ትምህርት በቤቴ®


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Education


A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...

Buy ads: https://telega.io/c/AAAAAFAvYe4hmoy1ouXbBA
📩 For comment- @Tmhert_bebete_info_bot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Education
Statistics
Posts filter


Forward from: Daily inspiration™
✔️ Things to always remember: 🚨

1. The past can't be changed.

2. Opinions don't define your reality.

3. Everyone's journey is different.

4. Judgements are not about you.

5. Overthinking will lead to sadness.

6. Happiness is found within.

7. Your thoughts affect your mood

8. Smiles and contagious.

9. Kindness is free.

10. It's okay to let go and move on.

➡️ @daily_inspiree ✈️


🔥ExitExamAI.et 🔥

ሰኔ 14/2016 ለሚጀመረው የመውጫ ፈተና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መጠቀም ለተሻለ ውጤት! ካለው የፍላጎት መጠን የተነሳ ለ April 23, ተይዞ የነበረው ይፋዊ የማስጀመርያ ቀንና ፈተናው የሚጀመርበትን ግዜ ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ May 01, 2024 (ሚያዝያ 23፣ 2016) የተዛወረ መሆኑን እንገልጻለን። ቀድመው በመመዝገብ ቦታዎን ይያዙ!

ለፈተናው ትዘጋጁ ዘንድ ChatGPTን4.0 በመሳሰሉ AI ሞዴሎችን በመጠቀም የተዘጋጀዉ ExitExamAI.et ለቅድመ ምዝገባ ክፍት መሆኑን ስንገልጽ በደስታ ነው!

የተለያዩ ኢንተርናሽናል ሞዴሎች በ AI የተደገፉ የጥናት ማቴሪያሎች፣ አጠቃላይ የጥያቄ ባንኮችንና የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መሰናዶዎን ወደ ለከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ ይረዳል።

ከታች ያለው ድህረ ገጽ በመጠቀም “join” የሚለውን በመጫን ቀድመው ይመዝገቡ!

ድህረ ገጽ፡ https://exitexamai.et

🚀 ExitExamAI.et will be officially launched on May 01, 2024!🚀

We're thrilled to announce that ExitExamAI.et has officially launched and is open for waitlist registrations! Considering the official exam date, we moved the released date from April 23, 2024 to May 01, 2024.

The AI models offers AI-driven study materials, question banks, international exams, previous models and question along with engaging daily challenges.

Visit: https://exitexamai.et/

Tg: @ExitExamAI


ለ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና መሰጠት ጀመረ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች 12ኛ ክፍል በመማር ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የሞዴል ፈተና መሰጠት ጀመረ።


ምዴል ፈተናው ከሚሰጥባቸው ክፍለ ከተማዎች አንድ የሆነው የልደታ ክፍለ ከተማ ሲሆን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ አድማሱ በክፍለ ከተማው በሚገኙ የመንግስትና የግል ት/ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 3ቀናት ሞዴል ፈተና ለተማሪዎች እንደሚሰጥ የገለፁ ሲሆን የሞዴል ፈተናው ዋና አላማ የተማሪዎችን ውጤት በማሻሻል በቀጣይ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎች ዝግጅ እንዲሆኑ ለማድግ መሆኑን ተናግረዋል።


ሀላፊዋ አክለውም የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው ተማሪዎች ለአገር አቀፍ ፈተና ብቁ ሆነው እንዲቀርቡ የማጠናከሪያ ትምህርት፣ የጥያቄና መልስ ውድድር፣ወርክ ሽቶችን በማዘጋጀትና በመስጠት ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲፈትሹና ውጤታማ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ተሰርቷል በማለት መግለፃቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

❤️ @temhert_bebete


እስካሁን ጥሪ ያልተደረገላቸው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ተማሪዎች

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

ተማሪዎቹ ከታህሳስ ወር ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም።

ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የጀማሪ መርሐግብር እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች መጋቢት 14/2016 ዓ.ም ጥሪ ሲያደርግ፤ በ2016 ዓ.ም ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ ሳያደርግ ቀርቷል።

እነዚህ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ ይደረግልናል በሚል በተስፋ ሲጠብቁ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ከአንድ ወር በኋላም ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አላደረገላቸውም።

"የትምህርት ጊዚያቸው እየባከነባቸው እንደሆነ"ና "አስቸጋሪ ጊዜያትን እያሳለፉ እንደሚገኙ" ለቲክቫህ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች፤ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጠይቀዋል።

የሪሚዲያል ፈተናው ይሰጣል ተብሎ በመንግሥት የተቀመጠው ጊዜ 45 ቀናት የቀሩት መሆኑ ሌላው ተማሪዎቹን እያሳሰበ ያለ ጉዳይ ነው።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ መቼ ጥሪ እንደሚደረግ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችን በስልክ እና በአጭር መልዕክቶች የጠየቀ ቢሆንም ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

ተማሪዎቹ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተዘዋውረው የሚማሩበት ዕድል ካለ፣ አማራጭ የፈተና ጊዜ የሚዘጋጅላቸው ከሆነ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ወይም/እና ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጡትን ምላሽ ወደናንተ እናደርሳለን።

❤️ @temhert_bebete


የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ በየነ ተዘራ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

የሪሚዲያል ትምህርት ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም መጨረሻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ #ኢፕድ

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete


#Update

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ በማህተም ተደግፎ ስለተለጠፈው " የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል ስለዚህ የሜኑ ማሻሻያ አድርገናል " የሚለውን ማስታወቂያ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

ተቋሙ በመግለጫው ምን አለ ?

- " ከዚህ ቀደምም ቢሆን በየወቅቱና እንዳስፈላጊነቱ ' የምግብ ሜኑ ማሻሻያ ' ሲደረግ ነበር። "

- " አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲሁም የሚድያ ተቋማት ዩኒቨርሲቲው ያደረገውን የምግብ ማሻሻያ ሜኑ አስመልክቶ ተጨባጭነት የሌለውን መረጃ በማሰራጨት የተቋሙን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት እና የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው። "

🔴 የትኞቹ ማህበራዊ ትስስር ገጾችና ሚዲያዎች ተጨባጭነት የሌለው መረጃ እንዳሰራጩ በግልጽ ስም አልጠቀሰም።

- " ከወራት በፊት የተደረገ የሜኑ ማሻሻያ ለማሳወቅ ማስታወቂያ ወጥቷል። ይህም የቀን ስህተት የነበረበት መሆኑን እና ' አዲስ የተደረገ የምግብ ሜኑ ማሻሻያ ' እንደሌለ እንገልጻለን። "

- " ኃላፊነት በማይሰማቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲሁም የሚድያ ተቋማት ' ዩኒቨርሲቲው በምግብ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ሊበትን ነው '  እየተባለ የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ በተቋሙ ዘንድ በፍጹም ተቀባይነት የለውም። "

🔴 የትኛው የማህበራዊ ትስስር ገጽ እና ሚዲያ ተማሪዎች ሊበተኑ ነው ብሎ እንዳሰራጨ ስም አልጠቀሰም።

- " ለተማሪዎቻችን ከምንጊዜውም በላይ የተቋሙ አቅም በሚፈቅደው መጠን ጥራት ያለውን ምግብ በበቂ ሁኔታ በማቅረብ የመማር ማስተማር ሥራው እንዳይስተጓጎል አበክረን እንሰራለን። "

- " ለተማሪዎቹ ወቅቱ በሚፈቅደው አግባብ ጥራቱን የጠበቀ ምግብ ለማቅረብ የሜኑ ማሻሻያ ከማድረግ ያለፈ በተማሪ ምገባ ላይ አንዳች ጉዳት  አይፈጽምም። "

- " አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና መገናኛ ብዙሃን ተቋሙን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ በዩኒቨርሲቲው ላይ የከፈቱትና እየከፈቱ የሚገኙት የገጽታ ማጠልሸት ድርጊት በፍጹም ተቀባይነት የሌለውም፤ በህግ አግባብ ያስጠይቃል። "

🔴 እዚህም ጋር የትኞቹ እንደሆኑ በግልጽ ስም አልተጠቀሰም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከሰሞኑን በወላይታ ሶዶ እና በዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተለጠፉትን ማህተም ያረፈባቸውን ተመሳሳይ ይዘት ስላላቸው ማስታወቂያዎች በተመለከተ መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

ተቋማቱ ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ፥ " እንደ ሀገር የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል። የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋም በየቀኑ ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት ተቆጥሯል " ይላል።

ይቀጥልና ፥ " ተቋሟችን የሚያደርገው ድጎማ ተማሪዎቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ ባሉን የምግብ ጥሬ እቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ነው " ሲል ይገልጻል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስታወቂያ ደግሞ " ባሉን የምግብ ጥሬ ዕቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ቢሆንም በአሁን ሰዓት እጅግ በጣም #እየከበደ ስለሆነ የሜኑ ማሻሻያ ለማድረግ ተገደናል " ይላል።

ይህ በተመለከተ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ሀብታሙ ተመስገን ፥ ማስታወቂያውን ሆነ ሀሳቡን #እንደማያዉቁት በመግለጽ " ማን ይህን ሀሳብ እንዳመጣ እንዲሁም ማስታወቂያ እስከ መለጠፍ ድረስ እንደደረሰ እናጣራለን " የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር አክብር ጩፋ ደግሞ ፤ " ሶሻል ሚዲያ ላይ  መረጃው ሲንሸራሸር እያየን ነው " ካሉ በኃላ ሁኔታዉን ለማጣራት #ማኔጅመንቱ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete




🚀 ExitExamAI.et

ለቅድመ ምዝገባ ክፍት መሆኑን ስንገልጽ በደስታ ነው! 🚀

የተለያዩ AI ኢንተርናሽናል ሞዴሎች በ AI የተደገፉ የጥናት ማቴሪያሎች፣ አጠቃላይ የጥያቄ ባንኮችን እና የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መሰናዶዎን ወደ ለከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ ይረዳል።

ከታች ያለው ድህረ ገጽ በመጠቀም “join” የሚለውን በመጫን ቀድመው ይመዝገቡ!

ድህረ ገጽ፡ https://exitexamai.et/

🚀 ExitExamAI.et is Now Live for waitlist registration ! 🚀

We're thrilled to announce that ExitExamAI.et has officially launched and is open for waitlist registrations!

Integrated AI models offers AI-driven study materials, comprehensive question banks, and engaging daily challenges designed to elevate your exam prep to new heights.

Visit: https://exitexamai.et/

Telegram: @ExitExamAI


ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት

ጉዳዩ፡- የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአገልግሎት ክፍያን ስለማሳወቅ፤

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ለሚስጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዝርዝር እንድታሳውቁን መጋቢት 23/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ መጠየቃችን ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የመውጫ ፈተናውን #ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች ለሚያገኙት የአገልግሎት ክፍያ በአንድ ተማሪ 👉500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 እስከ ሚያዚያ 15/ 2016 ዓ. ም ድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንድታደርጉ እያሳወቅን የተከፈለበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ (antedefar@gmail.com & lakbt2013@gmail.com) እንድትልኩልን እናሳስባለን።

ከት/ት ሚኒስቴር

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete


የተሻለ ውጤት የሚያመጡ  ተማሪዎች የአጠናን ልምዳቸው ምን ይመስላል❓

📢 12 ወሳኝ ነጥቦች

📖1 ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው ዓላማ ያስቀምጣሉ።
ይህ ማለት ምን ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው ያቅዳሉ።

📖 2 መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ስለሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ የራሳቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። መፅሀፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኃላ የነበራቸውን ግምት እያጠናከሩ...የተሳሳተው
ን እያስተካከሉ ይጓዛሉ።

📖3 ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ አጠር አድርገው ማስታወሻቸው ላይ ያሰፍራሉ።

📖4 አንብበው ለ መረዳት ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/ ደጋግመው ያነባሉ....

📖 5 ጥናት ከ መጀመራቸው በፊት ማጥናት ስለ ፈለጉት ርእሰ ጉዳይ ጥያቄዎች ይፋጥራሉ። መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በሃላ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ እንጂ ሁሉም ነገር በ ማንበብ ጊዜያቼውን አያጠፉም።

📖6 ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ከ አሁን በፊት ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን ይመረምራሉ::

📖7 በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት አይሞክሩም፡፡ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት መሞከር ትርፉ ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡

📖8 ሁልጊዜም ቢሆን ለትምህርት ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የተለየ ጊዜ አላቸው፡፡

📖9 ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት አላቸው...አያፈገፍጉም፣ አያቅማሙም፡፡

📖10 ሲያጠኑ የሚከብዳቸውን ክፍል ቅድሚያ ሰጥተው ያነባሉ፡፡

📖11 ተባብሮ በመስራት ያምናሉ፡፡ ያግዛሉ፣ ይጠይቃሉ፡፡

📖12 እራሳቸው ይገመግማሉ፡፡ ደካማ ጎናቸዉ በፍጥነት ያስተካክላሉ፡፡


❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete


#Update

የመውጫ ፈተና ከ ሰኔ 14-25

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ በማሰባሰብ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በኩል አረጋግጠው ባሳለፍነው ሳምንት ለትምህርት ሚኒስቴር መላካቸውን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete


Identify the sentence with the correct subject-verb agreement:
Poll
  •   A) The dog barks loudly.
  •   B) The dog bark loudly.
  •   C) The dogs barks loudly.
  •   D) The dogs bark loudly.
365 votes


Choose the correct form of the verb to complete the sentence: "She _____ to the party last night."
Poll
  •   A) go
  •   B) goes
  •   C) went
  •   D) going
383 votes


Which sentence is grammatically correct?
Poll
  •   A) She goed to the store yesterday.
  •   B) He have been studying for hours.
  •   C) They has already left.
  •   D) We went to the park yesterday.
321 votes


የመውጫ ፈተና አገልግሎት ክፍያ

ከኢ...ዲ.ሪ.ት/ሚ/ር በቁጥር 8/342/562/16 በቀን 09/08/2016 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ መሰረት ከሰኔ 14-212016 ዓ.ም ድረስ ለሚስጠው የመውጫ ፈተና አገልግሎት ክፍያን አስመልከቶ ተፈታኝ ተማሪዎች #እያንዳንዳቸው 500.00 /አመስት መቶ ብር/ እስከ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲከፍሉ አሳውቋል።

በዚሁ መሰረት በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ የዘንድሮ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ክፍያውን ይከፍሉ ዘንድ ዩንቨርሲቲዎች እያሳሰቡ ይገኛል።

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2016 ዓ.ም የቴ/ሙያ ኮሌጆችና የስልጠና ተቋማት በስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ከስታንዳርድ በታች ያመጡ ተቋማት ግኝት ላይ ውይይት እና የቀጣይ ውሳኔ ሀሳብ ቀረበ፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ በመክፈቻ ንግግራቸው ስታንዳርዱን መጠበቅ ግዴታ እንጂ ምርጫ እንዳልሆነ ጠቅሰው ባለስልጣኑ የሚያደርጋቸውን ድጋፍና ክትትል እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ብቁ እና ተወዳዳሪ ተቋምና ሰልጣኝ በመፍጠር የተቀመጠውን ስታንዳርድ መጠበቅ  ግዴታ መሆኑን ገልጸው  ይህ ካልሆነ ግን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል ብለዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ የባስልጣኑ ዋና አላማ የትምህርት ጥራትና ተገቢነት ማረጋገጥ ነው ይህ ተፈፃሚ የሚሆነው ደግሞ ሀገሪቱ ባስቀመጠችው ስታንዳርድ መሰረት ተቋማት ብቃት ሲኖራቸው እና ሰልጣኞቹ በብቃት ፈተና ብቁ  ሲሆኑ ነው  በሀገራችን ተቋማት እንዲስፋፉ እንፈልጋለን፤ይህ የሚሆነው ግን የተቋማት ባለቤቶች ቁርጠኛ ሆናችሁ ከባለድርሻ  አካላት ጋር አብሮ በመስራት  ብቁ ተቋም ስንፈጥር ነው ብለዋል፡፡


የባለስልጣኑ  የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዋር ሙላት የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆኑ በ2016 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የቴ/ሙያ  ትምህርት ስልጠና ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት  የተቋማት መረጃ፣የኢንስፔክሽን ግኝት፣የታዩ ጥንካሬዎች፣ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣የተሰጡ መፍትሄዎች፣ምክረ ሀሳብ ማጠቃለያ እና የውሳኔ ሀሳቦችን አቅርበዋል።


❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete


🚀 We found Hiddin Gem $BLEGGS Airdrop! 🚀

 ➽ Binance Smart Chain Meme

Excited about free tokens? Become a BLEGGSian today! Join BLEGGS Telegram here for your chance to participate in our exclusive airdrop. Don’t miss out—more $BLEGGS, more fun!

#BLEGGSian 🐣

MarketCap :  $250,000$+
Burn Plan: YES
Locked Liqudity : YES 
Airdrop:  YES
Official Contacrt : 0x3B7B142c198E0575110BC81BBAdDEB6AB0a6046c

Official Telegram: https://t.me/bleggs

🚀 Jump into $BLEGGS! Click to join our Telegram here and enter our airdrop event. Quick, easy, rewarding! #BLEGGSian 🌟


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል?

12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete


በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ምንም አይነት ቃላት ማንበብ እንደማይችሉ አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ አደረጉት ባለዉ ዓመታዊ ጥናቱ ላይ እንደገለፀው በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሚሆኑ የ 2ኛ እና የ 3ኛ ክፍል ተማሪዎች ምንም አይነት ቃላት ማንበብ እንደማይችሉ አረጋግጫለሁ ብሏል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሲያከናዉን የቆየዉን ጥናት ይፋ አድርጓል ። በዚህም ከትግራይ ክልል በስተቀር በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ 401 ትምህርት ቤቶች እና በ 16 ሺህ ተማሪዎች ላይ በተደረገ ጥናት ዉጤቱ መገኘቱን አስታዉቀዋል።

ይህ ቁጥር ከባለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር በመጠኑ መሻሻል አሳይታል የተባለ ሲሆን ከሁለት አመት በፊት የተደረገው ጥናት ምንም ማንበብ የማይችሉት 63 በመቶዎች እንደነበሩ ጥናቱ አመላክቷል።

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete

19 last posts shown.