🫴የሩድ ወሳኝ መልዕክት ለአሞሪም !
መጀመሪያ ዩናይትድ ፓሽን !
ሬድ ዴቭልስ ካራክተር !
ዩናይትድ ጠፍንገው ከያዙት ካቦው ስንብት ማግስት በላቀ የጨዋታ የድል ፍላጎት የደረጀ በህብረት የአሸናፊነት መንፈስ የሚችለውን ለማድረግ የሚዋደቅ ቡድን ሆኖ ዳግም ታየ ። ይህ የሩድ ሮያሊቲ ! የማንቸስተር ዩናይትድ ሜንታሊቲ ! የቫን ዘማን ፓሽን ! የሬድ ዴቭልስ መለያ ካራክተር ምልክት ነው ።
በዘመናዊው እግር ኳስ ከታክቲክ ቴክኒክ ትግበራ ከቡድን የጨዋታ ቅርፅና Game ስትራቴጂ ፊት አሸናፊ ቡድኖች አሸናፊ የዋንጫ አሰልጣኞች ከላቀ የMan Magement ስኪላቸው ጋር ሌት ተቀን አጥብቀው ማስረፅ የሚፈሹት የክለብ የትናንት አሸናፊነት የውጤት ታሪክ ላይ መሠረቱን የጣለ ለጋራ ስኬት ዓለማ በጋራ አንድነት የቡድን ህብረት መንፈስ እንደ ቤተሰብ በህብረት የቆመ ታጋይ አሸናፊ ስብስብን መፍጠር ነው ። ይህ ማንቸስተር ዩናይትድ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ሲበዛ አጥቶት የከረመው ኋያሉ ሰው ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በክብር በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ ዩናይትድ የናፈቀው ዋና የውጤት ቁልቁለቱ ምንጩም ነበር ።
ማንቸስተር ዩናይትድ ከጠንካራው የማሬስካ ቼልሲ ፊት እስከመጨረሻዋ ደቂቃ በህብረት ለድል ታገለ ። በኋያል የጋለ የፉክክር መንፈስ የደመቀው ፍጥጫም ከኦልድትራፎርድ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ ። ይህ የማንቸስተር ዩናይትድ ትክክለኛው መልክ ነው ። በዘመን ቀለም የደመቀው የገናናው ክለብ መለያ ባጅን ያጠለቁ ሁሉ ለመጨረሻው ድራማ በህብረት በጀግንነት ሊዋደቁለት የሚገባው የማንቸስተር ዩናይትድ ዕውነተኛው የአሸናፊነት ባህል ቀለም ነው ። በሩድ ሮያሊቲ በቫንዘማን ሜንታሊቲ ከሰፊ ክፍተቱ ጋር በብርሃን ፍጥነት ከዩናይትድ ካምፕ የተቀየረው ስብስብ ቀለም ነው ።
ሩድ ቫንስትሮይ በቀጣይ ከዩናይትድ ጋር በኋላፊነት ቀጠለም አልቀጠለም ለአዲሱ ዋና አሰልጣኝ ሩቢን አሞሪም የሚጠበቀው ቻሌንጅ በአደባባይ የተላለፈው ማንቸስተር ዩናይትድ መሆን መምሰል ያለበት የቀያይ ሰይጣናቱ ግልፅ መልዕክት ነው ።
https://vm.tiktok.com/ZMhxpfR9T#Manchesterunited