|«ልጄ ሆይ…» አሉ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት። ወደ ሕይወት ትግል ገና እየተቀላቀለ የሚገኝ ጎረምሳ ወጣትን እየተመለከቱ።
•ልጄ ሆይ… መጠበቅህን አደብ አሲዘው። የመጠበቅ ልጓምህን ተቆጣጠረው።
የኔ ልጅ ሰዎች መጥፎ ነገር በማድረግ ብቻ አይጎዱህም። ልብህን በአጉል ተስፋ አንጠልጥለው ከጌታህ ጋር ሊያጣሉህ ይችላሉና ተጠንቀቅ።
• ልጄ ሆይ… ሕይወት እንደ እናትህ ልብ አይደለችም። አትራራልህም። እንደ አባትህም እቅፍ አይደለችም። እንዳይበርድህ ሙቀት አታቀብልህም። ሕይወት የወቅት ዘመድ ነች። የአሁን ሁኔታ ነች።»
• ልጄ ሆይ ወደ ልብህ የዘለቀን አክብር። የተለየህን አትጥላ።
• ልጄ ሆይ… ሰዎች በመጥፎ ምግባር ላይ ስላየሀቸው ብቻ አትፍረድባቸው። በምታውቀው እኩይ ምግባር ላይ ስለተገኙ አትጠየፋቸው። ይህን ልብ አድርግ አላህ ምርጥ ነብያቶቹን በእጅጉ ቆሽሸው ለነበሩ ሰዎች ልኮ የቆሸሹትን አፅድቶ እንዳስከበራቸው።
• ልጄ ሆይ! ወንድሞችህ ከፊርዓውን የባሱ አይሆኑምና ከፊርዓውን ያነሰ ክብር ሰጥተህ አታዋርዳቸው። የአላህ ነብይ ሙሳ ፊርዓውንን በለዘብታ ቃል እንዲያናግረው መታዘዙን ዘንግተህ በወንድሞችህ ላይ አጉል አትጩህ!