❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካች_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ #ለብርሃን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፮ "አቅዲሙ ነገረ በኦሪት አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ #ይመጽእ_ወልድ_በስብሐት ዘይዜንዋ ለጽዮን ቃለ ትፍሥሕት ወካዕበ ይቤ #በአፈ_ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ #በስመ_እግዚአብሔር_ብርሃን_ዘመጽአ_ውስተ_ዓለም_ዘያበርህ_ላዕለ_ጻድቃን መርዓዊሃ #ለቤተ_ክርስቲያን ይርዳእ ዘተኃጒለ ያስተጋብእ ዝርዋነ ኃቤነ"። ትርጉም፦ ዳግመኛ #በዳዊት_አፍ እንደነገረ #በእግዚአብሔር_ስም_የሚመጣ_እርሱ_ምስጉን ነው፣ ለጽዮን የደስታን ቃል የሚነግራት ወልድ በክብር እንደሚመጣ አስቀድሞ በኦሪት ተናገረ፣ #ወደ_ዓለም_የመጣ_ብርሃን_በጻድቃን ላይ የሚያበራ #የቤተ_ክርስቲያን_ሙሽራ የጠፋውን ሊፈልግ የተበተነውን ሊሰበስብ ወደ እኛ መጣ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ "ዕለተ ብርሃን" ፦ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስንና የቅዱስ ያሬድን አስተምሕሮ መሠረት አድርጋ ታኅሣሥ 14 ቀን "ዕለተ ብርሃን" ትለዋለች። ሳምንቱን (ከታኅሣሥ 14-20 ነው)። በእነዚህ ዕለታት እሑድ በዋለበትን ቀን ማኅሌት ተቁሞ ብርሃን ተብሎ ይከበራል። ደግሞ "ሰሙነ ብርሃን" ስትል ታስባለች::
❤ "ብርሃን" በቁሙ የእግዚአብሔር ስሙ፤ አንድም የባሕርይ ገንዘቡ ነው። "እግዚአብሔር ብርሃን ነውና:: ጨለማም በእርሱ ዘንድ የለችምና።" (ዮሐ 1፥4)
❤ በዚህ ዕለት "ብርሃን" በሚል መነሻ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ታስተምሠራለች:-
1.እግዚአብሔር ብርሃን መሆኑን። (ዮሐ 1፥5)
2.አምላካችን በመጀመሪያው የፍጥረት ቀን (በዕለተ እሑድ) ዲያብሎስ ቅዱሳን መላእክትን ሲረብሽ "ለይኩን ብርሃን" ብሎ ብርሃንን መፍጠሩን። (ዘፍ. 1፥2 አክሲማሮስ)
3.ነቢያት አበው በጨለማው ዓለም ሆነው መከራ ሲበዛባቸው "ፈኑ ብርሃነከ - ብርሃንህን ላክልን" እያሉ መጮሃቸውን። (መዝ 42፥3)
4.ጩኸታቸውን የሰማ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ (እውነተኛው ብርሃን) ወደዚህ ዓለም መምጣቱን። (ሉቃ 1፥26)
5."እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ሲል የባሕርይ ብርሃንነቱን እንደ ነገረን። (ዮሐ 8፥12)
6.ብርሃነ መለኮቱን በገሃድ መግለጡን። (ማቴ 17፥1)
7.ብርሃን የሆነችውን ሕግ፤ ወንጌልን እንደ ሠራልን:: (1ዮሐ 2፥9)
8.ድንግል እመቤታችን ብርሃን፤ የብርሃንም እናቱ መሆኗን። (ሉቃ 1፥26፣ ራዕ 12፥1)
9.ቅዱሳኑ ብርህን መባላቸውን። (ማቴ. 5፥14)
10.እኛ በሰው ፊት ሁሉ እንድናበራ መታዘዛችን። (ማቴ 5፥16) ሁሉ ይታሰባል።
❤ እርሱ ፈጣሪያችን ክርስቶስ ጨለማውን በምሕረቱ አርቆልናልና ዳግመኛ ወደ ጨለማ እንዳንሄድ እየለመንን እናመስግነው።
❤ "ክርስቶስ ብርሃን ዘአሰሰልከ ጽልመተ።
ላዕለ ኪሩቤል ነቢረከ ዘትሬኢ ቀላያተ።
ስቡሕኒ ወልዑል አንተ"። (መልክአ ኢየሱስ) ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ፔጅ የተወሰደ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ፈኑ ብርሃንከ ወጽድቀከ። እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ"። መዝ 42፥3። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 13፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 26፥12-19። የሚነበው ወንጌል ዮሐ1፥1-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ አትናቴዎስ ወይም ቅዳሴ እግዚእነ ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃን በዓል፣ ዕለተ ሰንበትና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
@sigewe https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwLhttps://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886