"በዓሉ ያለአደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያድርጉ" - ኮሚሽኑ
የበዓል ስራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ ሁሉንም ስራዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከማከናወን መቆጠብና ስራዎችን በቅድመ ተከተል፣ እንደቤተሰብ አባል ብዛትና ችሎታ ስራን መከፋፈል ያስፈልጋል።
በአንድ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ላይ ሶኬቶችን ደራርቦ አለመጠቀም፣ ጋዝ ሲሊንደር ከመለኮስዎ በፊት በጋዝ ሲሊንደር መስመር ውስጥ ያፈተለከ ጋዝ አለመኖሩን ማረጋገጥ።
ከሰል በሚጠቀሙበት ጊዜ የከሰል ምድጃውን ከቤት ውጪ በማድረግ ከሰሉ ጢሱን እንዲጨርስ ማድረግና ወደ ቤት ካስገቡ በኋላም በርና መስኮት በመክፈት በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር ማድረግና ስራዎን ካጠናቀቁ በኋላም ምድጃውን ከቤት በማውጣት እሳቱን በውሃ በማጥፋት፣ ቤቱን ማናፈስ።
ለክብረ በዓሉ ወይም ለብርሃን አገልግሎት የለኮሱት ሻማ ከመጋረጃና ከሶፋ፣ ከሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ጋር እንዳይገናኝ ጥንቃቄ ማድረግና ከመተኛትዎ በፊት ወይም ከቤት በሚወጡ ጊዜ የለኮሱትን ሻማ ማጥፋትዎን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
በንግድ ማዕከላትም ነጋዴዎች የንግድ ሱቆቻቸውን ዘግተው ከመውጣታቸው በፊት የተዘነጉ የኤሌክትሪክ ሶኬቶችን እና የተለኮሱ ሻማዎች ካሉ መጥፋታቸውንና መቋረጣቸዉን ማረጋገጥ።
ከዚህ ዓልፎ ለሚያጋጥሙ ማናቸዝም አደጋዎች ኮሚሽን መ/ቤቱ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ። (ምንጭ፦ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን)
@ThiqahEth