🇷🇺
በሩሲያዋ የካዛን ከተማ ላይ በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት እስካሁን የተጎዳ ሰው አለመኖሩን ባለስልጣናት ተናገሩ
"
የካዛን ከተማ ከምትገኝበት ታታርስታን ሀላፊ ሩስታም ሚኒክሃኖቫ የተሰበሰበዉ አሁናዊ መረጃ እንደሚያሳየው 8 የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን አንዱ ጥቃት የኢንዱስትሪ ህንፃን ኢላማ ያደረገ ሲሆን ሌላኛው አቅጣጫዉ ተቀይሮ ባህር ላይ ያረፈ ሲሆን ስድስቱ የመኖሪያ ቤት አካባቢ አርፏል። እስካሁን ባለን መረጃ የቆሰለም የሆነ የሞተ ሰው የለም። በኢንዱስትሪው ውስጥ የነበሩ ሰራተኞች ሸሽተው ወደ ሌላ ቦታ እንዲጠለሉ ተደርጓል" በማለት የሪፐብሊኩ መሪ ፅህፈት ቤት በዛሬው እለት ጠዋት መግለጫ አውጥቷል።
ፅህፈትቤቱ በተለየ የኢንደስትሪ ህንፃውን የመታው ሰው አልባ አውሮፕላን ህንፃውን በመታበት ወቅት ወድቋል ብሏል።
✈️ በካዛን ያለው አየር ማረፊያ እንዲሁም በኡድሙርቲአ አቅራቢያ የሚገኘው ኢዝሄቭስክ አየር ማረፊያ ከፀጥታ ስጋቶች የተነሳ በዛሬው እለት ጠዋት ተጥሎባቸው የነበረው ግዜአዊ እገዳ ተነስቶላቸዋል በማለት የሩሲያ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
🔥በካዛን በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ምክንያት በከተማዋ በሦስት ወረዳዎች የሚገኙ ቤቶች በእሳት መቃጠላቸው ተገለፀ።
የካዛን ከንቲባ ጽህፈት ቤት ደህንነትን ለማረጋገጥ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በታታርስታን ዋና ከተማ ውስጥ ሁሉም የህዝብ ዝግጅቶች መሰረዛቸውን አስታውቋል።
"ዛሬ ካዛን ከፍተኛ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ደርሶባታል። ቀደም ሲል የኢንዱስትሪ ተቋማት ዒላማ ቢሆኑም አሁን ደግሞ ጠላት ጠዋት ላይ ቤታቸው ውስጥ ያሉትን ሲቪሎች ዒላማ እያደረገ ነው" ሲሉ ባለስልጣኑ በቴሌግራም ላይ ገልጿል። አክሎም በቦታው ላይ የኦፕሬሽን ዋና መሥሪያ ቤት እንደተቋቋመ እና ነዋሪዎች ወደ ጊዜያዊ ማረፊያዎች እንደተዛወሩ ተናግረዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ 📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉
APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉
@sputnik_ethiopia