አምስት መቶ አስራ አንድ ማህተሞችን በመጠቀም የሀስት ሰነዶች ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ።
አምስት መቶ አስራ አንድ (511) ማህተሞችን በመጠቀም የሃስት ሰነዶች ሲያዘጋጁ የነበሩ ወንጀል ፈጻሚዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
አቶ አሻግሬ በለጠ አለሙ የተባለው ግለሰብ እና ግብረአበሮቹ በአራዳ ክፍለ ከተማ ከ1500 እስከ 4500 ብር በማስከፈል የሃስት ሰነዶችን በማዘጋጀት የወንጀል ተግባር ሲፈፅሙ እንደነበር ነው የተገለጸው።
ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ሀስተኛ የሆኑ የመከላኪያ ሠራዊት የስንብት ወረቀት፣ የመከላከያ የፍቃድ ወረቀት፥ የብሔራዊ መረጃ መታወቂያ፣ የመከላከያ ልዩ ዘመቻ ም/አዛዥ ሻ/ቃ፣ የመከላከያ ሠራዊት መታወቂያ በፍተሻ ወቅት ተይዟል።
በተጨማሪም የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፌደራል አሰተዳደር ፓሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዳርክቶሬት፣ የፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ፥ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ማዕከላዊ፣ 31ኛ ክፍለ ጦር መምሪያ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሉ የሀሰት ሰነዶች በኤግዚቢትነት መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።
❤ t.me/tikvahethmagazine