስለሆነም ወደ አገሬ ተመልሸ ለመሄድ የነበረኝ ከፍተኛ ፍላጐትና ጉጉት ዕውን ሊሆን በመቃረቡ ደስ ብሎኛል።

ከአክብሮት ጋር
ልደቱ አያሌው
ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም

@Showapress


በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል

https://www.facebook.com/100068240109154/posts/pfbid02y5J7B4hTB7zck55sA77BVRKeLntw8w8NaAmC4ifDzoCfqighJBfTCjLnmTNK9MNul/?app=fbl


በጎጃም ቀጠና የገባው አ*ራዊት እባካችሁ ይህን ክላሽ በሲቪልያን ልብስ ቀይሩልን እያለ እየተማጠነ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

@showapress

7k 0 3 10 74

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ፋኖ ዛሬም እንደ ትላንቱ መማረኩን እና ድል ማድረጉን ቀጥሏል💪💪

ጀግናው የወሎ ፋኖ የማረከውን ሰራዊት እንደ በግ እየነዳው ነው✊

#ድል_ለፋኖ
#ድል_ለአማራ

@shiwapress

19 last posts shown.