ራስ ምታት
🛑🛑🛑
“ ምንኛ ያማረች ቢድዐ “
ሰይዱና ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ
ዘኪ :- ሰይዱና ኡመር ረ.ዐ ኒእመቱል ቢዱአቱ ሀዚሂ (ምነኛ ያማረች ቢድዐ ነች) ብለዋል ምን ትላለህ ???
ወሀብያ: - በቋንቋ ደረጃ ነው ቢድዐ ያሉት
ዘኪ :- በቋንቋ ደረጃ ቢድዐ ምንድ ነው?
ወሀብያ:- ከዚህ በፊት ምንም አይነት ምሳሌ የሌለው ወይም ተሰርቶ የማይታወቅ ነገር ነው
ዘኪ:- ስለዚህ ሰይዱና ኡመር ረ.ዐ በዲን ላይ የማይታወቀ አዲስ ነገር ነው ያመጡት ማለት ነው ⁉️ እንዳንተ አባባል
ወሀብያ :- ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ቂያም አልለይል ሰግደዋል አዲስ ነገር አይደለም
ዘኪ :- እሺ ታዲያ ለምንድ ነው ሰይዱና ዑመር “ ቢድዐ “ ብለው የሰየሙት ??? አንተ ደግሞ በቋንቋ ደረጃ ነው ያልከው : ነብዩ ዐለይሂስሰላት ወሰላም የሰሩትን ስራ ከሆነ ያስቀጠሉት ለምን ቢድዐ ብለው ይጠሩታል ???
ወሀብያ :- ወላሂ ግራ አጋባሀኝ
ዘኪ :- አብሽር እንቀጥልማ ፡ ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም በረመዳን የሰገዱት የትኛው ወቅት ላይ ነው ??
ወሀብያ :- ለሊት ላይ ነው የሰገዱት
ዘኪ :- ትክክል ፡ ኡመር ረ.ዐ የሰገዱትስ ??
ወሀብያ:- ከኢሻ በኃላ
ዘኪ:- እሺ ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ስንት ረከአ ነው የሰገዱት ???
ወሀብያ:- 11ረከአ
ዘኪ:- ሰይዱና ኡመር ረ.ዐ ስንት ረከአ ነው የሰገዱት?
ወሀብያ:- 23 ረከአ
( እዚህ ጋር ልብ ልንለው የሚገባ ጉዳይ አለ : እርሱም የወሀቢዮች ሙሀዲስ ተብዬው አልባኒና መሰሎቹ ተራዊህ ከ 11 ረከአ በላይ መጨመር ሱናን መቃረን ነው ብለው ያምናሉ ፡ በእጅ አዙር ሰይዱና ኡመር እነርሱ ዘንድ ሙብተዲእ ናቸው ፡ ሀገራችንም 11 ረከአ የሚሰገድባቸው መስጂዶች የዚህ አስተምህሮት ውጤቶች ናቸው )
ዘኪ :- ነቢያችን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ተራዊህ የሚባል ስም ያውቁ ነበር ??
ወሀብያ:- አይ ፡ ሰይዱና ኡመር ረ.ዐ ናቸው ተራዊህ ያሉት
ዘኪ :- ነብዩ ዐለይሂስሰላት ወስሰላም በጀመዐ ሰግደውታልን ??
ወሀብያ :_ እርሳቸው ሳያውቁ ሰሀቦች ከኃላቸው ሰገዱ እንጂ ጀመአ ሰብስበው አልሰገዱም ፡ ኡመር ረ.ዐ ናቸው ጀመአ እንዲሰበሰብ አድርገው በጀመዐ ያስጀመሩት በመስጂድ ውስጥ ኢማም አድርገው።
ዘኪ :- ሰለዚህ የሰይዱና ኡመር ረዲየሏሁ ዐንሁ ሰላት ከነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሰላት ጋር በብዙ ነገር ይለያል
✅ በረመዳን የተሰገደው ሰላት በሰይዳችን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለምና በኡመር ረ.ዐ መካከል :-
💠 ነብዩ ሰ፡ዐ፡ወ የሰገዱት 11 ረከአ
💠 ሰይዱና ዑመር 23 ረከአ
💠 የነብዩ ሰ፡ዐ፡ወ ሰላት አልለይል የሰገዱት የለሊቱ መጀመሪያ : መሀከልና መጨረሻ ላይ ነው
💠 ሰይዱና ዑመር ከዒሻእ በኃላ
💠 ነብዩ ሰ፡ዐ፡ወ የሰገዱት ብቻቸውን
💠 ሰይዱና ዑመር ጀመዐ ሰብስበው
🟢 ስለዚህ የተራዊህ ሰላት ከዒሻእ ሰላት በኃላ፣በጀመዐ ፣መስጂድ ውስጥ ፣፣23 ረከዓ ወዘተ ሆኖ መሰገዱ በሰይዱና ኡመር ረዲየሏሁ ዐንሁ የተጀመረ ስለሆነ ነው ሰይዱና ኡመር “ ምነኛ ያማረች ቢድአ ናት “ ሲሉ የጠሩት።
ወሀቢያ :- አሁን ግልፅ እየሆነልኝ
ዘኪ :- “ እየሆነልኝ “ ??? ገና ሙሉ በሙሉ አልሆነልህም ማለት ነው ?? አብሽር ወንድሜ ሸይኾችህ አእምሮህ ላይ የደራረቡብህን ድሪቶ አውልቀህ ጣልና ሀቅን ፈልግ
https://t.me/sufiyahlesuna