ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት ዲጂታል መታወቂን ግዴታ ማድረግ እንደሚችሉ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ።
ከዚህ ቀደም ብሔራዊ መታወቂያ በመባል ሲጠራ የነበረውና ስያሜው ዲጂታል መታወቂያ በሚል የተቀየረው ማንነትን መለያ ልዩ ቁጥር የመስጠት ሥርዓትን የሚመራ ረቂቅ አዋጅ በዓቃቤ ሕግ አስተያየት ተሰጥቶበት ወደ ሚኒስቴሮች ምክር ቤት ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል፡፡
ረቂቅ ሕጉ መታወቂያውን የማውጣት ግዴታ ያላስቀመጠ ሲሆን ነገር ግን አገልግሎት ሰጪዎችና እንደ ብሔራዊ ባንክ ያሉ ተቆጣጣሪ ተቋማት በየዘርፋቸው አስገዳጅ እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ ሲሉ የፕሮግራሙ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርዓያ ሥላሴ ገልጸዋል።
አገልግሎት ለማግኘት መታወቂያውን መያዝ ግዴታ ስለሚሆን ማንኛውም ሰው መታወቂያውን እንዲያዝ መፈቀድ ስላለበት የውጭ ዜጎችም ማንነታቸውን የሚገልጸውን ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት ታቅዷል፡፡ ሆኖም ዜጋ በመሆን የሚገኝ አገልግሎት ወይም ጥቅሞችን እንደማያጎናጽፋቸው ተጠቁሟል።
ዲጂታል መታወቂያን ከሌሎች መታወቂያዎች በተለየ ከተመዝጋቢው የፊት ገፅታ ፎቶግራፍ፣ የአይሪስ (ወደ አይን የሚገባውን የብርሃን መጠን የሚቆጣጠር የአይን ክፍል) ልየታ (Iris Scan)፣ እና የሁሉም የእጅ ጣቶች አሻራ ይወስዳል፡፡
ነዋሪዎች መረጃዎቻቸው ከተመዘገቡ በኋላ ማንነታቸውን የሚገልጽ የመለያ ቁጥር ያገኛሉ፡፡ ይኼንን ሥርዓት ለመምራት የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ አንድ ልዩ ቁጥር ለአንድ ተመዝጋቢ ብቻ የሚሰጥና ይህ ልዩ ቁጥርም ለሕይወት ዘመን ለተመዘገበው ሰው የማይቀየር እንደሆነ ይደነግጋል፡፡
ዲጂታል መታወቂያ በሙከራ ደረጃ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ለ100 ሺሕ ሰዎች፤ እስከ ሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ደግሞ ወደ አሥር ሚሊዮን የማድረስ ዕቅድ መኖሩን የዘገበው ሪፖርተር ነው።
@tikvahethmagazine