" በተፈጸመባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታለች፤ የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " - የቤተሰብ አባል
በኦሮሚያ ክልል ፣ በምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ' የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም ' በሚል ከዛፍ ጋር ታስራ በባለቤቷ ክፉኛ የተደበደበችና የተገረፈች የ3 ልጆች እናት በአስጊ ጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የቤተሰብ አባሏ ተናገሩ።
በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ የምትገኘው ኩሹ ቦናያ የተባለችው እናት በደረሰባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታ " የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " በማለት የቤተሰብ አባሏ ገልጸዋል።
የአካባቢው አቃቤ ሕግ በበኩላቸው ግርፋቱን መፈጸማቸው የተጠረጠሩ ባለቤቷን ጨምሮ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ መካሄዱን ተናግረዋል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፈዋል የተባሉት ሽማግሌዎች የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ጃርሶ ቡሌ (ዘመዷ) ምን አሉ ?
" ኩሹ ቦናያ የ3 ልጆች እናት ናት።
ገበያ ላይ አስሮ የመግረፉ ድርጊት የተፈጸመው ባለፈው ወር መስከረም 9/ 2017 ዓ.ም. ነው።
ግርፋቱ የተፈጸመባት ባለቤቷ ገልገሎ ዋሪዮ ይባላል።
ኩሹ እና ባለቤቷ ገልገሎ በትዳር 12 ዓመት ቆይተዋል
በኑሯቸው ችግር ውስጥ ሲወድቁ ባለቤቷ ወደ ውትድርና ይገባል። በውትድርና 4 ዓመት ያህል ቆይቷል።
እሷ ልጆቿን ለማሳደግ ብቻዋን ስትጥር ነው የቆየችው።
ገልገሎ ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ግን ባለቤቱን መደብደብ ይጀምራል።
በተደጋጋሚ ወደ ቤተሰቦቿ እየሸሸችም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ወደ ቤቷ ትመለስ ነበር።
ገልገሎ ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ከባለቤቱ ጋር መስማማት አለመቻሉም ፤ ዘወትር ባለቤቱን እና ልጆቹን ይደበድብ ነው።
በአገር ባህል መሰረት ሽማግሌዎች በባለትዳሮቹ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በተደጋጋሚ ለሽምግልና ተቀምጠዋል።
ችግሮች ሳይፈቱ ሲቀሩ ወደ አባቷ ቤተሰብ ሸሸች። ሽማግሌዎች ተነጋግረው ባለቤቷ ጠባዩን እንዲያሻሽል እርሷም ወደ ቤቷ እንድትመለስ መከሯት።
እርሷ ግን ነገሩን በደንብ እንዲያጤኑት ወደ ቤቷ ብትመለስ አንደሚገላት’ ተናገረች።
የሽማግሌዎቹን ቃል አላከበረችም በሚል ሽማግሌዎቹ ታስራ እንድትገረፍ ወስነውባታል።
የሽማግሌዎቹ ውሳኔ የቦረናን ባሕል አይወክልም ፤ ይህ የጥቂት ሰዎች ውሳኔ ነው።
በሚኖሩበት አካባቢ ባለ ዛፍ ላይ አሰሯት። ይህንን ያደረጉት ልጇ እያለቀሰ፣ ሌሎች ቆመው እያዩ ነው።
በስፍራው ተገኝተው የነበሩ በሙሉ ፎቶ እንዳያነሱ፣ ቪድዮ እንዳይቀርጹ ተከልክለው ነበር።
ስትገረፍ ከዋጪሌ ዱብሉቅ አንድ መኪና በድንገት መጣ።
አንድ ልጅ ከመኪናው ወርዶ ቪድዮ መቅረጽ ጀመረ ፤ በዚህም የተፈጸመውን ወንጀል ሌሎች ሊያዩት ይችለዋል።
የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ኩሹ በዛፍ ላይ ታስራ በባለቤቷ ግርፋት ከደረሰባት በኋላ ክፉኛ ተጎድታለች።
የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል።
የቤተሰብ አባላቶቿ የደረሰባትን ወድያውኑ አልሰሙም ነበር። ለሳምንት ያህል ሕክምና ሳታገኝ ቆይታለች።
ወንጀሉ አንደተፈጸመ ወድያውኑ ቪድዮው አልተለቀቀም ነበር። ከሳምንት በኋላ ነው ሰው ያየው። ወላጆቿም የሆነውን ያዩት ከቪድዮው ላይ ነው።
መጀመርያ በአሬሮ ሆስፒታል በኋላም ወደ ያቤሎ ሆስፒታል ሄዳ ሕክምና የተከታተለች ቢሆንም የተሻለ ሕክምና በማስፈለጉ ወደ ሐዋሳ ሆስፒታል ተልካለች። "
የዋጪሌ ወረዳ አቃቤ ሕግ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጉዮ አሬሮ ጥቃቱ በቃቃሎ መንደር መፈጸሙን እና ከተፈጸመ ከሳምንት በኋላ ሪፖርት መደረጉን ተናግረዋል።
" መረጃው እንደደረሰን የምርመራ ቡድን በማዋቀር መረጃ መሰብሰብ ጀምረናል " ብለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ሽማግሌዎቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ጨምረው ተናግረዋል።
" ክስ ለመመስረት የሕክምና ማስረጃ እንፈልጋለን። አሁንም የሕክምና ክትትል እያደረገች በመሆኑ መረጃው ገና ተጠናክሮ አልቀረበልንም። ሕጋዊው ጉዳይ ግን ሂደቱን ጠብቆ ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።
ቪድዮ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia