ትላንትና ዛሬ በተከሰቱ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
ዛሬ ግንቦት 17 ቀን ከቀኑ 5:49 ደቂቃ ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የቦሌ ለሚ እንደስትሪ ፓርክ ዕድሜዉ 35 ዓመት የተገመተ በፓርኩ የኤሌክትሪክ ባለሙያ የሆነው ግለሰብ በፋብሪካዉ ቤዝመንት በስራ ላይ እያለ በኤሌክትሪክ ተይዞ ህይወቱ አልፏል።
በሌላ በኩል ትላንት ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ቡልቡላ አካባቢ በሚገኝ ድልድይ ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2 -47681 የሆነ ተሽከርካሪ በእግረኞች ላይ ባደረሰዉ ግጭት ሁለት ሰዎች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን የአንድ ሰዉ ህይወት አልፏል ተብሏል።
ህይወቱ ያለፈዉ የ35 ዓመት ሰዉ በተሽከርካሪዉ ተገጭቶ 20 ሜትር ጥልቀት ባለዉ ገደልና ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጠላቂ ዋናተኞች ፍለጋ ሲያካሄዱ ቆይተዉ ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ አስከሬኑን አግኝተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
መረጃው፦ እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ነው
❤ t.me/tikvahethmagazine