“በማቲው ቲሰን ምልከታ፣ ለጳውሎስ የአሕዛብ ግርዘት አላስፈላጊ ጉንደላ ነው (ፊል 3፥2)። ለአይሁዳውያን ግን ይጠቅማል (ሮሜ 3፥2)። ከአሕዛብ ወገን የኢየሱስን ተከታዮች የተቀላቀሉ ምእመናን እንደ አይሁድ እንዲኖሩ (ግርዘት እና መሰል አይሁዳዊ ግብራትን እንዲፈጽሙ) ሊገደዱ አይገባም። ደግሞም አይሁዳዊ ምእመናንም እንደ አሕዛብ ያለ ሕገ ኦሪት ሊኖሩ አይገባም (1 ቆሮ 7፥17-20)። አሕዛብ በግርዘት (ወይም በቲሰን ቃላት፦ አብርሃምን ለመምሰል በሚያደርጉት “ኰስሜቲካዊ ጥረት”) የአብርሃም ልጆች እና ወራሾች ሊኾኑ አይችሉም። ቆዳቸው ላይ የሚያደርጉት ግርዘት ዘረመላቸውን ቀይሮ የአብርሃም ልጆች ሊያደርጋቸው አይችልም። ይኽ ተኣምር የሚፈጸመው በ“Pneumatic Gene Therapy” ነው። እግዚአብሔር የመሲሑን Pneuma (መንፈስ?)* ወደ አሕዛብ ምእመናን በማስረጽ የአብርሃም ልጆች አድርጓቸዋል። ጳውሎስ፣ በቲሰን ምልከታ፣ አሕዛብ በግርዘት የአብርሃምን ቤተሰብ ሊቀላቀሉ መፈለጋቸውን በመሲሑ Pneuma የአብርሃም ቤተሰብ መኾናቸውን እንደ መካድ ይቆጥረዋል። የመሲሑ Pneuma አሕዛብን እንደ መሲሑ የአብርሃም ልጆች እንዲኾኑ የሚያደርግ ብቻ ሳይኾን፣ እንደ መሲሑ እንዲኖሩ የሚያደርግ ነው።”
*ቲሰን Pneuma የሚለውን [ከሞላ ጎደል ኹል ጊዜ መንፈስ ተብሎ የሚተረጎመውን] ቃል የሚረዳበት እና የሚጠቀምበት ኢስጦኢካዊ መንገድ ለየት ያለ ነው።
ሔኖክ ኢሳይያስ፣ ጳውሎስ እና መሲሓዊው ምስጢር፡ ርዕዮተ-ዓለማዊ ማእቀፍ፣ ገጽ 72-73
መጽሐፉን [እና ሌሎች መጻሕፍትን] በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፦
ልደታ፣ መሠረተ ክርስቶስ ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 301
0994279744
0985671368
@thefaithofthefathers