የልማት አርበኛው የማሩ አበበ የህይወት ታሪክ መጽሀፍ ተመረቀ።
በጋዜጠኛ ዓይናለም ሀድራ እና በጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ የተዘጋጀው የአቶ ማሩ አበበን የህይወት ታሪክ የሚዳስስ መጽሐፍ እሁድ ግንቦት 20 2015 ዓ.ም 5 ኪሎ በሚገኘው በቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ ተመርቋል።
ታሪካቸው በመጽሀፍ የተሰነደላቸው የደን ልማት ባለሙያው አቶ ማሩ ኮተቤ ኪዳነምህረትን እንዲሁም አሁን እንጦጦ ፓርክ የተሰራበትን ስፍራ በማልማት ለሀገር ጠቃሚ ተግባር ያከናወኑ ናቸው፡፡
ከደን ልማቱም ባሻገር በመንገድ ቅየሳ የጎላ ሚና አበርክተዋል፡፡ አቶ ማሩ አበበ ለሀገር ትልቅ ስራ በማበርከታቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድም በስማቸው በደቡብ ወሎ ዞን ት/ቤት ተሰይሞላቸዋል፡፡
በምረቃ መርሀ-ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ ደን ልማት የብሄራዊ ደን ልቀት ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ይተብቱ ሞገስ በክብር እንግድነት የታደሙ ሲሆን ወጣት የደን ባለሀብቶች ከአቶ ማሩ የሥራ ትጋት ብዙ ሊማሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
የአቶ ማሩ የህይወት ታሪክ መጽሀፍ ምረቃ ላይ የአቶ ማሩ ቤተሰቦች እና ወዳጆች የታደሙ ሲሆን ወንድማቸው አቶ ዳኘው አበበ መጽሀፉን ሙሉውን በመግዛት ገቢውን በአቶ ማሩ ስም ለተሰየመው ት/ቤት ማደረጃ እንዲሆን አውለዋል፡፡
via ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ
❤ t.me/tikvahethmagazine