አዶናይ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


“በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ካልሆነ በቀር ብቻውን ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፤ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም።”
— ዮሐንስ 15፥4
ስለ አዶናይ መንፈሳዊ ቻናል ያላቹን ማንኛውንም ሀሳብና አስታየት በዚህ Bot በኩል ብታደርሱን እንቀበላለን @AdonaiComments_bot
ኢየሱስ ይመጣል 🔥

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


አላድግ ያለ ህፃን

ዳዴ ላይ የቆመ ዛሬም ዳይበር የሚደረግለት የ 21 አመት ህፃን ይኖር ይሆን 🤗 ? አይጠፋም እኮ ፈልጉ እስኪ ሰፈራቹ ውስጥ ወይ ደግሞ እናንተ መካከል 🥰 እንደው በባትሪ ፈልጋቹ ብታገኙ ግን ያ ያልኳቹ የ21 አመት ሰው በዛ እድሜው እንደ 2 አመት ህፃን መሆኑ ጤነኝነት ስላልሆነ ሰዎች ታማሚ ነው ይሏቿል ፤ በመንፈስስ አለም አሁንም ከጌታው ጋር ህብረት የማድረጊያ ጊዜ የሌለው ፣ ቸርች ለመሄድ የሰው እርዳታ የሚጠይቅ፣ እስካሁን ቆሮንጦስን አንብቦ የማያውቅ በጌታ ግን 20 አመት የሞላው ልጅስ ታውቁ ይሆን ? ይሄስ በእርግጠኝነት እናንተ ቤት ይኖራል 😁 በጌታ ቤት 20 አመት ቆይቶ ኮሽ ባለ ቁጥር የሚደነግጥ ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ዳገት የሆነበት አማኝ እንደኔ ጤናማ ክርስቲያን ነው ለማለት ይከብደኛል...የኢየሱስ እድገት በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት እንደነበር ልክ እንዲሁ የኛም እድገት በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ነው መሆን ያለበት ።

በእግዚአብሔርም ፊት እደጉ🥰


@thedayofPentecost
@thedayofPentecost


እንዲሁ ኢየሱስ ኢየሱስ እያላቹ ዘመናቹ ይለቅ 🔥


🎙️የግድ ታስፈልገኛለህ

ይሄ መዝሙር ፀሎትም ጭምር ነው

መንፈስ ቅዱስ የግድ ታስፈልገኛለህ 🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

1k 0 23 1 28

ስትደክሙበትም ይፈልጋቿል 😔

እውነት ነው ይሄ ጌታ ሁሌ ብርቱ ብንሆንለት እና እርሱን መስለን ብንኖርለት እንደ አባት ደስ ይለዋል ነገር ግን እንደ ልጅ ስንደክምበትስ ፣ መኖር ሲያቅተንስ 😔 የሚተወን ይመስላቿል ? ቆይ አንዴ የሆን መዝሙር ላስታውሳቿ ...

ሁሉ እንዲድን አንዷ እንዳጠፋ
ሚገደው ያ መልካም እረኛ 🥰
በረት ያሉትን ይተውና ይሄዳል እርሷኑ ፍለጋ🐑
ያሰማታል ድምፁን አውጥቶ
በእቅፉ ሊያስገባት ጓግቶ 😍
ነፍሱን ስለ በጓቹ ያኖረ እውነተኛ ፍቅር እርሱ ነው
💯


ይሄ አባት ከእርሱ ጋር መዋል ስታበዙ ብቻ ሳይሆን አቅም አጥታቹ ስደክሙበትም ይፈልጋቿል

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost


🎙️Nefse _Hoy 🥰

ይሄን መዝሙር ለነፍሳቹ ንገሯት

ቃላቹን ጠብቁ !

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost


“እግዚአብሔር ዓለቴአምባዬመድኃኒቴአምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴመታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።”
— መዝሙር 18፥2

2k 0 11 1 82

ይሄን በምስሉ ላይ የምታዩት ቢራቢሮ የመሆን ሂደት Metamorphosis ይባላል እንደምታዩት ቢራቢሮው መጀመሪያ አካባቢ ላይ በደንብ መሄድ አይችልም ፣ መልክም ብትሉ የሚስብ መልክ የለውም ብቻ ንፁ ትል ነው ነገር ግን ይሄ ትል የሆነ ጊዜ ላይ ከከበቡት ነገሮች ተለይቶ ብቻውን ራሱን ለመቀየር ይሞክራል ከዛም ትናንት ላይ ሰውነቱ ላይ ተጣብቀው አላስኬድ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አወላልቆ ተአምር በሚመስል መልኩ ክንፍ ኖሮት ስሙን ቀይሮ ዲራቢሮ ይሆናልይሄን እንደምሳሌ ያየነውን Metamorphosis የሚባለው የለውጥ ሂደት በእኛው ህይወት ስርዓት ውስጥ እንደ ትልቅ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን ፤ በዚህ ሰዓት ይሄን መልዕክቴን የሚያነቡ በህይወታቸው ተስፍ የቆረጡ ፣ በኃጢአት ልምምድ ውስጥ የሚገኙ ፣ በህይወታቸውም በፍፁም ሊቀይሩት በማይችሉት መጥፎ ሁኔታ ውስጥ የገቡ የሚመስላቸው ብዙ ልጆች ይኖራሉ ፣ የአባቴ ልጆች ዛሬ እኔ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ የእውነት ለፍጥረት ይሄን የሚያስደንቅ የለውጥ ስርዓት የሰጠ እግዚአብሔር የእናንተን የልጆቹን ድካም የሞላበትን ህይወት መለወጥ የሚከብደው ይመስላቿል ? በፍፁም አይከብደውም። ብቻ እናንተ እግሩ ስር ቆዩለት እንጂ እርሱ የእናንተን ደካማ ማንነት ከላያቹ አውልቆ የእርሱን ጥንካሬ ለመስጠት ዛሬም ዝግጁ ነው።

እግሮቹ ስር ቆዩና ራሳቹን ቀይሩ !


@thedayofPentecost
@thedayofPentecost




ኃጢአት አይደለም 👩‍❤️‍👨

እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሴትና ወንድን ሲፈጥር በውስጣቸው በፍቅር የታጀበ መፈላለግ እንዲኖር አድርጎ ነው የፈጠራቸው፤ ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ እንዲፈልግ፣ እንዲያፈቅርና አብሯት እንዲኖር የእግዚአብሄር ሀሳብ ነው ሴትም ለወንድ ልጅ እንዲሁ ነገር ግን ብዙዎች ይሄን በወንድና በሴት መካከል ያለውን የፍቅር ስሜት እግዚአብሔር ያስቀመጠው ስጦታ ነው ብለው ከማመን ይልቅ የእግዚአብሔር ፍቃድ የሌለበት የሰው ልጆች ስጋዊ ስሜት ብቻ አድርገው ይቆጥሩታል እነኚ ሰዎች ብዙ ጊዜ ይህንን እንድያስቡ የሚያደርጋቸው ትናንት ላይ በሰዎች ህይወት ወይንም በራሳቸው የፍቅር ህይወ ውስጥ በሚፈፅሟቸው ስተቶች ምክንያት ነው ለምሳሌ በዝሙት መውደቅ ሊሆን ይችላል እንደዚህ አይነት ስተቶች ደግሞ እግዚአብሔር በወንድና በሴት መካከል ያስቀመጠውን የፍቅር ግንኙነት ትክክል ባልሆነ መልኩ እንዲረዱትና ሴትን ልጅ በፍቅር አለመቅረብ እንደ ትልቅ ፅድቅ እንዲያዩት ብሎም ሴት ልጅ ሲሸሹ ከዝሙት እንደሸሹ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል ፤ በርግጥ ሁላቹም እንደምታውቁት ከትዳር በፊት በዝሙት መውደቅ ትልቅ ኃጢአት ነው ነገር ግን በዝሙት ወይም እናንተ በፍቅር ህይወታች ውስጥ በምትሰሯቸው ስተቶች ምክንያት የእግዚአብሔር ፍቃድ የሆነውን የፍቅር ግንኙነት እንደ ኃጢአት አድርጎ ማሰብም ሆነ ሴትን ልጅ በፍቅር አለመቅረብ እንደ ፅድቅ መቁጠሩ በፍፁም ትክክል አይደለም።

የፍቅር ህይወታቹ + በቅድስና የታጀበው ቃል ኪዳናቹ = ትዳር የሚባለውን ትልቅ ተቋም ይፈጥራል

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t


የርሀቧ ጥግ ኢየሱስን ጠራው

ገና በለሊት ቤት መቀመጥ አላስችል ብሏት የህይወቷን መምህር ፍለጋ ምንም በሌለበት መቃብር ስፍራ ላይ ብቻዋን እያለቀሰች 😭 አይኖቿ አስሬ የተከፈተውን መቃብር ታያለች የምትፈልገው መምህሯ ግን በቦታው የለም ፤ የኢየሱስን ከመቃብር መጥፋት ለማየት ከማርያም ጋር የመጡት ሌሎች ደቀ-መዛሙርት መቃብሩ መከፈቱንና የኢየሱስ ስጋ ከቦታው አለመኖሩን ከማየት ባለፈ እንደዚች ሴት የጌታ አለመኖር ጥያቄ አልሆነባቸውም መግደላዊት ማርያም ግን እርሱ እኮ ሞቷን ብለው የነገሯትን ረቢኒዋን ፍለጋ አይኖቿ እረፍት አጥተዋል በዚህ ሁሉ የጭንቅ ፍለጋ ውስጥ ግን አንድ ለማመን የሚከብዳትና የምታውቀውን ውብ ድምፅ ከበስተ ኃላዋ ሰማች " ማርያም " የሚል ድምጽ ፤ ይሄ ድምፅ ጥያቄዎቿን ሁሉ የሚመልስላት የምቶደው የመምህሯ ድምጽ ነበር... ማርያም በጣም በሚያስፈራ በመቃብር ስፍራ አጥብቃ የፈለገችው የህይወቷ መምህር በመጨረሻ ራሱን በትንሳኤ አካል ገለጠላት።

የርሀቧ ጥግ ኢየሱስን ጠራው 🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPenteco
st


የህይወቴ ርዕስ ፣ የአገልግሎቴ ሁሉ ድምቀት የወጣትነቴ ውበት መንፈስ ቅዱስ ... በዘመኔ ካላንተ ህልውና ካላንተ መገኘት የምኖርባቸው ቀኖች አይደሉም ሰዓታት አይኑሩኝ

ሁሌ ሁሌ ሁሌ... ሁሌ አንተን ብቻ
እስከ እድሜዬ መባቻ
🔥


እርሱ አልጨረሰም

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ አንድ የሚገርመኝ ታሪክ አለ ሉቃስ 8፡26 ላይ፤ እዚህ ሰው ላይ ተስፍ ያልቆረጠ አልነበረም፤ ቤተሰቡየጌርጌሴኖን ሀገር ሰዎች፣ በጤንነት ሳለ የሚያውቁት ጓደኞቹ ሁሉ እርሱ ላይ ያላቸውን ተስፍ ጨርሰዋል ፤ በዚህም የተነሳ ከሰው ተለይቶ በመቃብር ስፍራ ይህ ሰው ይኖር እንደነበር መጽሐፍ ይናገራል፤ እና በጣም የሚገርመው ሰውዬው ፈላጊ እንደሌለውና በማንም እንደማይፈለግ ህዝቡ ሁሉ ተረድተው ማንም በሌለበት የመቃብር ስፍራ ዋጋ እንደሌለው ሰው ጣሉት፤ነገር ግን ለዚህ ተስፍ ቢስ ሰው አንድ ወዳጅ ሊሆነው የፈለገ ሰው ነበር፤ ወዳጆቼ ይህ ሰው ለሰፈሩ ሰዎች ከአሳማ እንኳን ያነሰ ዋጋ ያለው ተደርጎ ነበር የሚቆጠረው ምክንያቱም ተስፍ የሌለው ስለመሰላቸው፤ ኢየሱስ ግን ይህ ሰው ላይ የለውን አላማ አይጨርሰም፤ ፈፅሞም ተስፍ አልቆረጠበትም፤ እንደ ቤተሰቡም መቃብር ስፍራ እንዲኖር አልፈቀደለትም፤ ለዚህም ነው እርሱን ለመርዳት ሲል የውሀውን መአበሉ ፀጥ አድርጎ ወደ ነበረበት ስፍራ የመጣው።
ውድ የአባቴ ልጆች እናንተ አበቃለት ብላቹ በጨረሳቹለት ጉዳይ ላይ ኢየሱስ ሲመጣ ከአዲስ ይጀምረዋል፤ ፈላጊ የሌላቹ የመሰላቹ እናንተ ናቹ እርሱ ግን እናንተን ለመርዳት በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ይበራል በደመናትም ላይ ይራመዳል፤

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የእግዚአብሔር ጥበቃ ልክ እንዲህ ነው 🔥

“እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።”
— መዝሙር 91፥3


@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


ማባከን አይደለም 😭

በየቀኑ አለም የምትሰጠንን የቤት ስራ አለመስራት ሰነፍ አያስብለንም ፣ እግሩ ስር መዋልም ሞኝነት አይደለም ማርያም በይሁዳ አይን ስትታይ ምናልባት አባካኝ ፣ የገንዘብ ጥቅም ያልገባት ሴት ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን ይሄ የኢየሱስ እግሮች ውበት ላልገባው ሰው እንጂ እንደ ማርያም በኢየሱስ ፍቅር ለተነካ ሰው ሶስት መቶ ዲናር ለእግሮቿ እንኳን የማይበቃ ስጦታ ነው ፤ እኛም ለዚህ ጌታ ወጣትነታችንን ስንሰጠውና ስንበረከክለት ላኑን ሰዎች ዘመኑ ያልገባን ዘመናዊነትን የማናውቅ ሞኞች ልንመስላቸው እንችላለን ነገር ግን እኛ ሰዎች እንደሚሉን ዘመኑ ሳንረዳው ቀርተን ወይ ደግሞ የሚመክረን አጥተን ሳይሆን እንደ ማርያም ሁሉን የሚያስንቅ ፍቅር ስለተካፈልን ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


አልዋሽህም አባ

አልዋሽህም ደና ነኝ ብዬ 😔
አልዋሽህም ብርቱ ነኝ ብዬ
እንደገና ስራኝ እንደገና
እንደገና ዳሰኝ እንደገና 😥

እግርህ ስር ልሰንብት እንደገና 😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


Fake Channel ❌

ይሄ በአዶናይ ስም የተከፈተ ከ 1.4k በላይ ተከታዮች ያሉት Channel ነው በእርግጥ ቻናሉ እስካሁን የማን እንደሆነ ባላውቅም እኔ ግን የከፈትኩት ቻናል እንዳልሆነ እንድታውቁ ፈልጋለሁ፤ በዚህ ቻናል ላይ የሚለቀቁትን መልዕክቶች ለሰዎች ማጋራትና በየቻናሎቻቹ መልቀቅ ምንም ጥፋት የለውም ነገር ግን እንዲህ ስምና ሎጎውን ጨምሮ የዚኑ ቻናል ትምህርቶች ሳያስፈቅዱ መጠቀም ሰዎችን ግራ ለማጋባት ካልሆነ በቀር ሌላ አላማ የለውም።


ያየኽውን እንደሚያይ ለዛም ራሱን እንደሚለይ ግብ የሆነ ያንተ ክብር ከነብሱም ጋር የማይማከር ስራኝ እንደዚህ እንደ ክቡር እቃ ላየኽው ለመጨረሻው ዝናብ እንድበቃ ስራኝ እንደዚህ እንደ ክብሩ እቃ ላየኽው ለክብር ቀን እንድበቃ 😭

አዘጋጀኝ ለክብርህ 🔥


ጥያቄዎቹ ራሳቸው ይናገራሉ

አንዳንዴ ለችግራቹ መፍትሄ እንደሚሆኗቹ የምታስቧቸው ቤተሰቦቻቹና ጓደኞቻቹ የእናንተ ችግር ሰሚ እንጂ ባለመፍትሄ መሆን ይከብዳቸዋል፤ በገንዘባችን እና በሰዎች ጥበብ የማንፈታው እግዚአብሔር ብቻ መልስ የሆነበት የሆነ ጥያቄ በእያንዳንዳችን ቤት ውስጥ ይኖራል ፤ ይሄ ጥያቄ በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ እንዳለ ይናገራል ፤ ለምሳሌ የሀና የልጅ ጥያቄ በባሏ መልስ ቢያገኝ ኖሮ እግዚአብሔር ሀናን ጎበኘ ተብሎ አይወራም ነበር ፤ አስተውላቹ ከሆነ በአንዳንድ ከባባድ ጥያቄዎች ምክንያት ለጥያቄዎች በቂ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ክብር ያገኛሉ እግዚአብሔር ለዚህ ነው በእርሱ ብቻ የሚመለስ ጥያቄ በእያንዳንዳችን ህይወት ውስጥ ያስቀመጠው፤ ሀና ቤት ለረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው ሳሙኤል የሆነ ቀን እግዚአብሔር በዛ ቤት እንዳለ እንደተናገረ ሁሉ እናንተም ቤት መፍትሄ ያጣቹባቸው ጥያቄዎቻቹ አንድ ቀን እግዚአብሔር እንዳለ በግልፅ ይናገራሉ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


ወገኖች ተዉ እናምልክበት 😁

እውነት ለመናገር እኔ በአምልኮ ሰዓት ሼም የሚይዘው፣ አዩኝ አላዩኝ የሚያበዛ ሰው ጎን ባትቀመጡ ባይ ነኝ 😊 አይታቹ ከሆነ አንዳንድ ወገኖቻችን ከተንቀሳቀሱ እንኳን የሚንቀሳቀሱት "ሚልኮን ትናቀኝ እንደለመደባት ተፈቶ ማምለክ መቼም አይሆንላት " የሚለው መዝሙር ሲዘመር ነው እንጂ ንቅንቅ አይሉም እሱንም ቢሆን የመዝሙሩ ቃል እንዳይፈፀምባቸው ፈርተው ነው 😁 ብቻ ከልባቹ ተፈታቹ አምልኩ፤ ደግሞ እንኳን ለዚህ ለከበረው ጌታ ይቅርና ክብር ለሌለው ጠንቋን እንኳን ሽር ጉድ ይባልለታል።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t

3.2k 0 15 15 71

ይሳቅን ፍለጋ...

እግዚአብሔር ለአብርሀም ልጅ እሰጥሀለው ብሎት ኪዳን ገባለት ነገር ግን የተነገረው የትንቢት ቃል ሳይፈፀም አመታቶች ይቆጠራሉ በዚህም ምክንያት አብርሃም ትኩረቱ ልጅ ላይ ብቻ ስለነበር በዚያም በዚም ብሎ ይወርስሀል ተብሎ የተነገረውን ልጅ ፍለጋ ሚስቱን ሳራን ትቶ ሞግዚቷ አጋር ጋር ገባ ነገር ግን ይሳቅን አገኛለው ብሎ አጋር ጋር የሄደው አብርሃም ከአጋር ማግኘት የቻለው የተጠበቀውን ይሳቅን ሳይሆን ያልታሰበውን እስማኤልን ነበር ....ለካስ የተስፍው ቃል ባለቤት ይስሀቅ ያለው ያረጀቺው ሳራ ጋር እንጂ ወጣቷ አጋር ጋር አልነበረም ፤ አብርሃም ተሸወደ 😊 የተወደዳቹ እግዚአብሔር የእናንተን ይሳቅ ጠብቃቹት እንጂ አቋራጭ መንገድ ተጠቅማቹ እንድታገኙት በፍፁም አይፈልግም፤ ጌታ የነገራቹን ቃል የሚፈፅምበት የራሱ ጊዜ አለው እናንተ ብቻ የተባላቹትን በተባላቹት ስፍራ ላይ ሆናቹ ጠብቁ

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t

20 last posts shown.