አንጋፋዋ አርቲስት ዘነቡ ገሰሰ ፦
👉 በፈታኒ
👉 በአያስቅም
👉 በ300 ሺህ
👉 በትህትና
👉 በተቆለፈበት
👉 በዓለሜ
👉 በወደው አይሰርቁ ... በሌሎችም እጅግ በርካታ ፊልሞች እና አጫጭር ሲትኮም ድራማዎች ላይ በመስራት በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዘርፍ ውስጥ ጉልህ ድርሻን የተጫወተችው አርቲስት ዘነቡ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተሰምቷል።
አርቲስት ዘነቡ የኪነጥበብን ስራ በራስ ትያትር ቤት ነው የጀመረችው ፤ በቅድሚያ በተወዛዋዥነት በኃላም ወደ ትያትር ክፍል አምርታለች፤ በአጃቢ ድምፃዊነትም የተሳተፈችባቸው ስራዎችም አሉ።
እጅግ በርካታ ፊልሞች ላይ የተሳተፈችው አንጋፋዋ አርቲስት ዘነቡ ፤ ትህትና በተሰኘው ፊልም የጉማ አዋርድ ረዳት ተዋናይ ሽልማትን ማግኘትም ችላለች።
አርቲስት ዘነቡ በጡት ካንሰር ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ የተሰማ ሲሆን አርቲስቷ የሁለት ሴት እና ሁለት ወንድ ልጆች እናት ነበረች፤ ሁለት የልጅ ልጆችንም አይታለች።
የአርቲስት ዘነቡ ገሰሰ ስርዓተቀብር ነገ ሚያዚያ 17 ቀን 2014 ዓ/ም በቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
@tikvahethmagazine