ኢትዮ ቴሌኮም ከሲንቄ ባንክ ጋር በአጋርነት 15 ቢሊየን የብር መጠን ያለው የቴሌብር የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎቶችን እና የዲቫይስ ፋይናንሲግ አገልግሎቶች ማስጀመሩን በይፋ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው!
በዛሬው ዕለት ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ ዜጎች የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በቴሌብር እንዲያገኙ እንዲሁም የቴሌኮምና ዲጂታል አገልግሎቶችን ለመጠቀም የሚያስችል የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎትን ለማቅረብ የአጋርነት ስምምነት አስጀምረዋል፡፡
በዚህ ትብብር መሰረት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች/ነጋዴዎችና ወኪሎች አነስተኛ ንግድ/ቢዝነስ እንዲጀምሩ ወይም እንዲያስፋፉ በዋስትና እና ያለዋስትና እስከ ብር 1.2 ሚሊየን የሚደርስ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል ስምምት የተደረገ ሲሆን፣ በዚህ አገልግሎት በዓመት እስከ ብር 10 ቢሊየን ለደንበኞች ለማቅረብ ታቅዷል፡፡
በተጨማሪም የደመወዝ ብድር አገልግሎቱ ወርሃዊ ደመወዛቸው በቴሌብር እና በሲንቄ ባንክ ለሚከፈላቸው የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች፣ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም በዓመት እስከ 1.3 ቢሊየን ብር የሚደርስ የብድር አቅርቦት ስምምነትን ያካተተ ነው፡፡
ሌላው በዛሬው ዕለት ሁለቱ ተቋማት በአጋርነት የስማርት ስልክ ስርጸትን እና የዲጂታል ሊትረሲን ለማሳደግ ያለመ የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ያስጀመሩ ሲሆን፣ ይህም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ስማርት ስልኮችን እና ሲም ካርዶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በረጅም ጊዜ ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በዚህም በአጋርነት በዓመት እስከ 2 ሚሊዮን ዲቫይሶችን ለማቅረብ ከሲንቄ ባንክ ጋር የ4 ቢሊዮን ብር የገንዘብ አቅርቦት ስምምነት ተደርጓል።
ለተጨማሪ፡
https://bit.ly/4cZKlLd