የስልጠና ምዝገባ ተራዘመ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለ4ኛ ዙር ሠልጣኞች የምዝገባ ቀናትን ማራዘሙን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ለ4ኛ ዙር ላዘጋጀው ሥልጠና የሚያካሄደውን የምዝገባ ጊዜ ማራዘሙን አስተውቋል፡፡
ለሥልጠናው ፍላጎት ያሳዩ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ፣ በየቅርንጫፎቹ የታየው የተመዝጋቢዎች መጉላላትን ለማስቀረት፣ ተጨማሪ ተመዝጋቢዎችንም ለማካተት እና በሚፈለገው መልኩ የደንበኞቻችንን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ፣ ምዝገባውን በእርጋታ ለማካሄድ ይቻል ዘንድ እስከ መጪው እሑድ ጥር 21 ቀን 2015 ድረስ ምዝገባው ለ4 ተከታታይ ቀናት ማራዘሙን የባንኩ ማኔጅመንት አስተውቋል፡፡
በመሆኑም ተመዝጋቢዎች በቀሪዎቹ ቀናት ተረጋግተው ምዝገባቸውን እንዲያካሂዱ ባንኩ አሳስቧል፡፡ ይህንኑ በማስፈጸም ላይ ላሉ የባንኩ ቅርንጫፎችም መመሪያ መተላላፉ ታውቋል፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
@tikvahethiopia