✅አባቴ እናዝናለን ፡ ካሁን በኋላ በምድር ላይ የሚቆዩት ግፋ ቢል ለስድስት ወራት ያህል ነው ።
........
✅እኚህ በምስሉ ላይ የሚታዩት አባት Stamatis Moraitis የሚባሉ በወጣትነት ዘመናቸው ሀገራቸው ግሪክን በወታደርነት ያገለገሉ ሰው ናቸው ።
እና በአንድ ወቅት ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን ለመጎብኘት በሄዱበት አሜሪካ ትንሽ ህመም ይሰማቸውና ወደ ሆስፒታል ይሄዳሉ ።
ሀኪሙ ግሪካዊውን ሰው በተለያየ አይነት የህክምና ዘዴ ከመረመረ በኋላ ፡ ሰውየው በማይድን የሳንባ ካንሰር እንደተያዙና ፡ ካሁን በኋላ በህይወት የሚቆዩት ለስድስት ወራት እንደሆነ ነገራቸው ። የዶክተሩን የምርመራ ውጤት ካዩ በኋላም ዘጠኝ አባላት ያሉት የዶክተሮች ቡድን ፡ ስለውጤቱ ትክክለኛነት ፈረሙበት ።
ይህን የሰሙት ሚስተር Stamatis አዘኑ ፡ ወደልጆቻቸው ቤት ከተመለሱ በኋላም መርዶውን ነግረዋቸው ተያይዘው ተላቀሱ ።
እንግዲህማ ወደ ሀገሬ ግሪክ ልሂድ ፡ ሞቴ እዛ ይሁን ቀብሬም አባት አያቶቼ ባረፉበት ቦታ ይፈፀማል በማለት ፡ ከጥቂት ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ግሪክ ተመለሱ ።
Stamatis Moraitis ወደ ግሪክ ከተመለሱ በኋላ ምንም እንኳን ከስድስት ወራት በኋላ እንደሚሞቱ ፡ በአስር ሀኪሞች የተፈረመ ፡ ወረቀት ቢይዙም ፡ ለወትሮ ከሚሰሩት ስራ አልታቀቡም ።
በህይወታቸው ውስጥ የተከሰተ ምንም አይነት ለውጥ እንደሌለ ቆጥረው ፡ እንደድሮው አትክልቶቻቸውን ይንከባከባሉ ፡ ወራት ለቀረው እድሜ ፡ ለመድረስ አመታትን የሚፈልጉ ፍራፍሬዎች ይተክላሉ ፡
እንዲህ እንዲህ እያሉ ፡ ሳይታወቅ ያቺ የቀጠሮ ወር ደረሰችና ፡ ለመሞት ቀናትን መቁጠር ጀመሩ ። ግን ምንም የለም ። ሰውነታቸው ደክሞ ከዛሬ ነገ ድንገት እወድቅ ይሆን እያሉ በስጋት በመጠባበቅም ፡ ስድስት ወሩን አለፉት ።
ሰባተኛ ወር ገባ ። ምንም የለም ።
አመት አለፈ ። ሰውየው ጭራሽ ንቁና ብርቱ መሆን ጀመሩ ። ሁለት ሶስት አመት አለፈ ። እንዲህ እንዲህ እያለ ፡ አስር አመት ሆናቸው እንደውም ፡ በፊት አልፎ አልፎ ይሰማቸው የነበረው የህመም ስሜት ራሱ ጠፋ ።
እናም በአስረኛ አመታቸው ፡ ልጆቻቸውና ፡ የልጅ ልጆቻቸው ወደ ሚኖሩበት አሜሪካ ሄደው ሊያዩዋቸው ፈለጉና ወደዛ ተጓዙ ።
ካሁን አሁን መርዶ እንሰማ ይሆን ብለው ለአመታት የጠበቁት ዘመዶቻቸው ጋር በአካል ተገናኙ ።
...........
ከቀናት ቆይታ በኋላ ፡ ከዛሬ አስር አመትበፊት ፡ ለመሞት ስድስት ወራት ብቻ እንደሚቀራቸው የነገሯቸው ዶክተሮች ያሉበት ሆስፒታል ሄደው ሰላም ሊሏቸው በዛውም አስሩም ዶክተሮች የፈረሙበትን ወረቀት ለዶክተሮቹ ሊያሳዩዋቸው ያዙና ወደ ሆስፒታሉ ሄዱ ።
ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ፡ አንድም ዶክተር ማግኘት አልቻሉም ። ሁሉም ሀኪሞች በተለያየ ጊዜ በህመም አልፈዋል ።
......
ግሪካዊው Stamatis Moraitis ከአስር አመታት በፊት ይህን ምርመራ ሲያደርጉ የስልሳ አመት አዛውንት ነበሩ ። እና ይሞታሉ ከተባሉ በኋላ ለሌላ ለ42 አመታት በህይወት ኖረው ፡ በ102 አመታቸው ከጥቂት አመታት በፊት አልፈዋል ።
.............
ጥያቄው አስር ዶክተር ፈረመ ? ሳይሆን ፡ ከላይ ተፈርሟል ወይ ነው ።